YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአብን አመራሮች አባላት ላይ የተካሄደ ፓለቲካዊ እስር አስመልክቶ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን ) መግለጫ።
@Yenetube @Fikerassefa
እንቦጭ በጢንዚዛዎች ሊበላ ነው።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእንቦጭ አረም በጣና ላይ መከሰቱን የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ካሳወቁበት ጊዜ ጀምሮ አረሙን ለማስወገድ የተለያዩ ስራዎችን ዩኒቨርሲቲው ሲሰራ የቆየ ቢሆንም አረሙን ማስወገድ አልተቻለም።አረሙ በጣና ሀይቅና አዋሳኝ በሚገኙ ወረዳዎች ላይ በፍጥነት እየተዛመተ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ችግሩ ያጋጠማቸው ሀገራት ስነ-ህይወታዊ ዘዴ/ጢንዚዛ/ በመጠቀም ውጤታማ የሆነ ስራ እንደሰሩ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን በስነ-ህይወታዊ ዘዴ/ጢንዚዛ/ ላይ ምርምር ሲያደርግ ቆይቶ አሁን እንቦጭን ብቻ የሚመገቡ ብሎች/ጢንዚዛዎች/ ወደ ጣና ሀይቅ ለመልቀቅ ያመች ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወሳኝ ውይይት አድርጓል፡፡ ጢንዚዛዎችን ቀጥታ ወደ ሀይቁ ከመለቀቃቸው በፊት ግን በአባይ ረግራጋማ ቦታዎች ላይ ሙከራ ተደርጎ ውጤቱን ከታወቀ በኋላ እንቦጭ በብዛት ከተስፋፋበት የጣና ሀይቅ እንዲለቀቁ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም የእንቦጭ አረምን በሳይንሳዊ ዘዴ ለማስወገድ በርካታ እንቦጭን ብቻ የሚመገቡ ጢንዚዛዎችን ከወንጅ ስኳር ኮርፖሬሽን የምርምር ማዕከል በማምጣት የተለያዩ የሙከራ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ከምርምሩ በተገኘው ውጤት መሰረት እንቦጭን ለማጥፋት ጢንዚዛዎች በጣና ሀይቅ ላይ ቢለቀቁ የሀይቁ የሙቀት መጠን ከ14-18 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ በመሆኑ ለጢንዚዛዎች መራባት ተስማሚ ስለሚሆን ውጤታማ እንደሚሆኑ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የብሉ ናይል ውሃ ምርምር ተቋም ተመራማሪ እንዲሁም በባዮሎጂ ት/ት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው በነበሩ ገልፀዋል፡፡የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ጋሻው ጥላሁን እንዳሉት እንቦጭን ለማስወገድ ሁሉንም የማስወገጃ አማራጮችን መተግበር እንዳለ ሆኖ ነገር ግን ጊዜንም ሆነ የገንዘብ ወጭ ብዙም የማይፈልገው ብልን/ጢንዝዛንም/ መጠቀም ተገቢና አዋጭ በመሆኑ በፍጥነት ፈቃዱን አግኝቶ ወደ ትግበራ መግባት እንዳሚገባ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:አሐዱ ሬዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች፣ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ የሰጠው ማሳሰቢያ!

<<በአሁኑ ስዓት በዩኒቨርስቲያችን የኩፍኝ በሽታ ምልክቶች እየታዩ ስለሆነ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ካሁን በፊት ቢከተቡም ባይከተቡም ክትባቱ በዘመቻ መልክ ይሰጣል፡፡ ስለሆነም የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ክትባቱን እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡የኩፍኝ መከላከያ ክትባቱ ህዳር 25-30/2012 ድረስ ለተከታታይ 6 ቀናት ክትባት ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ክትባቱን በተጠቀሰው ቀንና በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በተዘጋጁ የክትባት ጣቢያዎች እየመጣችሁ እንድትከተቡ እናሳስባለን፡፡
#ማሳሰቢያ ፡-ክትባቱ ለነፍሰጡሮች የተከለከለ ነው!!>>

@YeneTube @FikerAssefa
በአብን አመራሮች አባላት ላይ የተካሄደ ፓለቲካዊ እስር አስመልክቶ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን ) የተሰጠውን መግለጫ የኔቲዩቦች ቦታው ላይ ተገኝተን መግለጫውን ተከታትለናል እንዲሁም በካሜራችን ያስቀረነውን ቪዲዮ በዩቲዩብ ቻናላችን ከደቂቃዎች በኃላ እንለቅላችዋለን።

