YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
ሱዳን ቅሬታዋን አቀረበች 👌 የአረብ ሊግ ምክር ቤት በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከግብፅ ጎን እንደሚቆም ለመግለፅ በተዘጋጀ የውሳኔ ሐሳብ ረቂቅ ሱዳን ቅሬታ እንዳላት መግለጿን የመካከለኛው ምሥራቅ የዜና ወኪል ዘገበ። ሱዳን የአረብ ሊግ በውዝግቡ ጣልቃ ሊገባ አይገባም የሚል አቋም አላት። በ153ኛው የአረብ ሊግ ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ማሻሻያ የጸደቀው የውሳኔ ሐሳብ «ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ያላት ታሪካዊ…
በዘገባው መሠረት ኢትዮጵያ ከታችኛው ተፋሰስ አገሮች ጋር ሚዛናዊ ስምምነት ላይ ሳትደርስ ግድቡን በውኃ ለመሙላትም ሆነ ሥራ ለማስጀመር በተናጠል የምትወስደውን እርምጃ እንደሚቃወም የአረብ ሊግ ገልጿል።

በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ የተዘጋጀው ስምምነት «ፍትኃዊ፣ ትክክለኛው እና ሚዛናዊ» እንደሆነ የገለጸው ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ እንድትፈርም የአረብ አገሮች እንዲያግባቡ ጥሪ ማቅረቡን ሜና ዘግቧል።

«የውሳኔ ሐሳቡ በሁሉም አገሮች ቢደገፍም ሱዳን ተነሳሽነት አላሳየችም። እንዲያውም ሱዳን በውሳኔ ሐሳቡ ስሟ እንዳይካተት ጠይቃለች» ሲሉ አንድ ጉዳዩን የሚያውቁ የመረጃ ምንጭ መናገራቸውን #ሜና ዘግቧል።

አረብ ሊግ ለግብጽ ጥብቅና የቆመበት የውሳኔ ሐሳብ ጥቅሟን እንደማያስከብር የሞገተችው ሱዳን በውሳኔ ሐሳቡ ምክንያት “በአረቡ ዓለም እና በኢትዮጵያ መካከል ውዝግብ ይቀሰቀሳል” የሚል ሥጋቷን እንደገለጸች የሜና ዘገባ ይጠቁማል።

ምንጭ:- እሸት በቀለ
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበርው ጉባኤ መተላለፍ

የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(UNECA) በአዲስ አበባ ሊያካሂድ የነበረውን ጉባኤ ለሌላ ቀጠሮ አስተላለፈ፡፡

አህጉራዊ የኢኮኖሚ ኮሚሽኑ ስብሰባውን ያስተላለፈው በአለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እየተስፋፋ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

በቫይረሱ ስጋት ምክንያት ባይተላለፍ ኖሮ ጉባኤው ከ13 ቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ሊደረግ እቅድ ተይዞለት እንደነበርም ሰምተናል፡፡

ጉባኤው በአፍሪካ የፋይናንስ፣ የፕላንና የኢኮኖሚ እድገት ሚኒስትሮች ደረጃ ይካሄዳል ተብሎ የነበረ ሲሆን ባለስልጣናቱ በአህጉሪቱ የምጣኔ ሀብት ሁኔታ ላይ ይመክሩበታል ተብሎ ሲጠበቅ እንደነበርም ነው ለማወቅ የተችሏል፡፡

Via:- አዲስ ነገር
@YeneTube @Fikerassefa
በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ይህን አድርጉ፣ ይህን አታድርጉ፣ ይህንን ፈርሙ የሚል ዓይነት አካሄድ ተገቢነት የሌለውና ድፍረት የተቀላቀለበት አካሄድ” መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን የተናገሩ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ዛሬ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት ነው።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን በመቃወም ለዓረብ ሊግ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን እንደማትቀበለው አስታወቀች

ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን በመቃወም ለዓረብ ሊግ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡

በግብጽ ካይሮ በተካሔደው የዓረብ ሊግ 153ኛ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ግብጽ በግድብ ዙሪያ የሊጉ አባል አገራት ከጎኗ እንዲቆሙ ያቀረበችውን ሰነድ ላይ ነው ሱዳን ያላትን ልዩነት የገለፀችው፡፡

በስብሰባው ላይ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ፣ የአረብ ሀገራት በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ እና ሱዳን ጎን እንዲቆሙ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

ነገር ግን ሱዳን በህዳሴ ግድብ ላይ የዓረብ ሊግ ከግብፅ ጋር ለመቆም ያሳለፈውን የትብብር ውሳኔም እንደምትቃወም አስታውቃለች፡፡

በግብጽ የተዘጋጀውን ሰነድ እንደማትቀበል ያስታወቀችው ሱዳን ከሰነዱ ስሟ እንዲወጣም አድርጋለች፡፡

ግብጽ ኢትዮጵያን በመወንጀል ለሊጉ ያቀረበችው ረቂቅ የድጋፍ ሰነድ፣ የዓረብ ሀገራት ኢትዮጵያን በመቃወም ከግብጽና ሱዳን ጋር እንዲቆሙ የሚጠይቅ ነው፡፡

የዓረብ ሊግም ግብጽ በአባይ ዉሀ ላይ ያላትን ታሪካዊ መብት የሚደግፍ እና የኢትዮጵያን የተናጥል ውሳኔ የሚኮንን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ይሁንና ሰነዱ አይመለከተኝም ያለችው ካርቱም ከህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ሊጉ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር እንዲቆም የሚጠይቀውን ረቂቅ የድጋፍ ሰነድ ውድቅ አድርጋለች፡፡

በግብጽ የቀረበው ሰነድ፣ ኢትዮጵያን የሚያስቀይም ከመሆኑም ባለፈ የሀገሯን ብሔራዊ ጥቅም እንደሚጋፋም ነው ሱዳን በስብሰባው ላይ ያነሳችው፡፡

ሱዳን እንደዚህ ያሉ ሰነዶች እና መግለጫዎች በግድቡ ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችን ሊያደናቅፉ እና የዓረብ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት የበለጠ ሊያበላሹ እንደሚችሉ አንስታ መከራከሯ አግራሞት መጫሩም አህራም የተሰኘው የግብፅ ሚድያ ዘግቧል፡፡

Via:- ETV
@YeneTube @Fikerassefa
🎉የሀ የዲጅታል አርት ክፍት ሊሆን ሁለት ቀን ብቻ ቀርቶታል

ቅዳሜ እና እሁድ ከጠዋት 4:00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 11:30 በኖህ ፕላዛ፣ ከአለም ሲኒማ አጠገብ እንገናኝ።

መግቢያ በነፃ

@yehadigitalart
1
ብልፅግና የሀገር ህልውናን ለመታደግ ድርብ ሃላፊነት የወሰደ ፓርቲ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

https://www.fanabc.com/ብልፅግና-የሀገር-ህልውናን-ለመታደግ-ድር/
1
ስለ ኮሮና ቫይረስ የተሳሳቱ መረጃዎች እየተሰራጩ ነውና ተቋማት ግንዛቤ መስጠቱ ላይ ሊበረቱ ይገባል ተባለ፡፡

#Shager FM
@YeneTube @Fikerassefa
1
አንጋፋው መኢአድ እና ባልደራስ ሊዋሀዱ ነው

በእስክንድር ነጋ የተመሰረተው ባልደራስ እና በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ «መኢአድ” ነገ አርብ የካቲት 27,2012 አዲስ አበባ ላይ ጋዜጠኞችን ጠርተው የውህደት ፊርማቸውን እንደሚያደርጉ ፊደል ፓስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ውህደታቸው በመጪው ነሀሴ ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ ጠንከር እና ገዘፍ ብሎ ለመፎካከር ያለመ ነው።
በመኢአድ በኩል  ፕሬዚዳንቱ አቶ ማሙሸት አማረን  ሲወከሉ በባልደራስ ደግሞ አቶ እስክንደር ነጋ ተወክለው ፊርማ ይፈራረማሉ።

Via:- Fidelpost
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ከካይሮ አምባሳደሮቿን በአስቸኳይ ጠራች

ኢትዮጵያ በካይሮ እና ብራስልስ ያሉትን ጨምሮ ስምንት አምባሳደሮቿን በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መጥራቷ ተሰምቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ግብጽ፣ ሱዳን፣ አውሮፓ ህብረት (ቤልጂየም) ፣ ሞሮኮ፣ ኩባ፣ አልጀሪያ፣ አውስትራሊያ እና እንግሊዝ ያሉ አምባሳደሮች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል ተብሏል።

አምባሳደሮቹ የተጠሩት ኢትዮጵያ በነዚህ አገራት አዲስ አምባሳደሮችን የመሾም ፍላጎት ስላላት እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የገጠማትን የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍትሔ ለመስጠት መጠነ ሰፊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ ብትሆንም በግብጽ ላይ ወስዳው የነበረውን የዲፕሎማሲ የበላይነት ማስጠበቅ ተስኗታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የግብጽን የዲፕሎማሲ የበላይነት ለመቀልበስ እና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ለኢትዮጵያ ቁልፍ እና ስትራቴጂክ በሚባሉ አገራት እና ተቋማት አዲስ አምባሳደሮችን ለመመደብ በሒደት ላይ ናቸው።

ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከትናንት በስቲያ ለ15 ሰዎች የአምባሳደርነት ሹመት መስጠታቸው ይታወሳል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
የሕወሓት እና የብልፅግና ሃብት ክፍፍል ውዝግብ

የኢሕአዴግን ንብረት ለብልፅግና እና ሕወሓት ለማከፋፈል በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈውን የእኩል ድርሻ ክፍፍል ውሳኔ እንደማይቀበለው ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ።የአባሎችችን ቁጥር የተለያየ በሆነበትና ‹‹እኩል ባላዋጣንበት፣ እኩል የምንካፈልብት አግባብ የለም›› ያለው ብልፅግና 25 በመቶ ለሕወሓት አይገባም ሲል ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርቦ እየታየለት መሆኑን ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግሯል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተዳዳሪው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የኢሕአዴግ ወራሽነትን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ፤ 3ቱ ድርጅቶች (የቀድሞዎቹ አዴፓ፣ ኦዴፓ እና ደኢሕዴን) ኢሕአዴግ ያፈራውን 75 በመቶ እንዲወርሱና ቀሪው 25 በመቶ ለሕወሓት እንዲሰጥ ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡በጋራ እያላችሁ ያፈራችሁትን ንብረት ተካፈላችሁወይ ሲል አሐዱ ቴሌቪዥኝ የጠየቀው ብልፅግና የንብረት ክፍፍሉ ብዙ ውስብስብ ጉዳዮች አሉበት ብሏል፡፡ ንብረቱ ኦዲት መደረግ ስለሚገባው ክፍፍሉ መዘግየቱንም አሳውቋል፡፡በተያያዘ ብልፅግናን ተቀላቅለው የትግራይ ቅርንጫፍን መሰረቱ የተባሉት የሕወሓት የቀድሞ አመራርና አባላት በንብረት ክፍፍሉ ላይ የሚኖራው ድርሻ እንዴት ይስተናገዳል የተባለው ብልፅግና ገና እያሰብኩበት ነው፤ አልተወሰነም ብሏል፡፡

ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ የቅድመ ታሪክ ቅሪተ አካልና መካነ ቅርስ ሥፍራዎች መዳረሻ ሀገር በሚል በጀርመን በየአመቱ በሚካሄደው የፓትዋ ሽልማት አሸናፊ ሆነች።

የፓሲፊክ አካባቢ ተጓዦች ማህበር (ፓትዋ) ሽልማት በየአመቱ በጀርመን በሚካሄደው የበርሊን የዓለም የቱሪዝም ንግድ ትርዒት ላይ የሚሰጥ የእውቅና ስነ ስርዓት ነው።

በዘንድሮው የፓትዋ ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች 13 የዓለም ሀገራት አሸናፊ መሆናቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያም የቅድመ ታሪክ ቅሪተ አካልና መካነ ቅርስ ሥፍራዎች መዳረሻ ሀገር በሚለው ዘርፍ በቀዳሚነት አሸንፋለች።

በሌላ በኩል የኢፌዴሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ከሰሃራ በታች ምርጥ የቱሪዝም ሚኒስትር በሚል ተመርጠዋል።

Via:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
አንጋፋው መኢአድ እና ባልደራስ ሊዋሀዱ ነው በእስክንድር ነጋ የተመሰረተው ባልደራስ እና በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ «መኢአድ” ነገ አርብ የካቲት 27,2012 አዲስ አበባ ላይ ጋዜጠኞችን ጠርተው የውህደት ፊርማቸውን እንደሚያደርጉ ፊደል ፓስት የደረሰው መረጃ ያሳያል። ውህደታቸው በመጪው ነሀሴ ለሚደረገው ብሔራዊ ምርጫ ጠንከር እና ገዘፍ ብሎ ለመፎካከር ያለመ ነው።…
መኢአድ እና ባልደራስ በመዋሃድ በስምምነት የጋራ ሰነድ ፈርመዋል ። በአሁኑ ሰአትም በአገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ እየሰጡ ነው በመግለጫው የሰሞኑ የመገናኛ በዙሃን ትኩረት የሆነው የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሰፋፊ ሃገራዊ ጉዳዮች ተነስተዋል ሙሉ መግለጫውን በዩትዩብ ቻናላችን ከደቂቃዎች በኋላ እናጋራቹሃለን።

@YeneTube @Fikerassefa
የታላቁ ኅዳሴ ግድብ የድጋፍ ሰልፍ!

ዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ላይ የያዙትን አቋምና ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው።በዚህም በመጋቢት 13 ወይም 21 በአገር አቀፍ ደረጃ ሊደረግ የታሰበው ትዕይንተ ሕዝብ፤ በሕግ ባለሙያዎች፣ በዲያስፖራው ማኅበረሰብ ተወካዮች እና በአርቲስቶች አስተባባሪነት እንደሚካሄድ ተነግሯል።

ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ ዉሳኔን ኮንና የሱዳንን አቋም አድንቃለች።

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ አረብ ሊግ በህዳሴ ግድብ ላይ የግብፅ አቋም ያለምንም ማስረጃ ማፅደቁ ፍረደ ገምድልነት ነዉ ብሏል፡፡የአረብ ሊግ ዉሳኔ የታላቁን ህዳሴ ግድብ እዉነታ ያልተረዳ እንደሆነም ኢትጵዮጵያ ወቅሳላች፡፡

ሱዳን የአረብ ሊግ ያስተላለፈዉን ዉሳኔ መቃወሟም የአገሪቱ ወጥ አቋም እና ምክንያታዊነት የሚገልፅ ነዉ ብሏል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫዉ፡፡ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ለሱዳን መንግስት እና ህዝብ ያለዉን አድናቆት እና ክብር ገልጧል፡፡

ኢትዮጵያ ከአረቡ አለም ጋር በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ የታሪክ፤የባህል ፤የንግድእና በሌሎችም ዘርፎች ጥሩ ግንኙነት አላት ያለዉ መግለጫዉ በአንዲት ሉአላዊት አገር ላይ እንደዚህ አይነት ዉሳኔ ሊጉ ማስተላለፉ ያሳዝናል ብሏል፡፡ የአሁኑ ዉሳኔም የአረብ ሊግ በአለም አቀፍ ደረጃ ለሠላም ለፍትህና እና ለትብብረ የሚኖረዉን ሚና ጥያቄ ምልክት ዉስጥ የሚከት እና ታማኝነቱ ላይ ጥርጣሬ የሚያስነሳ እንደሆነም እንስቷል፡፡

ኢትዮጵያ የራሷን ሀብት የአሁኑን እና የመጪዉን ትዉልድ ተጠቃሚ ለማድረግ በፍትሃዊ እና የአለም አቀፉን የዉሃ ሀብት አጠቃቀም መመሪያን ተከትላ ግድቡን እንደምትገነባም አስታዉቃለች፡፡በመጨረሻም የአረብ ሊግ የወሰነዉን ዉሳኔ መልሶ በመርመር ፍረደ ገምድልነትን ትቶ ሚዛናዊ አመለካከት እንደሚኖረዉ ኢትዮጵያ ሙሉ እምነት አለኝ ብላለች፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራስ እና መኢአድ ተዋሀዱ እንዲሁም በአባይ ጉዳይ አቋማቸውን ገለፁ።
መግለጫው ላይ ተገኝተን ያጠናከርነውን ዘገባ ተመልከቱት።

⬇️⬇️⬇️
https://youtu.be/SFc5obuw8Jw
የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ተጨማሪ የ10 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ።

@YeneTube @Fikerassefa
ከደምቢዶሎ ዩንቨርሲቲ የታገትን ተማሪዎች ነን በማለት በሀሰት ሕብረተሰቡን አደናግረዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ


ከደንቢ ደሎ ዩንቨርስቲ የታገትን ተማሪዎች እኛ ነን በማለት የተሳሳተ የሀሰት ወሬ አውርተዋል ተብለው ተጠርጥረው የካቲት 3 ከባህርዳር ከተማ ተይዘው ለፌደራል ፖሊስ ተላልፈው የተሰጡት ና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በእስር ላይ የሚገኙት የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ 2 ሴት ተማሪዎች ቅድስት በጋሻው እና ሸዋዬ ጌትነት ለ 3 ጊዜ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው የ10 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሰጠ።

የካቲት 25 ረፋድ ላይ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው “ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ የምስክር ቃል እቀበላለው፣ተባባሪዎቻቸውን የነበሩትን መያዝ አለብኝ ፣የስልክ ምርመራ እንዲሰጠኝ ወደ ኢንሳ ደብዳቤ ልኬ መልስ እየጠበኩ ስለሆነ ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ” ሲል ችሎቱን ጠይቋል።

ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ ልጆቹን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ ተመሳሳይ ስራዎችን ነው እየሰራ ያለው ስለዚ የጠየቀው የምርመራ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ደንበኞቻችንን አስሮ ለማቆየት ነው። ፖሊስ በቂ ስራ አልሰራም ስለዚ የጠየቀው የምርመራ ጊዜ መሰጠት የለበትም ሲሉ የተከራክረዋል አክውም ፖሊስ ተጨማሪ ስራ ይቀረኛል የሚል ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና ወተው ክሳቸውን ይከታተሉ ሲሉ ተከራክረዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ችሎት የፖሊስ የምርመራ መዝገብ አይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 27 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቶ ነበር ።

ዛሬ ረፋድ ላይ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የፖሊስ መዝገብን ተመልክቶ ከጉዳዩ ውስብስብነት ና ክብደት አንፃር ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና ቢወጡ ተመልሰው ይመጣሉ ብለን ስለማንገምት 10 ተጨማሪ የምርመራ ግዜ ለፖሊስ በመስጠት ለመጋቢት 7/ 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ለ3 ጊዜ በአራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀርቡ ሲሆን የመጀመሪያ ችሎታቸውን የካቲት 4/ 2012 ቀርበው 11ቀን የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ የተፈቀደ ሲሆን በሁለተኛ የጊዜ ቀጠሮ የካቲት 15/ 2012 ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም በማለቱ ችሎቱ ተጨማሪ የ8 ቀን የምርመራ ጊዜ ሰቶ ለየካቲት 25 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጠ የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ ያስረዳል።

Via:- ዋዜማ ራዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa
1