YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አድማስ ራዲዮ ከጂጂ ጋር ያደረገውን ቆይታ አቀናብረን አቅርበንላችኃል።

https://www.youtube.com/watch?v=DAKlRkVX7eI&t=99s
የፀዲን | ሰው | ኦብሰሽን የተዘጋጀውን ኮንሰርት ላይ አስገራሚ እንቅስቃሴዎች | አፈትልኮ የወጣ ቪዲዮ ነው ተመልቱት።


📌በሾሻል ሚዲያ ላይ አነጋጋራ ቪዲዮ

youtube.com/watch?v=9YZpV5nNh-4
ትልልቅ የሙስና ወንጀል ተሰርቶባቸዋል ተብለው በተጠረጠሩ ተቋማት ላይ የተደረገው ጥናት ተጠናቋል - ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት

ትልልቅ የሙስና ወንጀል ተሰርቶባቸዋል ተብለው በተጠረጠሩ ተቋማት ላይ የተደረገው ጥናት መጠናቀቁን የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል ባለፉት ስድስት ወራት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጠጣር የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል በማቅረብ የተሳካ ስራ መስራቱን ተናግረዋል።

የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመከላከል በኩል በግብር ስወራ፣ ኮንትሮባንድ እና የጨው ምርት ሽያጭ አሻጥር ላይ አጣርቶ መረጃ ማቅረቡንም ነው የተናገሩት።ከግብር ስወራ እና የመንግስት ሀብት ምዝበራ አንፃር ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ሀብት ለማዳን ያስቻለ ስራ መሰራቱንም ገልጸዋል።የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል በተባሉ የመንግስት ተቋማት ላይ ጥናቶችን አጠናቆ ለመንግስት ማስረከቡንም አስታውቀዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ ነው!

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል፥ ስር ነቀል ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ ላይ ያለው አገልግሎቱ የስያሜ እና አሰራር ለውጥ የሚያደርግበት ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ረቂቅ አዋጁ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ስያሜን ወደ ብሔራዊ መረጃ ማዕከል (ኤን አይ ሲ) እንዲሻሻል ይጠይቃል።

ረቂቅ አዋጁ ከፖለቲካ፣ ብሔር እና ሃይማኖት ጥገኝነት የተላቀቀ ነፃ የመረጃ እና ደህንነት ተቋም የመፍጠር የማሻሻያ ስራ አንዱ አካል መሆኑንም ተናግረዋል። ተቋማዊ ማሻሻያውን ተከትሎ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት በአስር አመት ወስጥ ሊደርስበት የሚችለውን ደረጃ የሚያመላክት የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድም ተዘጋጅቷል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተቀሰቀሰ!

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ቅዳሜ በተማሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የመማር ማሥተማር ሥራው መቋረጡን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 11/2012 ዓ/ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ በተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ድንጋይ መወራወር ያስከተለው ግጭት በቁጥጥር ሥር ቢውልም የመማር ማስተማር ሥራው ለጊዜው መቋረጡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታደሠ ቀነዓ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

«በተማሪዎች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚፈልጉ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ተማሪዎች እያነሳሱ ነው» ያሉት ዶ/ር ታደሠ «የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የሆኑ ጥቂት ተማሪዎች ከሌላ ዩኒቨርሲቲ መጡ የተባሉ ተማሪዎችን አጋርነት ለማሳየት በሚል ግጭት ለመፍጠር ሲሞክሩ ነበር » ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው ግጭት ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራው መቋረጡን ዶ/ር ታደሠ ተናግረዋል።

በተማሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተከሰተ ጉዳት እንደሌለ እና የተፈጠረውን ግጭት ለመቅረፍ ከዛሬ ጀምሮ ከተማሪዎች እና ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት መጀመሩን ፕሬዚዳንቱ አክለው ገልጸዋል።

«ከሌላ ዩኒቨርሲቲ መጡ» ስለተባሉ እና ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን ግጭት እንዲቀሰቀስ እያደረጉ ያሉ ተማሪዎች ያሉዋቸውን ሰዎች በሚመለከት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር በመሆን መፍትሄ እያፈላለጉ መሆኑንም ዶ/ር ታደሠ አስታውቀዋል።

በዩኒቨርሲቲው የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ጊቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች ስለመኖራቸው የተጠየቁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጊቢውን የሚያስለቅቅ የጎላ ችግር ባለመኖሩ ጊቢውን ለቆ የወጣ ተማሪ የለም ብለዋል።