@Yenetube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእነ አቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ሳይሰማ ቀረ።

ችሎቱ ዛሬ የአቶ በረከት ሰምዖን እና የአቶ ታደሰ ካሳን የመከላከያ ምስክሮች ለመስማት የተሰየመ ቢሆንም 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የሰነድና የሰው ምስክሮች ባለመቅረባቸው ለሌላ ጊዜ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። የእነ አቶ በረከት ጠበቃ “በተለይ አስፈላጊ የሆኑ የመከላከያ ሰነዶች ለዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ መድረስ ስላልቻሉ ከቀጣዩ ቀጠሮ ቀን በፊት እንድናቀርብ ይፈቀድልን” ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። አቃቤ ህግ «የተሰጠው ምክንያት ተቀባይነት የለውም» በማለት ቅሬታ ቢያቀርብም ሆኖም ግን በአጭር ጊዜ ሰነዶቹን
የሚያቀርቡ ከሆነ እንደማይቀወም ተናግሯል። የ3ኛ ተከሳሽ የአቶ ዳንኤል ግዛው ጠበቃ ባለ 150 ገፅ የሰነድ ማስረጃ እና ከ6 የሰው ምስክሮች መካከል 3ቱን አቅርበው የመከላከያ ምስክርነት ለማሰማት ቢሞክሩም አቃቤ ህግ «ምስክሮቹ በአንድ ላይ መቅረብ አለባቸው ምክንያቱም ዛሬ የተገኙና ያልተገኙ ምስክሮች ተናብበው ምስክርነት ስለሚሰጡና ትክክለኛ ፍትህን ሊያዛቡ ይችላሉ» በማለት ተቃውሞ ተከራክሯል።

የተከሳሹ ጠበቃ የአቃቤ ህግን ክርክር ባይቀበሉትም ፍርድ ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የ3ኛ ተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች በአንድ ላይ እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ በመጨረሻ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ክስ የተመሰረተባቸው አቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ዳንኤል ግዛው አለን የሚሏቸው የሰነድና የሰው የመከላከያ ምስክሮችን ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. በፊት አንዲያስመዘግቡ አዟል። ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የመከላከያ ምስክሮች ለማድመጥ ለታህሳስ 30 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ተዘግቧል። አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሾች የጥረት ኮርፖሬት ከፍተኛ አመራሮች ሆነው ሲሰሩ የኮርፖሬቱን ንብረት ከአለአግባብ አባክነዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥር 2011 ዓ.ም. ሲሆን 3ኛው ከሁለቱ ተከሳሾች ጋር በመመሳጠር በተቋሙ ሙስና ሰርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱ የደህንነት ቀበቶ መመሪያ ከጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል።

አዲሱ የደህንነት ቀበቶ መመሪያ ከጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአሽከርካሪውና ለሁሉም ተሳፋሪዎች የፀና እንደሚሆን ተገለጸ።መመሪያው በመንግስትና በግል ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፣ እስከ 150 ኪሎ ሜትር በሚጓዙ ሚኒባሶች እና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ ከ5 እስከ 8 መቀመጫ ያላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ልዩ ባሶችና ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች ላይ ተግባራዊ ይሆናል።ከዚህ ባለፈም የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፣ ከ12 እስከ 15 ሰው የሚጭኑና በከተማ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ፣ የብዙሃን አገልግሎት የሚሰጡ የከተማ አውቶብሶች ለአሽከርካሪውና ፊት ወንበር ላይ ለሚቀመጡ ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ መጠቀም ይኖርባቸዋል።

በተጨማሪም ለግል አገልግሎት የሚጠቀሙ አውቶሞቢሎች የህፃናት ደህንነት መጠበቂያ ቦርድ ያለው ማካተት ይኖርባቸዋል ነው የተባለው። በአስመጪዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ አዲስ የመንግስት፣ የግል፣ የህዝብና የጭነት ተሽከርካሪዎች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሚወጣው መስፈርት መሰረት ለአሽከርካሪውና ለተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ የተገጠመላቸው መሆን አለበት።በብዙሃን ትራንስፖርት ቆመው የሚጓዙ እና አጭር ርቀት የሚጓዙ ቀበቶ እንዲያስሩ የሚያስገድደው ህግ አሁን በአዲሱ መመሪያ አስገዳጅነት እንደማይኖረው ተገልጿል።እንዲሁም በባለሁለትና በባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ በግዳጅ ስራ ላይ በተሰማሩ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም።

