⬆️⬆️የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ በአስተዳደሩ ስር የሚገኘውን የአንበሳ ከተማ አውቶብስ በአገልገሎት አሰጣጥ ለመጎብኘት በተሳፈሩበት ወቅት በባሱ ለነበሩ ሰዎች #አዲስ አመትን አስመልክቶ #የአንድ ዓመት የባስ ትኬት #ስጦታ አበረከቱ።
ምክትል ከንቲባው በቅርቡ በቅርቡ ከፌዴራል መንግስት ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዘዋወረውን አንበሳ የከተማ አውቶብስ ትራንስፓርት አገልግሎት አሰጣጥን ከተሳፋሪዎች ጋር አብረው በመጓዝ ተመልክተዋል።
በዚህ ወቅትም በበሳ እየተጓዙ ለነበሩ ተሳፋሪዎች ለአንድ ዓመት የሚያገለግል የባስ ትኬት በስጦታ አበርክተዋል።
እንዲሁም በአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ጉድለቶችን ለማሻሻልም አስተዳደሩ እንደሚሰራ አገልግሎቱን በጎበኙበት ወቅት አስታወቀዋል።
©fbc
@yenetube @mycase27

#ቴዲ አፍሮ ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ሰዎች #የአንድ_ሚሊዮን_ብር እርዳታ ሰጠ⤵️
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰዎች ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አደረገ፡፡
‹‹እርስ በርሳችን ተዋደንና ተፋቅረን መኖር ሲገባን በአገራችን እንዲህ ዓይነት ድርጊት መፈጸሙ ሊኮነን ይገባል፤›› ሲል ለሪፖርተር የተናገረው ቴዲ አፍሮ፣ ‹‹ባላሰቡትና ባልገመቱት ሁኔታ በተፈጸመ ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡት ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም ያጽናልን፣ እንዲህ ዓይነት ነገር ድጋሚ እንዳይከሰት ለፍቅር ተግተን መሥራት ይገባናል፤›› በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
©ሪፓርተር-ታምሩ ፀጋዬ
@YeneTube @Fikerassefa

በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ #የአንድ ሰው ህይዎት አለፈ
አደጋው ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ከ30 አካባቢ መድረሱን፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር #ማርቆስ ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
በወቅቱ ከፒያሳ ወደ ለገሃር ይጓዝ የነበረ ሚኒ ባስ ታክሲ ቼርችል ጎዳና ባንኮ ዲሮማ ትራፊክ መብራት ሲደርስ ከ ቪ8 መኪና ጋር ተጋጭቶ አደጋው መድረሱንም ነው የተናገሩት።
እስካሁንም በአደጋው የአንድ ሰው ህይዎት ሲያልፍ፥ በ10 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መደረሱን ኢንስፔክተር #ማርቆስ ገልጸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ #ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ኢንስፔክተር ማርቆስ ተናግረዋል።

Update #በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 09 ፖሊስ መሬትና መጋላ ጨብጡ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ትናንት እና ዛሬ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ #የአንድ ሰው ህይዎት ያለፈ ሲሆን በመኖሪያ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል።
♦️የድሬዳዋ ፖሊስ ግጭቱ እንዳይስፋፋ ከፌድራል ፖሊስና ከመከላከያ ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ግጭቱ የተፈጠረበት የከተማው ክፍል ወደ መረጋጋት መመለሱን አስታውቋል።
ምንጭ:- Ethiopian Live Update
@YeneTube @Fikerassefa
♦️የድሬዳዋ ፖሊስ ግጭቱ እንዳይስፋፋ ከፌድራል ፖሊስና ከመከላከያ ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ግጭቱ የተፈጠረበት የከተማው ክፍል ወደ መረጋጋት መመለሱን አስታውቋል።
ምንጭ:- Ethiopian Live Update
@YeneTube @Fikerassefa
እስራኤል ውስጥ የሚኖር አንድ #ኤርትራዊ ስደተኛ #የአንድ_ሚሊዮን ሸክል ወይም የ278 ሺህ ዶላር ሎተሪ ወጣለት።
እድለኛው ብዙ ካርዶች ገዝቶ ለሰዓታት ሲፍቅ ከቆየ በኋላ አሸናፊውን ቁጥር ማግኘቱን ሎተሪው የተገዛበት ደቡብ ቴላቪቭ የሚገኘው ኪዮስክ ባለቤት ቻናል 12 ለተባለ ጣቢያ ተናግረዋል። ሎተሪው እንደወጣለት ሲታወቅ እሱም ሆነ በኪዮስኩ ውስጥ የነበሩት ለጊዜው መደንገጣቸውን የተናገሩት የክዮስኩ ባለቤት ስደተኛው ስንት ካርዶችን እንደገዛ ግን አልገለጹም።
ስደተኛው ቁጥራቸው ያልተገለፀ ካርዶችን ገዝቶ እድሉን ሲሞክር አጠገቡ የነበረው ጓደኛው በቃህ ቢለውም ካርዶቹን መፋቅ መቀጠሉንም ተናግረዋል። የጀርመን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው በክዮስኩ ውስጥ የተቀረጸ ቪድዮ እድለኛው ኤርትራዊ በክዮስኩ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች በደስታ ሲያቅፍ እና ሲጨብጥ ያሳያል።
ምንጭ:- Dw
@YeneTube @FikerAssefa