ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ወ/ሮ ፍሬወይኒ መብርሀቱን አነጋገሩ!
የኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአለም አቀፉ መገናኛ ብዙሀን CNN የ2019 አመት ጀግና በሚል የተሸለመችውን ወ/ሮ ፍሬወይኒ መብርሀቱን ዛሬ ምሽት በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ፕሬዚዳንቷ ሽልማቱ ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር ስለሆነ ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብና ሴት ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ ተሸላሚዋ ጠንክራ እንድትሰራ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የመንግስት ድጋፍ እንደማይለያት አረጋግጠዋል፡፡
ወይዘሮ ፍሬወይኒ በበኩሏ በፕሬዚዳንቷ በተደረገላት አቀባበል መደሰቷን በመግለፅ ክብሩ ለሁሉም ኢትዮጵውያን ሴቶች እንደሆነ ተናግራለች፡፡ በሽልማቱ ያገኘችውን መነሳሳትም ሰፊ ስራዎችን በመስራት እንደምታስቀጥል እና በዘርፉ በርካታ የስራ እድል የመፍጠር ውጥን እንዳላት ገልፃለች፡፡ወይዘሮ ፍሬወይኒ በሴቶች የወር አበባ ወቅት ተገቢው የንፅሕና መጠበቂያ በማይገኝባት ኢትዮጵያ ዳግም አገልግሎት መስጠት የሚችል የወር አበባ መቀበያ አዘጋጅታ ለተማሪዎች እንዲዳረስ ማስቻሏ ለሽልማት እንዳበቃት ይታወሳል፡፡
Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa

Merry Christmas to all Christians around the world. I wish you a joyous holiday season and may it be an occasion to count all blessings.
Doctor Abiy Ahmed
@Yenetube @Fikerassefa
Doctor Abiy Ahmed
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
እንኳን አደረሳችሁ
በ አዲስ አበባ የተለያዩ እቃዎች አስመጪ
ብራንድ የወንድና የሴት ሰዓቶች
የሴት ቦራሳዎች
የመዋቢያ እቃዎች
አልባሳት
የምናስመጣቸው እቃዎች ጥራት እና በቀላሉ ገበያ ላይ አለመገኘት እንዲሁም ወደ ክልል ከተሞች መላክ መቻላችን ለየት ያደርገናል ።
ቦሌ መዳንአለም ሞል
+251993014846
ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይጎብኙን ይምረጡ ይዘዙን
👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg

የውጪ ንግድ.m4a
2.6 MB
የኢትዮጵያ የወጪ እና ገቢ ንግድ ሚዛን መካከል ያለው ልዩነት መንበርቀቁን ቀጥሎበታል፡፡ የባለፈው አመትም 15 ቢሊዮን ዶላር ጉድለት ማሳየቱ ተነግሯል፡፡
Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።
ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋርም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ በጉብኝቱ ተካተዋል።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለሁለት አስርት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከታደሰ በኋላ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።
በአሁኑ ጉብኝታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
Via:- FBC

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የሚዘጋጀው አዲስ ወግ የውይይት መድረክ በሂልተን ሆቴል እየተካሄደ ነው።
መድረኩ “የሚዲያው ሚና ሃሳቦችን ለማቀራረብ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
አዲስ ወግ የውይይት መድረክ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች መካሄዱ ይታወሳል።
በዛሬው መድረክ በዋናነት የሚዲያ አካላት የሃገርን ሰላም እና አንድነት ከማስጠበቅ አንጻር በሚኖራቸው ሚና ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።
አዲስ ወግ የውይይት መድረክ በተለያዩ ሃገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ የንግግር ባህል ማሳደግን አላማው ያደረገ መድረክ ነው።

💥እናመሰግናለን💥
በናንተ ልፋት እና ድካም 90 ሺ አድርሳችሁታል ቻናላችሁን እናመሰግናለን።
አብሮነታችሁን እጅግ በጣም እንፈልገዋለን 🙏
ቻናላችሁን ለጓደኛዎ ማስተዋወቅ እንዳይረሱ👏
T.me/Yenetube

በአዲስ አበባ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአራት ክፍለ ከተሞች ውሃ በከፊል ይቋረጣል ተባለ
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 18 እና ዕሁድ ታህሳስ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ በአራት ክፍለ ከተሞች ውሃ በከፊል አይኖርም ብሏል።
ከላይ በተጠቀሱት ቀናትም የገፈርሣ ውሃ ማጣሪያ ጣቢያ የገንዳ አጠባ ሥራ ስለሚከናወን ቀጥሎ በተጠቀሱት ወረዳዎች ውሃ አይኖርም ብሏል።
#አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከወረዳ 4 እስከ10፣
#ጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 8፣
#አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1፣ 8፣ 9 እና 1ዐ፣
#ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከወረዳ 9 እስከ 15
የውሃ አገልግሎት በከፊል ስለሚቋረጥ የባለሥልጣኑ ደንበኞች ከወዲሁ ጥንቃቄ አድርጉ ተብላችኋል።
Via:- ኢትዮ ኤፍ ኤም

ሰበር ዜና
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 5 አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ያላቸውን ጥያቄዎችን ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መንግስትም ለጣያቄዎቹ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡
1. በሞጣ የደረሰውን ችግር ለማጣራት በፌዴራል እስልምና ም/ቤቱ ለተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ክልሉ አስፈላጊውን እገዛ እንዲደረግ፣
2. ይህን ወንጀል ከመፈጸም በተጨማሪ ከባሕልና ልማዳችን ውጪ በኾነ መንገድ እምነት ተቋማት አቃጥለው ፉከራ እና ጭፈራ ሲያሰሙ የነበሩ ግለሰቦችና አካላትን በአስቸኳይ በመያዝ ተገቢውን ፍርድ አንዲያገኙ እንዲያደርግ፣
3. የንብረትም ሆነ ሌላ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸውና በክልሉ መንግሥት ይቅርታ እንዲጠየቁ፣
4. የተቃጠሉ መስጂዶችን በአፋጣኝ በማስገንባትየ ዘወተር አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ እንዲደረግ፣
5. በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኙ ሙስሊሞች ያለባቸውን ችግር የሚያጣራ እና የሚፈታ ኮሚቴ በአጭር ጊዜ ተቋቁሞ ወደ ተግባር እንዲገባ እንዲያደርግ በድጋሚ እናሳስባለን በማለት አምስቱን ጥያቄዎች ምክር ቤቱ አስቀምጧል፡፡

👍1
የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንጻዎች ለመጠገን የ400 ሚሊየን ብር የፕሮጀክት ጥናት መጠናቀቁን የጎንደር የአለም አቀፍ ቅርሶች አስተዳዳሪ አስታወቁ፡፡
አስተዳዳሪው አቶ ጌታሁን ስዩም ለኢዜአ እንደገለፁት የፕሮጀክት ጥናቱ በቀጣዮቹ አምስት አመታት የጥገና ስራውን ደረጃ በደረጃ ለማካሄድ የሚያስችል ነው፡፡
በጥናቱ አማራ ክልልን ጨምሮ የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡
የጥገና በጀቱ በፌዴራል መንግስት ድጋፍ እንደሚሸፈንና አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከክልሉ መንግስት በተመደበ በጀትና ከጎብኝዎች ገቢ በ36 ሚሊየን ብር የቤተ-መንግስቱ ዙሪያ አጥር ጥገና መጀመሩን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
የፌዴራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንጻዎች ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግ ጥናቶች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።
በ16ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸው የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንፃ እንደ አውሮፓውያን የቀመር ዘመን በ1979 በዩኔስኮ በአለም የሰው ሰራሽ ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑ ይታወቃል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 10 ዓመታት አቋርጦት የነበረውን ‹ኦሪጅናል› የትምህርት ማስረጃ መስጠት ዳግም መጀመሩ ተገለጸ፡፡
በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎች ‹ኦሪጅናል› የትምህርት ማስረጃቸውን ላለፉት 10 ዓመታት ሳያገኙ መቆየታቸውን እና በቅርቡ ችግሩ መቀረፉን የዩኒቨርስቲው የሬጅስተራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ ጸጋየ ተናግረዋል።
ከጥቅምት 17/2012 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች ኦሪጅናል የትምህርት ማስረጃዎች ደረጃውን በጠበቀ ምሥጢራዊ ሕትመት ተዘጋጅቶ ባለጉዳይ በጠየቀ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መስጠት መቻሉንም ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት።
ሕትመቶቹ በቀላሉ ለሀሰተኛ ማስረጃ አገልግሎት እንዳይዉሉ ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ እየተሠሩ መሆናቸውን አብመድ ዘግቧል።

በጋምቤላ ክልል የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሰባት ግለሰቦች ቁጥጥር ስር ዋሉ!!
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውሩ ያገኛቸውን ሰባት ተጠርጣሪዎች ባለፉት ሁለት ቀናት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር ዛሬ ለኢዜአ እንደለጹት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከ12 ህገ-ወጥ የጦር መሳሪዎችና ከ741 ጥይቶች ጋር ነው።
“ግለሰቦች የታያዙት ባለፉት ሁለት ቀናት በመንግስትና በግል ተሽከርካሪዎች የጦር መሳሪያዎችንና ጥይቶችን ጭነው ከኢታንግና ላሬ ወረዳዎች ወደ ጋምቤላ ከተማ ለማስገባት ሲሞክሩ ኢታንግ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ ነው” ብለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ታህሳስ 13/2012 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢና ትላንት ረፋድ ላይ በተለያዩ ሁለት ተሽከርካሪዎች በመደበቅ በድምሩ 12 ክላሽንኮቭ ጠመንጃና 741 የክላሽና የብሬን ጠመንጃ ጥይትችን ወደ ጋምቤላ ሊያስገቡ ሲሉ መያዛቸውን ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎቹ የምርመራ ሒደቱ እንደተጠናቀቀ ክስ እንደሚመሰረትባቸው የጠቆሙት ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
Via:- EPA

የንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ከ7መቶ ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለፀ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ የአብስራ ከበደ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ብር ከ7መቶ 12 ቢልዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ከተመሰረተም 77 ዓመታትን አስቆጥሯል። ባንኩ ሲመሰረት የመነሻ ካፒታሉ አንድ ሚሊዮን የማርያ ትሬዛ የነበረ ሲሆን፣ አሁኑ ላይ ከ7መቶ 12 ቢልዮን ብር በላይ ሃብት ማከማቸት ችሏል።
እንደዳይሬክተሩ ባንኩ አሁን ላይ ከ40ሺ በላይ ሰራተኞች እና ከ22ሚልዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን በአገሪቱ ለተከናወኑ የልማት ስራዎች ባንኩ ዋንኛ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን በማገልገል ላይ ነው።

ሀዋሳ ሰላሟ ተረጋግጧል - ጥራቱ በየነ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓልን አስመልክቶ ከጋዜጤኞች ለቀረበ ጥያቄ መልስ ሰጡ፡፡
ከበዓላት ጋር ተያይዞ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ፣የቱሪስት ፍሰት እና የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ም/ከንቲባው በከተማዋ ከሚስተናገዱ ታላላቅ መንፈሳዊ በዓል አንዱ የሆነውን የቅዱስ #ገብርኤል በዓል ስናስተናግድ ምንም አይነት #የዋጋ_ጭማሪ እንዳይኖር ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ቅድመ ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡
በተለይም በሀዋሳ ከተማ ከተካሄደው ሪፍረንደም በኃላ የከተማው ጸጥታ አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት አቶ ጥራቱ በከተማዋ በርካታ ስብሰባዎች መካሄድ፣የከተማው ገቢ ማደግ እና የኢንቨስትመንት ፍላጎት ጥያቄ እየጨመረ መምጣት የሰላም መኖሩ አረጋጋጭ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ጥራቱ አክለውም ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ የከተማው ነዋሪ ሁሉ በዓሉ በሚከበርበት አካባቢ የጽዳት ዘመቻ እያደረጉ መሆኑን ሲገልጹ የበዓሉ ታዳሚዎች ያለምንም ስጋት ወደ ከተማዋ እንዲመጡ #በመጋበዝ_ጭምር ነው፡፡
Via:- ሀዋሳ ከተማ መንግስት ኮምንኬሽን

የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦችን ግንኙነት የሚያጠናክር ምክክር ነገ በአዲስ አበባ ይደረጋል
የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦችን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ነገ በአዲስ አበባ ምክክር እንደሚደረግ የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሰላም ሚኒስቴር ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ይገኛሉ ነው የተባለው።