-መረጃው የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ነው
@YeneTube @FikerAssefa
የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር(ኦብነግ) በሕወሓት ጠሪነት “ሕገ መንግሥትና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓትን ማዳን" በሚል ርዕስ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፍ ለጠሪው አካል እንዳሳወቀ ጠቅሶ በማኀበራ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው ደብዳቤ ግን የሐሰት ዜና መሆኑን በትዊተር ገጹ አሳውቋል፡፡

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
እስካሁን ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን በጂቡቲ ለማቋቋም የተደረሰ ስምምነት እንደሌለ ተገለጸ።አምባሳደሩ እንዳሉት የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል ጂቡቲ ውስጥ ማቋቋምን በሚመለከት ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ያመላከቱ ሲሆን፤ ነገር ግን "እስከ አሁን የተደረሰ ህጋዊ ስምምነት የለም" ብለዋል።

ተጨማሪ👇👇👇

https://telegra.ph/NAVY-12-04-2
ቅድም ባልነው መሰረት ዛሬ ግንፍሌ አከባቢ በሚገኘው በአብን ዋና ቢሮ ተገኝተን የቀረፅነውን መግለጫ አቀናብረን በቻናላችን ላይ ለቀናል።

ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አድርጉን!!

https://www.youtube.com/watch?v=AsZ6ColQklU
የብልጽግና ፓርቲ የዕውቅና ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ!

በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውህደቱ አካል ለሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝና በአዋጅ አንቀጽ 91(4)ሀ መሰረት በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስረክቧል፡፡

Via EPRDF Official
@YeneTube @FikerAssefa
በመቐለ ከተማ ዛሬ በተጀመረው 'አገር ዓቀፍ መድረክ' የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች እንዳይሳተፉ "ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ባላቸው ሀይሎች" ጫና ተደርጎባቸዋል ሲሉ የህወሃት ሊቀመንበር ደ/ጺዮን ገ/ሚካዔል ወቀሱ።"ሕገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓትን የማዳን አገር ዓቀፍ መድረክ" በሚል መሪ ሀሳብ በተጀመረው ጉባዔ ንግግር ያሰሙት ሊቀመንበሩ "ይህ በህገመንግስቱ የተጎናፀፈውን መብት የረገጠ አፋኝ ተግባር በመሆኑ ስርዓት መያዝ አለበት" ብለዋል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀረቡ። የኤርትራ ማስታወቂያ ምኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው እንደገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ጨምሮ 21 አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንቱ አቅርበዋል። ሬድዋን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤርትራ ባደረጓቸው ጉብኝቶች አምባሳደሩ ሲያጅቧቸው ታይቷል። ሬድዋን ሑሴን ወደ አስመራ ከመዛወራቸው በፊት በአየርላንድ
የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሰርተዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ሉካንዳ ቤቶች በግብር ምክንያት ባደረጉት አድማ ወደ ቄራ የሚልኳቸውን የእርድ በሬዎች ዛሬ አላኩም።

ዓመታዊ ግብራችን አላግባብ ተተምኗል በሚል ምክንያት አብዛኞቹ የክርስቲያን ስጋ ቤቶች አድማ በማድረግ ወደ ቄራዎች ድርጅት ለእርድ የሚልኳቸውን በሬዎችን እንዳላኩ ከቄራዎች ድርጅት ሰራተኞች አረጋግጫለው።
በዚህ በገና ፆም ወቅት ቢያንስ በቀን 400 በሬ ለእርድ ወደ ቄራ የሚመጣ ሲሆን ዛሬ በአድማው ምክንያት ወደ ቄራ ለእርድ የመጡት በሬዎች ከ50 አይበልጡም።

እስከ ማምሻው ድረስ የሚቆዮት የቄራ ሰራተኞች ዛሬ እምብዛም ስራ ስሌለ ወደ ቤታቸው በግዜ ሄደዋል።

Via:-Tesfay getnet
@Yenetube @Fikerassefa
Breaking....
ቦርዱ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ።
ባለፈው ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም የህዝበ ውሳኔው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ የተደረገ ሲሆን፥ በዛሬው እለት ደግሞ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በዚህም 97 ነጥብ 7 በመቶ የሆኑት መራጮች ሲዳማ በክልልነት እንዲደራጅ ድምጽ ሲሰጡ፥ 1 ነጥብ 47 በመቶዎቹ ሲዳማ በደቡብ ክልል ለመቆየት ድምጽ ሰጥተዋል።

