ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ግንባታ ላይ እየተሳተፉ ካሉ 1 ሺህ 450 ሰራተኞች ጋር ምሽቱን በጋራ እራት በልተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወጣት የግንባታ ሰራተኞቹ እያሳዩት ያለውን ትጋት በማድነቅ ለሌሎች ወጣቶችም አርአያ መሆናቸውን በእራት ዝግጅቱ ላይ ተናግረዋል።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ከአዲሱ ህንፃ ላይ እየወደቀ ያለው እብነበረድ ጉዳት ከማድረሱ በፊት መፍትሄ እንዲሰጠው ተጠየቀ።
ለጌጥ ተብሎ የተለጠፈው እብነ በረድ እየወደቀ በመሆኑ ወደ ህንጻው በሚገቡና በሚወጡ ተገልጋዮችና ሠራተኞች ላይ ወድቆ አደጋ ሊያደርስ ስለሚችል ፈጣን መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ የአራዳ ክፍለ ከተማና ሠራተኞቹ አሳሰቡ።የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አበባ እሸቴ በተለይ ለጋዜጣው ሪፖርተር እንደገለጹት፤ ለኮንስትራክሽን ቢሮና ለፐብሊክ ሰርቪስ ጽህፈት ቤት ከተገነባው ህንጻ በሚወድቀው እብነ በረድ ምክንያት ጉዳት እንዳይከሰት የማረሚያ ሥራ እንዲሰራ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም አፋጣኝ ምላሽ አልተሰጣቸውም።ህንጻውን በበጋ ወቅት ስለተረከቡ በወቅቱ ፍሳሽ እንዳልነበረ የተናገሩት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አበባ ፤ ክረምት ላይ ፍሳሽ መኖሩን መመልከታቸውን ገልጸው፤ የህንጻውን የፍሳሽ ችግሮች የማስተካከል ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል ።
Via ኢፕድ

በሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት አዳዲስ ማዕድናት ተገኙ።
በሰሜን ሽዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፊልድስፓር እና ፑሚስ የተባሉ ነጭና አብረቅራቂ ብርሃናማ ቀለም ያላቸው ማእድናት መገኘታቸው ታወቀ። ማእድናቱ ለመስታወት፣ ሴራሚክ፣ ኮምፒዩተር ስክሪን፣ ለላብራቶሪ አገልግሎት የሚያገለግሉ መስታወቶችና ሌሎች ከመቶ ስልሳ በላይ ለሚሆኑ አገልግሎቶች የሚውሉ ናቸውም ተብሏል።የክልሉ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ማዕድናት ባካሔደው ጥናት ማዕድኖቹን ያገኘ ሲሆን፣ ናሙናቸውም ወደ ኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ተልኮ በምርምር ማረጋገጡንም የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ኤጀንሲ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ይታየው ተስፋሁን ገልፀዋል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

በቶሮንቶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢሬቻን በዓል አከበሩ።
በካናዳ ቶሮንቶ የሚኖሩ የኦሮሞ ኮሙዩኒቲ አባላት የኦሮሞ ህዝብ የምስጋና በዓል የሆነውን የኢሬቻ በዓል በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።በዓሉን በኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ መርጋ ፈይሳ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ታድመዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በካናዳ ቶሮንቶ የሚኖሩ የኦሮሞ ኮሙዩኒቲ አባላት የኦሮሞ ህዝብ የምስጋና በዓል የሆነውን የኢሬቻ በዓል በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።በዓሉን በኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ መርጋ ፈይሳ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ታድመዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን የመጤ ጠል እንቅስቅሴ በማውገዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ አውጥቷል ።
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
ንግድ ባንክ ከወለድ ነፃ ቅርንጫፍ ሊከፍት ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቷ የመጀመሪያ የሆነውንና የተሟላ ከወለድ ነፃ አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፉን ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ። የባንኩ የወለድ ነፃ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሀሰን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ ባንኩ እስከ ዛሬ ድረስ በመስኮት ደረጃ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በማሳደግ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ቢላል ቅርንጫፍ በሚል ጳጉሜ 2 ቀን 2011 ዓም ይከፍታል ብለዋል።ከወለድ ነጻ የአገልግሎት ቅርንጫፉን መክፈት ያስፈለገው የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም ባንኩን በወለድ አልባ መስኮቶች የተቀማጭ አገልግሎትን በመስጠት ቀዳሚ እንደሚያደርገውም ተናግረዋል።
ምንጭ: ኢ.ፕ.ድ

ዛምቢያ በዘረኝነት ጥቃት ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምታደርገውን የኳስ ጨዋታ ሰረዘች።
የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል። የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ባሳየው ቸልተኝነት ምክንያት መሆኑ ታውቋል።የዛምቢያ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ወደ ደቡብ አፍካ እንዳይጓዙም አስጠንቅቋል።
ምንጭ: ኢቢሲ
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል። የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ባሳየው ቸልተኝነት ምክንያት መሆኑ ታውቋል።የዛምቢያ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ወደ ደቡብ አፍካ እንዳይጓዙም አስጠንቅቋል።
ምንጭ: ኢቢሲ
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ዛምቢያ በዘረኝነት ጥቃት ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምታደርገውን የኳስ ጨዋታ ሰረዘች። የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል። የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን…
በተመሳሳይ ዜና ታዋቂው የናይጄሪያ ድምፃዊ ቡራን ቦይ በዘርኝነት ጥቃቱ ምክንያት በጭራሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዝ እእንደማይፈልግ ተናግሯል።
ናይጄሪያም በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቅቃለች።አቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች።
የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷልም ተብሏል።
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
ናይጄሪያም በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቅቃለች።አቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች።
የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷልም ተብሏል።
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 26 ሽጉጦች ቦምባስ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ በጉምሩክ ፈታሾች እና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ ከሽጉጦቹ ጋር ሁለት የሽጉጥ ሰደፍና 11 ካርታ የተያዘ ሲሆን ህገ-ወጥ መሳሪያው ኮድ3-30513 የሰሌዳ ቁጥር ባለው አይሱዙ ተሸከርካሪ ትናንት ከምሽቱ 3፡00 አካባቢ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
-የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
-የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሌሴቶ ጋር ይጫወታሉ።
የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን ለ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሌሴቶ ጋር በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡ዋልያዎቹ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ በ10 ሰዓት በርካታ ደጋፊዎች በተገኙበት ይፋለማሉ፡፡
Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን ለ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሌሴቶ ጋር በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡ዋልያዎቹ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ በ10 ሰዓት በርካታ ደጋፊዎች በተገኙበት ይፋለማሉ፡፡
Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሀንስበርግ መጤ በተባሉ እና የደቡብ አፍሪካ ዜግነት በሌላቸው የውጭ አገራት ዜጎች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት የደቡብ አፍካው ፕሬዘዳንት ሲሬ ራማፎዛ በይፋ አውግዘዋል።
And We say #ActionNeeded !
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
And We say #ActionNeeded !
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ገበያውን ለማረጋጋት ዘይት የማቅረብ እቅድ አለኝ አለ፡፡
ይሁንና ይህን ለማድረግ ከዚህ ቀደም ዘይት አስመጥቼ ገንዘቡ ተመላሽ ያልተደረገልኝ ከ590 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ሊመለስልኝ ይገባል ብሏል፡፡በኑሮ ውድነት እየተንገላታ ያለውን ዜጋ ለማገዝ ከመጭው አመት ጀምሮ ዘይት ላቀርብለት አቅጃለሁ ያለው ኢግልድ በቅድሚያ ግን ከዚህ ቀደም ዘይት አስመጥቼ ያልተከፈለኝ ገንዘብ ሊመለስልኝ ይገባል ብሏል፡፡የኢግልድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ወንዳለ ሀብታሙ እንዳሉት ከመጭው ጥቅምት ወር 2012 ዓ/ም ጀምሮ ከውጭ ዘይት በማስወጣት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ተወጥኗል፡፡
ይሁንና የስራ ማስኬጃ ገንዘብ እጥረት ስላለብን ከ2003 እስከ 2008 ዓ/ም ላስመጣነው ዘይት ያልተከፈለን 596 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ሊከፈለን እንደሚገባ ገንዘብ ሚኒስቴርን ጠይቀናል ብለዋል፡፡ገንዘቡ ከተመለሰለት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ከመጭው ጥቅምት ወር ጀምሮ በየወሩ 30 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለማስገባትና በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለማቅረብ አቅጃለሁ ብሏል፡፡
Via Sheger Radio

"አሁን ባለው ዋጋ ዳቦ ማቅረብ አባላቶቼን እየፈተነ ነው!" የአዲስ አበባ ዳቦ አምራቾች ማህበር
አሁን ባለው ዋጋ ዳቦ ማቅረብ አባላቶቼን እየፈተነ ነው፤ ዳቦ ቤቶች ዋጋ ጨምረው ለመሸጥ የተገደዱትም የዱቄት ዋጋ በመናሩ ነው ሲል የአዲስ አበባ ዳቦ አምራቾች ማህበር ተናገረ፡፡የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበኩሉ በመንግስት የድጎማ ዋጋ ዱቄት የሚያገኙ ዳቦ አምራቾች በምንም አይነት ሁኔታ ዋጋ መጨመር አይችሉም፤ ወቅቱን ያገናዘበ የዋጋ ማስተካከያ ለማድረግ ጥናት አድርጌ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አቅርቤያለሁ ብሏል፡፡
ምንጭ: ሸገር

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ የቆጣሪ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ለአንድ ቀን ከግማሽ አያስተናግድም።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ አገልግሎትን ለማሻሻል የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ እያደረገ እና ማቀናጀት ስራ እየስራ ስለሚገኝ ዓርብ ጳጉሜ 1 ሙሉ ቀን እና ቅዳሜ ጳጉሜ 2/2011 ግማሽ ቀን በመላ አገሪቱ አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል። ደንበኞች ከተጠቀሰው ቀን በፊት ወይም በኋላ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል።መስሪያ ቤቱ በኔትወርክ በተሳሰሩ በኹሉም ቅርንጫፎች ደንበኞች በተገቢው ሁኔታ አገልግሎት እንዲያገኙ በትጋት እየሰራ እንደሆነም አስታውቋል።

#Update
የናይጄሪያ ተማሪዎች ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ትልቁን የቴሌኮም ኩባንያ MTN ጨምሮ ከ18 በላይ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች በ7 ቀን ውስጥ ከናይጄሪያ እንዲወጡ አሳስበዋል።
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
የናይጄሪያ ተማሪዎች ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ትልቁን የቴሌኮም ኩባንያ MTN ጨምሮ ከ18 በላይ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች በ7 ቀን ውስጥ ከናይጄሪያ እንዲወጡ አሳስበዋል።
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዙሪያ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ይሰጣል።
የትምህርት ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት፣ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል።
መግለጫውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ እንደሚሰጡ ተገልጿል።
Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የትምህርት ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት፣ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል።
መግለጫውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ እንደሚሰጡ ተገልጿል።
Via:- Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሀገር አቀፍ የሥርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ተደረገ።
ጥናቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የሚሰጠው ትምህርት ምን መምሰል አለበት? ተማሪዎችም በየደረጃቸው ሊይዙ የሚገባቸው የእውቀት ደረጃ ምን ይመስላል? የሚለውን ይዘት የሚዳስስ እንደሆነ ተመልክቷል።
በውጭ ሀገር ባለሙያዎች እንደተደረገ የተገለጸው የሥርዓተ ትምህርት ማጠቃለያ ጥናቱ ይፋ የተደረገው ዛሬ ትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ በጠራው ጉባኤ ላይ ነው። ጥናቱን የውጭ ዜጎች እንዲያደርጉ የተፈለገበት ምክንያት «በነጻነት፣ እውነተኛ የጥናት ውጤት እንዲያመላክቱ ለማድረግ በመታሰቡ» መሆኑን በጉባኤ ላይ ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ትምህርት ላይ የተካሄደው የሥርዓተ ትምህርት ጥናት ምን አዲስ ነገሮችን እንዳካተተ ለጉባኤው ታዳሚያን አብራርተዋል። የጥናቱን ውጤት ተከትሎ አሁን በተግባር ላይ ያለው ሥርአተ ትምህርት በአንድ ጊዜ ይተካል ማለት እንዳልሆነም ተጠቁሟል። #ከ2013 ዓ. ም #ጀምሮ_ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀመር የተገለጸው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ የሚገባው በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚሆን ተገልጿል።
Via:- DW