Via:-DW Amharic
@Yenetube @Fikerassefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት ወቀሳ መልስ ሰጠ

ሰሞኑን ለሥራ ጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ሊያደርጉ የነበሩ የቻይና የሻንሺ ግዛት ልዑካን አባላት በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይጓዙ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ እገዳ ተደርጎባቸዋል የሚለው የትግራይ ክልል መንግሥት ቅሬታ የመገናኛ ብዙሃን ዓበይት የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቆይቷል።

የተፈጠረውን ክስተት ለማጣራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊዎችን አነጋግሯል:: 
ለመሆኑ የልዑካን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበፌደራል መንግስቱ ዕውቅና እና አስፈላጊውን 
ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነው ?

ለሚለው ጥያቄ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚስትር ሚኒስትር  ´ዴኤታ  አምባሳደር  ዶክተር ማርቆስ ተክሌ የፌደራል መንግስቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤዥያ እና ፓስፊቅ አገራት ጉዳዮች መምሪያ እና ቻይና ፔኪንግ  በሚገኘው የኢትዮጵያሚስዮን አማካኝነት 
ከወራት በላይ  ከግዛቲቱ ሃላፊዎች ጋር የደብዳቤ ልውውጥ እና ውይይት አድርጎ ለትግራይ ክልልም 
በደብዳቤ አሳውቆ በህጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አረጋግጠውልናል::

Via:- ጀርመን ድምፅ
@Yenetube @Fikerassefa
የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አቋርጠው ወደነበረው መደበኛ ትምህርታቸው መመለሳቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ ገለፁ።

ዶክተር ለታ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ከሌላ አካባቢ ካለው የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው የመጡ ተማሪዎች በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ካልተማሩ በሚል ለተወሰኑ ቀናት ትምህርት ተቋርጦ ቢቆይም መግባባት ላይ በመደረሱ መደበኛ ትምህርት ተጀምሯል።

ዶክተር ለታ እንዳሉት፤ በአማራ ክልል ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የኦሮሞ ተማሪዎች ወደጊቢው ገብተን ትምህርት ካልተማርን በሚል ጥያቄ አንስተው ነበር፣ በግቢው ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ ከሌላ ቦታ የመጡ ተማሪዎችን ተቀብላችሁ ካላስተማራችኋቸው አንማርም የሚል ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተዋል። ‹‹በወቅቱ የእኛ ምላሽ የነበረው፣ ተቋሙ የፌዴ ራል እንደመሆኑ ተቀብለን ማስተማር የምንችለው የተመደበልንን ብቻ እንደሆነ ነው።

ለዚህም ምክንያቱ ዩኒቨርሲቲ የራሱ የሆነ ህግና ደንብ ያለው በመሆኑ ነው።››

ሲሉ ጠቅሰው፤ተማሪዎችንም ሰብስበው ጉዳዩን በአግባቡ እንዳስረዷቸው ገልፀዋል። ጥያቄውንም ላቀረቡ ተማሪዎች መርዳት የሚገባቸው ነገር ካለ በፋይናንስም በኩል ቢሆን ለመርዳት እንደሚቻል ተናግረው፤ እነርሱን ተቀብሎ ለማስተማር ግን የተመደበላቸው በጀት በግቢው ላሉ ተማሪዎች ብቻ መሆኑን በመግለፅ እንደማይችሉ አሳውቀዋቸዋል።

ወደ ነበሩበት ዩኒቨርሲቲ እስኪ መለሱ ድረስ ሊያግዟቸው እንደሚችሉም የነገሯቸው በመሆኑም ለአንድ ሳምንት ያህል ተቋርጦ የነበረው ትምህርት መጀመሩን አመልክተዋል።

Via EPA
@Yenetube @FikerAssefa
በአንበጣ መንጋ የተወረረችው ሶማሊያ አንበጣን ለምግብነት ማዋል ጀምራለች።

የአንበጣ መንጋን ሙሉ በሙሉ በኬሚካል መግደል ስላልተቻለ በሱማሊያና በኢትዮጵያ የሰብል ዝርያዎችን በማውደም ላይ ይገኛል፡፡

ሰብላቸውና ምግባቸው በዚህ መንጋ እየተበላባቸው የሚገኙት ሱማሊያዊያን አንበጣውን እየጠበሱ ወደ መብላት መሸጋገራቸውን ፌስ ኦፍ አፍሪካ የተሰኘው ዌብሳይት ዘግቧል።

