YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ታጣቂዎች ከኤርትራ ዛሬ #አዲግራት ገብተዋል።
አዲግራት ሲገቡም የአከባቢው #ነዋሪ አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን፥ የቁረስ ግብዣ ተደርጎላቸዋል።
©fbc
@yenetube @mycase27
#የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ አባላትና አመራር ቡድን በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ገባ።

የኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ ኢብሳን ጨምሮ የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ #የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በርከት ያሉ ደጋፊዎች አቀባበል አደርገውላቸዋል።

📌በአሁኑ ወቅት ከንጋቱ ጀምሮ ከአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ከሚገኙ ከተሞች ቁጥሩ ከፍ ያለ ነዋሪ በተሰባሰበበት መስቀል አደባባይ የአቀባበል ስነ ስርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል ።
©fbc
@yenetube @mycase27
#የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ አባላት ከኤርትራ ዛሬ በአዲግራት በኩል መቀሌ ገብተዋል።

#መቀሌ ሲደርሱም የአካባቢው ነዋሪ አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን፥ የምሳ ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

📌ኦነግ በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ ለመንቀሳቀስ ከመንግስት ጋር መስማማቱን ተከትሎ የግንባሩ አባላትና አመራሮች ዛሬ ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል።

📌በኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ቡድን ረፋድ ላይ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን፥ በመስቀል አደባባይ ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት እየተከናወነለት ይገኛል።

📌የኦነግ አባላትም ከኤርትራ ወደ ሀገራቸው በገቡባቸው የትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
©fbc
@yenetube @mycase27
#የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ በዛሬው እለትም ቀጥሎ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ይገኛል።
ፎቶ ፦fbc
@yenetube @mycase27
#ቢሾፍቱ

#የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከጋሞ ብሔረሰብ የመጡ አባቶችና ወጣቶች #ቢሸፍቱ ደረሱ። #የኦሮሞ አባ ጋዳዎችም እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለዋቸዋል። የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ወራት አልፎ የበጋው ወራት በመጀመሩ ለአምላክ #ምስጋና የሚቀርብበት በዓል በመሆኑ የሁላችንም በዓል ነው እንኳንም የኛን በዓል #በዓላቸሁ አድርጋችሁ ለማክበር በመምጣታችሁ እናመሰግናለን ብለዋል።

📌ቀን ላይ የተላከ መልክት ነበር

©MOHAMMED NURE ENDRIES

@YeneTube @Fikerassefa
#የጸጥታ ችግር ያለባቸውን አና ወንጀለኞችን በሚከተሉት ቁጥሮች
#ለኢፌድሪ_መከላከያ_ሰራዊት ጥቆማ ይስጡ!

#ሰሜን_ሽዋ
1.ራታና ግድም------------0336610015
2-አጣየ ከተማ---------------0336610615
3-አንጾኪያ ገምዛ--------------0334440077
4.አለም ከተማ--------------0111320007
#የኦሮሞ_ብ /አስ/ዞን ፖሊስ መምሪያ----0335540092
1. ከሚሴ ከተማ --------------------------- 0335541476
2. ዳዋ ጨፋ -------------------------------- 0335540230
3. አርጡማ ፉርሲ ------------------------- 0334490245
4. ጅሌ ጥሙጋ ---------------------------- 0331180024
5. ባቲ ከተማ ------------------------------- 0335530004
6. ባቲ ዙሪያ -------------------------------- 0335531451
7. ዳዌ ሀረዋ ------------------------------ 0922927930
# ደቡብ_ወሎ ዞን /መረጃ/---- 0331115576

1-ኮምቦልቻ ከተማ-------------0335510005
2-ደሴ ዙሪያ--------------------0331117748
3-አምባሰል---------------------0332240212
4-ወረባቦ------------------------0332210001
5-ተሁለደሬ----------------------0332220006
6-ሀይቅ ከተማ------------------0332220955
7-ቃሉ-----------------------------0335512434/3826
8-ለጋምቦ----------------0331140076
9-ወረኢሉ-----------------0331160076
10-ጃማ------------------0332260008
11-ተንታ------------------0334410236
12-መቅደላ---------------0334500258
13-ሳይንት-----------------0334470058
14-መሃል ሳይንት-----------0587781094/99
15-ቦረና----------------------0332200035
16-መካነ ሰላምከተማ-------0332201003
17-ደላንታ--------------------0333350048/66
18-አልብኮ-----------0332150006
19-ለገሂዳ------------0331111232
20-አርጎባ------------0331190614
21-ወግዲ---------------334450284
22-ከላላ----------------0334510220
23-ኩታበር------------0334480254

#ደሴ_ከተማ ፖሊስ መምሪያ መረጃ/---0331117748
1ኛ ፖሊስ ጣቢያ------------0331111107
2ኛ ፖሊስ ጣቢያ-----------0331111601
3ኛ ፖሊስ ጣቢያ------------0331111011
4ኛ ፖሊስ ጣቢያ-----------0331115119
5ኛ ፖሊስ ጣቢያ-----------0338111033

#ሰሜን_ወሎ ዞን ፖሊስ/መረጃ/----03333310281
1-ወልዲያ ከተማ-------03333310283
2-ጉባላፍቶ--------------0333310433
3-ቆቦ ከተማ-------------0333340025
4-ራያ ቆቦ----------------0333340576
5-ሀብሩ-------------------0333330022
6-መርሳ ከተማ-----------0333330731
7-ላስታ--------------------0333361073
8-ላሊበላ ከተማ----------0333360264
9-መቄት-------------------0332110088
10-ዋድላ----------------0334431027
11-ግዳን-----------------0332120117
12-ዳውንት-------------0331190746

#የኢፌድሪ_መከላከያ_ሚኒስቴር
እባካችሁ ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ‼️
@YeneTube @FikerAssefa
ኦዲፒ‼️

በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የተሰጠ #መግለጫ

የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ #አይደናቀፉም!
በአገራችን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የፖለቲካ ምህዳሩ #ሰፍቶ ማንኛዉም አካል በነጻነት የመደራጀት፣ የፈለገዉን የፖለቲካ አጀንዳ በሰላማዊ መንገድ እንዲያራምድ፣ የሀገራችን ህዝቦች ለዘመናት የታገሉለትና ዉድ መስዋዕትነት የከፈሉበት እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እዉን እንዲሆን በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ረገድ #ተስፋ_ሰጪ ተጨባጭ ዉጤቶችም በመመዝገብ ላይ ናቸዉ፡፡

ሆኖም አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች ዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመዉ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ #አጀንዳቸዉን_ከማራመድ ይልቅ የብሄር ጽንፈኛ አስተሳሰብን አንግበዉ በመነሳት፣ ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴን ከህገ ወጥና #የግጭት መንገድ ጋር እያጣቀሱ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታይቷል፡፡

እነዚህ ጽንፈኛ የፖለቲካ ሃይሎች የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ለዘመናት በአብሮነት እና #በፍቅር የኖረን ህዝብ ሊያቃቅሩ ብሎም ሊያጋጩ የሚችሉ አጀንዳዎቸን በመቅረጽ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨትና ንፁሃን ዜጎችን በእሳት በመማገድ ሀገራችን ከማትወጣበት የግጭት አዙሪት ዉስጥ በመክተት የለዉጥ እንቅስቃሴዉን ማደናቀፍ ዋነኛ አላማቸዉ አድርገዉ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሰሞኑንም በአማራ ክልል #የኦሮሞ_ብሄረሰብ አስተዳደርና በክልሉ በሰሜን #ሸዋ_ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በነዚህ ሃይሎች ቀስቃሽነት ግጭቶች መከሰታቸዉና በሰዉ ህይወት፣በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡

ኦዲፒ በግጭቱ ለጠፋዉ የሰዉ ህይወት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ዉድመት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ በግጭቱ ዉድ ህይወታቸዉን ያጡ ወገኖች ፈጣሪ ነብሳቸዉን በገነት እንዲያኖር እየተመኘ ለተጎጂ ቤተሰቦችም #መፅናናትን ይመኛል፡፡ የጥፋት ድርጊቱንም አጥብቆ #ያወግዛል፡፡

በህዝብ ደም የሚነግዱ የፖለቲካ ቁማርተኞች የተፈፀመዉ ጥፋት በየትኛዉም መልኩ ተቀባይነት የሌለዉና ማንኛዉንም ህዝብ የማይወክል መሆኑን አዲፒ ይገነዘባል፡፡ የግጭቱን ጠንሳሾች እና ተሳታፊዎች ለህግ ለማቅረብ በህግ አስከባሪ አካላት የሚደረገዉን የህግ የበላይነት የማስከበር እንቅስቃሴ እንዲሳካ ፓርቲያችን ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደርጋል።

ፓርያችን ኦዲፒ የተፈጠረዉን ችግር ለማረጋጋት እና ተመሳሳይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና ከአማራ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በእኩይ የጥፋት ድርጊት የሰከሩ ሀይሎች ሰሞኑን የለኮሱት የጥፋት እሳት የህዝብ ለህዝብ ግጭት በማስመሰልና ችግሩ በኦሮሚያ ክልል እንዲስፋፋ በማድረግ ለዘመናት በወንድማማችነትና በመተሳሰብ በሰላም አብረዉ እየኖሩ ያሉ የኦሮሞና የአማራ ወንድማማች ህዝቦችን በግጭት እሳት በመማገድ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ታዉቋል፡፡

በሰላም አብሮ የሚኖሩትን ወንድማማች ህዝቦች ለማጋጨት የሚደረግ ማንኛዉም ሙከራና ድርጊት ህዝቦች ለዘመናት ባካበቱት የአብሮነት ዕሴት እና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሴራዉን ለማክሸፍ ኦዲፒ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንክሮ ይሰራል፡፡

በዚህ አጋጣሚም የኦሮሞ ህዝብ በተለመደዉ የአቃፊነት ባህሉ ወንድም ከሆነዉ የአማራ ህዝብ እና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለዉን አብሮነት በማጠናከር፣ በክልሉ በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚደረጉ የጥፋት ሀይሎቸን ሴራ ለማጋለጥ እና ለማክሸፍ እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ኦሮሚያ የሁሉም ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቤት እንደሆነች ኦዲፒ በጽኑ ያምናል፡፡ በክልላችን የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች አሁን የደረሰንበት የለዉጥ ምዕራፍ ላይ እንድንደርስ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አንድ ሆነዉ ከመሪዉ ፓርቲ ኦዲፒ ጎን ተሰልፈዉ ታግለዋል፡፡ ዉድ መስዋዕትነትም ከፍለዋል፡፡ ፓርቲያችን ኦዲፒ ለዚህም ታላቅ አክብሮት እንዳለዉ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

በክልላችን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሰላም፣ በእኩልነት፣ በወንድማማችነት እና በነጻነት እንዲኖሩ ችግሮች ሲከሰቱም ከአሁን ቀደም እየፈታናቸዉ በመጣንበት መንገድ እየተወያየን መፍትሄ እየሰጠን ለመሄድ ዝግጁ መሆናችንና ለጽንፈኛ እና ለከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች የሚከፈት በር እንደማይኖር፤ ለዚህም ፓርቲያችን መላዉን የክልሉን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ከማንኛዉም ጊዜ በበለጠ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

ፓርቲያችን ኦዲፒ የህዝቦች ወንድማማችነት፣ የኢትዮጵያን አንድነት እና የለዉጡን እንቅስቃሴ ለመገዳደር የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎችን ከመላዉ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከለዉጥ ኃይሎች ጋር በመተባበር በጽናት የሚታገላቸዉ መሆኑን ደግመን እናረጋግጣለን!

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ
ሚያዚያ 01፣ 2011
@YeneTube @FikerAssefa