የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ102 ኢንቨስተሮች 56 ሺህ ሄክታር መሬት መቀማቱን አስታወቀ።
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የእርሻ ኢንቨስትመንት ፈቃድ በማውጣት 651 ባለሀብቶች ወደ 350 ሺህ ሔክታር መሬት ወስደዋል፡፡ክልሉ አጠቃላይ የአፈፃፀም ግምገማ ባደረገበት ወቅት 102 የሚሆኑት ባለሀብቶች በአግባቡ ባለማልማታቸው የተቀሙ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ በየነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች በእርሻ ኢንቨሰትመንት ስም ወስደው ባላለሙት ላይ እርምጃ ተወስዷል።
በክልሉ በዚህ ስራ ዘርፍ ከተሰማሩ 651 ባለሃብቶች ውስጥ ከ102ቱ ባለሃብቶች 56 ሺህ ሄክታር መሬት ተቀምተዋል። እነዚህ ባለሃብቶች ከክልሉ ለአርሻ ስራ በሚል የተሰጣቸውን መሬት በማስያዝ ከልማት ባነክ ብደር በመውሰድ ገንዘቡን ለእርሻ ስራ ማስፋፊያ ከማዋል ይልቅ በአዲስ አበባ ፎቅ እንደገነቡበት በተደረገው ክትትል አረጋግጠናል ብለዋል።ልማት ባንኩ መሬቱን የያዘ መሆኑንን ገልፀው ፎቆቻቸውንም ቢሆን ሸጠው መክፈል አለባቸው የሚለው ጉዳይ ላይ ክልሉ እየሰራ መሆኑንም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡
በአግባቡ ባለማልማታቸው ሲባል ምን ለማለት ነው ስንል የክልሉን ባለስልጣን ጠይቀናል፡፡እርሳቸው ምላሸ ሲሰጡ እንዳሉት በትራክተር አርሳለሁ ብሎ በአህያ የሚያርሱ አልሚዎች መገኘታቸውን የነገሩን ሲሆን በተሰጣቸው መሬት ላይ ከሰል በማክሰል የተፈጠሮ ሀብትን ሲያወድሙ ነበር ብለዋል፡፡ከእነዚህ ባለሀብቶች ላይ የተነጠቀው መሬት እጣ ፋንታ ምን ይህናል ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄም ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው የወጡ ተማሪዎችን አደራጅተን እንዲያለሙ እናደርጋለን ሲሉ መልሰዋል።
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

Forwarded from YeneTube
Brand New Samsung A20 (2019)
32GB Internal Storage
3GB RAM
FOR MORE INFORMATION GO TO 👉 https://m.dalibr.com/ProductDetailM.php?proid=11

ኢ/ር ታከለ ኡማ የኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን ለተማሪዎች ምቹ አድርጎ ያደሰውን ት/ቤት ተመልክተዋል፡፡
የኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን በዛሬው ዕለት የተባበሩት መምህራን የአጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት እድሳትን በማጠናቀቅ ለአከባቢው ነዋሪዎች አስረክቧል፡፡
የኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን ከተባበሩት መምህራን አጸደ ህጻናት በተጨማሪ የጎሮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እድሳትን አከናውኗል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ የመማሪያ ስፍራዎቹ ለተማሪዎች ምቹ እንዲሆኑ የኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን ላከናወነው ደረጃውን የጠበቀ እድሳት በተማሪዎቹ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ቤት ዕድሳትን ጨምሮ ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚያደረገው የዩኒፎርም እና የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እና የምገባ መርሃ ግብር በሚቀጥሉት ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢ/ር ታከለ ኡማ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
Via Mayor Office

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ትብብር ገምጋሚ ቡድን (ICRG) ክትትል ሂደት መውጣቷ ተገለፀ!
ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጽ/ቤታቸው ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተወጣጡ ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እንዲሁም ሽብርተኝነትንና የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች ብዜትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስርዓቷን በከፍተኛ ደረጃ ያሻሻለች መሆኗን ዓለም አቀፍ ገምጋሚ የሆነው የፋይናንስ ግብረ- ሀይል (FATF) በመገምገም ጥቅምት 07 ቀን 2012 ዓ.ም ውሳኔ ማስተላለፉን ገልፀዋል፡፡
ምንጭ:የሰላም ሚኒስቴር

ግብጽ እና ኢትዮጲያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የጀመሩት ድርድር ካልተሳካ ወታደራዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ግፊት ማድረጋቸወን ቀጥለዋል።
አምስት ቢሊየን ዶላር እንደሚፈጅ በተነገረለት እና ሰባ በመቶም ግንባታው በተጠናቀቀው ግድብ ዙሪያ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተደረገው ውይይት ያለስኬት ተጠናቋል፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለአንድ መቶ ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልገውን የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎት እንደሚያሟላ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
ከኢትዮጲያ ተቃራራቢ የሕዝብ ብዛት ያላት ግብፅ የግድቡን የውሃ ማጠራቀሚ የመሙላት ሂደት የግብጽን የውሃ ድርሻ ይቀንሰዋል የሚል ስጋት አላት፡፡
የእስራኤሉ ዘ ታየምስ ኦፍ አስራኤል የተሰኘው የህትመትና የድረገጽ ሚዲያ ሰፋ አደርጎ ባወጣው ሀተታ ለመንግስት ቅርበት እንዳለው የሚነገርላቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ግድቡ ለግብጽ ብሔራዊ ደህንነት ስጋት ስለሆነ መንግስት ወታደራዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል በማለት ግፊት እያደረጉ ይገኛል፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/Yenetube-10-22-3

የደቡብ ጎንደር ዞን አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም በማሰብ ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ( አብን) የደቡብ ጎንደር ዞን ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሁለት አመራሮች ዛሬ በዋስ መለቀቃቸውን አብን አረጋገጠ።
የአብን ሊቀ መንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ የንቅናቄው የደቡብ ጎንደር ዞን ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቢሰጥ አሰፋ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጌታቸው አዱኛ በ5ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከእስር መፈታታቸውን ለዶቼቬለ በስልክ አረጋግጠዋል።ዶክተር ደሳለኝ እንዳሉት «ፖሊስ በተጠረጠሩበት ወንጀል ምስክር አለኝ ብሎ ነበር ።ምስክርም አላቀረበም።የስልክ ቅጅም አናቀርባለን ብሎ ነበር የስልክ ቅጂውም አልቀረበለትም።»ብለዋል ዶክተር ደሳለኝ።ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ሁኔታውን ከመረመረ በኋላ ከዚህ በላይ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት ተገቢ አይደለም ሲል በዋስትና ይለቀቁ ብሎ በወሰነው መሠረት ዛሬ በ5ሺህ ብር ዋስ መፈታታቸውን ተናግረዋል።ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በዋስ እንዲለቀቁ የወሰነው ትናንት ያስቻለው የደብረ ታቦር ወረዳ ፍርድ ቤት ነው። ሁለቱ የአብን ሃላፊዎች ከታሰሩ ከሶስት ሳምንት በላይ እንደሆናቸው ዶክተር ደሳለኝ ተናግረዋል።
Via DW

ሰኞ መስከረም 10/ 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ወረዳ 12 ከረፋዱ 3 ሰዓት ጀምሮ በተፈጠረ የወጣቶች ግጭት የተወሰኑት ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ሲገቡ እስከ ሁለት መቶ የሚደርሱት ለእስር መዳረጋቸውን ዶቼ ቬለ / DW /ያነጋገራቸው የአካባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ግጭቱ የተቀሰቀሰው አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ቀለም ያለውና ከጀርባው የምኒልክ ምስል የታተመበትን ቲሸርት "ለምን ለበስሽ? " ፤ " ብለብስስ " በሚል የተጀመረ ነው ያሉት የአይን እማኞች ሁኔታው ከአካባቢው ፖሊስ አቅም በላይ ሆኖ በርከት ያሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከደረሱ በኋላ ሊበርድ መቻሉንም ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ ወደ 2 መቶ የሚደርሱ ወጣቶች ታስረው እንደነበርና አብዛኞቹ ቢፈቱም ወደ 50 ያህሉ አሁንም አለመፈታታቸውንም አስታውቀዋል።
ችግረል በተከሰትልበት ክፍለ ከተማና የአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ጣቢያ ተገኝተን እንደተመለከትነው ፣ ወጣቶች ታስረዋል ጠያቂዎችም ያለ እረፍት ወደ ጣቢያው ሲገቡና ሲወጡ ተመልክተናል። ጥፋቱን አደረሱ የተባሉትን ወጣቶች እንዲሁም የከተማዋን ፖሊስ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ሊሳካ አልቻለም።
Via :- DW

አሳሳቢ እየሆነ የመጣዉ የፆታ ጥቃት በትግራይ
በትግራይ ክልል ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች በቂ ትኩረት ባለማግኘታቸው ተባብሰው መቀጠላቸው ተገለፀ።
በፆታ ጉዳይ ያለው የተዛባ ማሕበራዊ ግንዛቤ ማረም ባለመቻሉና መንግስት ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠቱ ችግሮቹ ተባብሰው እንዲቀጥሉ እንዳደረገ የሴቶች መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ፡፡
በትግራይ ክልል ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች በቂ ትኩረት ባለማግኘታቸው ተባብሰው መቀጠላቸው ተገለፀ፡፡ በፆታ ጉዳይ ያለው የተዛባ ማሕበራዊ ግንዛቤ ማረም ባለመቻሉና መንግስት ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠቱ ችግሮቹ ተባብሰው እንዲቀጥሉ እንዳደረገ የሴቶች መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት የወጣው የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያመለክተወ በትግራይ ክልል 12 በመቶ ሴቶች በየዕለቱ ፆታዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡
በክልሉ ከሚኖሩ ያገቡ ሴቶች መካከል 18.7 በመቶ በባሎቻቸው አካላዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 81 በመቶ በትግራይ ገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች በወላጆቻቸው ወይም አሳዳጊዎቻቸው አልያም የቀርብ ሰው ተገደው ትዳር እንዲመሰርቱ ይደረጋል፡፡
እነዚህና ሌሎች ሁነቶች በክልሉ ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች የከፋ መሆኑ ያመለክታሉ። በትግራይ ፆታ ተኮር ጥቃቶች ትኩረት እንዲያገኙ ከሚንቀሳቀሱ ሴቶች መካከል የሆነችው ዶክተር ሄለን ቴድሮስ በምትሰራበት መቐለ ሆስፒታል ሴቶች በባሎቻቸው፣ የፍቅር ጓደኛቸው አልያም ሌላ ሰው ጥቃት ደርሶባቸው ለህክምና እንደሚመጡ ትናገራለች፡፡
እንደ ዶክተር ሄለን ምልከታ በሁሉም የዕድሜ ደረጃ የሚገኙ ሴቶች ፆታዊ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ቢሆንም ለአቅመ ሄዋን ባልደረሱ ሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ መጥቷል ትላለች፡፡
በተለይም በትግራይ ገጠር አካባቢዎች ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ የከፋ ነው፡፡
በርካታ ሴቶች ከተደፈሩ በኋላ ደፋሪዎቻቸው እንዲያገቡ ይደረጋል፡፡ በትግራይ ክልል ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በመቃወም ከሚንቀሳቀሱ መካከል የሆነችው ዳናይት መኮንን ጥቃቱ አሳሳቢ ከመሆኑም በተጨማሪ ፍትሕ ዙርያ ያሉ ክፍተቶች ችግሩ የተባባሰ አድርጎታል ትላለች፡፡
Via:- Dw
@YeneTube @YeneTube

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኢትዮጵያ የነበረባትን 163.6 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ መሰረዛቸውን ሞስኮ ታይምስ ዘግቧል።
እንደዘገባው ሞዛምቢክ $40 ሚሊዮን ፣ ማዳጋስካር $89 ሚሊዮን እንዲሁም ታንዛኒያ መጠኑ ያልታወቀ የብድር መጠን ተሰርዞላቸዋል።
Via:- Eshet bekele
@YeneTube @FikerAssefa
እንደዘገባው ሞዛምቢክ $40 ሚሊዮን ፣ ማዳጋስካር $89 ሚሊዮን እንዲሁም ታንዛኒያ መጠኑ ያልታወቀ የብድር መጠን ተሰርዞላቸዋል።
Via:- Eshet bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት እኩለሌሊት ላይ የጀዋር መሀመድን ጠባቂዎች በሌሎች ለመቀየር ትዕዛዝ መተላለፉን እና ውሳኔው ለምን እንደተላለፈ ግልፅ እንዳልሆነለት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል። ይህንን ተከትሎ በሀረርጌ ደደር፥ኮምቦልቻ ሂርና እና ሌሎች ከተሞች መንገድ ዝግ ሆኗል። በአርሲም ከአሁን ሰዓት ጀምሮ መንገድ መዝጋት ተጀምሯል።
ምንጭ: ማለዳ ሚድያ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: ማለዳ ሚድያ
@YeneTube @FikerAssefa
ከጀሞ ቁጥር ሁለት ወደ መሀል አዲስ አበባ የሚመጣው መንገድ ጠዋት 12 ሰአት ላይ የተወሰኑ ወጣቶች መንገዱን ከዘጉት በኋላ 1:10 ገደማ ክፍት ማድረጋቸውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ደውዬ ጠይቄያለው።በአካባቢው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የባጃጅና የታክሲ መኪኖች ቁጥሮች ግን ከወትሮ በተለየ መልኩ ዛሬ ጠዋት ቀንሰዋል።
ምንጭ:- ተስፋዬ ጌትነት
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:- ተስፋዬ ጌትነት
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ ያለው የአክቲቪስት ጃዋር መሀመድ ቤት ብዙ ወጣቶች ቆመው ይታያሉ።የመከላከያ ዪኒፎርም የለበሱ ኮማንደሮች በአካባቢው ይገኛሉ።
አክቲቪስቱ ትናንት ለሊት የመንግስት ፀጥታ ሀይሎች ቤቱን ከበው እንደነበር በፌስ ቡክ ገፁ አሳውቆ ነበር።
Via:- Tsefay Getenet
@Yenetube @Fikerassefa

አሁን በደረሰኝ ዜና ጀሞ አንድ ኮንዶሚንየም አካባቢ ሱቆች ተዘገተዋል ። ድንጋይ የሚወረውሩ ወጣቶች በፊዴራል ፓሊስ ጋር እንዲበተኑ እየተደረገ ነው። ወላጆች ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት እያስወጡ ነው።
Via:- ተስፋዬ ጌትነት
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- ተስፋዬ ጌትነት
@YeneTube @Fikerassefa