YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኮሮናቫይረስ በተከሰተበትና በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት የምድራችንን የጤና ጉዳዮች በበላይነት የሚከታተለውና የሚመራው የዓለም ጤና ድርጅት መሪ መሆን ከባድ ኃላፊነት ነው።

ኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ከፊት ሆነው በሚመሩበት በዚህ ወቅት በሽታውን ለመግታትና ክትባትም ሆነ ፈዋሽ ህክምና እንዲገኝ ለማድረግ በየዘርፉ እየጣሩ ነው።

https://bbc.in/2TjX5VQ
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በተለያዩ አካባቢዎች ለመደራጀት የሚያደርጋቸው ጥረቶች "በብልጽግና ፓርቲ ካድሬዎች" እየተደናቀፉብኝ ነው ሲል ቅሬ አሰማ። ፓርቲው በመተማ እና በቢቸና ከተሞች አደራጆቹ መታሰራቸውንም ገልጿል።

አዴኃን ለውጡን ተከትሎ ከኤርትራ ከተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

#ElU
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ተራማጅ ፓርቲ (Ethiopian Progressive Party) በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች እንቅፋት እየገጠመው መሆኑን የፓርቲው መሪዎች ተናገሩ።

መሪዎቹ እንደሚሉት በአምቦ ከተማ 538 አባላቶቹ የፈረሙበት ሰነድ የፌድራል ፖሊስ ልብስ በለበሱ ሰዎች የተነጠቀ ሲሆን፣ በቡታጅራ ከተማ ደግሞ የ69 ሰዎች ፊርማ የያዘና የምርጫ ቦርድ ማህተም ያረፈበት ሰነድ በአንድ የከተማው ባለስልጣን ተወስዶበታል።

በአዳማ ከተማም ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፣ ፓርቲው ጉዳዩን በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርቧል።

Via:- #Elu
@YeneTube @Fikerassefa
በኢኦተ ቤተክርስቲያን ዼጥሮሳውያን የቤተክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ያቀረበለትን የቃለመጠይቅ ግብዣ ውድቅ አደረገ።
Via:- #Elu
@Yenetube @Fikerassefa
የተሰረቁ 4 መኪናዎችንና 8 ሞተር ሳይክሎችን ከ27 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦላይን ይሰጣል " ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር።

በአርትስ ቴሌቪዥን ላይ ተመልክተናል ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚመለከተውን አካል እግኝተን ነገ የተደራጀ መረጃ የምናቀር ይሆናል።
Via:- Arts TV
@YeneTube @FikerAssefa
በትናንትናው ዕለት በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ጠብ አንድ ተማሪ መገደሉን ወሎ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው እንዳለው ለተማሪው መገደል ምክንያት የሆነው ሌላ ተማሪ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

#Eshete Bekele
@Yenetube @Fikerassefa
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 71 በመቶ ደረሰ

በመንግሥት እና በሕዝብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 71 በመቶ ላይ መድረሱን የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ግድቡ መጠናቀቅ ከነበረበት በአራት ዓመታት በመዘግየቱ እና ተጨማሪ የገንዘብ ኪሳራ በማስከተሉ ምክንያት የሕዝቡ ተሳትፎ መቀዛቀዝ መታየቱንም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ግድቡን ለማጠናቀቅ የሕዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ለ3ኛ ጊዜ የ8100 የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንጭ:- ETV
@YeneTube @Fikerassefa
ትውልደ ኬኒያዊቷ አትሌት ሩዝ ጃቤት ለአራት ዓመታት ታገደች

በትውልድ ኬንያ ባህሬናዊቷ አትሌት ሩዝ ጃቤት የአበረታች መድኃኒት መጠቀሟ በመረጋገጡ ለአራት ዓመታት ከስፖርቱ ታገደች፡፡

አትሌቷ ትላንት በአለም አትሌቲክሰ ኢንቴግሪቲ የኒት የአራት ዓመታት እገዳ የተላለፋባት አር ኢ.ፒ.ኦ የተባለ አበረታቸ መድሃኒት መጠቀሟን በማረጋገጡ ነው፡፡

በ2016 የሪዮ ኦሎምክ በ3ሺ ሜትር መሰናክል ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፈችው የ23 ዓመቷ ባህሬናዊቷ አትሌት ቅጣቱ እ.ኤ.አ ከታህሳስ 01/2017 ጀምሮ ለዓራት ዓመታት የሚፀና ይሆናል ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡

Via:- ETV
@YeneTube @Fikerassefa
ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሀላፊም ሆነው ሰርተዋል።ከመቀሌ ዮንቨርስቲ በህክምና ትምህርት ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከጣልያኑ ፓርማ ዩንቨርስቲ በአለም አቀፍ ጤና ላይ ያተኮረ ትምህርት ተከታትለው ከስምንት አመት በፊት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
ለኢትዮጵያ ክብር ብዙዎች ዋጋ ከፍለዋል ። ይህን በፍጹም አንረሳውም ። ካራማራ ላይ ከጠላት ጋር ተናንቀው ህይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር የሰጡ ጀግኖቻችንን እንዘክራለን።

ክብር ለጀግኖቹ !
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት እንደተሾመለት ዋዜማ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አዲሱ ፕሬዝዳንት አቢ ሳኖ ትናንት የሹመት ደብዳቤ የደረሳቸው ሲሆን ዛሬ ስራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

Via:- Wazema Radio
@YeneTube @Fikerassefa
የኦጋዴን ጦርነት፡ የሲያድ ባሬ ወረራ ሲታወስ

የኦጋዴን ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የተደረገው ጦርነት የዛሬ 42 ዓመት የካቲት 26/1970 ዓ.ም. ነበር የተጠናቀቀው።

በ1966 ዓ.ም ሶማሊያ የአረብ ሊግን ተቀላቀለች። በወቅቱ የሶማሊያ መሪ የነበረው ሜጀር ጄኔራል ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ። ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን የሲያድ ባሬ [ዚያድ ባሬ] ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከዩናይትስ ስቴትስ ጋር ወዳጅነት አለው። በወቅቱ በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ የነበሩት ሶቪዬት ኅብረትና አሜሪካ ምሥራቅ አፍሪካ ገቡ።

https://www.bbc.com/amharic/amp/news-51749412?__twitter_impression=true
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ከዓለም የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፕሬዝዳንት አንድሪው ሱሊቫን ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

ከውይይቱ ጎን ለጎን ከዓለም አቀፍ ኢንተርኔት ሶሳይቲ በመጡ የቴክኒካል ባለሙያዎች ለኢመደኤ ሠራተኞች በዓለም አቀፍ በይነ-መረብ እና ደህንነት ዙሪያ ግንዛቤ ሊያዝባቸውና ጥንቃቄ ሊደረግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡
Via:- Elu
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከተማም 33 ማዕከላት በኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ሲስተም የተገናኙ ሲሆን፤ ማንኛውም ደንበኛ የቅድመና የድህረ ክፍያ አገልግሎቶች በየትኛውም ማዕከል ማግኘት ይችላል፡፡

Via:- EEU
@YeneTube @Fikerassefa
ከዚያድ ባሬ መራሹ የሶማሊያ ወራሪ ኃይል ጋር በነበረን ተጋድሎ ወሳኝ ድል ላስመዘገብንበት የካራማራ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ።

የ1967ቱ የሶማሊያ ወረራ ሀገራችን ከአብዮት ፍንዳታው ጭጋግ ባልወጣችበትና የእርስ በርስ ግጭት ላይ በነበረችበት ጊዜ የተከሠተ ነው። ኢትዮጵያን የወረሩ አብዛኞቹ ኃይሎች እንደሚሠሩት ስሕተት ዚያድ ባሬም ተሳሳተ። ሀገር የደከመች መስሎት ኢትዮጵያን የማሸነፊያ ጊዜ የደረሰለት መሰለው። በዚህ የተሳሳተ ስሌት ተመርቶ ወረራውን ፈጸመ። በመጀመሪያ አካባቢ እንዳሰበውም የጎላ መከላከል ሳይገጥመው ሰፊ የሀገራችንን መሬት ማካለል ችሎ ነበር።

ነገር ግን ኢትዮጵያውያን እንደፍግ ተኝተው እንደ እቶን በተነሡ ጊዜ ምን እንደሚያደርጉ በዚህ ወረራ ጊዜ ታየ። በአጭር ጊዜ “የእናት ሀገር ጥሪ” የተሰባሰቡ፣ በቂ የሥልጠናም ሆነ የዝግጅት ሁኔታ ያልነበራቸው፣ ነገር ግን ከየትም የማይበደሩት የሀገር ፍቅርና የማሸነፍ ወኔ ያላቸው ውድ ኢትዮጵያውያን ወረራውን በስኬት መቀልበስ ቻሉ።
መንግሥታትን በሀገር ውስጥ ክዋኔያቸው በአንድም በሌላም ልንመዝናቸው እንችላለን። ነገር ግን የሀገርን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር ለማስጠበቅ የሚከፈሉ መሥዋዕትነቶች በየትኛውም ዘመን ቢፈጸሙ የሀገራችን ታሪካዊ ኩራት ናቸው።

የደርግ መንግሥትም በአጭር ጊዜ ጥሪ አቅርቦ፣ አሠልጥኖና አደረራጅቶ የሀገርን ክብር ለማስመለስ ያደረገው ተጋድሎና ያስመዘገው ድል የሁላችንም የኢትዮጵያውያን የአልበገር ባይነትና ለሀገር የመሥዋዕትነት የመክፈል ታሪካችን አካል ነው።

ሁሌም በውስጣችን ክፍተት ሲኖር የውጭ ጠላት እንጋብዛለን፤ ስንጠናከር ግን የታፈርንና የተከበርን እንሆናለን። በዚህ አጋጣሚ ከኢትዮጵያውያን ጎን ተሠልፈው የተዋጉትንና ውድ ሕይወታቸውን የሠዉትን የኩባ እና የየመን ወታደሮችን ውለታ ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል።

ክብር ሀገርን ለማቆየት ራሳቸውን መሥዋዕት ላደረጉ ኢትዮጵያውያን!
@YeneTube @Fikerassefa
ሱዳን ቅሬታዋን አቀረበች 👌

የአረብ ሊግ ምክር ቤት በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከግብፅ ጎን እንደሚቆም ለመግለፅ በተዘጋጀ የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ሱዳን ቅሬታ እንዳላት መግለጿን የመካከለኛው ምሥራቅ የዜና ወኪል ዘገበ።

ሱዳን የአረብ ሊግ በውዝግቡ ጣልቃ ሊገባ አይገባም የሚል አቋም አላት።

በ153ኛው የአረብ ሊግ ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ማሻሻያ የጸደቀው የውሳኔ ሐሳብ «ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ያላት ታሪካዊ መብት ሊሸራረፍ አይገባም» የሚል ነው ተብሏል። ሜና እንደዘገበው የውሳኔ ሐሳቡ ሲጸድቅ ሱዳን በይፋ ቅሬታዋን ገልጻለች

#ሚና #እሸትበቀለ
@Yenetube @Fikerassefa