YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በካፋ ብሔር የክልልነት ጥያቄ ዙሪያ ለመወያየት አዲስ አበባ የተገኙ ተወካዮች ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ቀጥሮን ጠፋ ሲሉ አማረሩ። በጠቅላይ ሚንስትሩ ጋባዥነት አዲስ አበባ ቢገኙም ውይይቱ በሰላም ሚንስቴር ሰዎች እንደሚመራ ሲያዉቁ የስብሰባውን አዳራሽ ለቀው መውጣታቸውንም ገልጸዋል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ባሕር ሃይል ጦር ሠፈር በጅቡቲ ልታቋቁም እንደሆነ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

የባሕር ሃይሉ #ማዘዣ_ጣቢያ ባሕር ዳር ይሆናል፡፡ ዐቢይ በጥቅምት በጅቡቲ ባደረጉት ጉብኝት በጉዳዩ ላይ ከፕሬዝዳንት ኢስማዔል ጉሌህ ጋር ተነጋግረዋል፡፡ ፈረንሳይ ለጦር ሠፈሩ ግንባታ ድጋፍ ታደርጋለች፡፡

የመጀመሪያ ዙር ባሕር ሃይል አባላትንም አሰልጥናለች- ይላል የካፒታል ኒውስ ዘገባ።
@Yenetube @Fikerassefa
የሠላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እና የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ከከፋ ህዝብ ከተውጣጡ አካላት ጋር ውይይት አካሄዱ

የሠላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እና የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ከከፋ ህዝብ የተውጣጡ አካላት ጋር ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ተሳታፊ የሆኑ የከፋ ህዝብ ተወካዮች እንዳሉት የካፋ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ህገ-መንግስታዊ በመሆኑ በመንግስት በኩል ተገቢው ምላሽ መሰጠት እንዳለበት አፅኖት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ከከፋ ህዝብ ተወካዮች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ እንደገለጹት በመንግስት በኩል ህዝቡ ህገ-መንግስታዊ የሆነ ጥያቄዉን ህጋዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማቅረብ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

አክለውም ራሳችንን ችለን በክልል እንደራጅ የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ሌሎች ዞኖችም መኖራቸው ከግምት ውስጥ በማስገባት የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ ቀጣይ ህዝቡን ያሳተፈ ውይይት እና ምክክር እያካሄደ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በተመሳሳይ ትላንት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከወላይታ ዞን ህዝብ የተውጣጡ አካላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸዉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
@Yenetube @Fikerassefa
Audio
ጅዋር ከDW !!

የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሀመድ በጀርመኗ ኑርንበርግ ከተማ ከደጋፊዎቹ ጋር በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ባለፈው ቅዳሜ ከመወያየቱ አስቀድሞ ዶቼቬለ በኑርንበርግ ቃለ መጠይቅ አድርጎለት ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa
Sport!

ሊዮኔል ሜሲ የ2019 የባሎን ዶር አሸናፊ ሆኗል::
ሜሲ ይህን ሽልማት ሲያገኝ ለስድስተኛ ጊዜ ነው!!


ጥቆማ የስፓርት ቻናላችን ይቀላቀሉ - @Yenesport

@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
😍ለጫማ አድናቂዎች😍
ለወንድም ለሴትም ሚሆኑ አዳዲስ ጫማዎችን እነሆ ብለናል::

💥ማስታወሻ:ተደራሽነታችን በአዲስ አበባ እንዲሁም ሁሉንም የክልል ከተምችን ያካትታል
🎯አድራሻ:-ገርጂ መብራት ሀይል ዊዝደም ህንፃ ፊት
ስልክ:-0900628132
0116296465
በቴሌግራም ለማግኘት ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉን👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢህአዴግ ውህደት የህዝቦችን መቀራረብ ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን የሱማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ተናገሩ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ኤርትራዊው ድምፃዊ በአዲስ አበባ ጥቃት ደረሰበት!

