YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለህብረተሰቡ መልዕክት ለማስተላለፍ በአዲስ አበባ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማሳወቁ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የሃይማኖት ተቋማቱ ምዕመናን በሽታውን ከመከላከል አንጻር ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ተቋሙ በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው ጉዳዮች በመግለጫው ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ምዕመናን በጤና ሚኒስቴር የሚሰጡ መመሪያዎችን እንዲተገብሩ ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡

በቀሪው የዐቢይ ፆም ጊዜያት በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት የምህላ ጸሎት እንዲደረግም ማወጃቸው የሚታወስ ነው።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በትናንትናው ዕለት በስሜን ብሔራዊ የተከሰተ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ። በተመሳሳይ በፓርኩ መጋቢት 6/12 ተመሳሳይ አደጋ ተከስቶ ነበር።
@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር ዜና - እንቅስቃሴዎች ታግደዋል!!

ኢትዮጵያ ትምህርት እና ስፓርታዊ እንቅስቃሴ አግዳለች!!

Ethiopia suspend schools, Sporting Events.
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
ሰበር ዜና - እንቅስቃሴዎች ታግደዋል!! ኢትዮጵያ ትምህርት እና ስፓርታዊ እንቅስቃሴ አግዳለች!! Ethiopia suspend schools, Sporting Events. @Yenetube @Fikerassefa
ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት እንደሚዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

@Yenetube @Fikerassefa
#EPL

የኢትዮጵያ ፕ/ሊግ 18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች እና ሌሎች በአገሪቱ የሚደረጉ የሊግ ጨዋታዎች ለቀጣይ 15 ቀናት በኮሮና ቫይረስ ስጋት ይቋረጣሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
ዩንቨርስቲ_አልተዘጋም

ከዩንቨርስቲዎች ውጪ ስፓርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ትምህርት ቤቱች ለ 15 ቀን ይዘጋሉ።

@Yenetube @FikerAssefa
በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 5 ደርሷል።

- ዩንቨርስቲዎች አልተዘጉም

- ፕሪምየር ሊጊ ለ15 ቀን ተቋርጧል

- ስብሰባዎች ተከልክለዋል

- የዩንቨርስቲዎች በያሉበት ካንፓስ እንዲቆዩ በማደሪያቸው ሆነው የሚማሩበት መንገድ ይመቻቻል።

- የሀይማኖት ተቋማት እንቅስቃሴዎችን ቢቀንሱ

- የፅዳት ዘመቻ መጀመር ቫይረሱን ለመከላከል ዋነኛ መንገድ ነው

@Yenetube @Fikerassefa
የተያዙ ሰዎች የጤናቸው ሁኔታ - #ሊያ_ታደሰ

- በቫይረሱ የተጠቁ ግለሰቦች ጤናቸው ደና ነው የጉንፋን ምልክት ብቻ ነው የሚታይባቸው።

-ዛሬ በቫይረሱ የተያዘ ግለሰብ #ከዱባይ ነው የመጣው ኢትዮጵያ የገባው ማርች 12 እንዲሁም ማርች 13 ላይ ምልክት አሳይቷል ክትትል ተደርጎበት ቫይረሱ እንዳለበት ታውቋል።

- ከአምቡላንስ ያመለጠው ግለሰብ ናሙና የተወሰደ ለሊት ነው ውጤቱ ገና አልተገለፀም።

#ዶርሊያታደሰ #ጤናሚንስትር
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሳሙና፣ አልኮል እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያዎች "በስፋት እንደሚሰራጩ" ጠ/ሚ አብይ አህመድ ገልጰዋል።

የንጽህና መጠበቂያዎቹ ሰዎች በቀላሉ እንዲያገኟቸው በተለያዩ አካባቢዎች እንዲቀመጡ ይደረጋል ብለዋል

- (ፋና)
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እኔና የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት በአንድነት በዓለም ጤና ድርጅት እና በ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም የኮቪድ-19 ቫይረስን ለመከላከል የቀረበውን የ#ጤናማ እጆች ጥሪ ተቀብለናል"

--- ጠ/ሚር አብይ አህመድ-----

@Yenetube @Fikerassefa
የሚ/ር መ/ቤታችን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

ተላላፊነቱን ለመቀነስ ሰራተኞች መግቢያና መውጫ በር ላይ በተዘጋጀው የእጅ መታጠቢያ በመጠቀም በሳሙና የመታጠብ ባህልን ሊያጎለብቱ ይገባል።

በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ ተመሳሳይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን።

- ትራንስፖርት ሚንስትር - ዳግማዊት ሞገዝ
@Yenetube @Fikerassefa
ወለጋ ❗️

እውነት ነው አሁን ነው ትክክለኛው ሰአት ነው ምዕራብ ኦሮምያ ኢንተርኔት መከፈት ያለበት ሰአት ነው።

የሰይፉ ፋንታውን ሳይቀር በቴሌቪዥን እኛን የሚጠብቀን እግዚአብሔር ነው በማለት ትላንት ከእንግዳው ጋር በሙሉ ልብ ተጨባብጧል።

#ይህ_ተገቢ_ተግባር_አይደለም

በምዕራብ ኦሮምያ ሰዎች ስለ ኮኖና ቫይረስ በቂ ትምህርት ለማግኘት ኢንተርኔት አስፈላጊ ነው!!

መንግስት ይህንን ጉዳይ ሊያጤንበት ይገባል።
@Yenetube @Fikerassefa
#ወለጋ_አዲስ_ነገር_የለም

በምዕራብ ኦሮሚያ ለወራት ተቋርጦ የቆየው የቴሌኮም አገልግሎት ከኮሮናቫይረስ ክስተት ጋር በተያያዘ እንዲከፈት እየቀረበ ባለው ጥያቄ ዙሪያ እስካሁን የተለየ ነገር እንደሌለ የኢትዮቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ለቢቢሲ ገለጹ።

"እንደሚታወቀው ቀደም ብሎ አገልግሎቱ የተዘጋው በዚህ ምክንያት አይደለም። ስለዚህ የተለየ የወሰድነው እርምጃ የለም፤ የተለየ ነገር ካለ እናሳውቃለችኋለን"

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ለአረጋዊያን አልኮል በነፃ እንሰጣለን
/
እንደዚህ አይነት ኢትዮጵያዊያን አሉ
/
ፋርማሲ ቤቶች ከማሪዛ ፋርማዚ ትምህርት ወሰዱ
/
እናመሰግናለን !!
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መስማት የተሳናቸው ሰዎች በአካባቢያችሁ ካሉ ይህንን ቪዲዮ አሳዩዐቸው።

መረጃው ይደርሳቸው ዘንድ እባካችሁ ይህን ቪዲዮ ሼር አድርጉላቸው።

@Yenetube @Fikerassefa
#ሶማልያ_ኮሮና_ቫይረስ

ጎሮቤት ሀገር ሱማልያ የመጀመሪያ በኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንደተገኘ በጤና ሚንስትሯ በኩል ይፋ አድርጋለች።

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቆም ጠይቋል።

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከ45000 በላይ ተማሪዎች ያሉት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከ 25% በላይ የሚሆኑት የአዲስ አበባ ልጆች ናቸው።

@YeneTube @Fikerassefa
ግብፅ አየር መንገድ አለም አቀፍ በረራ አቆመ!!

የግብፅ አየር መንግድ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ኢንተርናሽናል በረራዎችን አገደች።
ግብፅ ከ110 ሰው በላይ በኮሮና ቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች መኖራቸው ይታወቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከአንብላንስ ያመለጠው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ሆነ።

ከዚህ ቀደም አንድ ከሳውዲ አረብያ መጥቶ የኮቪድ-19 ምልክቶች አሳይቶ ወደ ለይቶ ማቆያ ሊወሰድ ሲል አምልጦ ደቡብ ወሎ ውስጥ መያዙን መግለጻችን ይታወሳል፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ግለሰቡ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ በላቦራቶሪ ምርመራ ተረጋግጧል፡፡

#EPHI
@YeneTube @Fikerassefa
ኤርትራ ዜግቿን እንቅስቃሴያቸውን እንዲገድብ አሳስባለች!!

ምንም እንኳ ኮሮናቫይረስ በኤርትራ ሪፖርት ባይደረግም፤ የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚንስቴር የበሽታውን ስርጭት ቀድሞ ለመከላከል በማሰብ ዜጎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የኤርትራ ዜጋም ሆነ ነዋሪ፤ አስቸኳይ ካልሆነ በቀር በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ከሚደረጉ ጉዞዎች እንዲቆጠቡ ጤና ጥበቃ ሚንስቴሩ አሳስቧል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ ሰዎች ከሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች ዜጎች እራሳቸውን እንዲያርቁ ምክር አዘል ማሳሰቢያዎች ተላልፈዋል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
👍1