YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ከእስር ተፈትቶ ከወዳጆቹ ጋር ተቀላቅሏል፡፡

Via Jano Band
@YeneTube @FikerAssefa
ሕወሀት ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ቅርንጫፍ እንደሚከፍት አልተነጋገርንም አለ።

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ ግንኙነት መሠረት አደረጃጀቱን በማስፋት በቅርቡ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጽሕፈት ቤቶችን ይከፍታል ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቢሮ እንደሚከፍት ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ግን የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

ብልጽግና ለትግራይ ክልል የተሾሙ ግለሰቦች እንዳሉ ሰምቻለሁ ያሉት አቶ ጌታቸዉ እነማን እንደተሾሙ ግን ወደ ፊት የሚሆነዉን የምናይ ይሆናል ብለዋል፡፡

ብልጽግና በትግራይ ክልል ብዙ ደጋፊ አለው ብዬ አላምንም ያሉት አቶ ጌታቸው ማንኛዉም ፓርቲ ህጋዊ እስከሆነ ድረስ ግን በትግራይ ክልል የመንቀሳቀስ መብት አለዉ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
በደቡብ ክልል ማጂ ወረዳ ቱም ከተማ በዛሬው ዕለት በተደረገ ተቃውሞ ላይ የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ተቋም ተናገሩ። የዞኑ ባለሥልጣናት እና የዐይን እማኞችም ጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ከተገደሉት በተጨማሪ ሌሎች ከአስር በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አረጋግጠዋል።

ሰልፉ የተደረገዉ አዲስ በተዋቀረው በምዕራብ ኦሞ ዞን የምትገኘው የማጂ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ መታሰራቸውን በመቃወም ነበር። «አስራ አንድ ሰው [በጥይት] ተመቷል። ሶስቱ ሴቶች ናቸው። ትልልቅ ሰዎች እና ሕፃናትም አሉበት» የሚሉት የዐይን እማኙ «ሰልፍ ሲደረግ መንገድ ይዘጋል። መንገድ ሲዘጋ መከላከያ እና ልዩ ኃይል መጣ። ከዚያ በአካባቢው በተሰበሰበው ሕዝብ ላይ ምንም ነገር ሳያማክር ተኩስ ጀመረ» ሲሉ መነሾውን አብራርተዋል።

የማጂ ወረዳ ጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ አኩ እንደሚሉት ቱም በተባለችው ከተማ በተደረገው ሰልፍ ስድስት ሰዎች በጸጥታ አስከባሪዎች ተገድለዋል።
አቶ ከበደ "ዛሬ ጠዋት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች በልዩ ኃይል እና በመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት ተመተው እኛ ጋ ተኝተዋል። የሞቱት ሬሳቸው ሳይነሳ እዚያው ነው ያለው። የሞቱት ወደ ስድስት የሚሆኑ ሰዎች ናቸው" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በአራት ጥይት የቆሰሉ አንድ ሰው ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ማጂ መላካቸውን ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ

➡️ በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች ሶስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ አንደ መቶ (372,100) በሙቀት መለያ (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡

➡️በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ሰባት (220,357) በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አምስት ሺህ አራት መቶ ስባ ስድስት (5,476) በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡

➡️ሰማንያ ሁለት (82) ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

➡️ከነዚህም ጥቆማዎች ሀያ (20) የበሽታውን ተመሳሳይ ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስለ ነበራቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ግለሰቦች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ሠዓት በለይቶ ማቆያ ውስጥ ተለይቶ ያለ በበሽታው የተጠረጠረ ሰው የለም፡፡

➡️በ8335 የነጻ የስልክ መስመር በአጠቃላይ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሁለት (3,922) ጥሪዎች የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንድ ሺህ ሶስት መቶ አርባ (1,340) ከኮቬድ-19 ጋር የተገናኙ መረጃዎች ናቸው፡፡

-EPHI
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ➡️ በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች ሶስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ አንደ መቶ (372,100) በሙቀት መለያ (ኢቦላና ኮቪድ-19 በማጣመር) አልፈዋል፡፡ ➡️በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ሰባት (220,357) በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ…
"ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በ አገራችን የተረገገጠ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ የለም ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረዉ በመለያ ማእከል ክትትል ተደርጎላቸዉ ከቫረሱ ነጻመሆናቸዉ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንድ ተጠርጣሪ በማለያ ማእከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ናሙና ተወስዶ ላብራቶሪ እተሰራ ነዉ፡፡ ዉጤቱም እንደደረሰ እናሳዉቃለን፡፡ ሕብረተሰቡ በቫረይሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰዉ አለመኖሩን አዉቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡"

-EPHI
@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ሊያ ታደሰ | ኮሮና ቫይረስ #Update

ዛሬ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠረ ግለሰብ በለይቶ ማቆያ መግባቱን የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ዴታ ሊያ ታደሰ ገልፃለች። ይህ ግለሰብ ከቤንጂንግ በFeb 22 የመጣ ሲሆን እራሱን በቤት ውስጥ ለይቶ ቆይቶ ነበር።

ነገር የግን የራስ ምታቱ መጠን መጨመሩን ተከትሎ የጤና ሚንስትር ማቆያ ውስጥ መግባቱን ሚንስተሯ በቲዊተር ገጷ ላይ አስፍራለች። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውጤቱ ዛሬ ማታ እንደሚገለፅ ሚንስተሯ ጨምራ ተናግራለች ።

@Yenetube @Fikerassefa
አስደሳች ዜና፡ ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት ዕድል

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዓይን ህክምና ት/ት ክፍል ከሂማሊያን ካታራክት ፕሮጀክትና ቪዥን ኬር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከየካቲት 29

-- መጋቢት 5 2012 ዓ.ም. በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ክፍል ለ500 ተጠቃሚዎች ነጻ የዓይን የሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በመሆኑም ይህንን አገልግሎት ማግኘት የሚፈልግ ማንኛዉም የህብረተሰብ ክፍል በተጠቀሱት ቀናትና ቦታ በመገኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እናሳስባለን፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@Yenetube @Fikerassefa
የመብራት መቋረጥ…

"ወደተለያዩ ቦታዎች ስልክ በመደወል እንዳጣራነው ከአዲስአበባ በተጨማሪ አዳማ ፣መቐለ፣ሀዋሳ፣ሀረር፣ድሬ
ደዋ፣ጅግጅጋ፣ አዲግራት:ጎንደር : ጅማ : ባህር ዳር መብራት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል።

ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ወደ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለስልጣን ብንደውልም ስልካቸው ሊሰራልን አልቻለም።"

-Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
የኤሌክትሪክ መቋረጥ...

በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ላይ የተፈጠረ ችግር ለመብራት መቋረጡ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ Capital ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኤሌክትሪክ መቋረጥ... በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ላይ የተፈጠረ ችግር ለመብራት መቋረጡ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ Capital ዘግቧል። @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር እቶ ሞገስ መኮንንም የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል::

ለዚህ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለአሁን እለመታወቁን: ነገር ግን ከግልገል ጊቤ ሦስት ከሚቀርበው የኃይል አቅርቦት መስመር ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አቶ ሞገስ ግምታቸውን ተናግረዋል:: አክለውም የድርጅቱ ባለሙያዎች የኃይል መቋረጡን ምክንያት ለመለየትና አገልግሎቱን ለመመለስ እየሰሩ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል::

በአጭር ጊዜ ውስጥም በአዲስ አበባ ያጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እንደሚስተካከልና በተከታይነትም የሌሎቹም አካባቢዎች አገልግሎት እንደሚመለስ አቶ ሞገስ ለቢቢሲ ገልጸዋል::በአንዳንድ ስፍራዎችም ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እየተመለሰ መሆኑን ለማወቅ ችለናል::

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢራን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 210 ደርሷል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

የሀገሪቱ መንግሥት ይፋ ባደረገው መረጃ 34 ሰዎች እንደሞቱ ቢያሳውቅም BBC Persian አገኘሁት ባለው መረጃ እስካሁን 210 ሰዎች ሞተዋል። ይህም መንግስታት የሟቾችን ቁጥር እየደበቁ ነው የሚለውን ጥርጣሬ የሚያጎላ ነው ተብሏል።

ከዚው ጋር በተያያዘ CNN በሰራው ዘገባ መንግስታት መረጃን ሚደብቁ ከሆነ በ1918 ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ህይወት እንደቀጠፈው የእንፍልዌንዛ (Spanish flu) ወረርሽኝ ነገሮችን ወደከፋ ደረጃ ሊያደርስ እንደሚችል ዘግቧል።

Join:- @Coronavirusupdatess

@YeneTube @FikerAssefa
ምን አዲስ ነገር ተሰማ ስለ ኮሮና ቫይረስ

- ቻይና የኬኒያን ዜጎችን አስጠንቅቃለች በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የቻይና ዜጎች በኬንያ መገለል እየደረሰባቸው በመሆኑ ቻይና የኬንያኖችን እንዳስጠነቀቀች ቻይና ፒፕል ዘግቧል።

- ጣልያን በኮሮና ቫይረስ ዛሬ ብቻ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 166 ሲሆን የሞት ቁጥር ደሞ በ4 ጨምሯል በአጠቃላይ በባይረሱ የተጠቁ 821 ሲደርሱ የሞቱ በአጠቃላይ 21 ደርሰዋል።

- አንድ ሆንግ ኮንድ ከተማ የሚገኝ ውሻ ተመርምሮ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ታውቋል።

- ኬንያ ወደ ቻይና በረራ አቁማለች።

📌አዘር ባጃን
📌አምስተርዳም
📌ሜክሲኮ
📌አይስ ላንድ ዛሬ ኮሮና ቫይረስ ሀገራቸው መግባቱ ያረጋገጡ ሀገሮች ናቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
በስራ ፈጠራ እንዲሁም በመዝናኛው ዘርፍ የሚታወቀው ካሌብ ሚያኪንስ በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።

የዛሬ ሳምንት ወደ ለንደን ሊበር በወጣበት ባጋጠመው የመኪና አደጋ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

ለአድናቂዎቹ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን።
@YeneTube @FikerAssefa
በጊቤ 3 የሀይል ማመንጫ ካሉት አስር ተርባይኖች ዘጠኙ ብልሽት አጋጥሟቸዋል።

ፎርቹን ለጉዳዩ ቅርበት ካለው አካል ሰምቻለው እንዳለው የሀይል ማመንጫውን ወደነበረበት ለመመለስ ቢያንስ የአንድ ሰአት ስራ(ጥገና) ይፈጃልም ብሏል። ጊቤ 3 ግድብ ለግንባታው 1.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን 1870 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል እያመነጨ ይገኛል።

ምንጭ: ፎርቹን
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ፕላጃሪዝም ፖሊሲን መጀመሩን አስታወቀ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ፕላጃሪዝም (Anti-Plagiarism) ፖሊሲ ከየካቲት 22/2012 ዓ.ም ጀምሮ ሊተገብር መሆኑን በይፋ እየገለጸ ይህ ፖሊሲ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በፖሊሲው መሰረት ከዚህ በኋላ ማንኛውም መመረቂያ ጽሁፍ (Thesis/ Dissertation) በኧርከንድ (URKUND) ሶፍትዌር አማካኝነት ተመርምሮ ከፕላጃሪዝም ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥ ዲግሪ እንደማይሰጥ ያሳውቃል፡፡

ፕላጃሪዝም አንድ የምረቃ ፅሁፍ የሚያዘጋጅ ወይም የምርምር ስራ የሚሰራ ሰው ሌሎች ሰዎች የሰሩትን ስራ የራሱ እንደሆነ አድርጎ በመውሰድ የአካዳሚክ እና የምርምር ሕግጋትን በመጣስ የሚፈፅመው ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡ፕላጃሪዝም ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፍ በሚያዘጋጁበት ጊዜ በራሳቸው ጥረት እና ልፋት የራሳቸው የሆነ (original) ስራ ሰርተው እንዳያቀርቡ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ላይ ትልቅ ጉዳት ሲያደርግ የቆየ ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡

ቀደም ሲል የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ፕላጃሪዝም በመጠቀም የመመረቂያ ጽሁፉን በማዘጋጀት 2ኛ ዲግሪ ወስዶ ከነበረ ተማሪ ላይ ድርጊቱ በማስረጃ በማረጋገጡ በሴኔት ሕጉ መሰረት ዲግሪው እንዲነጠቅ አድርጓል፡፡ ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ይህ ችግር በመማር ማስተማሩና በምርምር ስራ ላይ በየጊዜው እያስከተለ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በመገንዘቡ የፀረ-ፕላጃሪዝም ፖሊሲ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በመሆኑም ይህ ፖሊሲ ተግባራዊ ሲሆን ችግሩ ከሞላ ጎደል ይቃለላል የሚል ሙሉ እምነት አለው፡፡

-አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
ከቤጂንግ የመጣው ቻይናዊ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ነው ተባለ!

ከዚህ ቀደም ብሎ አንድ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ያሳየ በማለያ ማእከል ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት መሆኑን እና ናሙናው ተወስዶ ላብራቶሪ እተሰራ መሆኑን የገለጽን መሆኑ ይታወቃል፣ በመሆኑም አሁን በደረሰን ውጤት መሰረት ግለሰቡ #ከበሽታው_ነጻ (ኔጌቲቭ) መሆኑ በላቦራቶሪ እንደተረጋገጠ መግለጽ እንወዳለን ብሏል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket