ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች ነጻ ሆኑ።
አሜሪካንን በከፍተኛ ሁኔታ ከፍሎ የነበረውና በአገሪቱ ምክር ቤት ፕሬዝዳንቱን ከስልጣን ለማስነሳት የቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ፤ ትራምፕም ነጻ ሆኑ።በፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባላት በበላይነት በተያዘው የአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ በተሰጠ ድምጽ፤ ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም የቀረበባቸው ክስ 52 ለ 48 በሆነ ድምጽ እንዲሁም የአገሪቱን ምክር ቤት ሥራ በማደናቀፍ ለሚለው ክስ ደግሞ 53 ለ47 በሆነ ድምጽ ብልጫ ክሶቹ ውድቅ ተደርገዋል።
የፕሬዝዳንቱ ተቀናቃኞች የሆኑት ዴሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ይሆናሉ በተባሉት ጆ ባይደን ላይ ዩክሬን አጥፍተዋል ብላ ምርምራ እንድታደርግ ግፊት አድርገዋል ሲሉ ከሰዋቸው ነበር። ትራምፕ ባለንበት የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ላይ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ በመሳተፍ ክስ ተመስርቶበት ምርጫ የተወዳደረ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ይሆናሉ ተብሏል።
የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ትናንት በሰጠው ታሪካዊ ድምጽ የአሜሪካ 45ኛው ፕሬዝዳንት ከዩክሬን ጋር ባደረጉት ያልተገባ ግንኙነት ሳቢያ ከስልጣናቸው ከመባረር አትርፏቸዋል።. ትራምፕ ቀርቦባቸው ከነበሩት ክሶች በአንዱ እንኳን ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው ቢሆን ኖሮ ስልጣናቸውን ለምክትላቸው አስረክበው ዋይት ሐውስን ጥለው መውጣት ይጠበቅባቸው ነበር።ትራምፕ ላይ የቀረበው ክስ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት እንዲታይ ያጸደቀው በተቀናቃኞቻቸው ዴሞክራቶች የሚመራው የተወካዮች ምክር ቤት ነበር።
በቀጣዩ ምርጫ ለሁለተኛ ዙር ለመወዳደር እየተዘጋጁ ያሉት ትራምፕ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ክሱን ውድቅ እስኪያደርገው ድረስ "ምንም አይነት ጥፋት አልፈጸምኩም" በማለት ሲከራከሩ ቆይተዋል።የፕሬዝዳንቱን የምርጫ ዘመቻ ከሚመራው ቡድን የምክር ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የተሰጠ መግለጫ እንዳለው "ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሆነዋል። እናም አሁን የአሜሪካን ሕዝብን ለማገልገል ወደ መደበኛው ሥራ የመመለሻ ጊዜ ነው" ብሏል።"ምንም ማድረግ የማይችሉት ዴምክራቶች ትራምፕን እንደማያሸንፉ ቢያውቁም፤ ይህንን ክስ አቅርበዋል" ሲል ይህ አስቀያሚና እርባና የሌለው ውጣ ውረድ የዴሞክራቶች የምርጫ ዘመቻ ታክቲክ ነው ሲል ከሷል።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 563 ደረሰ!
በቻይና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱ ተነገረ።በትናንትናው እለት ብቻ በሁቤይ ግዛት 70 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።ከዚህ በተጨማሪም 3 ሺህ አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኝተዋልም ተብሏል።ከዚህ ባለፈም በሆንግ ኮንግ እና ፊሊፒንስ ሁለት ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋልም ነው የተባለው።በጃፓኗ የወደብ ከተማ ዮኮሃማ ደግሞ 10 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።ከዚህ ባለፈም 3 ሺህ 700 ሰዎች ለሁለት ሳምንታ በልዩ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ ተደርገዋልም ነው የተባለው። የቫይረሱ ስርጭት አድማሱን እያሰፋ ሲሆን፥ አሁን ላይ ከቻይና ውጭ ከ260 በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው እየተነገረ ነው።
ምንጭ፦ ሬውተርስ/FBC

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት ከ104 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሬያለሁ አለ፡፡
ለመፍጠር ታቅዶ ከነበረው አንፃር ማሳካት የተቻለው 93 በመቶውን እንደሆነ ከስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የስራ እድሉን ካገኙት መካከል 83 በመቶዎቹ ወጣቶች ናቸው፡፡
ሴቶች የ45.99 በመቶ ድርሻ ሲኖራቸው የዩኒቨርስቲና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተመራቂዎች ይገኙበታል፡፡በጊዜ ማዕቀፉ ለ317 አካል ጉዳተኞች የስራ እድል ማመቻቸቱን ቢሮው በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ የከተማ ግብርና፣ ንግድ እንዲሁም አገልግሎት ዘርፉ፣ በግልና የመንግስት ተቋማት የስራ እድሉ የተገኘባቸው መስኮች ናቸው ተብሏል፡፡
Via Sheger FM

የታዋቂው ስፓርታከስ ፊልም መሪ ተዋናይ ኪርክ ዳግላስ በ103 አመቱ አረፈ። ልጁ ሚካኤል ዳግላስ በኢንስታግራም ገፁ እሱና ወንድሞቹ አባታቸውን በማጣታቸው እንዳዘኑ አስፍሯል። ዳግላስ በ1960ዎቹ የሆሊዉድ ወርቃማ ዘመን ስማቸው ከሚነሳላቸው ተዋንያን አንዱ የነበረ ሲሆን 3 ጊዜ ለኦስካር ሽልማት መታጨትም ችሎ ነበር። በ1996 የህይወት ዘመን የኦስካር ሽልማትም ተበርክቶለታል።
ምንጭ:Variety
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:Variety
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ 120 አውቶቡሶችን ማሰማራቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።
የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ካስገባቸው አዲስ የአንበሳ ከተማ አውቶቡሶች 20ዎቹ በልዩ ሁኔታ የሚሰማሩ ናቸው፡፡በተለይም በከተማዋ ችግሩ ባስ ባባቸው አካባቢዎችን በመምረጥ ተሸከርካሪዎች ችግር በሚታይባቸው ስፍራዎች በተወርዋሪነት አገልግሎት እንደሚሰጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ መልካሙ ሌሊሳ ለኢቲቪ ገልጸዋል።
በልዩ ሁኔታ አገልግሎት የሚሰጡት 20 አውቶቡሶች የትራንስፖርት ችግሩ በሚባባስበት ጠዋት ስራ መግቢያና ማታ ስራ መውጫ ሰዓት ላይ በተሻለ ሁኔታ ፈጥነው በመድረስ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡አውቶቡሶቹ ከተለመደው አሰራር ወጣ በማለትም 35 ሰዎችን በወንበር ብቻ በመጫን ሰው በሚበዛበት መገናኛ፣ ፒያሳና ሜክሲኮ መስመር ወደ ስራ መግባታቸውን አቶ መልካሙ ተናግረዋል።እንደ ቢሮው ገለጻ ተሸከርካራቹ በየመንገዱ ቆመው ሰው የሚጭኑ ሳይሆኑ በልዩ ሁኔታ ከመነሻ እስከ መድረሻቸው ቀጥታ በፍጥነት እንደሚጓዙ ባለስልጣኑ ገልጻል።
ምንጭ: ኢቲቪ

የኬኒያው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ተቃወሙ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮሮና ቫይረስ በተስፋፋበት ወቅት ወደ ቻይና ጉዞ ማድረጉ ተገቢ እንዳልሆነ የኬኒያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬኒያታ ተናገሩ፡፡አየር መንገዱ በዚህ ወቅት ወደ ቻይና መብረሩ ቫይረሱ አፍሪካን ወደ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡ኬኒያታ‹‹ ጭንቀታችን ቻይና ቫይረሱን ትቆጣጠረዋለች የሚለው ሳይሆን የሚያሳስበን ደካማ የጤና ሥርዓት ባለን አገራት ውስጥ እንዳይገባ ነው›› ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በሚያደርገው የቀጥታ በረራ አምስት መዳረሻዎች ሲኖሩት ፤ ወደ ቤጂንግ፣ ሻንጋይ፣ ጉዋንዙ፣ ቼንጉዱ እና ሆንግ ኮንግ በረራዎቹን ማድረጉ ቫይረሱ ወደ አህጉሪቱ እንዳይገባ ስጋት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡አየር መንገዱ አሁንም ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ አላቋረጠም፡፡ትላንት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ተወልደ ገብረ ማርያም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ቻይና በረራ ማቆም ዋስትና አይሰጥም ብለዋል፡፡ባሳለፍነው ሳምንት ኬኒያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ማቋረጣቸውም የሚታወስ ነው፡፡
Via Addis Maleda

የኦነግ ሸኔ የታጠቀ ቡድን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልክ ንብረት አቃጥለው የጦር መሳሪያዎችን መዝረፋቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በክልሉ 7 ሰዎች ታግተው ተወስደዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሃሰት መሆኑንም የክልሉ ፖሊስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ል ኮሚሽነር ነጋ ጃራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የኦነግ ሸኔ የታጠቁ አካላት ወደ ክልሉ ገብተው ንብረት አቃጥለው እና ዘርፈው ሸሽተዋል ብለዋል።እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ ድርጊቱ የተፈጠረው ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም በአሶሳ ዞን ውስጥ ባባሲ ወረዳ ውሽማ ጥርጊጊ የሚባል ቀበሌ ላይ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 የሚባሉ ቦታዎች ነው፡፡
ከዚህ በፊት በዚህ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ 4 ሰዎች አካባቢውን ለቀው የሄዱና በኋላም የኦነግ ሸኔ ቡድን የተቀላቀሉ ነበሩ፡፡የኋላ ኋላ እነርሱን ጨምሮ ወደ 28 የሚደርሱ የታጠቁ ሀይሎች በ25/5/2012 ወደ ቀበሌው መጥተው የቀድሞውን የቀበሌ ሊቀ መንበር አቶ አደም ጉምዛ የተባለውን ግለሰብ ያገኙታል፡፡እኚህን የቀድሞ ሊቀመንበር ባገኙ ሰዓት በወቅቱ የነበራቸው ፍላጎት የጦር መሳሪያና ከዚህ በፊት የተሰበሰበ ግብር አለ እርሱን ማምጣት አለብህ ብለው በጠየቋቸው ሰዓት ምንም እንደሌለ በመንገር ይመልሷቸዋል፡፡
በኋላም የዚህን ሰውዬ 6 ቤቶች አቃጥለው 3 ኩንታል ቦሎቄ ፤ ሁለት ኩንታል ጤፍ 1 ኩንታል ጥቁር አዝሙድ ግማሽ ኩንታል ተልባና ሁለት ኩንታል ኑግ በሳት ማቃጠላቸው ተገልጿል።በዛው ቀበሌ ውስጥ ያገኙትን የኢትዮጵያና የክልሉን ሰንደቅ አላማ በማቃጠል ከሚኒሻዎችና ከግለሰቦች ላይ 3 ክላሽና 6 ኋላ ቀር መሳሪያዎችን ነጥቀው መሸሻቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡የክልሉ የፀጥታ ሀይል ወዲያው ወደ አካባቢው ያሰማራን ቢሆንም ሰዎቹን በወቅቱ ማግኘት አልቻልንም በማለት ነግረውናል፡፡
ፀረ-ሰላም ሀይሎች በባህሪያቸው አንድ ቦታ ተረጋግተው የሚቀመጡ ባለመሆናቸው የፀጥታ አካሉ ወደ አካባቢው አምርቶ አሰሳ ቢያደርግም ሊያገኛቸው ግን አልቻለም፡፡በአሁኑ ሰዓት አካባቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነሩ በእኛ ግምገማ እስካሁን በማህበራዊ ሚዲያ የሚራገበው ወሬ አሉባልታ ነው ብለዋል፡፡በክልሉ የታገቱ 7 ሰዎች አሉ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ግን ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ።
በእርግጥ ንብረት ላይ ጉዳቶች አድርሰው ሸሽቷል፡፡ ከዛ ውጪ ወደ አካባቢው ያሰማራናቸው የፀጥታ ሀይሎች በቦታው ደርሰው ህዝቡን አረጋግተው ይህንን መረጃ አድርሰውናል ብለዋል፡፡ይህ ከሆነበት እለት አንስቶ የኦነግ ሸኔ አባላት ለጥቃት ወደ ክልሉ መግባታቸውን ምልክቶች ታይተዋል በመሆኑም በዚህ ፀረ-ሰላም ሀይል ላይ እርምጃ ለመውሰድና ለመቆጣጠር የክልሉ ፀረ-ሽምቅ ሀይል ፤ የክልሉ ፖሊስ ፤የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በጋራ በመሆን በአካባቢው እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡
Via Ethio FM

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ ከየካቲት 9-11 ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ፡፡ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና ከፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ጋር በሀገሪቱ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ፡፡ ፖምፒዮ ከአፍሪካ ሴኔጋል እና አንጎላንም ይጎበኛሉ፡፡
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የአትሌት አባዲ ሃዲስ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ!
የወጣቱ አትሌት አባዲ ሀዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬ እለት የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የትግራይ ክልል አትሌቲክሰ ፌዴሬሽንና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ የክለብ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ አትሌቶች፣ የዞን አመራሮች፣ ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ በተገኙበት ከቀኑ 7፡00 ላይ በትውልድ ስፍራው ማይጨው ከተማ ልዩ ስሙ እንዳመሆኒ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡
Via EAF

ሳዑዲ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የ5 አፍሪካ ሀገራት ዜጎች በ3 ወራት ውስጥ ከወጡ ቅጣታቸውን አነሳላቸዋለሁ ማለቷን ሳዑዲ ጋዜት ዘግቧል፡፡ ስደተኞቹ የፓስፖርት፣ ትራፊክ እና ሌሎች የተከማቹ ቅጣቶችና ክፍያዎች ያሉባቸው ናቸው፡፡ ሌላ ጊዜ ከተመለሱ ግን ቅጣቱ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮናን ቫይረስ ምልክት ማየቱን ቀድሞ ይፋ ያረገው (Whistleblower) ዶክተር ህይወቱ አለፈ!
ሊ ዌንሊያንግ የተባለውና ባለፈው ታህሳስ አጋማሽ ላይ የኮሮና ቫይረስን ምልክት በ7 ታካሚዎች ላይ ማየቱን ቀድሞ በዊቻት ግሩፕ ለሆስፒታሉ ማህበረሰብ በማሳወቁ በፖሊስ ክትትልና ማስፈራሪያ ደርሶበት የነበርው ዶክተር በቫይረሱ ተጠቅቶ ህይወቱ ማለፉን CNN ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
ሊ ዌንሊያንግ የተባለውና ባለፈው ታህሳስ አጋማሽ ላይ የኮሮና ቫይረስን ምልክት በ7 ታካሚዎች ላይ ማየቱን ቀድሞ በዊቻት ግሩፕ ለሆስፒታሉ ማህበረሰብ በማሳወቁ በፖሊስ ክትትልና ማስፈራሪያ ደርሶበት የነበርው ዶክተር በቫይረሱ ተጠቅቶ ህይወቱ ማለፉን CNN ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
የደህንነት ካሜራዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት እየሰጡ ነው ተባለ!
የተማሪዎችንና የግቢውን ደህንነት ለመጠበቅ በደህንነት ካሜራ የታገዘ የቁጥጥር አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመለከተ፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ካሉ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ መርሀግብሮች የሚያስተምራቸው 50 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች አሉት፡፡በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተማሪዎች ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት እንደሌሎቹ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲም አለመረጋጋቶች ተፈጥረው የተወሰኑ የትምህርት ክፍሎች ስራ አቁመው የነበረ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በአደረገው ከፍተኛ ጥረት ትምህርት እንደገና መጀመሩንና ተማሪዎች ለፈተና መዘጋጀታቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ገልፀዋል፡፡
የተማሪዎችንና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በደህንነት ካሜራ የታገዘ የቁጥጥር አገልግሎት እየተሰጠ አንደሆነ ፕረዚደንቱ ዶ/ር አስራት ለDW በስልክ ተናግረዋል፡፡ ካሜራዎቹ በዋናነት በምግብ አዳራሾች፣ በመግቢያ በሮች፣ በተማሪዎች መማሪያና ማደሪያ ህንፃዎች፣ በቤተ መጽሐት ተገጥመው የ24 ሰዓት የቁጥጥር ስራዎችን ያከናውናሉ፣ መረጃዎችን ይሰጣሉ ብለዋል፡፡
እስካሁንም በማራኪ፣ በአፄ ፋሲልና በአፄ ቴዎድሮስ ካምፓሶች፣ አንዲሁም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 158 የደህንነት ካሜራዎች ተገጥመው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ 100 የደህንነት ካሜራዎችን በፀዳ ግቢና በየግቢው ኮሪደሮችና በሌሎች የደህንነት ስጋት ባላባቸው ቦታዎች ለመግጠም የቅደመ ሁኔታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናችን ዶ/ር አስራት አብራርተዋል፡፡
ምንጭ: ዶይቸ ቨለ

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በዓመት ከአንድ ቢሊየን በላይ እንክብሎችና ሽሮፖችን ማምረት የሚያስችል የመድኃኒት ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑ ተነገረ።
ዛሬ ጥር 28/2012 የመሰረት ድንጋይ የተጣለለት ይህ ፋብሪካ በ10 ሚሊዮን ዶላር መነሻ ካፒታል በአገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ባለሃብቶች በጋራ ይገነባል። አፍሪክዩር የተሰኘው ይህ የመድኃኒት ፋብሪካ ግንባታ ከ18 እስከ 24 ወራት ባለው ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሏል። ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር አንድ ቢሊዮን እንክብሎችንና ሽሮፖችን በዓመት በአንድ ፈረቃ የሚያመርት እንደሚሆን ተገልጿል። ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባም ለ109 ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራልተብሎም ይጠበቃል።
ምንጭ:ፋና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ከሚያደርገው በርከት ያለ ቀጥተኛ በረራ አንፃር ቫይረሱን ወደ አፍሪካ ሊያስገባ የሚችልበት እድል ከፍተኛ ነው ተብሏል።
ከላይ በምስሉ ላይ እደምትመለከቱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር በማገናኘት ቀዳሚ ሆኖ ይታያል።
ምስሉ የቢቢሲ ነው!
@YeneTube @FikerAssefa
ከላይ በምስሉ ላይ እደምትመለከቱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይናን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር በማገናኘት ቀዳሚ ሆኖ ይታያል።
ምስሉ የቢቢሲ ነው!
@YeneTube @FikerAssefa
የጃዋር መሀመድ ጥበቃዎች መነሳታቸውን ኦቢኤን ዘገበ!
በቅርቡ ኦፌኮን የተቀላቀሉት ጃዋር መሃመድ የፌደራል ፖሊስ ሲያደርግላቸው የነበረውን ጥበቃ ከእሁድ ጥር 17/2012 ጀምሮ ማንሳቱን የኦሮሚያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ኦቢኤን በምሽት ሁለት ሰአት ዜናው ላይ አንዳስነበበው መንግስት ለማንኛውም ተፎካካሪ ፓርቲ አመራርም ሆነ አባል የግል ጥበቃ ስለማያደርግ እና አሰራሩም ስለማይፈቅድ ጥበቃዎቹ እንደተነሱ የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ደግሞ አደረኩት ባለው ማጣራት ጃዋር ጠባቂዎቻቸው ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ እንዲያደርጉ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ በፃፈው ደብዳቤ ማስታወቁን አረጋግጫለው ብሏል፡፡የጋዜጣው ኤዲቶሪያል ክፍል ወደ ጃዋር መሃመድ በተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ባደርግም ለግዜው አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል ብሏል፡፡
#Updated
ሁሉ ሰላም ነው ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ተወያይተን የተስማማንበት ነው ብሏል ጃዋር መሃመድ
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

በባምባሲ ወረዳ ሰሞኑን ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት ቦሽማ ቀርኪኪ ቀበሌ ገብተው ጉዳት ለማድረስ ቢሞክሩም በህብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት አለመድረሱ ተገለጸ፡፡
የባምባሲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱላሂ መሀመድ ጉዳዩን አስመልክተው እንደገለጹት ባለፈው ጥር 25/2012 ዓ.ም ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት በወረዳው ቦሽማ ቀርኪኪ ቀበሌ ገብተው እንደነበር ተናግረዋል፡፡እነዚህ አካላት በዚሁ ቀን ከጧቱ 1፡00 አካባቢ ወደ ቀበሌው ሲገቡ የተደራጀ መረጃ ይዘው እንደነበር ያስታወሱት አስተዳዳሪው፣ ከቀበሌ አመራሮች እና ከሚሊሻ አካላት የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ የተለያዩ አስገዳጅ ሙከራ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት፡፡
በዚህም በቀበሌው አስተዳዳሪ ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን የሚናገሩት አቶ አብዱላሂ፣ በአስተዳዳሪው ላይ መጠነኛ የአካል ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፣ ህክምና አግኝተው በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡የወረዳው አስተዳዳሪ አክለውም፣ የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ለመዝረፍ ባደረጉት ሙከራ 1 የመኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ መቃጠሉን ተናግረዋል፡፡ከዚህ ውጪ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን የሚናገሩት አቶ አብዱላሂ፣ "ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ" በሚል የሚናፈሰው መረጃ መሠረት የሌለው መሆኑ ሊታወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ችግሩ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የክልሉ ጸጥታ አካላት እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በቦታው በመገኘት እየተሠራ ያለው ህብረተሰቡን የማወያዬትና የማረጋጋት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ጠቁመዋል፡፡ በቀበሌው አሁን ሠላማዊ ሁኔታ መኖሩንም አክልው ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው በተለይም የመሬት ወረራ እና መሠል ሌሎች ህገ-ወጥ ፍላጎት በመኖራቸው መንግስት በቀጣይ በዚሁ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ከህብረተሰቡ ጥያቄ መነሳቱን የጠቀሱት አቶ አብዱላሂ፣ "ወረዳው ችግሮቹን ለመፍታት ትኩረት ሠጥቶ ይሠራል" ብለዋል፡፡
"ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ ሲገለጹ የነበሩት ህብረተሰቡን የሚያደናግሩ መሠረት የሌላቸው መረጃዎች ሊታረሙ ይገባል" የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው፣ "አሁንም ህዝቡ ተረጋግቶ እንዳይኖር የሚፈልጉ አካላት በመኖራቸው፣ ህብረተሰቡ እነዚህን አካላት በመታገል ረገድ ከመንግስት ጎን መቆም ይጠበቅበታል" ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ምንጭ: የቤ/ጉ/ብ/ክ/መ/መ/ኮ/ቢሮ

በቻይና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ31 ሺህ ሲያልፍ ከ600 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል!
በቻይና በውሃን ግዛት በተቀሰቀሰ ኮሮና ቫይረስ የሚያዙ እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።የቻይና ብሄራዊ የጤና ኮሚሽን በዛሬው እለት እንዳስታወቀው በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 636 ደርሷል።ከዚህ ውስጥ አዲስ የ73 ሰዎች ሞት የተመዘገበ ሲሆን፥ 69ኙ ቫይረሱ በተቀሰቀሰባት ሁቤይ ግዛት መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ትናንት ከነበረው በ3 ሺህ 143 ጭማሪ ማሳየቱን እና አሁን ላይ በአጠቃላይ በቻይና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 31 ሺህ 161 ማድረሱን የኮሚሽኑ ሪፖርት ያመላክታል።
በቻይና በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ካጡት ውስ፥ በሀገሪቱ የቫይረሱን መቀስቀስ ቀድሞ ያስጠነቀቀው የ34 ዓመቱ ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ አንዱ ነው።የዶክተሩ ህልፈት በበርካቶች ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፥ የቻይና መንግስትም ምርመራ መጀመሩ ነው የተገለፀው።በተያያዘም የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጭ በ25 ሀገራት መታየቱን እና በፊሊፒንስ እና በሆንግ ኮንግ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።የዓለም ጤና ድርጅት የዓለም የጤና ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል 675 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንድሚያስፈልግ ገልጿል። ሀገራትም ለዚህ ስራ ትብብር እንዲያደርጉም ጥሪውን አቅርቧል።
ቢቢሲን ጠቅሶ ኤፍ.ቢ.ሲ እንደዘገበው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረጅም ዓመት ያገለገሉ ምስጉን ሰራተኞቹን ሊሸልም ነው።
አየር መንገዱ እንዳስታወቀው በነገው ዕለት ከ20 እስከ 40 አመት ለሰሩ ለ1 ሺህ 200 ሰራተኞች እውቅና እና ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ገልጿል፡፡አየር መንገዱን ለረጅም ጊዜ እና በጡረታ ለተገለሉ ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞቹን በነገው እለት ሊያመሰግን እንደሆነ ነው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ያስታወቀው፡፡በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሳናድ ከተባለው የአውሮፕላን ጥገና አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድና በአውሮፕላን ሞተር ጥገና የሚታወቀው የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ሳናድ ኤሮቴክ የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን አየር መንገድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም እና የሳናድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማንሱር ጃናሂ ስምምነቱን በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።ሳናድ በአውሮፕላን ጥገና እና በአቪዬሽን አካዳሚ መቀመጫውን ዱባይ ያደረገ ረዥም ልምድና አቅም ያለው ተቋም እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

ኖቬል ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት የተዘጋጀ ሳምንታዊ መግለጫ!👇👇👇
➡️ እስከአሁን ድረስ 29 ጥቆማዎች በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውስጥ ለሚገኘው የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰዋል፡፡ 29ኙ ላይ በተደረገው ማጣራት፣ 14ቱ ምልክቶች ያሳዩ ስለነበረ (suspected cases ) ፤ በሽታው እንዳለባቸው ወይም እንሌለባቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ወደ መቆያ ስፍራ (Isolation center)) እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡ወደ ደቡብ አፍሪካ 11 ናሙናዎች ተልከው ስምንቱ (8) ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ 3 ናሙና ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ የምርምራው ውጤት እየተጠበቀ ሲሆን በቀጣዬቹ ቀናት 3 ናሙናዎች ለምርመራ የሚላኩ ይሆናል፡፡
➡️ ከቻይና ዉሃን ከተማ የሚመጡ ማናቸውም መንገደኞች ወደ ለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲገቡ ተወስኗል በመሆኑም ወደ ሀገር እንደገቡ በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው አስፈላጊው የህክምና ክትትል የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡
➡️ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ከሌላው መንገደኛ ጋር ሳይቀላቀሉ የሙቀት ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን በተጨማሪም ከቻይና ለሚመጡ መንገደኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የኢሚግሬሽን ልዩ መስኮት ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡
➡️ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የጤና ሁኔታ መከታተል እንዲቻል ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቶ አገልግሎቱም ተጀምሯል፡፡
➡️ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ለሚሰሩ ሁሉም አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን
phemdatacenter@gmail.com ወይም ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡
ምንጭ: ጤና ሚኒስቴር