አንበጣውን የተመገቡ አንድ አዛውንት ለዚሁ ሚዲያ እንዳሉት የጀርባ ህመም እና የደም ግፊታቸው ህመም እንደቀነሰላቸው ተናግረዋል።

የተለያዩ የማህበረሰብ አንቂዎች ወይም አክትቪስቶች ደግሞ የአገሬው ዜጎች አንበጣን ለምግብነት እንዲያውሉ በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ የተወሰኑት ደግሞ ነዋሪዎች እና አንበጣን እንደ አሳ ጠብሶ በመሸጥ ላይ የሚገኙ ምግብ ቤቶችን ከስራቸው እንዲቆጠቡ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው ተብሏል።

በተበበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ የአለም የምግብ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሣየው ፣ አንድ አንበጣ 170 ሺህ ቶን ሰብል በአመት ይመገባል ይህም 1 ሚሊየን ሰው መመገብ የሚችል ነው ተብሏል፡፡

Via:-Ethio fm
@Yenetube @Fikerassefa
በአሁኑ ሰአት በአማራ ክልል በተቃጠሉት 4 መሰጂዶች በማስመልከት ተቃውሞ #በአፋር ከተማ እየተደረገ ነው።

#ከመስጂዶቻችን_ላይ_እጃችሁን_አንሱ!!
መልክት እያስተጋቡ ይገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናሳወቃለን።
@Yenetube @Fikerssefa
የማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት በውጭ አገር የትምህርትና ስልጠና ዕድል እንዲያገኙ የሚያደርግ አዋጅ ፀደቀ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ባቀረበው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ ላይ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባል በውጭ አገር የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ የሚያመቻች አዋጅ ፀደቀ።

ዛሬ ታኅሳስ 14/2012 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የፌደራል መረሚያ ቤት የረጅም ዓመት ልምድ ያለው ማሰልጠኛ እንዳለው ተጠቅሶ፤ ነገር ግን ተደጋጋሚ ወንጀሎችን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግን ወደ ውጭ አገር ልኮ ማሰልጠን እንደሚቻል ተቀምጧል።

በዚሁ አዋጅ ላይ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በፌደራል መንግስት ከሚመደብለት በጀት በተጨማሪ ከውስጥ የሚያገኘውን ገቢ የገንዘብ ሚኒስቴርን እያስፈቀደ መጠቅም እንደሚችልም ተቀምጧል።

Via :- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ በአስከተማ ከተማ 01 ቀበሌ በግብርና ቢሮ እሳት ቃጠሎ ተከስቶ ከፍተኛ ንብረት ወደመ፡፡

በጋ/ወ/ፖ/ጽ/ቤት መርማሪ ፖሊሰ ሳጅን ተቀባ ደሳለኝ እንደተናገሩት ቃጠሎው የተነሳው በግብርና ቢሮ ውስጥ መሆኑን ገልፀው ታህሳስ 13/2012 ዓ.ም ለታህሳስ 14/2012 ዓ.ም ሊነጋ 10፡00 አካባቢ ሲሆን መረጃዎችና ንብረቶች መውደማቸውን ተናግሯል ፡፡

በአጠቃላይ የውሃ ማሰባሰብ ቢሮና ሞተር ሳይክል ፣ የተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ፣ የምግብ ዋስትና ቢሮ ፣ የማህበራት ቢሮ ፣ የውሃና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ፣ የመሬት አስተዳደር አንድ ቢሮና ንብረት ክፍል እንዲሁም የቅየሳ መሳርያዎች እና ፋይሎች በሙሉ መውደማቸውና የእሳቱ ቃጠሎም በህብረተሰቡ ተሳትፎ መቆጣጠር እንደተቻለ ገልጸዋል ፡፡

የእሳቱ መነሻ ምክንያት በውል ባይታወቅም ሆን ተብሎ የተፈፀመ እንደሆነ በመገመት አስፈላጊውን ማጣርያና ክትትል እየተደረገ መሆኑን መርማሪው ተናግሯል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሁለት አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን ታኅሣሥ 14 ቀን 2012 ዓ.ም አካሔደ።ም/ቤቱ በቅድሚያ በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ አጽድቋል። በመቀጠልም በሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1174/2012 አጽድቋል።

