YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዱከም ከተማ በ120 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተመረቀ!

ከስድስት አመታት በፊት በጉጂ ዞን የተቋቋመው "Guji Highland coffee plantation"የተሰኘው ድርጅት በቡና ልማት ስራ ላይ ተሰማርቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ድርጅቱ ስራው ለማዘመን በዱከም ከተማ ያስገነባውን ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ና አባገዳዎች በተገኙበት አስመርቋል፡፡በዱከም ከተማ በ120 ሚሊዮን ብር ወጪ ገንብቶ የተመረቀው ፋብሪካ ለ140 ሰዎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የፋብሪካው ባለቤት አቶ ወዴሳ ያቺሲ ፍብሪካው በዘርፉ ያለውን ችግር በመቅረፍ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ ጉል ሚና አለው ብለዋል፡፡
የዱከም ከተማ ከንቲባ አቶ ተሾመ ግርማ ባለሀብቶች በተናጠል ጥሬ ምርትን ለገበያ ከማቅርብ ተደራጅተው ምርቱን በማቀነባበር እሴት ጨምረው ለማቅረብ መትጋት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡የኦሮሚያ ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ገነት አብደላ በከልሉ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶች የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ እንዲሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- OBN
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ካለፈው ሳምንት ወዲህ አጠያያቂ ሆኖ ቀጥሏል!

ካሳለፍነው ሳምንት ወዲህ በለቡ፣ ጀሞ፣አስኮ፣በአቃቂ ክ/ከተማ የተለያዩ አካባዎች፣ ኮየ ፈጬ እና በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ በተደራጁ ወጣቶች ምክንያት ሰላም ደፍርሷል፤ ህብረተሰቡም ስጋት ውስጥ ወድቋል፡፡ የተደራጁ ወጣቶቹ ከየት መጡ ሳይባል መንገድ ይዘጋሉ፣ የጥላቻ ንግግሮችን በአደባባይ ያስተላልፋሉ፣ የተለያዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዜጎችን ያስፈራራሉ ንብረትም ያወደሙ እንዳልጠፉ ለማወቅ ችለናል፡፡

በማህበራዊ ድህረገፆች ደግሞ መንገድ በድንጋይ ከመዝጋት ጀምሮ የተለያዩ የድርጅቶች ማስታወቂያዎችን እና አርማዎችን ሲያወርዱ፣መንገድ ዘግተው በርካታ ህገወጥ ድርጊቶችን ሲፈፅሙ ተመልክተናል፡፡የደንብ ልብስ የለበሱ የፀጥታ አካላት ህግ ከማስከበር ይልቅ ቆመው ሲታዘቡ ለማየትም ችለናል፡፡

ጉዳዩ በጊዜ ካልተቀረፈ ስጋቱ ወደ መሀል ከተማ የማይመጣበት ምክንያት የለም እና ቆሞ ከመታዘብ ውጪ የፀጥታ ሀይሎች ህግ እንዲያስከብሩ የየአካባቢው ነዋሪዎች ሀሳባቸውን አካፍለውናል፡፡በአዲስ አበባ የተፈጠረው የሰላም እጦት አሁንም ቀጥሏል፤ ይህ ሁሉ ሲፈጠር ለመሆኑ ፖሊስ ቆሞ መታዘቡን ይቀጥላል፣ ወይስ ሰላም ያስከብራል በሚለው ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ ምክር ቤት ቀርበው ከአባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኝ መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ በዚህ ሳምንት በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ በሚደረገው ድርድር የውጭ አሸማጋይ ጣልቃ እንዲገባ ግፊት እንደምታደርግ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ተናገሩ።

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከነገ በስቲያ ረቡዕ በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ በሚጀመረው የሩሲያ እና አፍሪካ ጉባኤ ጎን በጉዳዩ ላይ ይነጋገራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሬውተርስ ዘግቧል። “በዚህ ስብሰባ በድርድሩ አራተኛ ወገን እንዲሳተፍ ከስምምነት እንደርሳለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ አንድ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ባለሥልጣኑ “በሚቀጥሉት ሳምንታት ከአንዳች ቀመር ላይ እንስማማለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል። ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር ላይ ለአመታት የተደረገው ድርድር ፍሬ ባለማፍራቱ በአሸማጋይነት እንዲገባ በተደጋጋሚ ብትጠይቅም ኢትዮጵያ ግን ግብፅ ያቀረበችውን የአደራዳሪ ይግባ ጥያቄ «ተገቢ ያልሆነ» ስትል ውድቅ አድርጋለች።

