YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#FakeNewsAlert

የሀዋሳ የመጠጥ ውሀ ተመርዟል እየተባለ በስፋት እየተሰራጨ ስላለው ወሬ ዛሬ ጠዋት የከተማውን ከንቲባ አቶ ሱካሬ ሹዳ በስልክ አናግሬአቸው ነበር። ስለጉዳዩ ሲሙልሱም:

"እኛም ትናንት ወሬውን ሰምተን ነበር። እንደው ለማንኛውም እናጣራው ብለን ላቦራቶሪ ልከነው ነበር። በውጤቱም ምንም አይነት መመረዝ እንደሌለው ተረጋግጧል። ይህ ህብረተሰቡን ለማሸበር ሆን ተብሎ የሚነዛ ወሬ ነው፣ ሌላ የሀሰት መረጃም ይመጣል ብለን እንገምታለን። በዚህ የውሀ ጉዳይ ዛሬ ዝርዝር መረጃ ለመገናኛ ብዙሀን እንሰጣለን።"

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"በሰላም ሚኒስትር እና የደህዴን ሊቀመንበሯ ሙፈርያት ካሚል ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ" ተብሎ እየተሰራጨ ስላለው መረጃ እውነትነት ለማረጋገጥ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሄርሜላ ሰለሞን ጋር ደውዬ ነበር። ዳይሬክተሯ ወሬውን ለማጣራት ወ/ሮ ሙፈርያት ጋር ከደወለች በሁዋላ ይህንን መረጃ አቀብላኛለች:

"ሚኒስትሯ ቀኑን ሙሉ ሀዋሳ ስብሰባ ላይ ነው የዋሉት። እንኳን ሙከራ ሊደረግ ለመሞከር እድል የሚኖርበት ሁኔታ አልነበረም። ለማንኛውም የተባለው ሙሉ ለሙሉ ውሸት ነው ብለው ሚኒስትሯ እራሳቸው አሁን በስልክ ነግረውኛል። ምንም የተለየ ነገር አልተፈጠረም።"

ይህንኑ ጉዳይ ከአንድ የክልሉ ባለስልጣን (ስማቸው እንዲጠቀስ አልፈለጉም) ለማረጋገጥ ሞክሬ "ፌክ ኒውስ ነው አባቴ" ተብያለሁ።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

ይህንን የሀሰት ወሬ እያሰራጨ ያለው Ethio 360 media የሚል 7,000 ገደማ ተከታይ ያለው የሀሰት ገፅ ነው። ትክክለኛው የEthio 360 Media ገፅ ወደ 87,000 ገደማ ተከታይ ያለው ነው።

ወደፊትም ሌላ የሀሰት ዜና ሊለቁ ስለሚችል ጥንቃቄ አይከፋም በሚል ላጋራችሁ ወደድኩ!

-Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ "የፈተና ውጤቱን አንቀበልም አሉ" ተብሎ የተናፈሰው ወሬ የሀሰት እንደሆነ ተረጋግጧል።

-Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"ጅማ ውስጥ አንድ የሀይማኖት አባት ተገደሉ፣ ሬሳቸው ተጥሎ ተገኘ" እየተባለ የሚወራው ፍፁም ውሸት እንደሆነ ከክልሉ ባለስልጣናት እንዲሁም ከቤተ- ክህነት ለማረጋገጥ ችያለሁ።

በአዲሱ አመት ለፌክ ዜና አሰራጮች ልቦናውን ይስጥልን!

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከጠ/ሚር ቢሮ ተባረረ" ተብሎ በአንዳንድ የፌስቡክ ገፆች የተፃፈው የሀሰት መረጃ እንደሆነ ከተለያዩ ቦታዎች ለማረጋገጥ ችያለሁ።

Via :- Elias meseret
@Yenetube @Fikerassefa
#FakeNewsAlert

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ሰራተኞች የእድገት መሰላልና የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ ተደረገ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

የጎንደር ከተማ ውሀ ተመርዟል?