ኢትዮጵያ ከሌሶቶ ጋር የምታደርገው የ2022 የኳታሩ አለም ዋንጫ ማጣሪያ ቋሚ 11(4-3-3) የሚከተለውን ይመስላል:
📌 ግብ ጠባቂ
ጀማል ጣሰው
📌 ተከላካዮች
ረመዳን ናስር
አስቻለው ታመነ
ያሬድ ባዬ
አህመድ ረሺድ (ሺሪላ)
📌 አማካዮች
ጋቶች ፓኖም
ሽመልስ በቀለ
ቢንያም በላይ
📌 አጥቂዎች
ዑመድ ዑክሪ
ሙጂብ ቃሲም
አማኑኤል ገ/ሚካኤል
ጨዋታው 10:00 የሚጀመር ሲሆን በAmhara TV በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።
@YeneTube @FikerAssefa
📌 ግብ ጠባቂ
ጀማል ጣሰው
📌 ተከላካዮች
ረመዳን ናስር
አስቻለው ታመነ
ያሬድ ባዬ
አህመድ ረሺድ (ሺሪላ)
📌 አማካዮች
ጋቶች ፓኖም
ሽመልስ በቀለ
ቢንያም በላይ
📌 አጥቂዎች
ዑመድ ዑክሪ
ሙጂብ ቃሲም
አማኑኤል ገ/ሚካኤል
ጨዋታው 10:00 የሚጀመር ሲሆን በAmhara TV በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።
@YeneTube @FikerAssefa
#የ8ኛ_ክፍል_ፈተና_ውጤት_ይፋ ተደረገ
ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ የ2011 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ አደረገ፡፡
በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረው አለመረጋጋት ለፈተና ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል በርካታ ተማሪዎች ያቋረጡ ቢኖርም በአሁን ጊዜ በመደበኛ፣ በማታና በግል በአጠቃላይ 340 ሺህ 85 ከተመዘገበው 331 ሺህ በፈተና የተቀመጡ ሲሆን ከተመቀመጡት ውስጥ 70 በመቶ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃለፊ አቶ ተሰማ ዲማ ገልፀዋል፡፡
የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ በጥሬ ማርክ ለወንዶች 45 ለሴቶች 43 እና ለዓይነ ስውራን 40 እንዲሆን በተደረገው ውሳኔ በክልሉ በመደበኛ፣ በማታ እና በግል በአጠቃላይ ፈተና ላይ ከተቀመጡት 331 ሺህ ተማሪዎች ወስጥ 230 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደሚቀጥለው 9ኛ ክፍል ማለፋቸውንም ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ፈተናዎች ብቻ ይወሰናል ተባለ።
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት የሚወሰነው በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ፈተናዎች ብቻ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በ12ኛ ክፍል ፈተና እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።በዚህም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት በተሰጡ ፈተናዎች ብቻ የሚወሰን ነው ብሏል። በዚህም
📌 እንግሊዝኛ
📌 አፕቲቲውድ
📌 ሂሳብ
📌 ጂኦግራፊ
📌 ፊዚክስ
ውጤቶች የተማሪዎቹን መግቢያ ይወስናሉ ተብሏል። ምክንያቱም በቀሪዎቹ ሁለት ቀናት የተሰጡት ፈተናዎች የውጤት መጋሸብ የታየባቸው ናቸው ተብሏል። ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ መግቢያ የመቁረጫ ነጥብም ይፋ ይሆናል ነው የተባለው።
ምንጭ:ፋና