የግብፅ ባለሥልጣናት በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሀ አሞላል እና አስተዳደር ላይ በሚደረገው ድርድር የዓለም ባንክ በአሸማጋይነት እንዲገባ ሐሳብ ማቅረባቸውን ሬውተርስ ዘግቧል። ግብፅ በውሃ መጋራት ላይ ልምድ ያላቸው አሜሪካ ወይም የአውሮፓ ኅብረት አሸማጋይ ቢሆኑ ፈቃደኛ መሆኗንም ዘገባው ጠቁሟል። በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቅርቡ በካይሮ እና በኻርቱም የተደረጉ ድርድሮች አንዳች ውጤት ሳያፈሩ ቀርተዋል። የግብፅ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለሥልጣን «ልዩነታችን እየሰፋ ነው» ሲሉ ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በኮንታ ልዩ ወረዳ አማያ 03 ቀበሌ ዱካ ዛሌ መንደር ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሸቱ 10 ሰዓት አከባቢ በደረሰው የመሬት ናዳ የ22 ሰዎች ህይወትና ንብረት መውደሙ ይታወሳል፡፡ የኮንታ ልዩ ወረዳ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻቸው በአማያ ከተማ ሀዘናቸውን እየገለጹ ናቸው፡፡የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ከጥቂት ሰዓት በኋላ ከስፍራው ተገኝተው በአደጋው የተሰማቸውን ሀዘን ይገልጻሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በአከባቢው እየተስተዋለ ያለው የመሬት ናዳ በአከባቢውና ለተቀሩትም ሥጋት እንደሆነባቸው ነው አስተያየታቸውን በተለይ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሰጡ የአማያ 03 ቀበሌ ነዋሪዎች የተናገሩት፡፡

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስም የተቋቋመው የባህል ማዕከል ተከፈተ!

የሎሬቱ ሀውልት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆምላቸው ነው በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስም የተቋቋመው የባህል ማዕከል ተከፈተ። የሎሬቱ ሀውልት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆምላቸው ነው።
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን አምቦ ካበቀለቻቸው ባለ ምጡቅ አዕምሮ መካከል በስነፅሁፍና በትያትር ዘርፍ በፈርጥነት የሚጠቀሱ ምሁር ቢሆኑም፤ በሚገባቸው ልክ ክብር እንዳለተሰጣቸው በሎሬቱ ስም ዛሬ በአምቦዩኒቨርሲቲ የመታሰቢያ የባህል ማዕከል በተከፈተበት ወቅት ተገልጿል።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ታደሰ ቀና እንዳሉት፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የጥበብ ሰው ብቻ ሳይሆኑ የሰብአዊ መብትሟጋች ነበሩ። በስራዎቻቸው በሀገራቸው የተዘጉትን ታሪካዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች ሲተቹና እንዲስተካከሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ነበር፡፡በዩኒቨርሲቲው የተቋቋመው የባህል ማዕከል ሁለት አላማ ያለው ሲሆን፤ አንዱ አዲሱ ትውልድ ታላላቆቹን እንዲያውቅ፣ የሰሩትን ስራ እንዲረዳና አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን በወቅቱ ክብር ይናፍቀኛል ተቻችሎ የሚኖር ህዝብ ያስቀናኛል ድንቁርና ያስፈራኛል ጦርነት ያስጠላኛል ሲል ህብረብሄራዊ አንድነትን ፣ብልፅግናና ሰላምን የሰበኩ የጥበብ ሰው ናቸው፡፡

ዛሬ ለሀገራችን የሚያስፈልጋትም ይህ ነው ብለዋል፡፡በዕለቱም አንጋፋ አርቲስቶች ፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የሎሬቱ ቤተሰቦች፣ የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች የተገኙ ሲሆን ለማዕከሉ ማደራጃና ለሚቆመው ሀውልት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ የመስክ ጉብኝት አደረጉ!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ የመስክ ጉብኝት አደረጉ።ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የግምባር ቀደም አርሶ አደሮችን የቡና ማሳ የጎበኙ ሲሆን፥ አርሶ አደሮቹ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በመጠቀምና ያረጁ ቡናዎችን በመጎንደል ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል። የክልሉ መንግስት በዚህ ዓመት ለቡና ልማት 147 ሚሊየን ብር መመደቡን የገለፁት አቶ ሽመልስ፥ የገበያ ትስስር ለማጠናከር ለባለሀብቶች እና የህብረት ስራ ማህበራት ብድር የሚውል 15 ቢሊየን ብር መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በመሆኑም የጅማ ዞን አርሶ አደሮች የቡናን ጥራት በመጠበቅና ለአቮካዶና ሌሎች ቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ለንብ ማነብ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
ሰሞኑን በአማራ ወጣቶች(ፋኖ) እና በኦሮሞ ወጣቶች (ቄሮ) መካከል በባንድራ እና በጽሁፎች ላይ አለመግባባት ተፈጥሯል።በሁለቱም አካል ለጉዳዩ መነሻ የሚሰጡ ምክንያቶች አሉ። የኦሮሞ ወጣቶች እንደሚሉት ከሆነ በወሎ ደሴ ከተማ አንድ የኦሮምኛ መጽሀፍ ያሳተመን ድርጅት የአማራ ፖሊስ እና ፋኖ አሽገውታል ለእሱም አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት ነው ይላሉ። በአንጻሩ የአማራ ወጣቶች እንደሚሉት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በሚያመሩ አማርኛ ጽሁፍ ያለባቸውን መኪናዎች መንግድ ላይ የኦሮሞ ወጣቶች አስቁመው ጽሁፉን ማንሳታቸው ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ትላንት እና ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ኮያ ፈጬ እና ቦሌ ቡልቡላ ላይ በወጣቶቹ መካከል አለምግባባት ተፈጥሮ ሰንብቷል። የሚመለከተው የመንግስት አካል እስካሁን በጉዳዮቹ ላይ መግለጫም ይሁን መረጃ ልህዝብ ያልሰጠ ሲሆን ህዝቡ በአንጻሩ ይህን የግጭት ጅማሮ መንግስት ባስቸኳይ ካላስቆመው ጉዳዩ ወደ ለየለት ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ማለዳ ሚድያ አነጋገሬያቸዋለው ያላቸው ሰዎች ገልጸዋል።

Via Maleda Media
@YeneTube @FikerAssefa
የማህጸን በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እየተሰጠ ነው።

ክትባቱ እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፥ እድሜያቸው ከ14 አመት ጀምሮ ላሉ ሴት ልጆች በትምህርት ቤቶች እና በጤና ጣቢያዎች የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሀላፊ በክትባቱ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፥ በሽታው በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ በሸታዎች ከጡት ካንሰር በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።ክትባቱ ምንም አይነት የጎንዮሽ ችግር የሌለው ሲሆን፥ በስድስት ወር ልዩነት ለሁለት ጊዜ የሚወሰድ መሆኑንም ተናግረዋል።በአዲስ አበባ ከተማ ክትባቱ በዘመቻ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን፥ በዘንደሮው ዓመት ከ23 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴት ልጆች ክትባቱን ለመስጠት ታቅዷል።

ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የጎንደር የጸጥታ ሁኔታ!!

ሰሞኑን በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው ሲጣራ ከነበሩ 119 ተጠርጣሪዎች መካከል ሃምሳ ስምንቱ መለቀቃቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። የከተማው የሰላም እና የህዝብ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን እንደገለፁት በግጭቱ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እና ሰዎች መፈናቀላቸውን ተናግረዋል። ስለ ሟቾቹ እና ተፈናቃዮቹ ብዛት የተጠየቁት ኃላፊው ቁጥሩን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። የጎንደር ከተማን ተዘዋውሮ የተመለከተው የDW ዘጋቢ የከተማው ነዋሪው መደበኛ የዕለት ከዕለት ስራውን ሲያከናውን ታዝቧል። አቶ ተስፋም በጎንደር ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ያለው ሰላም ወደ ቀድሞው ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል እና በሶማሌ ክልል መካከል የተፈጠረ ችግር በውይይት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሰላም ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ዘላቂ መፍትሔ ዳይሬክተር ጄኔራል ምግባሩ አያሌው እንደገለፁት ሚኒስቴሩ ወደ ሁለቱ ክልሎች የላከው የልዑካን ቡድን የሁለቱን ክልሎች የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንስ ለማካሄድ ከስምምነት ደርሰዋል።

ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሰው ግብረ ኃይል ለችግሩ እልባት ለመሻት መጠነ ሰፊ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተር ጀኔራሉ ፣ የመፍትሄ ሃሳቦች ጎን ለጎን በመሰጠት እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አክለዋል። በዋናነት ለችግሩ እልባት ተሰጥቷል፤ በቀጣይነት ዘላቂ የሆነ ሰላም በአካባቢው እንዲኖር የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰራም ተናግረዋል።

Via:- EBC
@YeneTube @FikerAssefa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ግብጽ እና ኢትዮጵያን እያወዛገበ ያለው በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ቀጥሏል። በሚቀጥለው ዓመት ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ የተባሉት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ግንባታም በመከናወን ላይ ይገኛል። የግድቡ ሰሞነኛ መልክ ምን እንደሚመስል ከቪዲዮው ይመልከቱ።

