#ቴዲ አፍሮ ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ሰዎች #የአንድ_ሚሊዮን_ብር እርዳታ ሰጠ⤵️
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰዎች ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አደረገ፡፡
‹‹እርስ በርሳችን ተዋደንና ተፋቅረን መኖር ሲገባን በአገራችን እንዲህ ዓይነት ድርጊት መፈጸሙ ሊኮነን ይገባል፤›› ሲል ለሪፖርተር የተናገረው ቴዲ አፍሮ፣ ‹‹ባላሰቡትና ባልገመቱት ሁኔታ በተፈጸመ ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡት ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም ያጽናልን፣ እንዲህ ዓይነት ነገር ድጋሚ እንዳይከሰት ለፍቅር ተግተን መሥራት ይገባናል፤›› በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
©ሪፓርተር-ታምሩ ፀጋዬ
@YeneTube @Fikerassefa

እስራኤል ውስጥ የሚኖር አንድ #ኤርትራዊ ስደተኛ #የአንድ_ሚሊዮን ሸክል ወይም የ278 ሺህ ዶላር ሎተሪ ወጣለት።
እድለኛው ብዙ ካርዶች ገዝቶ ለሰዓታት ሲፍቅ ከቆየ በኋላ አሸናፊውን ቁጥር ማግኘቱን ሎተሪው የተገዛበት ደቡብ ቴላቪቭ የሚገኘው ኪዮስክ ባለቤት ቻናል 12 ለተባለ ጣቢያ ተናግረዋል። ሎተሪው እንደወጣለት ሲታወቅ እሱም ሆነ በኪዮስኩ ውስጥ የነበሩት ለጊዜው መደንገጣቸውን የተናገሩት የክዮስኩ ባለቤት ስደተኛው ስንት ካርዶችን እንደገዛ ግን አልገለጹም።
ስደተኛው ቁጥራቸው ያልተገለፀ ካርዶችን ገዝቶ እድሉን ሲሞክር አጠገቡ የነበረው ጓደኛው በቃህ ቢለውም ካርዶቹን መፋቅ መቀጠሉንም ተናግረዋል። የጀርመን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው በክዮስኩ ውስጥ የተቀረጸ ቪድዮ እድለኛው ኤርትራዊ በክዮስኩ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች በደስታ ሲያቅፍ እና ሲጨብጥ ያሳያል።
ምንጭ:- Dw
@YeneTube @FikerAssefa