የተፈጥሮ ሀብት፣ መስኖ እና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል የቀረበውን በኢፌዴሪ መንግሥት እና ጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ ለማስተላለፍ የተፈረመውን ስምምነት ዓለም አቀፍ ደንቦችን መሠረት አድርጎ የተካሔደ መሆኑን መነሻ በማድረግ አዋጅ ቁጥር 1175/2012 ሆኖ እንዲጸድቅ ውሳኔ አሳልፏል።በሌላ በኩል በውጭ አገራት ለተሰጡ የግልግል ዳኝነት የተሰጡ ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ውሳኔዎች መርምሮ ለሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል።

ምንጭ፦የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በጅግጅጋ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሔደ

በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ በመስጊዶች ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ዛሬ ታኅሳስ 14/2012 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በርካቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ድርጊቱን አውግዘዋል።

አብዲአዚያ አሊ የተባሉ ጸሐፊ (freelance writer) ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በርካታ ቁጥር ያላቸው የጅግጅጋ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ የወጡ ሲሆን ሰላማዊ የነበረውን ሰልፍም ወደ ረብሻ ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩም አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰልፉ መሐል ወደ ግርግር በማምራት አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ እንደተደረገ እና መክሸፉን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ተናግረዋል።
የተፈጠረውን ግርግር እና ረብሻ ለማክሸፍም ከፀጥታ አካላት ወገን የተኩስ ድምጾች እንደተሰሙ ምንጮች ከስፍራው ጨምረው ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ አቅራቢያም የተኩስ ድምጽ መሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። በርካታ የጸጥታ አካላት ተሸከርካሪዎችም ወደ ዩኒቨርስቲው አቅጣጫ እያመሩ እንደሆነም ከስፍራው ተገልጿል።

በጅግጅጋ ከተማ ተካሔደውን ሰልፍ በተመለከተ ክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የኮሙኒኬሽን አማካሪ መሐመድ ኦላድ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ሰልፉ መካሔዱንና በሰልፉም መሐል የተኩስ ድምጽ የተሰማ ቢሆንም አስለቃሽ ጭስ ወይም የጥይት ለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆን እንዳልቻሉ እና እየተጣራ እንደሆነም ተናግረዋል።

Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
የውሃ እና ኢነርጅ ሚንስትሩ ስለሺ ጌታሁን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በካርቱሙ የሕዳሴው ግድብ ስብሰባ ግብጽ ኢትዮጵያ በዐመት 49 ቢሊዮን ኪውቢክ ውሃ ትልቀቅልኝ፤ የአስዋን ግድብ ከፍታ ከ165 ሜትር ዝቅ አይበልብኝ የሚል አቋሟን ትታለች ብለዋል፡፡ የአባይ ወንዝ ተፈጥሯዊ ፍሰት ይጠበቅ የሚለውን አዲስ ሃሳቧን ግን ኢትዮጵያ አልተቀበለችውም፡፡ ኢትዮጵያ ድርቅ ማለት ከ35 ቢሊዮን ሜትሪክ በታች ውሃ ሲፈስ ነው ስትል፣ ግብጽ ከ40 ቢሊዮን በታች ከሆነ ነው በማለቷ በድርቅ ትርጓሜ ላይ ስምምነት አለመደረሱን ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በወላይታ ዞን እስር ላይ የነበሩ ግለሰቦች መፈታታቸው ተገለፀ!

የወላይታ ዞን ክልልነት ጥያቄን ተከትሎ ከታኅሳስ 9/2012 ጀምሮ የታሰሩ ግለሰቦች ከወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አንዱዓለም ታደሰ ውጪ ከእስር መፈታታቸው ተገለፀ። በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ወላይታ ሶዶ ከተማ ከትናንት ታኅሳስ 9/2012 ምሽት ጀምሮ እስከ አርብ ጠዋት ድረስ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው የቆዩ ሲሆን ከግለሰቦቹ መካከል ከወብን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ውጪ ሁሉም መለቀቃቸውን የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር ውለው የቆዩት ግለሰቦች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የክልልነት ጥያቄውን አስመልክቶ ሰፊ ንቅናቄ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፣ በቁጥጥር ስር የዋሉትም ታኅሳስ 10/2012 ከሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ምክንያት እንደነበር ተገልጿል።ታኅሳስ 10 ረፋዱ ላይም ወርቅነህ ገበየሁ እና አሸናፊ ከበደ የተባሉ ግለሰቦች የተለቀቁ ሲሆንኅ ከሰዓት በኋላ ደግም የቀሩት ተለቀዋል። የወብን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አንዱዓለም ታደሰ ትላንት አመሻሹ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለፁት ተከተል ላቤና፤ አሸናፊ ከበደ፣ ወርቅነህ ገበየሁ እና ቡዟየሁ ቡቼ የተባሉት ከእስር የተፈቱ ግለሰቦች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚሟገቱ እንደሆኑ ገልፀዋል።

ብርቱካን የተባሉ አንዲት ሴት ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውለው መቆየታቸውን የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ተከተል ላቤና ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል።ኃላፊው በቁጥጥር ስር እንዲቆይ መደረጉ አግባብነት የሌለው ነው ያሉ ሲሆን፣ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ስንሔድ ለማየት ተከልክለናል ብለዋል። ‹‹በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ችለናል፤ ሆኖም ሊያሳስረው የሚችል ምንም ዓይነት ምክንያት ባለመኖሩ በአፋጣኝ ሊፈታ ይገባል›› ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የክልልነት ጥያቄው በተባለው ጊዜ ምላሽ አለማግኘቱንም ተከትሎ፣ በወላይታ ዞን ካሉት 22 ወረዳዎች ሶዶ እና አረካ ሳይጨምር በ20 ወረዳዎች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉንም ጨምረው ገልፀዋል። ሰልፉ ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር እና በሰዎች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰም ተገልጿል።ሕዝቡ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ፍፁም ሰላማዊ ነበር። ይሄንንም ተከትሎ ምንም ዓይነት ጉዳት በሰዎች ላይ እንዳልደረሰ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በዞኑ እና በሶዶ ከተማ በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተከተል ተናግረዋል።

በወረዳዎቹ ከተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በኋላም በወላይታ ሶዶ ከተማ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታሁን ጋረደው እና የዞኑ አስተዳዳሪ እንዲሁም አገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች የተሳተፉበት ውይይት ተደርጓል። የክልሉ ምክር ቤት ሕገ መንግሥቱን በተከተለ መንገድ የዞኑን ጥያቄ ማስተናገድ እንዳለበትም በውይይቱ እንደተጠቆመ ታውቋል።‹‹በከተማዋ ተዘግተው የነበሩ የንግድ ማእከላት ወደ ቀድሞ ሥራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ›› ያሉት ተከተል፣ የክልልነት ጥያቄው ተገቢውን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ የክልልነት ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።የወላይታ ዞን አስተዳዳሪን በጉዳዩ ላይ በስልክ እና በጽሑፍ መልዕክት ለማነጋገር አዲስ ማለዳ በተደጋጋሚ ጥረት ብታደርግም ሳይሳካላት ቀርቷል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ዶክተር አሚን ጤና ሚኒስቴርን በዚህ ሳምንት በይፋ ይሰናበታሉ።ለሌላም ስራ ወደ አሜሪካ ያቀናሉ።

የስራ መልቀቂያ እንዳስገቡ ከወራት በፊት የተነገረላቸው የጤና ሚኒስትሩ ወጣቱ ዶክተር አሚን አማን ዛሬ የመልቀቂያቸው ደብዳቤ ተቀባይነት አግኝቶ ከሚኒስትር መ/ቤቱን ላገለገሉበት የምስጋና ሰርተክፌት እንደተዘጋጀ ተነግሮኛል ። ጎዴ ለስራ የሚገኙት ዶ/ አሚን ነገ ወይም ከነገ ወዲያ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸን ተቀብለው ጤና ሚኒስቴርን ይሰናበታሉ።ዶክተር አሚን አሜሪካ የሚገኝ ለግዜው ስሙ ያልተነገረኝ አለም አቀፍ ተቋም ስራ እንደገኙም ከቅርብ ምንጮች አረጋግጫለው።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
በሞጣ የሐይማኖት ተቋማት ቃጠሎን ለማውገዝ በተደረገ የጅግጅጋ ሰልፍ የሰው ሕይወት አለፈ «በመጨረሻ በተፈጠረ ብጥብጥብ 1 ግለሰብ ሕይወታቸው እንዳለፈ ማረጋገጥ እንችላለን» ሲሉ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አማካሪ መሐመድ ኦላድ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል

@YeneTube @FikerAssefa