YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአራት ክፍለ ከተሞች ውሃ በከፊል ይቋረጣል ተባለ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 18 እና ዕሁድ ታህሳስ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ በአራት ክፍለ ከተሞች ውሃ በከፊል አይኖርም ብሏል።

ከላይ በተጠቀሱት ቀናትም የገፈርሣ ውሃ ማጣሪያ ጣቢያ የገንዳ አጠባ ሥራ ስለሚከናወን ቀጥሎ በተጠቀሱት ወረዳዎች ውሃ አይኖርም ብሏል።

#አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ከወረዳ 4 እስከ10፣
#ጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 8፣
#አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1፣ 8፣ 9 እና 1ዐ፣
#ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ከወረዳ 9 እስከ 15

የውሃ አገልግሎት በከፊል ስለሚቋረጥ የባለሥልጣኑ ደንበኞች ከወዲሁ ጥንቃቄ አድርጉ ተብላችኋል።

Via:- ኢትዮ ኤፍ ኤም
@Yenetube @Fikerassefa