YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማራ ክልል መንግስት (#አዴፓ) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (#አብን) ለአማራ ህዝብ ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማምጣት በአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ ሁሉ ወደፊት በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው በማስመር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ሁለቱም ድርጅቶች ገልፅዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
#አብን_ኦነግ‼️

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንደሌለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አስታወቀ። የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቶሌራ አደባ "የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ምንም አይነት የታጠቀ ኃይል በዚያ አካባቢ አልነበረውም፤ የለውምም" ሲሉ ተናግረዋል።

ከወራት በፊት በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር መካከል ዕርቅ ለማውረድ የአባገዳዎች ኅብረት ጣልቃ በገባበት ወቅት አቶ በየነ ሰንበቶ የኦነግ ጦር "በሰሜን ሸዋ፤ ከሜሴና እና በከረዩ አለ።" ብለዉ ነበር። አቶ በየነ ሰንበቶ "ወሎ ከሚሴ ያሉትን ከአማራ ክልል ጋር እንነጋገራለን" ሲሉም ተናግረው ነበር።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ ግን "እኛ እየሰራን ያለንው የፖለቲካ ሥራ ብቻ ነው። የምናዘው በእኛ ስር የሚታዘዝ ምንም ሰራዊት የለም" ሲሉ መልሰዋል።

አጣዬ፣ ማጀቴ፣ ሰንበቴ እና ካራ ቆሬ በተባሉ አካባቢዎች ከተፈጸሙ ጥቃቶች በኋላ በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ባለሥልጣናት የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ተጠያቂ አድርገዋል። አቶ ቶሌራ ግን በአካባቢዎቹ ለተፈጸሙት ጥቃቶች ተጠያቂው #የአማራ,ብሔራዊ_ንቅናቄ (አብን) የተባለው የፖለቲካ ፓርቲ ነው ሲሉ ወንጅለዋል። አቶ ቶሌራ ጥቃቱን ያደረሱት "አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ የፌድራልም ያልሆነ ወይንም የክልሉም [የአማራ ክልል] ያልሆነ ባንዲራ ይዘው ነው የሚሔዱት። እንደሚመስለኝ በዚያ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ተፎካካሪ ፓርቲ #አብን_የሚሉት ነው የሚመስለኝ" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ቃል አቀባይ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር በኩል የቀረበውን ወቀሳ ፈፅሞ አይቀበሉም። አቶ ክርስቲያን "ጥቃቱን እና ወረራውን የፈጸሙ ኃይሎች የኦነግን አርማ የያዙ፤ ራሳቸውን የኦነግ አባላት ነን ብለው የሚናገሩ፤ ጥቃት በሚፈፅሙባቸው መሳሪያዎች ጭምር የኦነግን አርማ አድርገው የሚታገሉ ናቸው። ይህ በሆነበት ሁኔታ አንድም እንኳ የጦር መሳሪያ የሌለው፤ ሰላማዊ ትግል እያደረገ ያለውን አብንን መኮነን በአደባባይ የሰሩትን ነውር ለመሸፋፈን የሚያደርጉት ጥረት ሆኖ ነው የምናገኘው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሰሞኑን በሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች በተፈጸመው ጥቃት የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር አሁንም በግልፅ አይታወቅም።

በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዋል።

የጸጥታ ኃይሎቹ “አስፈላጊውን ህጋዊ እና ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ” ትዕዛዝ መተላለፉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ነው።

ምንጭ:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
#አብን #GERD

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ ድጋፍና እርዳታን ለማግኘት ማስያዣ መሆን እንደሌለበት አብን አስታወቀ።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ግብጽ እስካሁንም የ1929ኙና የ1959ኙ ኢትዮጵያን ያገለለዉ ስምምነት እንዲመለስ ነዉ የምትፈልገዉ ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ አቋም ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል።

ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ መንግስት ከህዝቡ ጋር መምከርና ቀደም ሲል በነበረበት አቋም ጸንቶ ነዉ መቀጠል ያለበት ብለዋል፡፡

ንቅናቄዉ አሁን ላይ በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር መስመር የሳቱ የሚመስሉ ግንኙነቶች አሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጾ በፖለቲካ ዓለም ዉስጥ ፍጹም ታማኝ ወዳጅ ባለመኖሩ ግንኙነታችን ግልጽ መስመር ሊኖረዉ ይገባል ብሏል፡፡

Via :- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
#Adawa #አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች፣ ለአማራ እና መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለ124ኛው የአድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል፤

አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ ለመከፋፈል የአውሮጳ ሃያላን በጀርመን በርሊን ኮንፈረንስ ከተሰባሰቡና ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ጣሊያን ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለማድረግና ሀብቷን ለመመዝበር፣ በሂደትም ኮሎኒያሊስት ሰፋሪዎችን አየሩ ተስማሚ በሆነው በኢትዮጵያ ደጋማ መሬቶች ለማስፈር ቋመጠች። ኢትዮጵያን አንበርክካ የቅኝ ግዛትን ኅልሟን ለማሳካት የጦር ክተት ዘመቻዋን አወጀች፡፡

ጠንቃቃና ብልህ የነበሩት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ (እምየ ምኒሊክ) የፋሽስት ጣሊያንን ኅልም ለማምከን መስከረም 17 ቀን 1888 ዓ.ም ሕዝባቸው ለአገሩ ነፃነትና ለማንነቱ እንዲፋለም ብሔራዊ የክተት ዘመቻ ጥሪ አወጁ፡፡

ተጨማሪ⬇️
https://telegra.ph/Adawa-03-01-2