YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የግድቡ ውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት መፈረም አለበት፡ አሜሪካ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በውሃ የመሙላትና የሙከራ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም እንዳለበት አሜሪካ አርብ ለሊት ባወጣችው መግለጫ አመለከተች። የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው ቀደም ሲል የነበረውና ግንባታው በታችኛው የተፋሰሱ አገራት ላይ ጉልህ ጉዳት እንዳይደርስ በሚለው የመርህ ስምምነት መሰረት "ግድቡን በውሃ የመሙላትና ሥራውን የመሞከር ሂደት ስምምነት ሳይደረግ መከናወን የለበትም" ብሏል።የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑቺን ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት ከዚህ በፊት በነበሩ ስምምነቶች መሰረት ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም አለበት።

ተጨማሪ👇👇👇👇
https://telegra.ph/Moreonthis-02-29
ኢትዮ ቴሌኮም የሳይበር ጥቃት ደረሰበት

ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮ ቴሌኮም የውስጥ ሲስተም ውስጥ #የራንሰምዌር (Ransomeware ) ጥቃት መድረሱን ሰራተኞችም የኢሜል ልውውጦቻቸው መጠባበቂያ ሳይቀሩ ከዋና ሲስተም ጋር እንዳይገኙ እና ይህንን ካደረጉ ልውውጦቻቸው ሊያጡ እንደሚችሉ አርብ የካቲት 13 ለድርጅቱ ሰራተኞች የተላኩ መልክቶች አረጋገጡ።

ከድርጅቱ የዲጅታል ዲቪዥን የተላከው አጭር የጽሑፍ መልክት አርብ ይድረስ እንጂ ሰራተኞች ግን ከማክሰኞ የከቲት 10 ጀምሮ ሁሉም የቴሌኮም ሰርዓቶች ቀመው እንደነበር አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ታመኝ ምንጮች ገልፅዋል።

ምንጮቹ እንደሚሉት ከሲአርኤም ከተባለው እና የደንበኞች መረጃዎችን ከሚይዘው ሲስተም ውጪ ያሉ የቴሌኮሙ ሰርአቶች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።


የቀረውን ከጋዜጣው ላይ ያንብብ
ምንጭ :- አዲስ ማለዳ ✏️ YeneTube
@Yenetube @FikerAssefa
ሰበር ዜና

አሜሪካ በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ትዕዛዝ ማስተላለፏን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ።

አሜሪካ ኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከስምምነት ሳይደርሱ የህዳሴው ግድብ ውሃ መሙላት አይችልም የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ኢትዮጵያም አሜሪካ ባስተላለፈቸው ውሳኔ ዙሪያ እንደ አገር አቋም ለመያዝ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡን ከኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

Via:-Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸዉን ለሚከታተሉ 30 አይነስዉራን ተማሪዎች የላፕቶፕ ስጦታ አበረከቱ፡፡

ስጦታዉ የተበረከተላቸዉ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን ለመከታተልና የመመረቂያ ጽሁፋቸዉን ለማዘጋጀት የላፕቶፕ ችግር ያለባቸዉ ተማሪዎች ተለይተዉ ነዉ፡፡ቀዳማዊት እመቤት በፅ/ቤታቸዉ ጠርተዉ ካበረታቷቸዉ በኋላ የላፕቶፕ ስጦታዉን አበርክተዉላቸዋል፡፡ላፕቶፖቹ ታይዋን ከሚገኝ ASHL FOUNDATION ከተባለ ድርጅት በጽ/ቤታቸዉ በኩል የተገኙ ናቸዉ፡፡

Via Office of First Lady
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተጀመረውን ወይይት ወደ አፍሪካ ህብረት ማምጣት እንደሚገባ በናይል ትብብር መድረክ የምስራቅ ናይል አህጉራዊ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ፈቂ አህመድ ነጋሽ ተናግሩ።

አቶ ፈቂ እንዳሉት ኢትዮጵያ የግድቡን ድርድር አሁን እየተደረገ ባለበት መድረክ እንዲቀጥል ማድረግ አልነበረባትም ብለዋል።

ይሁንና አሁን ላይ የእነ አሜሪካ ፍላጎት ግልጽ በመሆኑ ድርድሩን ወደ አፍሪካ ህብረት እና ናይል ተፋሰስ አገራት ማዕቀፍ ማምጣት ይኖርባታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ግድቡን እየገነባች ያለችው በራሷ ሉኣላዊ ግዛት ላይ ነው፣ወንዙም ሉአላዊ ሃብቷ ነው የአሜሪካ ትዕዛዝና መግለጫ ሊገድባት አይገባም ሲሉ አሳስበዋል።

ግብጽና ሱዳን ድርድር ከፈለጉ ግን ኢትዮጵያ ድርድሩን መቀጠል አለባት ነገር ግን ድርድሩ ሚዛናዊነትን በሚያስጠብቅ መልኩ መሆን ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።

Via:- Ethio Fm
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መንግሥት ከጥቂት ሰዓት በኋላ በኅዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ያለውን አቋም የተመለከተ መግለጫ ያወጣል።

አሐዱ ቴሌቪዥን ዩናይትድ ስቴትስ ያወጣችውን "ስምምነት ሳይፈረም የግድቡ ውኃ ሙሌትና ኃይል ማመንጨት እንዳይጀመር" የሚል አቋም ተከትሎ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ስብሰባ መቀመጡን አረጋግጧል።

በዚህም በጥቂት ሰዓት ውስጥ የኢትዮጵያን አቋም የሚያሳውቀው መግለጫ እንደሚወጣ ስብሰባው ውስጥ ካሉ ተደራዳሪዎች መረጃ ደርሶናል።

ምንጭ:-አሐዱ ቴሌቪዥን
@Yenetube @FikerAssefa
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ።

የኢትዮጵያ ፌዴራለዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒሰቴር የአሜሪካ የግምጃ ቤት ዲፓርትመንት ሴክሬታሪ በየካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ28 ፌብሩዋሪ 2020) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችበትን ስብሰባ ተከትሎ የወጣውን የፕሬስ መግለጫ በከፍተኛ ቅሬታ ተመልክተውታል። ስብሰባው የተካሄደው ኢትዮጵያ አስቀድማ ለግብጽ፣ ለሱዳን እና ለአሜሪካ ስብሰባው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ አሳውቃ እያለ ነው፡፡

የግድቡ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በመርሆዎች መግለጫ ስምምነቱ መሰረት የግድቡን ሙሌት ከግንባታው ትይዩ በፍትሐዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም እና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች መሰረት የምታከናውን ይሆናል።

ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ ለማዘጋጀት የሚደረገው ድርድር ተጠናቋል በሚል የተሰጠውን መግለጫ አትቀበልም።

በዋሽንግተን ዲሲ የግብጽ ዐረባዊት ሪፐብሊክ ፈርሞበታል የተባለው “ረቂቅ” የሶስቱ ሀገራት የድርድርም ሆነ የሕግ እና ቴክኒክ ቡድኖች ውይይት ውጤት አይደለም።

የቴክኒክ ጉዳዮች ድርድሩም ሆነ የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅቱ ላይ የሚደረገው ድርድር አልተጠናቀቀም፡፡ ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ የሚዘጋጀው በሶስቱ ሀገራት ብቻ እንደሆነ አቋሟን ቀድማ አሳውቃለች።

ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን በሚያውቁት እና በተስማሙበት እንዲሁም በመርሆዎች መግለጫ ስምምነት መርህ አንቀጽ ስምንት አድናቆታቸውን በሰጡት ሂደት መሰረት ሁሉንም የግድብ ደህንነት የሚመለከቱ ጉዳዮች በዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ምክረ ሃሳብ መሰረት የተሰጡትን ምክረ-ሃሳቦች መፈጸሟን ትቀጥላለች።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብን ለማዘጋጀት ቀሪ መሰረታዊ ልዩነቶችን ለመፍታት ኢትዮጵያ ከግብጽ ዐረባዊት ሪፐብሊክ እና ከሱዳን ሪፐብሊክ ጋር የጀመረችውን ሂደት ለመቀጠል ቁርጠኛ ናት።

via :- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ የታላቁ የኅዳሴ ግድብ «የመጀመሪያ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ ለማዘጋጀት የሚደረገው ድርድር ተጠናቋል በሚል» አሜሪካ ያወጣችውን መግለጫ ውድቅ አደረገች።

የኢትዮጵያ መንግሥት «ሥምምነት ሳይፈረም የታላቁ የኅዳሴ ግድብ የመጨረሻ ሙከራ እና የውኃ ሙሌት ሊከናወን አይገባም» የሚለው የአሜሪካ ግምዣ ቤት መግለጫ ከፍተኛ ቅሬታ እንደፈጠረበት አስታውቋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 80ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

@Yenetube @Fikerassefa
የህዳሴ ግድብ በአባይ ውሃ መጠን ላይ ተጽዕኖ እስካላመጣ ድረስ ሱዳን ግድቡን ትደግፋለች – አምባሳደር አብደል ቢላል አብደልሰላም

የህዳሴ ግድብ በአባይ ውሃ መጠን ላይ ተጽዕኖ እስካላመጣ ድረስ ሱዳን ግድቡን እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አብደል ቢላል አብደልሰላም ተናገሩ።አምባሳደሩ በግድቡ ላይ በሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ሱዳን ለግብጽ ወግናለች በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚነዛውን መረጃ አጣጥለውታል።ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጅማሮ አንስቶ ላለፉት ስምንት ዓመታት አያሌ ምክክሮችን ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ያም ሆኖ ግን ካለስምምነት የተቋጨው የሶስትዮሽ ድርድሩ በመጨረሻ ወደ አሜሪካና ዓለም ባንክ አደራዳሪነት መሸጋገሩ ይታወሳል።

በአሜሪካና ዓለም ባንክ ታዛቢነት ለሳምንታት የዘለቀው ድርድሩ፤ በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ ቀጠሮ ተይዞለት በነበረ ስምምነት ኢትዮጵያ በተደራዳሪዎቿ በኩል ያልቋጨቻቸው ጉዳዮች እንዳሏት በመግለጽ መድረኩን እንደማትታደም አሳውቃ ነበር።ይህን ተከትሎም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሱዳን ለግብጽ እንደወገነች ተደርጎ እየተስተጋባ ይገኛል።በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አብደል ቢላል አብደልሰላም በተለይ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የሚሰራጨው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው።የዚህ መሰረተ ቢስ መረጃ ምንጮችም መቀመጫቸውን ግብጽ ካደረጉ የማህበራዊና መደበኛ መገናኛ ብዙሃን የሚመነጭ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሱዳን ባላት እውነተኛ ፍላጎት ለግድቡ ያልተቆጠበ ድጋፍ በማድረግ ከኢትዮጵያም ጋር በትብብር መስራቷን አስታውሰው፤ የሱዳን ድጋፍ ባይታከልበት ኖሮ ፕሮጀክቱ እዚህ አይደርስም ብለዋል።ሱዳን ከቴክኒካል የውሃ ግድብ አሞላል ጉዳዮች ይልቅ በአባይ ወንዝ ዙሪያ የጋራ ትብብር ሁልጊዜም አስፈላጊ መሆኑን እንደምታምን ገልጸው፤ አገራቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በውሃ መጠን ላይ ጉዳት የለውም የሚል እምነት መያዟን ተናግረዋል።አምባሳደሩ አያይዘውም ጥቃቅን ልዩነቶች ይፈታሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸውና አገሮቹ በጉዳዩ ላይ ረጅም ርቀት የተጓዙ በመሆኑ ያን ያህል ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው ነው የገለጹት።“በህዳሴው ግድብ ላይ በተደረጉ ድርድሮች የተለያዩ ከበድ ያሉ ጉዳዮች በመታለፋቸው ቀሪ ጉዳዮች ከዚህ ግባ የማይባሉ ናቸው” ብለዋል።

ምንጭ:- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ጃዋር መሃመድ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ከምርጫ በኋላ ቢከናወን መልካም ነው ብሏል!

ምርጫ 2012 እስከሚካሄድ ድረስ ኢትዮጵያ ከኀዳሴ ግድቡ ድርድር እንድትወጣ ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ ጥሪ አቀረበ።

ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫውንና በቅርቡ በአበዳሪ የገንዘብ ተቋማት ለኢትዮጵያ ቃል የተገባውን ብድር በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ላይ ጫና ለማሳደር እየተጠቀመችበት ነው ብሏል ፖለቲከኛው።

በዋሽንግተን በተደረገው የመጨረሻው ዙር ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንዳትሳተፍ ጠቅላይ ሚንስትሩ መወሰናቸው ትክክል ነበር ያሉት ፖለቲከኛው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአቋማቸው ሊፀኑ ይገባል ብሏል።

ግብፅና ሱዳን አስቸጋሪ የአገር ውስጥ ጉዳይ በገጠማቸው ወቅት ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበረ ያስታወሰው ጃዋር፤ ኢትዮጵያ ያሉባትን አንገብጋቢ የአገር ውስጥ ጉዳዮች (ምርጫው 2012ን ጨምሮ) እስከምታጠናቅቅ ድርድሩ ላልተወሰነ ጊዜ ሊራዘም ይገባል ብሏል።

መንግሥት የድርድሩን ጉዳይ ወደ አፍሪካ ኀብረት በመውሰድ የአባል አገራቱን ድጋፍ እንዲሰበስብም መክሯል።

ምንጭ:- አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @Fikerassefa
የአምባሳደር ፓርክ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል።

ኢ/ር ታከለ ኡማ እድሳት ሲደረግለት የቆየውን አምባሳደር ፓርክ ተመልክተዋል።0.4 ሄክታር ላይ ያረፈው ፓርኩ አዳዲስ ዲዛይኖችን አካቶና ለተለያዩ አገልግሎቶች በሚመች መልኩ ነው የታደሰው።ለነዋሪዎችም ተጨማሪ የመዝናኛ ቦታ አማራጭ የሚፈጥር ይሆናል።የከተማ አስተዳደሩ በተለይን አረንጓዴ ስፍራዎችን የማልማትና ነባር ፓርኮችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩና መሰረተልማቶችን ባሟላ መልኩ እድሳት እያደረገላቸው ይገኛል።

Via Mayor office
@YeneTube @FikerAssefa
#አብን #GERD

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ ድጋፍና እርዳታን ለማግኘት ማስያዣ መሆን እንደሌለበት አብን አስታወቀ።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ግብጽ እስካሁንም የ1929ኙና የ1959ኙ ኢትዮጵያን ያገለለዉ ስምምነት እንዲመለስ ነዉ የምትፈልገዉ ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ አቋም ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል።

ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ መንግስት ከህዝቡ ጋር መምከርና ቀደም ሲል በነበረበት አቋም ጸንቶ ነዉ መቀጠል ያለበት ብለዋል፡፡

ንቅናቄዉ አሁን ላይ በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር መስመር የሳቱ የሚመስሉ ግንኙነቶች አሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጾ በፖለቲካ ዓለም ዉስጥ ፍጹም ታማኝ ወዳጅ ባለመኖሩ ግንኙነታችን ግልጽ መስመር ሊኖረዉ ይገባል ብሏል፡፡

Via :- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካ ግምዣ ቤት በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያወጣው መግለጫ "ተቀባይነት የሌለው እና እጅጉን ለአንድ ወገን ያደላ ነው" ሲሉ ወቀሱ።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
#አሳዛኝ_ዜና የማስታወቂያ ባለሞያው ጋሽ ውብሸት ወርቅ አለማው ከዚህ አለም በሞት እንደተለዩ ethio FM(ታዲየስ አዲስ) ዘግቧል።

የኔቲዩብ ለአድናቂዎቻቸው እንዲህም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለኝ።

@YeneTube @Fikerassefa
አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ ጋሽ ውብሸት ወርቃለማሁ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ።

አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በተለይም በከተሞች ውስጥ ጋሽ ውብሸት ወርቅ አለማው ሲባል በድምጻቸው ይለያቸዋል የተወለዱት እ.ኤ.አ. በ 1938 ዓ.ም. ማfድ ያፊት በተባለ መንዝ አካባቢ ነበር ይህ ጀግና የቤተሰብ ዘጠነኛ ልጅ ነው የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ከልጆቹ አንዱ ፕሮፌሰር ነው ሌላኛው ደግሞ የፋይናንስ ባለሙያ እና ባለሀብት ነው ውብሸት ከኔዘርላንድ በፈጠራ ማስታወቂያ ዲፕሎማ አላቸው በተጨማሪም ከአሜሪካ የባዮግራፊካል ተቋም በማስታወቂያ እና በሕዝብ ግንኙነት ውስጥ ዲፕሎማ አግኝተዋል ጋሽ ውብሸት ፣ አገሩን ከምንም ነገር በላይ ይወዳል በበጎ አድራጎት ስራቸው እና በደም ባንክ አምባሳደርታቸው ይታወቃሉ ከዚያ በላይ ፣ ለሰብአዊ ስራዎች ከ 155,000,000 ብር በላይ ለማሰብሰብ ችለዋል፡፡

የወሎ ህዝብ በድርቅ በተጠቃበት እና የደቡብ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በጎርፍ በተመታበት ወቅት ጋሽ ውብሸት የተለያዩ የገንዘብ ማሰባሰብ እንቅስቃሴዎችን በማደራጀት የራሳቸውን ሃላፊነት ተወጥተዋል በተጨማሪም ከጥቂት ዓመታት በፊት ድሬዳዋ ከተማ በጎርፍ በተጥለቀለቀች ጊዜ ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ዓላማ ካለው የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በቴሌኮን በማዘጋጀት ረገድ ሚና ተጫውተዋል ተጎጂዎችን በተቻለ መጠን በፍጥነት ወደነበሩበት ለመመለስ ትልቅ አስተዋጻኦም አድርገዋል ጋሽ ውብሸት ከዚህ በተጨማሪም የብሄራዊ ድም ባንክ አምባሳደርም በመሆን አገልግለዋል ጋሽ ውብሸት በተወለዱ በ74 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

የኔ ትዩብ ለቤተሰቦቻቸው ለስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለአድናቂዎቻቸው መጽናናትን ይመኛል::

ምንጭ:- AllAfrica.com ✏️ YeneTube
@Yenetube @Fikerassefa