''ወዲ ማማ'' በሚል የቅጽል ስም የሚታወቀው ኤርትራዊ ሙዚቀኛ፣ ተክለ ነጋሲ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በማይታወቁ ሰዎች ጥቃት እንደተፈጸመበት ተነገረ።

ድምጻዊው ባለፈው እሁድ ከሰዓት በኋላ ገርጂ በሚገኘው አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በእግሩ በሚጓዝበት ወቅት ማንነታቸውን በማያውቃቸው አምስት ሰዎች ጥቃቱ እንደተፈጸመበት ተክለ ለቢቢሲ ተናግሯል።

ጨምሮም ጥቃቱን ከፈጸሙበት ሰዎች ጋር ምንም አይነት ንግግር እንዳልነበረና አላማቸው ጉዳት ማድረስ እንደነበረ ገልጿል። "ምንም አይነት ንግግር አልተናገሩኝም፤ በቀጥታ ወደ ድብደባ ነበር የገቡት" ሲል ተናግሯል።

ድምጻዊው ተክለ ነጋሲ ሱዳን ውስጥ በነበረበት ጊዜ በደረሰበት የመኪና አደጋ እግሩ ተሰብሮ እንደነበር ጠቅሶ፤ እግሩ ላይ ብረት እንዳለውና ጥቃት ያደረሱበት ሰዎች በተደጋጋሚ በአደጋው ጉዳት የደረሰበት እግሩን ይመቱት እንደነበር ተናግሯል።

ከዚህም በመነሳት ከባድ አደጋን ለማድረስ ዕቅድ እንደነበራቸውና ጥቃቱ የታቀደና "በደንብ የሚያውቁኝ መሆን አለባቸው" በማለት ግምቱን አስቀምጧል።

ድማጻዊ ወዲ ማማ በደረሰበት ድብደባ ሳቢያ በቀኝ እጁ፣ በአፍንጫው፣ በጭንቅላቱና የግራ ኩላሊቱ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበትም ለቢቢሲ ተናግሯል።

Via:- BBC News Amharic
@Yenetube @Fikerassefa
የግዮን ሆቴል ጣሪያ ወድቆ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጸው ከ15 ደቂቃዎች በፊት ስቴዲየም አካባቢ የሚገኘ ግዮን ሆቴል ጣሪያው መውደቁን ተናግረዋል።የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ እንዳሉት የሆቴሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጣሪያው መውደቁን ተናግረዋል።በአደጋው እስካሁን የተጎዱ ሰዎች ያልተወቀ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ቦታው አቅንተው አደጋውን ለመቆጣጠር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በሴካፋ ውድድር አትሳተፍም!

ኢትዮጵያ በመጪው ቅዳሜ በሚጀመረው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር /ሴካፋ/ እንደማትሳተፍ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።ኢትዮጵያ ከሕዳር 27 እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2012 ዓ.ም በዩጋንዳ በሚካሄደው ውድድር እንድትሳተፍ የምድብ ድልድል ውስጥ መካተቷ ይታወቃል።ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከውድድሩ ከሚገኘው ጥቅምና ከሚወጣበት ወጪ አንጻር መሳተፉ አስፈላጊ አይደልም ብሏል። የፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ባህሩ ጥላሁን እንደገለጹት ፌዴሬሽኑ ያለውን ውስን በጀት ለሴካፋ ውድድር ማዋሉ ጠቃሚ እንዳልሆነ ያምናል። ከዚህም ባለፈ አንድ ውድድር የሚለካው በተሳትፎ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጥቅሞች ተገምግመው በመሆኑ በውድድሩ መሳተፉ ጠቃሚ አይደለም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።እናም ኢትዮጵያ በምድብ ድልድል ውስጥ የተካተተች ብትሆንም በውድድሩ አትሳተፍም ሲሉ አረጋግጠዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በካይሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውሃ ጉዳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ!

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ጉዳይ ዙሪያ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በግብፅ ያካሄዱት የቴክኒክ ስብሰባ ተጠናቀቀ።ስብሰባው የግድቡ የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅን በሚመለከት ህዳር 5 እና 6 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው ስብሰባ ውይይት ተደርጎባቸው የጋራ መግባባት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ ነው የተካሄደው።የኢፌዴሪ ውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ፥ የአባይ ውሃ ለኢትዮጵያ ድህነትን ማጥፊያ እና የህልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፥ የአሁኑንና የወደፊት ትውልድ የመጠቀም መብትን የማይገድብ መሆኑን ተናግረዋል።ስብሰባው በግድቡ ሙሌት እና የውኃ አለቃቀቅ ዙሪያ በአዲስ አበባ በተጀመረው ውይይት መሰረት ቀጥሎ የተካሄደ ነው።በስብሰባው ላይ የዓለም ባንክ እና የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በታዛቢነት መሳተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።በአዲስ አበባው ምክክር ሶስቱ ሀገራት በግድቡ ውሃ አያያዝና አለቃቀቅ ዙሪያ አቋማቸውን አንፀባርቀው በስፋት መወያየታቸው ይታወሳል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
ፌደራሊስት መሆናቸውን የሚገልጹ የፖለቲካ ሃይሎች በመቀሌ መሰብሰባቸውን የትግራይ ክልል ብዙኻን መገናኛ ዘግቧል፡፡ ስብሰባው ሕገ መንግሥታዊነት እና ኅብረ ብሄራዊው ፌደራላዊ ሥርዓት ባጋጠሙት ፈተናዎች እና ዕድሎች ላይ ይመክራል፡፡ የስብሰባው አዘጋጅ ትግራይ ክልል ነው፡፡ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካዔል በሀገሪቱ የጠቅላይነት አዝማሚያ እየተንሰራፋ መምጣቱ ስጋት እንደፈጠረ በመክፈቻ ንግግራቸው አውስተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ በቀጣዩ ምርጫ በኦሮሚያ ክልል አብላጫውን ወንበር አገኛለሁ ብሎ እንደሚያምን ሊቀመንበሩ ኦቦ ዳውድ ኢብሳ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡ በፌደራሉ ፓርላማም በርካታ ወንበሮችን እንደሚያገኙ ዕምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ግንባሩ ለምርጫ የሚቀርበው ባሁኑ አደረጃጀቱ ነው፡፡ ከኦሕዴድ ጋር የተጀመረውን ውይይት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀጠል አስቸጋሪ ይሆናል ብለዋል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በአሜሪካን የመጀመሪያ ቀን የመከላከያ ትብብር ውይይቱን አካሄዷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት የብልፅግና ፓርቲን የማትቀላቀል ከሆነ አረና ትግራይ የብልፅግና ፓርቲን በደስታ ይቀላቀላል::

አምዶም ገብረስላሴ (የአረና ትግራይ ህዝብ ግንኙነት)
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ!

አራቱ ሴናሪዎች /እጣ ፈንታ/ ይፋ የተደረጉት ህዳር 23/2012 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል "የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032" በሚል ርእስ በተደረገዉ የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ ።
በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፣፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።የዴስቲኒ ኢትዮጵያ በአገሪቱ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ክልሎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ምሑራን የተውጣጡ 50 ሰዎች በጥንቃቄ በመምረጥ ላለፉት ስድስት ወራት ዝግ ስብሰባዎችን በማካሄድ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት አገራችን ሊገጥሟት የሚችሉ አራቱን ሴናሪዎች መቅረፁን የዴስቲኒ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ንጉሴ አክሊሉ ተናግረዋል ።

አራቱ ሴናሪዎች አፄ በጉልበቱ ፣ ሰባራ ወንበር ፣ የፋክክር ቤት እና ንጋት ናቸዉ ።
በመድረኩ ላይ ክብርት የሰላም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ይህን ሴናሪዮ ለማዘጋጀት የተነሱ ግለሰቦችን፣ የተለያዩ የፖለቲካ አቋም ይዘዉ በሃሳብ አንድነት ተሰባስበዉ ለሴናሪዮ ሃሳብ ያዋጡ 50 ሰዎችን አመስግነዋል።ሳይቸግረን የቸገረን ራስን በሌላዉ ቦታ አስቀምጦ መየት ነዉ ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ይህን ሴራኒዮ ያዘጋጁ አካላት አብሮ በመቀራረብ ዉስጥ ያለ ሃይልን አሳይተዉናል ብለዋል ።ከአራቱ ሴናሪዮ (እጣ ፈንታዎች) ውስጥ ለኢትዮጵያ “ንጋት” እንደሚመኙ የገለፁት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ለዚህም ነገን ዛሬን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።የሴራኒዮ አባላት ያሳለፏቸዉን ዉጣ ዉረድና የቀጣይ ምኞታቸዉን ከ1-3 ደቂቃ እየተሰጣቸዉ ሃሳባቸዉን አካፍለዋል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa