YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ፀጋዬን ጨምሮ ሚንስትርና ዴኤታዎች ለአምባሳደርነት ሹመት ከኃላፊነታው ተነሱ፡፡

የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት ከሾሟቸው መካከልየፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚንስትሯ የዓለም ፀጋይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታዎቹ ሂሩት ዘመነ እና ማርቆስ ተክሌ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸው ይገኙበታል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ባጫ ጊኒ እንዲሁም ይበልጣል አዕምሮ፣ ምህረተአብ ሙሉጌታ እና ተፈሪ መለስም በሙሉ አምባሳደርነት ማዕረግ ሲሾሙ ሌሎች 6 ሰዎች በአምባሳደርነት ማዕረግ ተሹመዋል፡፡

በአምባሳደርነት ሹመታቸው ከመንግሥት አስፈፃሚነት የተነሱት ተሿሚዎች የተመደቡባቸው አገራት አልተገለጹም፡፡

ምርጫ:- አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @Fikerassefa
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ ሀገራት ለሚያገለግሉ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሰረትም ፦

1. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
2. ወይዘሮ የአለም ፀጋይ
3. ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ
4. አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ
5. አቶ ባጫ ጊና
6. አቶ ይበልጣል አዕምሮ
7. አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ
8. አቶ ነብያት ጌታቸው እና
9. አቶ ተፈሪ መለስ በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት
እንዲሁም
1. አቶ አድጐ አምሳያ
2. አቶ ጀማል በከር
3. አቶ አብዱ ያሲን
4. አቶ ለገሠ ገረመው
5. ወይዘሮ እየሩሳሌም አምደማርያም እና
6. አቶ ሽብሩ ማሞ ደግሞ በአምባሳደርነት ማዕረግ ተሾመዋል።

ምንጭ:- ፋና
@YeneTube @Fikerassefa
ለረጀም ዓመታት በባለቤትነት እሰጥ አገባ ውስጥ መቆየቷ ለአጠቃላይ ዕድገቷ መሰናክል ሆኗል በምትባለው ድሬደዋ ሰሞኑን የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ግንባር / ኦነግ/ አዲስ አበባ (ፊንፊኔ) እና ድሬደዋ የኦሮሚያ አካል በመሆናቸው የፌደራል መንግስቱ እንደ ፌደራል ቋንቋው ሁሉ ውሳኔ ሊሰጥ ይገባል ማለቱን ህብረት ለዴሞክራሲ እና ነፃነት ፓርቲ አውግዞታል፡፡

የሶማሌ ክልላዊ ፓርቲ ሆኖ በመደራጀት ላይ የሚገኘው ህብረት ለዴሞክራሲ እና ነፃነት ፓርቲ ቃል አቀባይ አቶ አደን አላሊ ለሚዲያ እንደተናገሩት ፓርቲያቸው ሰሞኑን የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ግንባር / ኦነግ አዲስ አበባ /ፉንፊኔ እና ድሬደዋ የኦሮሚያ አካል ናቸው በሚል የፌደራለ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥ ያወጣውን መግለጫ ተገቢ አይደለም ሲል ውግዞታል ፡፡

እንዲህ ያለውን ተገቢ ያልሆነ ጥያቄ ያመጣው የቀደመው መንግስት ራሱ የአህአዴግ አካል ነው የሚሉት ቃል አቀባዩ ያመጡበት ምክንያት በሁለት አካላት ብጥብጥ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡ ከተማይቱን የመሰረተው እና የሰራው እንደዚሁም እስከዛሬ የኖረው ሶማሌ ነውያሉት አቶ አደን  ከሶማሌ ጋር አብረው የሰሩ አካለት መኖራቸውን ጠቅሰው የፓርቲው አቋም ሌሎች ነዋሪዎች መብተቸው ተጠብቆ ከተማዋ ወደ ሶማሌ ክልል እንድትገባ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡"አሁን እየሆነ ያለው ነገር አዲስ ነገር" ነው ያሉት አቶ አደን ይህን መሰሉን ነገር ያመጣው ኦነግ ነው ብለዋል ፡፡

በጉልበት ድሬደዋን እና መሬት እንወስዳለን ማለት አይሆንም ብለዋል  ፡፡የቀደመ የዘመናዊ ከተማ ተመስሌትነት የነበራት ድሬደዋ ዛሬ ላለችበት ተጎታች ዕድገት መንስዔው ዛሬም ድረስ በፌደራል መንግስቱ መፍትዔ ያላገኘው የይገባኛል ጥያቄ ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡

በቀድሞው ኢህአዴግ /ሶዴፓ ጣምራ በተዋቀረ ምክር ቤት እና አስፈፃሚ አካል በምትተዳደረው ድሬደዋ 40፡40፡20 በሚል የተቀመረው የስልጣን ክፍፍል ቀመር ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል፡፡

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
በጎንደር ታስረው የሚገኙ 13 ካናዳዊያን ዛሬ ለፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚጠይቁ ግሎብ ኤንድ ሜል ዘግቧል፡፡

ታሳሪዎቹ ዐርብ’ለት የ14 ቀናት ቀጥሮ ተሰጥቶባቸዋው ነበር፡፡ ካናዳ ሂውማኒተሪያን ለተሰኘው ረድዔት ድርጅት የሕክምና ባለሙያዎች የታሰሩት ያለ ፍቃድ የሕክምና ሥራ ሰርተዋል፤ ጊዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶችንም ያላግባብ አስወግደዋል ተብለው ነው፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
በደቡባዊ ሱማሊያ የመንግሥት ወታደሮች ከጁባላንድ ራስ ገዝ ታጣቂዎች ጋር ሰሞኑን ተኩስ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

የራስ ገዟ ኢንፎርሜሽን ሚንስትር የኢትዮጵያ ወታደሮች የመንግሥትን ወታደሮች እንዳገዙ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ ግጭቱ ኢትዮጵያን እና የጁባላንድ አጋር የሆነችውን ኬንያን ጎራ ወደለየ ቅራኔ እንዳያስገባቸው ተሰግቷል፡፡

Via:- ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
Who controls the River Nile?
BBC World Service
48 ሜጋባይት ዋይፋይ ብትጠቀሙ ይመረጣል።

Who control the River Nile? የቢቢሲን ዘገባ እንድታደምጡት ጋብዞኖታል።
@Yenetube @Fikerassefa
ትረምፕ በህዳሴ ግድብ ዙርያ ከአል ሲሲ ጋር በስልክ አወሩ። “በኢትዮጵያ ቅር ተሰኝቻለው” ስቴፈን ሙኒችን

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ባለፈው ሳምንት አርብ እና ቅዳሜ በነበረው ውይይት ላይ አለመገኘቷን ተከትሎ አየተካረረ የመጣው የአባይ ጉዳይ ያሳሰባቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 24 ወደ ካይሮ ስልክ ደውለው የግብፁን ፓሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ጋር በስልክ ያወሩ ሲሆን ጉዳዩን በዲፕሎማሳዊ መንገድ ለመፍታትና ሱዳን ፣ግብፅና ኢትዮጵያን ለማስማማት አሜሪካ የምትችለውን ጥረት ታረጋለች ማለታቸውን ሪውተርስ ዘግቧል።

አል ሲሲም ” ግብፅን ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የሚከፈለውን መስውአት ትከፍላለች ” ሲሉ ለፕሬዝዳንት ትረምፕ ተናግረዋል።
የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሀላፊ ስቴፈን ሙኒችን ኢትዮጵያ በድርድሩ ላይ በላመገኘቷ ቅር ተሰኝቻለው ” ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል።
” ሶስቱን ሀገሮች ለማቀራረብ አየጣርን ነበር።

ድርድሩም ጥሩ እየተጓዘ ነበር። ኢትዮጵያ በመቅረቷ ግን ቅር ተሰኝተናል። ድርድሩ ለተዳራዳሪዎቹ ቀጠና በጣም ጠቃሚጉዳይ ነው።

ጉዳዩ የደህንነት ጉዳይ አለበት፣የውሀ ጉዳይ አለበት ።አሳሳቢም ጉዳይ ነው።” በማለት ሙኒችን ተናግረዋል።

Via:- Fidelpost
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ሁሉም ወገኖች መደመጣቸውን፣ አሜሪካም ወገንተኛ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ምን እያደረጋችሁ ነው ተብለው የተጠየቁት የአሜሪካ ግምዣ ቤት ሴክሬታሪ ስቴቨን ምኑችን ጥያቄውን በቀጥታ ሳይመልሱ ቀርተዋል።
ከግብጽ በተጨማሪ ሱዳን ከስምምነት ሳይደረስ ግድቡ በውኃ ሊሞላ አይገባም የሚል አቋም እንዳላት ምኑችን በአሜሪካ ኮንግረስ Ways and Means Committee ለተባለ ኮሚቴ ተናግረዋል። ኮሚቴው ከውጭ ግንኙነት ጋር የማይቀራረብ የመንግሥት በጀት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ነው።

የኔቫዳው የኮንግረስ አባል ስቴቨን ሖርስፎርድ ሚዛናዊ ብትሆኑ ኢትዮጵያ ወደ ድርድሩ ልትመለስ ትችላለች ብዬ አስባለሁ ሲሉ ለምኑችን ነግረዋቸዋል።

via:- Eshet Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
አምነስቲ አብዲሳ ረጋሳ ፖሊስ ያሉበትን እንዲያሳውቅ ጠየቀ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስምንት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር የተፈቱ ሲሆን የቀድመው የኦነግ የቀድሞ ጦር አዛዥ የነበሩት እና በአሁን ወቅት የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አብዲ ረጋሳ ፖሊስ ያሉበትን እንዲያሰውቅ ጠየቀ።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
የዓለም ባንክ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ 12 ቢሊየን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገባ

የዓለም ባንክ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ትግል ውስጥ ያሉ አዳጊ አገራትን ያግዝ ዘንድ የ12 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል።

ዓለም ባንክ ገንዘቡን የሚሰጠው በብድር፣ በእርዳታና በቴክኒክ ድጋፍ መልክ ሲሆን፣ ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የዓለም መሪዎች ኮሮና ቫይረስ ኢኮኖሚያቸውን እንዳያሽመደምድ ብርቱ ዝግጅት ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው።

ኮሮና ቫይረስ የአገራቱ ኢኮኖሚዎች ላይ የሚያስከትለው መቀዛቀዝ አገራትን ችግር ውስጥ ሊከት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ይህ የዓለም ባንክ እርዳታ አገራት የኮሮና ቫይረስን ስርጭት በመከላከል ረገድ የጤና አገልግሎት ስርዓቶቻቸውን እንዲያጠናክሩና ቫይረሱ የሚያሳድረውን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ከግል ዘርፍ ጋር እንዲሰሩ ለማስቻል ነው ተብሏል።
"ለማድረግ እየሞከርን ያለነው የቫይረሱ ስርጭት እንዲገታ ነው" ብለዋል የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ።

ዓለም ባንክ እንዳስታወቀው እርዳታውን በቅድሚያ የሚሰጠው በጣም ድሃ ለሆኑ አገራትና ለቫይረሱ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ለሆኑ አገሮች ነው።
ኮሮና ቫይረስ በ70 አገራት ላይ እንደተሰራጨ የሚታወቅ ነው።

ዓለም ባንክ ቃል የገባው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከባንኩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የሚገኝ ሲሆን አራት ቢሊየን የሚሆነው ደግሞ ቀደም ሲል ከነበሩ ፈንዶች ተዘዋውሮ የሚመጣ እንደሆነ ተገልጿል።

እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ 92 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 80 ሺህ የሚሆኑት የተመዘገቡት ቻይና ውስጥ ነው። በሌላ በኩል ሶስት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ ብዙዎቹ መሞታቸው የተመዘገበው በቻይና ነው።

በዛሬው እለት 38 ሰዎች በቻይና መሞታቸው የታወቀ ቢሆንም የቻይና መንግሥት እንቅስቃሴን የሚገቱ ጥብቅ እገዳዎችን በመጣሉ ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ አዳዲስ በኮሮና ቫይረስ የመያዝ ሪፖርቶች ቀንሰዋል እየተባለ ነው ሲል #ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Via:- BBC /Walta
@YeneTube @Fikerassefa
የግብጽ መገናኛ ብዙኃን አሁንም ዐይናቸው ኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡

የግብጽ መገናኛ ብዙኃን የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ላይ ትኩረት አድርገዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የግብጽ መገናኛ ብዙኃን ትኩረታቸውን ከግድቡ እና ከኢትዮጵያ ብዙም ባያርቁም ከሰሞኑ ደግሞ ዋነኛ አጀንዳቸው አድርገውታል፡፡ የዘገባዎቻቸው ትኩረቶች የኢትዮጵያን አቋም ከማጣጣልና ከባለሥልጣኖቻቸው የቃላት ውርወራ ማስተናገጃነት ባያልፍም በየምክንያቱ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠታቸውን ቀጥለዋል፡፡

ትናንት የካቲት 24/2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ሰፊ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም የግብጽ መገናኛ ብዙኃን አወዛጋቢ ዘገባዎችን ሠርተዋል፡፡

‹ዴይሊ ኒውስ ኢጂብት› የተሰኘው የዜና ምንጭ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ብቸኛው አማራጭ ድርድር እንደሆነ ሀገራቸው እንደምታምን የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶክተር ኢንጂነር) መናገራቸውን ዘግቧል፡፡ ይህ የዜና ምንጭ በዚሁ ዘገባው ሚኒስትሩ በድርድሩ ጉዳይ ግብጽ ያቀረበችውን ሐሳብ ከዚህ ቀደም ውድቅ ማድረጋቸውንም አስነብቧል፡፡

ትናንት የተሰጠውን መግለጫ በተመለከተ ዴይሊ ኒስው ኢጂፕት በሠራው ሌላ ዘገባ ደግሞ ግድቡን በተመለከተ አሜሪካ የያዘችውን ኢትዮጵያን የሚጎዳና ሌሎችን ብቻ የሚጠቅም ሐሳብ ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው ስለመግለጻቸው ነው ትኩረት ያደረገው፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በሉዓላዊ ግዛቷ ውስጥ በሙሉ ነጻነቷ የምትገነባው በመሆኑ ሐሳቡን እንደማትቀበለው መግለጻቸውንም ዘገባው አካትቷል፡፡

Via:- AMMA
@YeneTube @Fikerassefa
የ3ኛው ዙር የ8100 የታላቁ ህዳሴ ግድብ የስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ ተጀመረ።

#8100 #itmydam
@Yenetube @Fikerassefa
ብልፅግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች ላይ የተሰጡትን ስጦታዎች መቀማቱን አስታወቀ።

በኦሮሚያ ክልል ብልፅግናን እንደግፋለን በማለት ለስጦታ ያዋጧቸውን ሀብቶች በተለይ በሬና ግመሎችን የመቀማት ድርጊት ሲፈፅሙ የነበሩ የአንዳንድ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንደነበሩ ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አወሉ አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ላለፉት 3 ሳምንታት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች ላይ ድንጋይ በመወርወር ፤ መንገድ በመዝጋት እንዲሁም ለፓርቲው የቀረቡ ስጦታዎችን በመቀማት ችግር የፈጠሩ አካላት እንደነበሩ አንስተዋል፡፡

በዋናነት በአወዳይ ፤ ደደር ፤ ባሌ መደ ወላቡና ሀረርጌ አካባቢዎች እነዚህ ችግሮች በስፋት የተስተዋሉባቸው ናቸው ብለዋል አቶ አወሉ።

እነዚህን ሲያደርጉ ከነበሩት የተወሰኑትን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በአብዛኛው ጀማሪ ፖለቲከኞች ስለሆኑና ያልገባቸው ነገሮች ስላሉ ቀስ ብለው ይታረማሉ የሚል እምነት ስላለን በትግስት አልፈናቸዋል በማለት ተናግረዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፎቹ እስከመደባደብና ድንጋይ መወርወር ሁኔታዎች በሰፊው የተስተዋሉ መሆናቸውን ያነሱት አቶ አወሉ የከፋ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ የነበሩት ግለሰቦች የማን አባላት እንደሆኑ በመለየት በህግ አግባብ እንዲታዩ አድርገናል ብለዋል፡፡

ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ተምረው በቀጣይ በሚከናወኑ የድጋፍ ሰልፎች ላይ አባላቶቻቸው ከመሰል ድርጊቶች እያረሙ የሚሄዱበትን ሁኔታዎች ይፈጥራሉ ብለን እናስባለን በማለትም ገልፀዋል፡፡

ለድጋፍ በወጡ አባላቶቻችን ላይ የታየ ምንም የስነ-ምግባር ጉድለት ሪፖርት ያልተደረገ መሆኑን የነገሩን ሲሆን ችግሮች ሪፖርት ሲደረጉልን ግን በስራ ላይ በዋለው የፓርቲ አመራሮችና አባላት የስነ-ምግባር ደንብ መሰረት እርምጃ የምንወስድ ይሆናል ብለዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
የኤርትራ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያው አባ ብርሃነእየሱስ ጉዳይ መንግሥትን ማብራሪያ ጠየቀች።
@YeneTube @Fikerassefa
የ157 ሰዎች ሕይወት ያለፈበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ አንደኛ ዓመት እየተቃረበ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋውን የተመለከተ ጊዜያዊ ዘገባ ፣ የአደጋው አንደ ዓመት ከመድረሱ አስቀድሞ እንደሚያወጣ አስታውቋል። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ አደጋውን በተመለከተ የወጡት መረጃዎች ምን ያህል አጥጋቢ ነበሩ ትላላችሁ? አስተያየታችሁን አካፍሉን።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
በአሁን ሰዓት የካቲት 25/2012 ዓ/ም የአርቲስት ውብሸት ወርቃለማው የቀብር ስነስርዓት የሽኝት ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

Via:- ዋልተንጉስ ዘሸገር
@Yenetube @Fikerassefa
የህዳሴው ግድብ በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ መነጋገሪያ ሆኗል

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ አነጋግሯል፡፡
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት በተመለከተ የወጣው መግለጫ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን አሜሪካዊያንንም አስቆጥቷል።

ታዋቂ አሜሪካዊያን ፖለቲከኞችና ዲፕሎማቶች አሜሪካ በኢትዮጵያ እንዲፈረም ያቀረበችውን የስምምነት ሰነድ ተችተውታል።
ሚኒስትሩ መኑቺን ትናንት በአሜሪካ ምክር ቤት ቀርበው በነበረበት ጊዜ ጉዳዩ የኮንግረስ አባል በሆነው ስቴቨን ሆርስፎርድ የአሜሪካንን ገለልተኝነት በሚያጠይቅ ሁኔታ ተነስቶ ማብራሪያ ተጠይቆበታል።

ምንጭ፡- ዋልታ
@YeneTube @Fikerasssefa