YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ እና ፕሪቶርያ አካባቢ ከሌሎች ሀገራት በመጡ ሰዎች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት የናይጄርያ፣ የዛምቢያ እና የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት አውግዘው መግለጫ አውጥተዋል። ደቡብ አፍሪካ በርካታ ዜጎች ያላት ኢትዮጵያስ? እስካሁን ምንም... እዛ ያለው ኤምባሲ ጥንቃቄ አድርጉ ከማለቱ በስተቀር!

የአሁኑ ጥቃት "ስራችንን ወሰዳችሁብን" ባሉ የከባድ መኪና ሹፌሮች የኩዋዙሉ ናታል ግዛት ውስጥ የተጀመረ ሲሆን በርካታ ሱቆች እንዲወድሙ እና እንዲዘረፉ ምክንያት ሆኗል። እስካሁንም 5 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

Via Elias Meseret
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን የመጤ ጠል እንቅስቅሴ በማውገዝ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ አውጥቷል ።

#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
ዛምቢያ በዘረኝነት ጥቃት ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምታደርገውን የኳስ ጨዋታ ሰረዘች።

የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል። የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ባሳየው ቸልተኝነት ምክንያት መሆኑ ታውቋል።የዛምቢያ መንግስት የጸጥታው ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ወደ ደቡብ አፍካ እንዳይጓዙም አስጠንቅቋል።

ምንጭ: ኢቢሲ
#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ዛምቢያ በዘረኝነት ጥቃት ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋር የምታደርገውን የኳስ ጨዋታ ሰረዘች። የዛምቢያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊያደርገው የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ በአገሪቱ ባለው የዘረኝነት ጥቃት ምክንያት መሰረዙን አስታውቋል። የጨዋታው መሰረዝ በዛምቢያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ላይ በደቡብ አፍሪካ እየደረሰ ባለው የዘረኝነት ጥቃት እና መንግስት ጥቃቱን…
በተመሳሳይ ዜና ታዋቂው የናይጄሪያ ድምፃዊ ቡራን ቦይ በዘርኝነት ጥቃቱ ምክንያት በጭራሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዝ እእንደማይፈልግ ተናግሯል።

ናይጄሪያም በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቅቃለች።አቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች።

የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷልም ተብሏል።


#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሀንስበርግ መጤ በተባሉ እና የደቡብ አፍሪካ ዜግነት በሌላቸው የውጭ አገራት ዜጎች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት የደቡብ አፍካው ፕሬዘዳንት ሲሬ ራማፎዛ በይፋ አውግዘዋል።

And We say #ActionNeeded !


#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
#Update

የናይጄሪያ ተማሪዎች ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ትልቁን የቴሌኮም ኩባንያ MTN ጨምሮ ከ18 በላይ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች በ7 ቀን ውስጥ ከናይጄሪያ እንዲወጡ አሳስበዋል።

#xenophobia #Southafrica
@YeneTube @FikerAssefa
#Update

ደቡብ አፍሪካ ከቅርብ ወራት ወዲህ ተከታታይ የጥላቻ ጥቃቶችን እያስተናገደች ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ ከሳምንት በፊት የታክሲ አሽከርካሪ፣በመጋቢት ደግሞ በደርባን በሚገኙ የውጭ ዜጎች ሱቆች ላይ በተፈጸመ ጥቃት 3 ሰዎች ተገድለዋል።

#Southafrica #xenophobia
@YeneTube @FikerAssefa