ቦርዱ የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት በመገምገም፥ የድምር እንዲሁም ሌሎች የምርጫ ውጤት አለመጣጣም ያለባቸውን ጣቢያዎች በማየት ውሳኔ ማሳለፉንም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በመሆኑም በአጠቃላይ ድምጽ ከተሰጠባቸው 1 ሺህ 692 ምርጫ ጣቢያዎች እና ተጨማሪ 169 ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች መካከል በ233ቱ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የድምርና የውጤት አለመጣጣም ችግር ማግኘቱን ገልጿል።
ችግሮቹ አስፈጻሚዎች ቁጥር በሚደምሩበት ወቅት የተገኘ የቁጥር ድምር ችግር እና ድምጽ የሰጡ መራጮች፥ ከተመዘገቡት አንጻር ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
እንዲህ አይነት ችግሮች በሚያጋጥሙበት ወቅት የችግሩን ምንጭ ለማወቅ የድጋሚ ቆጠራ መደረግ ቢኖበትም፥ ቦርዱ በአማራጭ ውጤቶቹ መካከል ያለው የውጤት ልዩነት ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር በውጤቱ ላይ ለውጥ ስለማያመጣና በሂደቱ ተአማኒነት ላይ ጥያቄ ስለማያስነሳ፥ የድጋሚ ቆጠራ በማዘዝ ውጤት ማሳወቂያ ጊዜው መጓተት የለበትም በሚል የድጋሚ ቆጠራ ማካሄድን አስፈላጊ ሆኖ እንዳለገኘውም ጠቅሷል።
በዚህም መሰረት ዓለም አቀፍ የምርጫ ውጤት አስተዳደር ልምድን፣ የምርጫው አይነት ህዝበ ውሳኔ መሆኑ እና በተወሰኑ ጣቢያዎች የተፈጠረው አለመጣጣም በአጠቃላይ የድምጽ ሰጭዎች ድምጽ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ ውስንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦርዱ ችግር የተገኘባቸውን ጣቢያዎች ሁኔታ በማየት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ከተመዘገበው መራጭ በላይ ድምጽ ተሰጥቶ የተገኘባቸው የ127 ምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እንዲሰረዝ እና በቆጠራ እና በድምር ስሌት ስህተት ከተገኘባቸው ጣቢያዎች መካከል የታየው ልዩነት 10 ድምጽ እና ከዚያ በታች የሆኑ ልዩነቶች ዋጋ እንዳላቸው ድምጽ እንዲቆጠሩ ወስኗል።

ከዚህ ባለፈም ከ10 ድምጽ በላይ የድምር ልዩነት የተገኘባቸው ጣቢያዎች ውጤት እንዳይካተት የወሰነ ሲሆን፥ በዚህ መሰረት 37 ምርጫ ጣቢያዎች በከፍተኛ የድምርና የስሌት ስህተት የተነሳ ውጤታቸው ተሰርዟል።

በአጠቃላይ 164 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያሉ ውጤቶች በተጠቀሱት ምክንያቶች የተነሳ እንዲሰረዙ የተደረገ ሲሆን፥ 71 የምርጫ ጣቢያዎች ግን የድምር ልዩነቱ ከ10 ድምጽ በታች በመሆኑ ስህተት ቢኖራቸውም ውጤታቸው ዋጋ ኖሮት እንዲቀጥል ተደርጓል።


ቦርዱ መሰል ችግሮች በሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ ቢፈጠሩ ሊኖራቸው ከሚችለው ተፅዕኖ አንጻር ችግሮቹ የተፈጠሩበትን ምክንያት የሚያጣራ የቴክኒክ ቡድን አቋቁሟል፡፡

የቴክኒክ ቡድኑን ውጤት መሰረት አድርጎም ለቀጣዩ ምርጫ አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የአስፈጻሚዎች ስልጠና እና የምርጫ ሂደቱን የማሻሻል ስራዎችን እንደሚሰራም ገልጿል።

በመጨረሻው ውጤት መሰረትም የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 2 ሚሊየን 304 ሺህ 577 ሲሆኑ ድምጽ የሰጡ መራጮች 2 ሚሊየን 279 ሺህ 22 ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 248 ሺህ 97 መሰረዙንም ቦርዱ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa