በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ከ5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የተሰበሰበውን ገንዘብ ይፋ አድርጓል፡፡የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ከተመሠረተ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ በነዚህ ጊዜያት ከአንድ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ በቀን አንድ የአሜሪካ ዶላር በመሰብሰብ ላይ ነው፡፡እስካሁን በተሠራው ሥራ ከ5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ተሰብስቧል፡፡ ገንዘቡ ከ25 ሺህ 645 ኢትዮጵያውያን ዲያፖራዎች የተሰበሰበ ነው ብሏል በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፡፡እንደ ኤምባሲው መረጃ በ46 ምዕራፎች በ77 ሀገራት ከሚኖሩ ዜጎች ገንዘቡን ማግኘት ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ሙሉ በሙሉ በበጎ ፍቃደኞች የሚሰጥ ነው፡፡ገንዘቡም ሙሉ በሙሉ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚውል እንደሆነ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ምንጭ፦ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa

የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በ7ሚሊዮን ብር ወጪ የደንብ ልብስ ተዘጋጀላቸው።
በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለ362 ሠራተኞቹ የደንብ ልብስ ያሰፋ ሲሆን ለእያንዳንዱ ሠራተኛ በ20 ሺሕ ብር ገደማ ኹለት የደንብ ልብስ ከነመጫሚያው በማዘጋጀት እና በየአንድ ዓመቱ አዳዲስ ደንብ ልብስ ለመስጠት ማቀዱ ታወቀ።በጽሕፈት ቤቱ በተለያዩ የሥራ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እና ባለሃብቶች የግብር አገልግሎት ለማግኘት ወደ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ እንደሚመጡ የተገለጸ ሲሆን፣ ደንበኞችን ደረጃውን በጠበቀ አለባበስ ለማስተናገድ እና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የራሱ የሆነ መለያን ለመፈጠር እንደሚረዳ የገቢዎች ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኡሚ አባጀማል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ለዩኒፎርም ዝግጅቱም ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

‹‹መንገድ መዝጋት ኋላቀር ፓለቲካ ነው።››
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት የተናገሩት
@YeneTube @Fikerassefa

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄ ምላሽ እየሰጡ ነው::
•በዘንድሮውም ሆነ በሚቀጥለው ችግር አልባ፤ ተግዳሮት የሌለው ምርጫ ማድረግ አይቻልም። ዴሞክራሲ ልምምድ የሚፈልግ ነው። ምክንያት እየፈለጉ አሁን እንችልም ብንል ብዙ ችግር ነው ያለው። የህዝብን ይሁንታ አግኝቶ በሙሉ ልብ መስራት ይሻላል።
•የምርጫ ቦርድ አሁን ያለው ቁመና ከአምና እና ካቻምና በተሻለ ቁመና ላይ ነው የሚገኘው። በቂ በጀት መንግስት የመደበ ሲሆን፥ ቦርዱ እስካሁን ከነበሩት አባላት በተሻለ የህዝብ እና የምክር ቤቱን ይሁንታ አግኝተው ተመርጠዋል። ቦርዱ በገንዘብም በእቅምም የተሻለ ነው።
•የመንግስት ዴሞክራሲያዊ እና ነፃ ምርጫ እንዲደረግ ነው ፍላጎቱ። ይህም እንዲሆን በጀት በጅቷል።
•የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫን ተከትለው የሚመጡ ግጭቶች የሚያስከፍለውን ጉዳት ከምርጫ 97 በተግባር ተምሯል። ህዝቡ ምርጫን አስታኮ የሚከሰት ግጭትን የሚፈልግ ህዝብ አይደለም። ችግር አለ ተግዳሮት አለ ሆኖም መንግስት እና ህዝብ ተግባብተው ከሰሩ ችፍሩን መፍታት ይችላሉ።
•በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሃን፣ ሲቪክ ማህበራት ሚናቸውን ከተወጡ እንደዚሁም ፓርቲዎች ህዝብን አሳምነው ከተመረጡ ስልጣን ለመረከብ እንዲሁም ከተሸነፉ ውጤቱን ለመቀበል ዝግጁ ከሆኑ የተሻለ ምርጫ ማድረግ ይችላል።
•የምርጫ ህጉ በሚያስደንቅ ሁኔታ ለካቢኔ ሳይቀርብ የምርጫ ቦርድ ባለደርሻ አካላትን አወያይቶ አፅድቋል።
•ኢህአዴግ ከሌለ ሀገር የለም መንግስት የለም ማለት ስህተት ነው። ፓርቲ እኮ አድሜው 40 ዓመት ነው። የእኛ ስምምነት ሰላም ያመጣል። እኛ ከሌለን ግን ኢትዮጵያ የለችም ትክክል አይደለም። ኢህአዴግ ቢኖርም ባይኖርም ኢትዮጵያ ትቀጥላለች።
•የኢህአዴግ ውህደትን በተመለከተ ባለፉት 10 ዓመታት ውይይት ሲደረግበት ነበር። በሃዋሳው ጉባኤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ተገቢውን ስራ ካከናወነ ከቀጣዩ ጉባኤ በፊት ውህደቱን ይፈፀም ብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
•ውህደቱ አያስፈልግም የሚል ሀሳብ እስከዛሬ አልሰማሁም። ውህደቱ ግን አሁን መሆን የለበትም የሚል በግለሰብ እና በፓርቲ ደረጃ ይነሳል። ጥናቱን ካየን በኋላ ግን የኢህአዴግ ምክር ቤት የሚያፀድቀው ይሆናል።
•ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 40 ዓመታት ብዙ ዜጎችን አጥተናል። ከትናንትናው መገዳደል መማር የሚችል ህዝብ ደግሞ ወደዚያ ኪሳራ አይገባም።
•ህዝቡ በክላሽ ዘላቂ ድል አይመጣም ብሎ በቃ ሊል ይገባል።
Via:- FBC