የከተማው ውሀ እና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀይማኖት በለጠ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ የነገሩኝ:

"በሶሻል ሚድያ የሚናፈሰውን ይህን ወሬ ሰምተነዋል። ነገር ግን ወሬው የሀሰት እና ህዝብን ለመረበሽ የተሰራጨ ነው። ይህን እያሰራጨ ያለው የተደራጀ ሀይል ነው። ሁሌ ግርግር ሲፈጠር እንዲህ አይነት የሀሰት ወሬ እየተለመደ ነው። ውሃው እንደሁሌው የተደራጀ የ24 ሰአት ጥበቃ እየተደረገለት ነው። ምንም አይነት የተፈጠረ ችግር የለም፣ በላቦራቶሪ ተጣርቶም ችግር እንደሌለበት ተረጋግጧል። በአካባቢው ሚድያ ዛሬ ጠዋት መልእክት እናስተላልፋለን።"

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️
#FakeNewsAlert

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ” በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ፌስቡክ ገጽ የተዘገበው ዜና የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬ እለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ድርድር ያላደረገ ሲሆን የኢቢሲም ሆነ የኢቢሲን ዜና መሰረት በማድረግ የዘገቡ ሌሎች ሚዲያዎች ዜናዎችን ከማሰራጨታቸው በፊት ማጣራት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳስባል፡፡ ቦርዱ ማንኛውንም የመረጃ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

Souce: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ሰልፍ እንዳያረግ እንደተከለከለ ገልፆ ለዛሬ ታስቦ የነበረው ሰልፍ እንደተሰረዘ ትናንት ገልፆ ነበር። ነገር ግን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ስም የተከፈተ አንድ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ ሰልፉ እንደሚካሄድ ፅፎ ህዝቡን እያደናገረ ነው።

ይህ አደገኛ ፌክ ኒውስ ነው! እውነት መስሎት ሰልፍ የወጣ ሰው ከፖሊስ ጋር አላስፈላጊ ፍጥጫ ውስጥ ሊገባ ይችላል።

ጥቆማ: የፌደራል ፖሊስ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ይህ ነው:
https://www.facebook.com/Addisababapolice/
#FakeNewsAlert

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እያለሁ የታሪክ አስተማሪዬ የነበረው መምህር ታዬ ቦጋለ ይችን መልእክት አስተላልፍልኝ ብሎኛል!

"እንደሰማኸው ተመርዤ የነበረ ቢሆንም አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ። በሞት ተለየ እየተባለ የሚፃፈው የሀሰት ነው። ጥርጣሬዬ በአንድ የቲቪ ቃለ- መጠይቅ ወቅት የተሰጠኝ ውሀ ይህንን መመረዝ አስከትሏል። አንድ ዶክተር በጣም ከፍተኛ መመረዝ እንዳጋጠመኝ አሳውቆኛል። ነገር ግን ክትትል እያረግኩ ነው፣ ጥሩ ሁኔታ ላይም እገኛለሁ።"

Via:- ኤልያስ መሰረት
@Yenetube @Fikerassefa
#FakeNewsAlert

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በምግብ ተመርዘው ታመዋል ተብሎ የተሰራጨው ወሬ የሀሰት ፈጠራ ነው። "ምኞት ይሆናል እንጂ አልተመረዝኩም አልታመምኩም "ብለውኛል ሲል ጉዳዪን ያጣራልኝ የቅርብ ወደጃቸው በመልክት አሳውቆኛል።

Via Tesfaye Getnet
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

ትናንት በቦሌ ክ/ከተማ 24 ቀበሌ አካባቢ ከተከሰተው ክስተት ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ለኢትዮ ኤፍ.ኤም መግለጫ ሰጥተዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ መረጃዎች የሀሰት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገግጿል፡፡ፖሊስ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በቀጣይ በምርመራ የሚያገኘውን ውጤት ለህዝብ የሚገልፅ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ባልታወቀ ታጣቂ ቆስለዋል" የሚል መልእክት በስፋት ሲሰራጭ ነበር።

ዛሬ ማታ የካናዳው ጠ/ሚር አቀባበል ፕሮግራም ላይ አየናቸው። ነው ወይስ ቶሎ ተሻላቸው? 😊

#StopFakeNews
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ዶክሌ በህይወት አለ !! #FakeNewsAlert

ስለ ኮሜዲያን ወንዶሰን መሸሻ (ዶክሌ) በሾሻል ሚዲያ የሚወራ ወሬ ከእውነት የራቀ ነው።

ዶክሌ በህይወት አለ ረጅም እድሜ እና ጤና ለዶክሌ እንመኛለን።

ያረጋገጠው ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገው #ተቦርነ_በየነ የቀድሞ የኢሳት ፕሮግራም መሪ የአሁን Ethio360 ተቀላቅሎ እየሰራ የሚገኝ።

//የሚታመን ምንጭ ነው//

ሼር አድርጉ በፌስብክ ገፃችሁ!!

@YeneTube @Fikerassefa
#FakeNewsAlert

በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ በዛሬው እለት የተቃጣ የግድያ ሙከራ ከሸፈ በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ መረጃ እንዳለ ተመልክተናል።ይሁንና በስም የተጠቀሱት ከፍተኛ አመራሮቻችን ማለትም አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፤አቶ አገኘሁ ተሻገር ፤እንዲሁም ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮቻችን ላይ ምንም አይነት የተቃጣ የግድያ ሙከራ የሌለና ልክ እንደወትሮው ሁሉ ያለምንም ችግር በስራ ላይ የሚገኙ መሆኑን እየገለፅን እንዲህ አይነት ህዝባችንን ለማደናገር የሚለቀቁ መረጃወች የሚለቀቁበት አላማና ፍላጎት ከማን እንደሚመነጭ በመረዳት መረጃወቹን ከማሰራጨት በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ለማሳሰብ እንወዳለን።

-የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

(Via FDRE Defense Force)

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አውሮፕላን በሕውሐት ቡድን እንደተመታ ተደርጎ በዚህ ቡድን ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው ምስል ፍፁም ሐሰት ነው።የሀሰቱ ምስል የተወሰደው የዛሬ ዓመት ከቢሾፍቱ አየር ኃይል ጊቢ ለልምምድ በረራ የተነሳና ሞተሩ ላይ ባጋጠመው ችግር በተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ የወደቀውን አውሮፕላን ነው።

በሌሎች ሀገራት ያጋጠሙ የአውሮፕላን አደጋዎችም ለዚህ የሀሰት ወሬ ማጀቢያ ጥቅም ላይ ውለዋል።

እውነታውን እንዲታወቅ ምስሎቹን አያይዘናል።

ሐሰተኛ ምስሎችን እነዚህን የማረጋገጫ መንገዶች በመጠቀም ይለዩ!

የትና መቼ ጥቅም ላይ እንደዋሉ ይነግርዎታል።

Yandex.com/
• TinyEye:- tineye.com/
• FotoForensics:- fotoforensics.com/
• Googel image

@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ የሱዳን ቅርንጫፍ በትዊተር ገፁ "ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ከአማራ ክልል ወደ ሱዳን ተሻግረዋል፣ በጠ/ሚር አብይ መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል እየተደረገ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት ፍራቻ አሁንም እየተመሙ ነው" የሚል መልዕክት ያለው ፅሁፍ በፎቶሾፕ የተቀነባበረ እንጂ በገፁ ላይ እንደማይገኝ ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ይህ ፎቶ በዛሬው እለት በማህበራዊ ሚዲያው በስፋት ሲሰራጭ የነበረ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

ሱዳን ፖስት የተባለ ድረ-ገጽ ደቡብ ሱዳን በሀገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለማባረሯ እንዲሁም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ስለመውሰዷ በትናንትናው እለት አስነብቧል። መረጃውንም በርካታ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች ጭምር አጋርተውታል።

ሱዳን ፖስት ያሰራጨው መረጃ "ውሸት" መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮጵያ ቼክ ዛሬ ጠዋት አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ቼክ ከደቡብ ሱዳን ኤምባሲም ተመሳሳይ ማረጋገጫ ያገኘ ሲሆን "ይህ ፍፁም ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ነገር አልነበረም፣ ሆን ተብሎ ሀገራቱን ለማጋጨት የሚደረግ ሴራ ነው" ተብሏል።

በቅርብ ወራትም "ደቡብ ሱዳን ለግብፅ የጦር ሰፈር መገንቢያ ሰጠች" የሚል የሀሰት ዜና ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።

Via @EthiopiaCheck
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ደህንነት አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ የሀሰት እንደ ሆነ ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ለማሳሰብ እንወዳለን" በማለት የጠ/ሚር ፅ/ቤት ከደቂቃዎች በፊት አስታውቋል።

ፅ/ቤቱ መግለጫውን ያወጣው በማህበራዊ ሚድያ ላይ ጠ/ሚሩ ጉዳት እንዳጋጠማቸው እና ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር እንደሄዱ የሚገልፅ ፅሁፍ መውጣቱን ተከትሎ ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ ባለፈው አንድ ሰአት ውስጥ ከተጨማሪ ሁለት ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው የተሰራጨው መረጃው ፍፁም ውሸት ነው፣ ጠ/ሚሩም መደበኛ ስራቸው ላይ ይገኛሉ። ይህን መረጃ በመጀመርያ ያሰራጨ ግለሰብም ፅሁፎቹን አሁን አጥፍቷል።

የህብረተሰቡን ሰላም እና መረጋጋት የሚያውኩ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ባለማጋራት ሀላፊነታችንን እንወጣ።

Via PMOEthiopia & @EthiopiaCheck
@YeneTube @FikerAssefa