YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ #ጃዋር_መሀመድ ድጋፋቸውን እና #ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል።

ለኦሮሞ መብት ተሟጋቹ ጃዋር መሀመድ ድጋፋቸውን እና ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አደባባይ ወጥተዋል። ጃዋር መሀመድ በዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች እና በአውሮፓ ሀገራት እየተዟዟረ ከደጋፊዎቹ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ቀጥሏል። ዛሬ በኑርንበርግ ከተማ ድጋፋቸውን ለመግለፅ አደባባይ የወጡት ኢትዮጵያውያን የኦነግን ጨምሮ የሌሎች ክልሎችን ባንዲራዎችም ይዘው ተስተውሏል።

ተቃውሟቸውን ለማሰማት የከተማዋ ባቡር ጣቢያ አካባቢ የወጡት ደግሞ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ያለውን ባንዲራ ይዘው ነበር። ተቃዋሚዎች በቅርቡ ጃዋር መሀመድ መንግሥት ጠባቂዎቼን ሊያነሳብኝ ነው የሚል መልዕክት ለደጋፊዎቹ ማስተላለፉን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሞቱ 86 ሰዎችም የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት አድርገዋል። ጃዋርም ለፍርድ ይቅረብ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ክልል የመሆን ጥያቄ ካቀረበው የዎላይታ ዞን ባለሥልጣናት እና የማህበረሰቡ ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ የዎላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቢ፤ የሰላም ምኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ የደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የሐይማኖት መሪዎች ጭምር ተገኝተዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር «ፍሬያማ ውይይት አድርገናል» ብለዋል።

በውይይቱ የተሳተፈው እና የላጋ የተባለው የዎላይታ ወጣቶች ማኅበራዊ ንቅናቄ መሥራቾች አንዱ የሆነ አሸናፊ ከበደ «ዎላይታ ራሱን ችሎ ክልል ከመሆን ሌሎች አማራጮች ይኖራሉ አይኖሩም? የሚሉ ጉዳዮች እና ሌሎች ተያያዥ አማራጭ የሆኑ ጉዳዮች ምንድናቸው? እዚያ ላይ እንወያይ» ማለታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል።

ተሳታፊዎች «የአስራ አምስት ሚሊዮን የዎላይታ ሕዝብ አቋም እና ፍላጎት ህገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት የዎላይታ ሕዝብ ራሱን ችሎ በራሱ ክልል የመሆን አማራጭ ተወዳዳሪ እና አቻ የለውም» የሚል ምላሽ ለጠቅላይ ምኒስትሩ እንደሰጡ አሸናፊለዶይቼ ቬለ አስረድቷል።

የዎላይታ ዞን ክልል ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ በመጪው ታኅሳስ አስር ቀን አንድ አመት ይሞላዋል። ለጥያቄው መልስ ለማግኘት ከታኅሳስ አስር በፊት የሕዝበ ውሳኔ የሚካሔድበት ቀን እንዲታወቅ እንደሚፈልጉ አሸናፊ ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል።

የዎላይታ ዞን የዴሞክራሲ ተቋማት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የኮምዩንኬሽን ኃላፊ አቶ አለማየሁ አፈወርቅ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም በይፋ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት አሁንም ግፊት እየተደረገ ነው።

የደቡብ ክልል ምክር ቤቱ የዎላይታ ዞን ያቀረበውን ጥያቄ ለመመለስ «መወሰን የማይችል ከሆነ አመት ከሞላ በኋላ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሔዶ አንዳንድ ሥራዎችን ለመስራት በዞኑ ምክር ቤት እንደ ይግባኝ የተዋቀረ ኮሚቴ አለ።

ከዚያ በዘለለ ማሟላት ያለበትን አሟልቶ ነው የሔደው። አሁን ደግሞ ደኢሕዴን ወደ ብልፅግና ፓርቲ ተቀላቅለናል። በጠቅላላ ጉባኤ ተወስኗል። ብልፅግና እንደ ሀገር አንድን ብሔረሰብ መወከል የሚችል፤ ማሳተፍ የሚችል ነው ብለን እናምናለን።

የዎላይታም ጥያቄ በብልፅግና የማይመለስበት ምክንያት የለም ብለን እናምናለን» ሲሉ አቶ አለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
የብልፅግና ፓርቲ ስምምነቱን የፈፀሙ ድርጅቶች ሊቀ መናብርት ፊርማ።
@Yenetube @Fikerassefa
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ላይን በመጪው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ ያቀናሉ። ከርዕሰ-ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋሳቂ ማኅማት ይገናኛሉ።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው!

በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ ኤችአይቪ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ገለፀ።ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አፋር፣ ትግራይ፣ አማራና ቤንሻንጎል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በኤችአይቪ ወረርሽኝ ውስጥ መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኑኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ ለቢቢሲ ተናግረዋል።


https://telegra.ph/AIDS-12-02
በሲዳማ ክልል የፓርቲው ቅርንጫፍ እንደሚከፈት አስታወቁ የዞኑ አስተዳዳሪ ገለፁ።

የብልጽግና ፓርቲ እየተበራከቱ የመጡ የህዝብ ፍላጎቶችን መመለስ በሚያስፈልግበት ወቅት የተወለደ ፓርቲ መሆኑን የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ፡፡ የሲዳማ የክልልነት ሂደት ሲጠናቀቅም በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እንደሚከፈት አስታውቀዋል፡፡ዋና አስተዳዳሪው አቶ ደስታ ሌዳሞ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት በርካታ የህዝብ ፍላጎቶች ታይተዋል፤ ጥያቄዎችም ተነስተዋል፡፡ ይህን ሊመልስ የሚችል ቁመና ያለው ፓርቲ አስፈላጊ እንደመሆኑም የብልጽግና ፓርቲ ወቅቱ የፈጠረው ፓርቲ መሆኑ እሙን ነው፡፡የብልጽግና ፓርቲን በመመስረት ሂደትም የሲዳማ ተወላጅ የደኢህዴን አባላት ተሳታፊና የውሳኔው አካል እንደመሆናቸው የሲዳማ የክልልነት ሂደት ሲጠናቀቅ በፓርቲው ሕገ ደንብ መሰረት የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በክልሉ ይኖራል፡፡

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
Center for Advancement of Rights and Democracy(CARD) አሳሳቢ የጥላቻ ገለጻዎች በአሜሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በቅርቡ ጀዋር መሃመድ በዩናይትድ ስቴትስ ከደጋፊዎቹ ጋር ውይይት ሊያደርግ ባቀናባቸው ከተሞች መንፀባረቁን ታዝቦ ይህንን መግለጫ (መልዕክት) አስተላልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ የ352 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ።

ከገንዘብ ድጋፉም 110 ሚሊየን ዩሮ በቀጥታ ለመንግስት በጀት ድጋፍ የሚውል መሆኑም ታውቋል።የጀርመን የኢኮኖሚ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ገርድ ሙለር የተመራ ልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት እያደረገ ነው።ልኡኩ በዛሬው እለትም ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኝቶ ተወያይቷል።በውይይቱ ወቅትም የጀርመን መንግስት ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የሪፎርም ስራዎች ለመደገፍ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።ከዚህ ባለፈም የጀርመን መንግስት የግብርና ስራን ለመደገፍ ከ100 በላይ የግብርና መሳሪያዎች ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
ለ30 ሺሕ ሰዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው!

ከኅዳር 22 እስከ 24 በሚሊኒየም አዳራሽ በሚከናወነው ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽን እና ኮንፍረንስ ከ 30 ሺሕ ለሚበልጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገለፀ።የአዲስ አበባ የግል የጤና ተቋማት አሠሪዎች ማኅበር ባዘጋጀው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ፣ የልብ እና የደም ግፊት ምርመራ፣ የስኳር፣ የዐይን እና የጥርስ ህክመና እንዲሁም የኤ.ች አይ. ቪ ምርመራ ከአገር ውስጥ የግል የጤና ተቋማት እና ከተለያዩ የውጪ አገራት በመጡ ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ዜና እረፍት!

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።አቶ ተገኔ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።አቶ ተገኔ ለረጅም አመታት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ አብዲ መሃመድ የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግ ምስክርን ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ!