‹‹ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በእኔ ልክ ስለ ሰላም ጉዳይ ያነጋገሪ መሪ የለም።››
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት የተናገሩት
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት የተናገሩት
@YeneTube @Fikerassefa
‹‹የትግራይን ክልል እየመሩ ያሉ ሰዎች የክልሉን የውሃ ችግር መፍታት እንጂ ከአማራም ሆነ ከሌሎች ክልሎች ጋር መጋጨት የሚፈልጉ ሰዎች አይደሉም››
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት የተናገሩት
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት የተናገሩት
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ሰሞኑ ለሰራተኞቹ አስከ 180 % የደሞዝ ጭማሪ ያደረገበት ምክንያት ከፍተኛ የሰራተኞች ስራ መልቀቅ ስላጋጠመውና የውጭ ባንኮች ወደሀገር ውስጥ ቢገቡ እንኳን በተሻለ ክፍያ ሰራተኞቹን እንዳይወስዱ ከወዲው ለመከላከል እንዲያስችለው መሆኑን ከባንኩ ሰራተኞች ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል! !
Via:- Tsefay Weledyes
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- Tsefay Weledyes
@YeneTube @Fikerassefa
‹‹አዲስ ቱሞሮ የሚል አዲስ ትልቅ መኖሪያ ከተማ [ፕሮጀክት] ጎተራ አካባቢ ከቻይና ጋር ተፈራርመን እንገነባለን።……ከአራት ሺሕ አምስት ሺሕ የጎዳና ተዳዳሪዎች የሚያነሳ ቤት እንገነባለን።››
ዶ/ር አብይ አህመድ
@YeneTube @Fikerassefa
ዶ/ር አብይ አህመድ
@YeneTube @Fikerassefa
ወጣቶችን ማስጨረስ ይብቃ!!
"ትላንትም ዛሬም ወደ ፊትም በውጊያ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሸፍ የሚፈልጉ አካላት ተመሳሳይ ናቸው፡፡
ሌሎችን ማስጨረስ እንጂ እራሳቸው መሞት አይፈልጉም፡፡ እነዚህ እራሳቸው መሞት የማይፈልጉ ሀይሎች ወጣቶቻችንን እንዲያስጨርሱ ሊንፈቅድላቸው አይገባም፡፡" ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa
"ትላንትም ዛሬም ወደ ፊትም በውጊያ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሸፍ የሚፈልጉ አካላት ተመሳሳይ ናቸው፡፡
ሌሎችን ማስጨረስ እንጂ እራሳቸው መሞት አይፈልጉም፡፡ እነዚህ እራሳቸው መሞት የማይፈልጉ ሀይሎች ወጣቶቻችንን እንዲያስጨርሱ ሊንፈቅድላቸው አይገባም፡፡" ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
#EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፓርላማ መክፈቻ ንግግርን አስመልክቶ የቀረበው የድጋፍ ሞሽን ያልተጠበቀ ተቃውሞ ገጠመው። አንድ የፓርላማ አባል ሞሽኑን ሲቃወም 19 አባላት ደግሞ ድምፅ ከመስጠት ታቅበዋል።
Via:- Tesfay Weledyes
@Yenetube @FikerAssefa
Via:- Tesfay Weledyes
@Yenetube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያደረገው የ18 በመቶ ደሞዝ ጭማሪ ውዝግብ አስነሳ!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ22 ሺሕ በላይ ለሚሆኑት ቋሚ እና ጊዜያዊ ሠራተኞቹ የደሞዛቸውን እስከ 18 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ቢያደርግም የዋጋ ግሽበትንና የኑሮ ውድነትን ያላገናዘበ ነው ሲሉ የድርጅቱ ሠራተኞች በማህበራቸው በኩል ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ጭማሪው ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ጀምሮ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2011 ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ውሰጥ በቋሚነት እና በጊዜያዊነት ተቀጥረው እየሠሩ ላሉ ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች የተደረገ ሲሆን፣ በደረጃ አራት እርከን ወይም የደሞዛቸውን 18 በመቶ በመጨመር ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።
Via Addis Maleda

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከተባበሩት መንግስታይ የጸጥታ ምክር ቤት ጋር በክልላዊ ሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ኖቤል በመሸለማቸው ደስታቸውን ገልጸው ለክልላዊ ሰላም የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም የአቋም ለውጥ እና በቅንነት የሰላም እና የአመራርን ዋጋ መገንዘብ ክልላዊ ሰላምን በዘላቂነት ለማስጠበቅ እንደሚረዳ ተናግረዋል።
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በኮብልስቶን ድንጋይ ሰው የገደለው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ!
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አካባቢ የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ስጠኝ በሚል በኮብልስቶን ድንጋይ የሰው መግደል ወንጅል የፈጸመው ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በጽኑ እስራት ተቀጣ፡፡የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ጋዲሳ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 የተመለከተውን በመተላለፍ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው መብራት ሀይል ወይም አሎሚስት ግሮሰሪ ተብሎ አካባቢ ከሚገኘው ፀሀይ ሚልኬል አረቄ ቤት ውስጥ ከሟች ፋሲካ ተስፋዩ ጋር መጠጥ በመጠጣት ላይ እያለ ተከሳሸ ሟችን ላይተር ስጠኝ ሲለው ሟች አልስጥም ሲለው ተከሳሽ ወደ ወጪ በመውጣት የኮብልስቶን ድንጋይ ይዞ በመምጣት ሟች በተቀመጠበት የቀኝ ጭንቅላቱን አንድ ጊዜ በመምታት በራሱ ላይ ጉዳት በመድረሱ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገ በመሆኑ በፈፀመው ተራ የሆነ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሷል፡፡
ተከሳሽ የዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ተነቦለት እንዲረዳ ከተደረገ በኃላ እንደ ክሱ ኣቀራረብ የወንጀል ድረጊቱን መፈፀሙን የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ዐቃቤ ሕግም ተከሳሽ በአመነው መሰረት የጥፋተኝነት ፍርድ እንዲሰጥ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽን በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በማለት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ ተከሳሽ የዘወትር ፀባይ መልካም እንደነበር፣ ድርጊቱን ማመኑ እና የቤተስብ አስተዳዳሪ መሆኑን በማቅለያ በመያዝ ጥቅምት 06 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ8 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
ምንጭ:Federal Attorney General

ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቀረቡላቸው ጥያቄዎች ላይ የሰጧቸው መልሶች
- በክልሎች መካከል ያለው የትጥቅ እና የቃላት ፉክክር የመጣው ከባለፈው ችግር ካለመማር እና ከባለፈው ወረት ካለመጠቀም ነው፡፡
- ዓለም ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ባለመማሯ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት መከሰቱንም በምሳሌነት አንስተዋል።
- አሁን ያለው ችግር ምን ዓይነት ውጊያ ይገጥመናል የሚለውን ካለመገንዘብ ነው ካሉ በኋላ ለዚህ ችግር ዋነኛ ምክንያት የሆኑት “ዕድሜ ጠገብ ፓርቲዎች እና ሰዎች” እንደሆኑ ተናግረዋል።
https://telegra.ph/Yenetube-10-22

በአጠራጣሪ እንቅስቃሴ ላይ አገኘኋቸው ያላቸውን 38 ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የጎንደር ከተማ አስተዳደር የሰላምና ደኅንነት መምሪያ አስታወቀ።
ከተያዙት ወጣቶች መካከል አንድ ግለሰብ አራት መታዎቂያዎችን፣ ሌላ አንድ ወጣት ደግሞ 7 የውጭ ሀገር ሲም ካርዶችን እንደያዘ አረጋግጫለሁ ብሏል መምሪያው፡፡
https://telegra.ph/YeneTube-10-22-2

የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን የሚያስችል ሳይንሳዊ ጥናት ተጀመረ!
አብያተ ክርስቲያናቱ ታሪካዊ ይዘታቸውን እንደጠበቁ ለመጠገን የስነ-ምድርና የአርኪዮሎጂ ጥናት መጀመሩን የኢትዮ-ፈረንሳይ የጥናት ቡድን ገልጿል። የአብያተ ክርስቲያናቱ የሙከራ ጥገና በመውጭው የአውሮፓዊያኑ አዲስ ዓመት ይጀምራል ተብሏል።
በ1970 ዓ/ም በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት ቤተክርስቲያናቱ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል። ከ10 ዓመት በፊት በአምስት ዓመት ጊዜ ይነሳል ተብሎ በ11 ሚሊዮን ዩሮ የተሰራው መጠለያ ተጨማሪ አደጋ በመሆን የቅርሱን ህልውና እየተፈታተነ ይገኛል።
በመሆኑም በቅርሱ ላይ የደረሰውን የመሰንጠቅ አደጋ ለመጠገንና መጠለያውን ለማንሳት ዘርፈ ብዙ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያስፈልግ አጥኝዎቹ ይናገራሉ። ስንጥቁን ለመጠገንና መጠለያውን ለማንሳት የአርኪዮሎጂ፣ የስነ ምድር፣ የቅርጽ ጥናት በማድረግ ላይ መሆናቸውን አጥኚዎቹ ገልጸዋል።
በቅርሱ ላይ መረጃ ለመሰብሰብ የሚገጠሙ 3ዲ ካሜራዎች በተጨማሪ በየሁለት ሰዓቱ መረጃ የሚያደርሱ የሌዘር ስካን መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ ብለዋል። የጉዳት መጠናቸው ጊዜ የማይሰጥ ቅርሶች እየታዩ ጥገና እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ፤ ከጥቂት ወራት በኋላ ከቤተክርስቲያናቱ አንዱ በሆነው ቤተ-ጎለጎታ ላይ የሙከራ መጠለያ ይሰራለታል ተብሏል።
አሐዱ ቴሌቭዥን

ገበያ ላይ ከዋለ ሳምንት እንኳን ያልሞላው መደመር መጽሀፍ ከተተመነለት ዋጋ በላይ እየተሸጠ ነው ተባለ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተጻፈው እና ባለፈው ቅዳሜ በ46 ከተሞች ተመርቆ ለገበያ የዋለው መደመር መጽሀፍ፤ በሦስት ቀናት ውስጥ 500 ሺህ ቅጂዎቹ እንደተሸጠ ታውቋል፡፡የታተሙት መጽሀፎች ብዛት 1 ሚሊዮን ቅጂ ሲሆኑ እስካሁን ግማሽ ሚሊዮኖቹን መሸጥ መቻሉን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ መዋዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡መጽሀፉም ከተተመነበት 300 ብር ዋጋ በላይ እየተቸበቸበ ስለመሆኑ እንደሚያውቁ የተናገሩት ዲያቆን ዳንኤል ችግሩ የሚመነጨው አውራ የሆኑ አሳታሚዎች ባለመኖራቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡የዋጋ ማሻቀብ ችግር በዚህ መጽሀፍ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የመጽሀፍ ገበያው ላይ የሚስተዋል ነውም ብለዋል፡፡ቀሪዎቹ 500 ሺህ የመደመር መጽሀፍ ቅጂዎች በፍትሀዊ ስርጭት በሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የሚሰራጩ መሆናቸውንም ዲያቆን ዳንኤል ተናግረዋል፡፡
ምንጭ: Ahadu TV

በአርባምንጭ ከተማ አባያ ሀይቅ ላይ በደረሰ የጀልባ መስመጥ አደጋ አምስት ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ፖሊስ አስታወቀ።
የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው አደጋው የደረሰው ትናንት ከቀኑ 9:00 ሰዓት አካባቢ ነው። በአደጋው ከጀልባዋ ኦፕሬተር ውጭ በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩ አምስት ሰዎች እስከስሁን የደረሱበት አለመታወቁን የፅህፈት ቤቱ የመረጃ ባለሙያ ኮንስታብል ብሩክ ተክለ ሃይማኖት ገልጸዋል።ጀልባዋ ላንቴ ተብሎ ከሚጠራው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ አካባቢ ሰዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን ጭና ወደ አርባምንጭ ከተማ በመጓዝ ላይ እንደነበረች ኮንስታብል ብሩክ ተናግረዋል። ጀልባዋ ላንቴ ከሚባለው አካባቢ ስትነሳ አምስት ተሳፋሪዎችና 15 ኩንታል በቆሎ ጭና እንደነበር በህይወት የተረፈው የጀልባዋ አፕሬተር ለፓሊስ በሰጠው ቃል መረጋገጡንም አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት ተሳፋሪዎች በህይወት ይገኛሉ የሚለው ተስፋ የመነመ ቢሆንም ፖሊስ ከትናነት ምሽት ጀምሮ በሀይቁ ላይ ፍለጋ እያደረገ እንደሚገኝ ኮንስታብል ብሩክ ጨምረው ገልጸዋል።
Via DW

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ሩስያ አመሩ!
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሩስያ አፍሪካ የጋራ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ሩስያ አምርተዋል።የጋራ ፎረሙ ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት በኋላ የሚካሄድ የመጀመርያው የአፍሪካ ሩስያ የትብብር መድረክ ነው።በሩስያ ሶቺ ከተማ በሚካሄደው ፎረም ከ35 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችም በላይ ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቆይታቸውም የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጨምሮ ከአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Via ETV