YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኤክስፖርት ዘርፍ ከአምናው የበጀት አመት አጋማሽ አንፃር መጠነኛ መሻሻል ቢያሳይም ማሳካት የተቻለው ግን የዕቅዱን 80 በመቶ ነው፣ በዚህም ባሳለፍነው 6 ወራት 1.33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ከፍተኛ ውጤት ከታየባቸው ዘርፎች አንደኛው የአበባ ንግድ ሲሆን የእቅዱ 183% ማሳካት ተችሏል።

ምንጭ:Capital
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል በሸካና ቤንች ማጂ ዞኖች የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ!

በደቡብ ክልል በሸካ እና ቤንች ማጂ ዞኖች የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ የፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው እንደገለጸው፥ ባለፉት 2 ሳምንታት ቴፒ ከተማን ጨምሮ በተፈጠረው ግጭት የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።ግጭቱ በአካባቢው የመዋቅር አደረጃጀት ጥያቄን ወደ ግጭት ለመውሰድ በሞከሩ የተደራጁ ቡድኖች የተፈጠረ ስለመሆኑም ገልጿል።ከአንድ አመት ወዲህ በአካባቢው ተደጋጋሚ ግጭቶች ሲከሰቱ ይስተዋላል።

ተጨማሪ👇👇👇😒

https://telegra.ph/BenchiandSheka-02-07
75 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈትተው ዛር ሌሊት ከታንዛኒያ ተነስተው ነገ ጠዋት አዲስ አበባ ይገባሉ፤!

ከህገ-ወጥ ስደት ጋር በተያያዘ በታንዛኒያ መንግስት ቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ የታንዛኒያ ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ እስር ቤቶች የሚገኙ 1443 ዜጎችን በማስፈታት ወደ አገር ቤት ለመመለስ ኤምባሲው በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓትም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሁሉ በማጠናቀቅ ዜጎችን የመመለሱን ስራ በይፋ ጀምሯል።ለመጀመሪያ ዙር ጉዞ ዝግጁ የሆኑ 75 ዜጎች ሙትዋራ ሉሉንግዌ ከሚባል እስር ቤት ተፈትተው ዳሬ ሰላም የደረሱ ሲሆን ነገ ከጠዋቱ 1፡30 (7፡30) አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ። በቀጣዩ ሳምንትም ከረበዕ ጀምሮ የተቀሩትን ዜጎች የማጓጓዝ ስራው ይቀጥላል።

ዜጎችን ወደ አገር የመመለሱ ስራ በዋናነት በኢትዮጵያ መንግስት የሚከናወን ሲሆን ለ 1443 ዜጎች የአየር ትኬት አቅርቦት የኢትዮጵያ መንግስት ያደርጋል። የዓለም አቀፉ ልደተኞች ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት የአገር ውስጥ መጓጓዣ በማቅረብና ወደ አገር ከተመለሱ በኋላ ባለው የመልሶ ሟቋቋም ስራ ውስጥ ይሳተፋሉ።በዳሬ ሰላም ኤምባሲ መከፈቱን ተከትሎ እስከ አሁን ድረስ 1100 የሚሆኑ ዜጎች በተለያየ ወቅት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ የሚታወስ ነው።


ምንጭ: በዳሬሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ጃፓን በጎዳናዋ የሚንቀሳቀስ መስኪድ ለሙስሊሞች አዘጋጀች።

የተንቀሳቀሽ መስጊዱ በ2020 በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለሙስሊም ተሳታፊዎች ንፁህና ደህንነቱ የተጠበቀ የፀሎት ስፍራን ማዘጋጀትን አላማው ያደረገ ሲሆን በዚህ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ጃፖን ለሁሉም ሀይማኖት ተከታዮች በተለያዩ የውድድር ስፍራዎች አስፈላጊ መገልገያዎችን ለማዘጋጀት እየተሰናዳች መሆኑ ተጠቁሟል።ይሄ የመጀመሪያው ተንቀሳቃሽ መስጊድ 48 ስኩዌር ሜትር ስፋት ሲኖረው፥ ከመኪናው የኋላ ክፍል የሚከፈት የተሟላ የፀሎት ክፍል አለው 50 ሰወዎችን ማስተናገድ የሚችል ነው።
በጃፓን ከ100,000 እስከ 200,000 ሙስሊሞች እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን 105 መስጊዶች እንደሚገኙ የሀገሪቱ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አስታውቀዋል።

Via EOC-Tokyo 2020
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ሀገራት እና መንግስታት መሪዎች ለአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

እስካሁንም  የጅቡቲው ፕሬዚዳንት አስማኤል ኦማር ጌሌህ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን እሁድ እና ሰኞ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ከዚያ ቀደም ብሎ የህብረቱ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ጉባኤም ትናንት እና ዛሬ ተካሂዷል።ጉባኤው “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት”በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።ለጉባኤው ከህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተጨማሪ የተመድ ዋና ፀሃፊ እና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሀላፊዎች ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሠላምና ፀጥታ ም/ቤት አባል ሆና ተመረጠች!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሠላምና ፀጥታ ም/ቤት አባል በመሆኗ ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ለማገልገል በአባልነት ተመርጣለች፡፡ ከምስራቅ አፍሪካ ክልል ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ጅቡቲ ለቀጣዩ ሁለት ዓመታት ለማገልገል ተመርጣለች፡፡የአፍሪካ የሠላምና የፀጥታ ም/ቤት 15 አበላት ያሉት ሲሆን በአፍሪካ ህብረት ግጭትን ለመከላከልና ለመፍታት የተቋቋመ አካል ነው፡፡

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa
አፍሪካዊቷ ሀገር ኢኳቶሪያል ጊኒ ቻይና ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት የሚያግዝ የ2 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ከዚው ጋር በተገናኘ ቢቢሲ የሁለቱን ሀገራት GDP ለንፅፅር ያቀረበ ሲሆን የቻይና ጥቅል ሀገራዊ ምርት 13.6 ትሪሊዮን ዶላር ሲሆን የኢኳቶሪያክ ጊኒ 13.4 ቢሊዮን ዶላር ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የመሰረት ድንጋዩ ዛሬ ይጣላል የተባለው የቡና ፓርክ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ፡፡

የቡና ፓርኩ በአዲስ አበባ በ30 ሄክታር መሬት ላይ በ50 ሚሊየን ዶላር እንደሚገነባ ባሳለፍነው ነሀሴ ላይ ነበር ይፋ የተደረገው።በ50 ሚሊየን ዶላር ይገነባል የተባለው የቡና ፓርክ የመሰረት ድንጋይ ዛሬ የቀመጣል ቢባልም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያን እስፔሻሊቲ ቡና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ያስተዋውቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ የቡና ፓርክ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ መርሃ ግብር መራዘሙን ባለስልጣኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡ባለስልጣኑ ይህ ፕሮግራም ለምን እንደተራዘመ እና የግንባታ መሰረተ ድንጋዩ መቼ እንደሚካሄድ ከመናገር ተቆጥቧል።

ምንጭ:Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ባልተፈቀደ አግባብ የኢትዮጵያን ፓስፖርት በእጃቸው ያስገቡ 29 የውጭ ሀገር ዜጎች ፓስፖርቶችን እንደተሰረዘ የኢምግሬሽን ሃላፊዎች ማስታወቃቸውን ሸገር ዘግቧል፡፡ ፓስፖርት በገንዘብ የገዙ 3 የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር ተባረዋል፤ ሌላኛው ደሞ ሊወጣ ሲል ታስሯል፡፡ ፓስፖርት በሕ ወጥ መንገድ በመስጠት የተጠረጠረ የተቋሙ ሠራተኛ ታስሯል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ።

ከአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ጋር የተለያየው ሀዲያ ሆሳዕና የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና አርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያን በምትካቸው ሾሟል።አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ዛሬ በክለቡ ጽህፈት ቤት በመገኘት እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የሚያቆያቸውን የኮንትራት ፊርማ አኑረዋል።

በቀሪዎቹ የሊጉ ጨዋታዎችም ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ክለቡን በሊጉ ለማቆየት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ክለቡ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ ቅጣት እንደተጣለበት ይታወሳል።ዘንድሮ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ሀዲያ ሆሳዕና ካደረጋቸው 12 ጨዋታዎች በ7ቱ ተሸንፎ በ9 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከክለቡ የፌስ ገጽ ዋቢ አድርጎ ፋና ነው የዘገበው።

@YeneTube @FikerAssefa
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።በቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።በዚህ ወቅት በሀገራቱ መካከል ሊኖር በሚችለው የኢንቨስትመንት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ትብብሮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል።ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋርም የካናዳ ባለሀብቶችም አብረው አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፥ በነገው እለት በሚካሄደው የቢዝነስ ፎረም ይካፈላሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈረንጆቹ የካቲት 6 ጀምረው እስከ የካቲት 14 ቀን 2020 በሚቆየው ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ሴኔጋል ያቀናሉ።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
#Coronavirusupdate

የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከሰላሳአንድ ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 637 ደርሷል።

Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ባልታወቀ ታጣቂ ቆስለዋል" የሚል መልእክት በስፋት ሲሰራጭ ነበር።

ዛሬ ማታ የካናዳው ጠ/ሚር አቀባበል ፕሮግራም ላይ አየናቸው። ነው ወይስ ቶሎ ተሻላቸው? 😊

#StopFakeNews
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው አና በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ በተከሰተ ናዳ ለተፈናቀሉ ወገኖች መቋቋሚያ የሚሆን የአርባምንጭ ከተማ አስተዳዳር ቃል በገባው መሰረት በዛሬው እለት በአካል በመገኘት የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አበረከተ፡፡

በዛሬው እለት የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን ደነቀ በተገኙበት

➡️የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በአርባምንጭ ዙርያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው -የ300 ሺህ ብር
➡️ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ በተከሰተ ናዳ ለተፈናቀሉ ወገኖች-የ200 ሺህ ብር
➡️የአርባምንጭ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ በተከሰተ ናዳ ለተፈናቀሉ-በጥሬ ገንዘብ 50ሺህ ብር --የአርባምንጭ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው በአይነት 200 ኩንታል በቆሎ
➡️የኦሞቲክ ጄኔራል ትሬዲንግ ( ፓራዳይዝ ሎጂ ) በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው በአይነት 500መቶ ብርድ ልብስ
➡️የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው በአይነት 100 ኩኒታል በቆሎ መቋቋሚያ እንዲሆን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ምንጭ: የከተማ አስተዳደሩ ኮ/ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ለሚበሩ ካፒቲኖች እና የበረራ አስተናጋጆች የሰርጂካል ጭንብል እንዲያጠልቁ አዟል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ወደ ቻይና የሚያደርገውን ጉዞ እንዲያቆም ግፊት እየተደረገበት ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከባለፈው እሮብ ጀምሮ ወደ ኤዥያ ፣አፍሪካ ፣እና መካከለኛው ምስራቅ ለሚበሩ ለ ካፒቲኖች እና የበረራ አስተናጋጆች የሰርጂካል ጭንብል እንዲያጠልቁ ያዘዘ ሲሆን መልሶ ግን ትናንት አርብ ባወጣው ማስታወቂያ የሰርጂካል ጭንብሉ መጋዘን ውስጥ በቂ ክምችት ስለሌለ ቻይና ለሚበረሩ የካቢን ክሪው አባላቱ ብቻ እንደሚሰጥና መደበኛው አፍ ላይ የሚደረገው ጭንብል ግን ህንድ ፣ጃፓን ፣ሲንጋፓር ፣ፊሊፔንስ ለሚበሩ የካቢን ክሪው አባላት ስራ ላይ ሲሰማሩ እንዲያደርጉ አዟል።

Via:- Fidel Post
@YeneTube @Fikerassefa
የኮሮና ተዋህሲና በኢትዮጵያ የነዋሪዎች ስጋት

የኮሮና ተዋህሲ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ እስካሁን 29 ጥቆማዎች ታይተው በ14ቱ ላይ የበሽታው አጠራጣሪ ምልክቶች ስለታየባቸው በማቆያ ክትትል እየተደረግባቸው መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ። ከነዚህ ውስጥ ስምንቱ የደም ናሙናቸው ደቡብ አፍሪካ ተልኮ በተደረገው ምርመራ ነጻ የሆኑ ሲሆን ሌሎች ስድስት ሰዎች ፣ አንዱ ቻይናዊ ፣ አምስቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ወቅት የምርመራ ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኳል ተብሏል።

በጉዳዩ ዙሪያ ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች ቫይረሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ይገባል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ቢያቆም ፍላጎታቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

Via:- DW
@YeneTube @Yenetube
የአፍሪካ ሀገራት እና መንግስታት መሪዎች እንዲሁም የሌሎች ሀገራት መሪዎች ለአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

እስካሁንም የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ እና የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በተጨማሪም የካናዳ እና የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን እሁድ እና ሰኞ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ከዚያ ቀደም ብሎ የህብረቱ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ትናንት ተጠናቋል።ጉባኤው “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።ለጉባኤው ከህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተጨማሪ የተመድ ዋና ፀሃፊ እና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሀላፊዎች ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እና ልዑካን ቡድናቸውን ዛሬ ማለዳ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ካናዳ በአያሌ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደ ሆነች ተናግረዋል።በኢትዮጵያ የሚካሄዱትን ለውጦች እና ሪፎርሞች እንደሚያደንቁና እንደ ወዳጅ፣ ደግሞም እንደ አጋር በጎን ሆነው ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉም አውስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በዲሞክራታይዜሽን እና ሁለተናዊ ብልጽግናን በመገንባት ላይ ስለተመሠረቱት ባለብዙ ገጽታ ቀጣይ የሪፎርም ሥራዎች ገልጸዋል።

ሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የጋራ ፍላጎት በሚስተዋልባቸው የልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ንግድ፣ የኢነርጂ ኢንቨስትመንት፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ መድኃኒት እና ተያያዥ ግብአቶች ላይ በጋራ ስለመሥራት ተወያይተዋል። የቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ በጋራ መሥራትንም አንዱ የትብብር አቅጣጫ አድርገው አንስተዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በድሬደዋ ጅቡቲ መንገድ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ አስራ ስድስት ሰዎች ሞቱ!

በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን ትራፊክ ምርመራ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጉሌድ ገዲድ እንደገለጹት በድሬደዋ ጅቡቲ መንገድ ከድሬደዋ ሃያ ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ላስዴሬ በተባለ ቦታ ንጋት አስራ አንድ ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አስራ ስድስት ሰዎች ሞተዋል። ኃላፊው እንዳሉት በደረሰው አደጋ አምስት ሰዎች ከባድ እና ሰባት ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ። በግጭት አደጋው ሶስት ሚኒባስ እና ሁለት የጭነት ትራከር ተሽከርካሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስዔ በከፍተኛ ፍጥነት ማሽከርከር እንደሆን የተናገሩት ምክትል ኢንስፔክተር ጉሌድ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። በቅርቡ ስራ የጀመረው የድሬደዋ ጅቡቲ የክፍያ መንገድ ከፍጥነት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ከፍተኛ አደጋ እያስተናገደ መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር በመግለጫቸው ጠቁመዋል። በደረሰው የትራፊክ አደጋ ሳቢያ ለሰዓታት ዝግ ሆኖ የነበረው የድሬደዋ ጅቡቲ መንገድ በአሁኑ ሰዓት ለትራፊክ ክፍት ተደርጓል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
13 ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በትላንትናው ምሽት 13 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ማዋሉን በሃላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ የሃላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳሰበ፡፡የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ በበኩሉ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በተደራጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

Via South TV
@YeneTube @FikerAssefa