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በተሰማሩ አካላት እስከሞት ቅጣት የሚያደርስ ህግ እየረቀቀ መሆኑን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በሰው የመነገድና ሕገ-ወጥ ድንበር የማሻገር ወንጀል ለመከላከል ረቂቅ ሕጉ አስፈላጊ ቢሆንም፤ የሞት ቅጣት መያዙ ግን ስህተት ነው፡፡ የሞት ፍርድ ጨካኝና ኢሰብዓዊ የሆነ ሊመለስ የማይችል ቅጣት በመሆኑ ተፈጻሚነቱ ሊታቀብና ለወደፊቱም ሊቀር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
👎1
ምርጫ ቦርድ ለብልፅግና ፓርቲ የእውቅና ሰርተፊኬት ለመስጠት ወሰነ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ጥያቄ እና፣ የፓርቲ መለያ ሰንደቅ አላማ የማጸደቅ ጥያቄን ያቀረቡ ፓርቲዎችን ጉዳይ አይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚህም መሰረት
1.የኢህአዴግ አባል የነበሩ ሶስት ፓርቲዎች እና ሌሎች አምስት ፓርቲዎች በጋራ ራሳቸውን በማክሰም ብልጽግና ፓርቲን መመስረታቸውን በማሳወቅ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጣቸው ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም በጽሁፍ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡ ሲሆን ቦርዱም ጥያቄያቸውን በፓለቲካ ፓርቲዎችና ምርጫ አዋጅ 1162/2011 መሰረት መርምሮ ውሳኔውን ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቦርዱ የእውቅና ጥያቄ ከቀረበለት በኋላ በተጨማሪ መሟላት ያለባቸውን ሰነዶች በታህሳስ 01 ቀን 2012 ዓ.ም በመጠየቅ በጥያቄውም መሰረት ታህሳስ 06 ቀን 2012 ዓ.ም የጥያቄዎቹ ምላሾችና ማብራሪያዎች ተሟልተው መቅረባቸውን በማረጋገጡ ብልጽግና ፓርቲን ለመመስረት
1. የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ( ኦዴፓ)፣
2.የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች
ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን)፣
3.የሃረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ)፣
4.አማራ ዴሞክራያዊ ፓርቲ ( አዴፓ) ፣
5. የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ)፣
6. የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ፣
7.የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ (ጋህአዴን)
8.የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ቤጉህዴፓ)
በተናጠል በጠቅላላ ጉባኤያቸው ውሳኔ መሰረት አድርገው ውህደቱን ለመቀላቀልና ፓርቲያቸውን ለማክሰም የወሰኑት ውሳኔዎች እንዲሁም ውህደቱን ለመመስረት ያደረጉትን ስምምነት በሙሉ ህጉን ተከትሎ የተፈጸመ በመሆኑ ቦርዱ ፓርቲዎቹ ተሰርዘው ብልጽግና ፓርቲ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ወስኗል፡፡በዚህም መሰረት ውህዱ ፓርቲ በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 92/2 መሰረት በተመዘገበ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ውህደቱ ያስገኘውን ሃብትና ንብረት እና እዳ የሚያሳይ የሂሳብ ሪፓርት ለቦርዱ እንዲያቀርብ በውሳኔው ውስጥ ተካቷል፡፡
2.የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ በምዝገባ ወቅት ያቀረበው ሰንደቅ አላማ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ይመሳሰላል በሚል በቦርዱ የቀረበለትን ጥያቄ እንደማይመሳሰል በመግለጽ ልዮነቱን አብራርቶ ቦርዱ እንዲቀበለው ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ቦርዱ በሁለቱ ሰንደቅ አላማዎች መካከል አለ የተባለውን ልዩነት መርምሮ የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ የጠቀሳቸው ልዮነቶች ለማስተዋል የሚያስቸግሩ በመሆናቸው እና ድምጽ ሰጭዎችን የሚያምታቱ ሆነው ስለሚገኙ ሰንደቅ አላማውን ቀይሮ በማቅረብ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
3.እናት ፓርቲ በሚል አገር አቀፍ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ ያለ ፓርቲ በአዋጅ 1162/ 2011 መሰረት ጊዜያዊ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ በአዋጁ ላይ የተቀመጠውን ጊዜያዊ ሰርተፍኬት መውሰጃ መስፈርት በማሟላቱ እናት ፓርቲ የጊዜያዊ እውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ቦርዱ ወስኗል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