Via:- Dw
@YeneTube @Fikerassefa
የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ሲባል ከዓለም አቀፍ ዋጋ እጅጉን አሳንሶ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ እና የኮንትራት ክህደትን ለማስቆም አዲስ ግብረ ሃይል መቋቋሙን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ። ግብረ ኃይሉ የተቋቋመው በሚኒስቴሩ፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን አና በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሲሆን በተለይም አንዳንድ እንደ ሰሊጥ እና ቡና ያሉ የግብርና ምርቶች ወደ ውጭ ለመላክ ሲባል በተጋነነ ዋጋ ከአምራቾች መግዛትን በመከላከል አኳያ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም ዋጋ አሳንሶ በመሸጥ ተጠርጥረው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቡና ነጋዴዎች መታገዳቸው ይታወሳል።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሶዴፓ/ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ሊተገበር ጫፍ የደረሰውን ኢህአዴን ወደ አንድ ውህድ ፓርቲ ለመለወጥ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ አስታውቋል።

ባለፉት 27 ዓመታት የፌዴራሊዝም ስርዓት በሚገባ እየተገበረ እንዳልነበረ ያስታወሰው ፓርቲው ኢህአዴግ ባለፉት አመታት የነበሩትን ስኬቶች ለማስቀጠል፣ የነበሩትን ስህተቶች ለማረምና አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር እንዲሁም አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ እራሱን ለመለወጥና አጋር ድርጅቶችንም ለማቀፍ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በስራ ላይ ካለው የፌዴራል ስርዓት ጋር የማይቃረን እና አሃዳዊ ስርዓት የመፍጠር ዓላማ የሌለው ነው ብሏል።

@YeneTube @Fikerassefa
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ክርስቲያን ታደለ ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት ፍርድ ቤት ቀን ቆርጧል፡፡ ለክስ መመስረቻ ከጥቅምት 7 ጀምሮ 15 ቀናት እነደፈቀደ ንቅናቄው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ በጥቅምት 7ቱ ችሎት ዐቃቤ ሕግ ክስ መመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ባለው አቤቱታ ላይ ለመወሰን ነበር ችሎቱ ዛሬ የተሰየመው፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን ባንዲራ ቤተክርስቲያን ላይ ሰቅላችኋል፤ ለበዓልም በአደባባይ ይዛችሁታል በማለት ምዕመናንን የሚያስሩ እና የሚያዋክቡ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ- ብሏል ማኅበረ ቅዱሳን በፌስቡክ ገጹ ያሰራጨው የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ መግለጫ፡፡ ጸረ-ቤተክርስቲያን ርዕዮተ ዐለም ቀርጸው የሐሰት ታሪኮችን በመገናኛ ብዙኻን የሚነዙ አክቲቪስት ነን ባዮችንና ፖለቲከኞችን መቃወም ያስፈልጋል፡፡ ለጉዳዩ ቤትክርስቲያኗ ኮሚቴ እንድታቋቁም፣ ዐለም ዐቀፍ ሰላማዊ ሰልፍም እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

-Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
«በድሬደዋ ከተማ የሰዎች ሕይወት አልፏል በሚል» ተቃውሞ አዲስ አበባን ከድሬደዋ እና ሀረር ጋር የሚያጘናኘው ዋና መንገድ ትናንት ቆቦ እና ጨለንቆ አካባቢዎች ለሰዓታት ዝግ ሆኖ ከቆየ በኋላ ተከፍቷል።በዚሁ ሳቢያ ከምሥራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ አካባቢዎች ወደ ድሬደዋ ይገባ የነበር ጫት እና ሌሎች አትክልቶች ሳይገቡ ውለዋል፡፡ የሰው ሕይወት መጥፋት ለመንገዱ መዘጋት ምክንያት ነው በሚል በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ቢሰራጭም፤ የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ የሞተ ሰው አለመኖሩን በማመልከት፤ ግጭት ለማባባስ የተደራጁ አካላት የሚነዙት ወሬ ነው ሲል ገልጿል። 

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ምክር ቤቱ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ይወያያል!

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል።ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ነው ስብሰባውን የሚያካሂደው።በስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ላይ የቀረበ የድጋፍ ሞሽን የሚያጸድቅ ይሆናል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

-Fana
@YeneTube @FikerAssefa
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በ ፓሪስ ተገናኝተው ተወያይተዋል።ውይይታቸው በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በዘርፈ~ብዙ ትብብር ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ በተለይ በሃገራቱ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር በትኩረት ለማሻሻል መግባባት ላይ ደርሰዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በጣሊያን እና በፈረንሳይ የነበራቸውን የውጭ ሃገር የስራ ተልዕኮ አጠናቀው ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

#DPMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa