YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሀዋሳ ሰላሟ ተረጋግጧል - ጥራቱ በየነ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓልን አስመልክቶ ከጋዜጤኞች ለቀረበ ጥያቄ መልስ ሰጡ፡፡

ከበዓላት ጋር ተያይዞ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ፣የቱሪስት ፍሰት እና የጸጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ም/ከንቲባው በከተማዋ ከሚስተናገዱ ታላላቅ መንፈሳዊ በዓል አንዱ የሆነውን የቅዱስ #ገብርኤል በዓል ስናስተናግድ ምንም አይነት #የዋጋ_ጭማሪ እንዳይኖር ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ቅድመ ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡

በተለይም በሀዋሳ ከተማ ከተካሄደው ሪፍረንደም በኃላ የከተማው ጸጥታ አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት አቶ ጥራቱ በከተማዋ በርካታ ስብሰባዎች መካሄድ፣የከተማው ገቢ ማደግ እና የኢንቨስትመንት ፍላጎት ጥያቄ እየጨመረ መምጣት የሰላም መኖሩ አረጋጋጭ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ጥራቱ አክለውም ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ የከተማው ነዋሪ ሁሉ በዓሉ በሚከበርበት አካባቢ የጽዳት ዘመቻ እያደረጉ መሆኑን ሲገልጹ የበዓሉ ታዳሚዎች ያለምንም ስጋት ወደ ከተማዋ እንዲመጡ #በመጋበዝ_ጭምር ነው፡፡

Via:- ሀዋሳ ከተማ መንግስት ኮምንኬሽን
@Yenetube @Fikerassefa