YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ነገ ወደ ፈረንሳይ #ያቀናሉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአውሮፓ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉበኝት ነገ #ይጀምራሉ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን በፈረንሳይ የሚጀምሩ ሲሆን፥ በነገው እለትም ወደ #ፈረንሳይ እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

በፈረንሳይ በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በመቀጠልም ወደ #ጀርመን የሚያቀኑ ሲሆን፥ በዚያም ከመራሂተ መንግስት #አንጌላ ሜርክል ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በጀርመን ቆይታቸውም ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ከሚውጣጡ 25 ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍራንክፈርት ይወያያሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝት “#አንድ_ሆነን_እንነሳ_ነገን_በጋራ_እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑም ተነግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያደርጉት #በሀገራቱ መሪዎች በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው።
ምንጭ ፦ኤፍ.ቢ.ሲ
@yenetube @mycase27
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት #ጀርመን በርሊን ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በርሊን ሲደርሱም የሀገሪቱ ባለስልጣናት እና በበርሊን የሚኖሩ #ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውላቸዋል
@yenetube @mycase27