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት በእነ አቶ አብዲ መሃመድ ኡመር የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግ ምስክርን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡በዚህም መሰረት ከጥር 14 እስከ ጥር 22 2012 ዓም ድረስ የአቃቤ ህግ ምስክርን ለመስማት ነው ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ የሰጠው፡፡በተጨማሪም በዚህ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ መጥሪያና በጋዜጣ ጥሪ ያልቀረቡ አስር ተከሳሾች ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት ወስኗል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት የሶማሌ ክልል ፖሊስ ለሶስት ተከሳሾች መጥሪያ እንዲያደርሳቸው ፍርድ ቤቱ ያዘዘ ሲሆን የክለሉ ፖሊስ ባደረገው አሰሳ ሁለቱ ከሃገር መውጠታቸውንና የተቀረውን አንድ ተከሳሽ በመያዝ ለፌዴራል ፖሊስ ማስረከቡን በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡ፍርድ ቤቱም ከሃገር የወጡት ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትእዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ ደግሞ የተረከበውን ተከሳሽ በቀጣይ ችሎት እንዲያቀርብ፤ ካልተረከበም ቀርቦ እንዲያሳውቅ አዟል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
"ከጀርመን ፌደራል የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ጌርድ ሙለር እና ከፌደራል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ሁበርተስ ሄል ጋር ዛሬ ጠዋት ተገናኝተን ጥሩ ዉይይት አካሂደናል።
የጀርመን መንግሥት የለውጡን ሂደት ለመደገፍ ቃል በገባው መሠረት 352.5 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት ስምምነት በመፈረሙ ያለኝን ደስታ እገልጻለሁ"

ጠ/ር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
@Yenetube @Fikerassefa
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በግጭት ሳቢያ ጥለው የወጡ ተማሪዎችን ከአዲስ አበባና አካባቢው ለመመለስ አውቶቡስ አዘጋጅቷል። ነገር ግን ነገ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ የሚጓዘው አውቶቡስ በመሙላቱ ያልተመዘገቡ በግላቸው ወጪ እንዲመለሱ ተነግሯቸዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በአሜሪካ ጉብኝት እያደረገ ነው።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።በመከላከያ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ በዛሬው እለት ዋሽንግተን ዲ.ሲ መግባቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።ጉብኝቱም የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አምባሳደር ፍጹም ገልፀዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
😍ለጫማ አድናቂዎች😍
ለወንድም ለሴትም ሚሆኑ አዳዲስ ጫማዎችን እነሆ ብለናል::

💥ማስታወሻ:ተደራሽነታችን በአዲስ አበባ እንዲሁም ሁሉንም የክልል ከተምችን ያካትታል
🎯አድራሻ:-ገርጂ መብራት ሀይል ዊዝደም ህንፃ ፊት
ስልክ:-0900628132
0116296465
በቴሌግራም ለማግኘት ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉን👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
#አስደሳች ዜና ለሞባይል መለዋወጫ ሱቆች
በስክሪን ኘሮቴክተር መሰቃየት ቀረ
አንዴ ገዝተው እስከ ሁል ጊዜ ከጥሩ ትርፍ ጋር ለሁሉም አይነት ስልክ የሚያገለግል።

በ 12000 ብር ብቻ

አሁኑኑ በ 0911522626
0953120011

ይደውሉ። ወይም በ @natyendex መልእክት ያስቀምጡ።

For more @natcomputers
Forwarded from YeneTube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
ጃዋር - DW

የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሐመድ በቅርቡ በሚደረገው ምርጫ እንደ ፖለቲከኛ እንዴት እንደሚወዳደር እስካሁን እንዳልወሰነ አስታወቀ።

ጀዋር ለዶቼቬለ በሰጠው ቃለ ምልልስ የራሱን ፓርቲ መስርቶ ወይም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተጣምሮ መወዳደርን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ከገዥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይቶ እንደሚወስን ተናግሯል።

የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ውህደትንም የፌደራል ስርዓቱን የሚሸረሽር ሲል ተችቷል።

#መሉ_ቃለ ምልልሱን እንደደረሰን እናደርሳችኃለን።

@Yenetube @Fikerassefa
ሲአን! ሲዳማ ዞንን የሚመራው አካል አዲሱን ሲዳማ ክልል መረከብ የለበትም አለ!!

ሲዳማ ዞንን የሚመራው አካል አዲሱን ሲዳማ ክልል መረከብ የለበትም ሲል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ለሸገር ተናግሯል፡፡ ክልሉን የመምራት ሃላፊነት የሚወስደው እንደ አዲስ ለሚሰባሰቡ የሕዝብ ወኪሎች ብቻ ናቸው ብሏል፡፡

የዞኑ አስተዳደር ግን ሲዳማ ክልልን ለመምራት የ5 ዐመት ዕቅድ እና ረቂቅ ሕገ መንግሥት ማዘጋጀቱን ይናገራል፡፡

Via:- Wazema
@Yenetube @Fikerassefa