YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (#ኦብነግ) ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ስለተደረሰው #ስምምነት የሰጠው አስተያየት የስምምነቱን መንፈስ የሚያንፀባርቅ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መንግስት #አስታወቀ

ድርድሩን በቅርበት የሚያውቁና ስማቸውን ይፋዊ መግለጫ እስኪሰጥ የሸሸጉ የመንግስት ተወካይ #ለዋዜማ እንደተናገሩት ስምምነቱ ኦብነግ ወደሰላማዊ ትግል እንዲመለስና ጥያቄዎቹን በጋራ በሚቋቋም ኮሚቴ እያቀረበ እንዲፈታ ከሚል ውጪ ትርጉም ያለው አልነበረም።

በኦብነግ በኩል የሚሰጠው አስተያየት ለፕሮፓጋንዳ #ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር የውይይቱን መንፈስ አያሳይም ብለዋል ባለስልጣኑ።

ኦብነግ መንግስት የእስከ መገንጠል መብታችንን በህዝበ ውሳኔ እንድናረጋግጥ ተስማምቷል ሲል ለቢቢሲ መግለጫ ሰጥቶ #ነበረ

ቢቢሲ ዘግይቶ ባወጣው #ማረሚያ " ቀደም ሲል በወጣው ዘገባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ጋር ካደረገው ተከታታይ ውይይት በኋላ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ተስማምቷል ተብሎ የተፃፈው #ስህተት ነው" ብሏል::
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27