YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አፍሮ-ፅዮን ኮንስትራከሽን በአማራ ክልል በዋግህምራ ዞን ሰቆጣ ወረዳ ድብርሳይል አንደኛ እና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ግንባታውን አከናውኖ መስከረም 05 ቀን 2012ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በሚገኙበት ያስመርቃል፡፡

ት/ቤቱ በውስጡም
📌 ሁለት ብሎኮች እያንዳንዱ አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሉት በድምሩ ስምንት ክፍሎች
📌 አንድ ብሎክ የላብራቶሪ ክፍል በውጡ ሶስት ክፍሎች ያሉት የሳይንስ ክፍል፣ የዳይሬክተር ቢሮ እና የስታፍ ክፍል የያዘ
📌 አንድ ብሎክ ሁለት ክፍሎች ያሉት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል
📌 ሁለት ብሎኮች እያንዳንዳቸው ስምንት በር ያላቸው የመፀዳጃ ቤቶችን በአጠቃላይ የገንዘብ መጠን በ7.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ገንብቶ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የበኩሉን ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

መረጃው የደረሰኝ ከድርጅቱ ነው።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ሄርማን ኮኸን(የቀድሞ የUnited States የአፍሪካ ህብረት ረዳት አምባሳደር የአማራን ሕዝብ የገለጹበት መንገድም ሆነ የገለጹት ጉዳይ ይዘት ትክክል እንዳልሆነ ተናግረናል።ዛሬ በቲውተር ገጻቸው የአማራን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል። ወደፊትም ለአገላለጻቸው ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

Via አሰማኸኝ አስረስ
@YeneTube @FikerAssefa
ካፒታል ጋዜጣ የሳይበር ጥቃት ደረሰበት። ጥቃቱ የጋዜጣውን የ21 አመት መረጃ እውድሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለተለያዩ ባለሀብቶች ያበደረው 5 ቢሊዮን ብር የማይመለስበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተሰምቷል። 16 ቢሊዮን ብር ብድር በመበላሸቱ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ባንኩ ከዚህ ውስጥ 11 ቢልዮን ብር መመለሱ የሚያጠራጥር ሲሆን 5 ቢልዮኑ ግን ማስመለስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድርሱን ከባንኩ ሪፖርት ተረድቻለው ብሏል አዲስ ማለዳ ጋዜጣ በዛሬ እትሙ።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ ሕልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ከ100 ዓመት በላይ የተሰበሰቡ እጽዋቶችን የያዘው ሙዚየም አደጋ ላይ ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ሳይንስ ፋኩልቲ ከ100 ዓመታት በላይ ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ የተሰበሰቡ የእጽዋት እና እንስሳት ናሙናዎችን የያዘው የሙዚየም ህንጻ አደጋ ላይ እንደሚገኝ ባለሙያዎች ገለጹ። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በበኩሉ ጥናት አድርጎ በቅረቡ ህንጻውን ለማደስ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ስፖርት!!!

ከምን ጊዜም የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ካሜሮናዊው የቀድሞ የማዮርካ፣ ባርሴሎና ፣ ኢንትርሚላን፣ አንዚ ማካቻካላ፣ ቼልሲና ትራንዝ ቡሳስፖር አጥቂ ሳሙኤል ኤቶ ጫማውን ሰቅሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ:

የኦሮሚያ ቤተክሀነት ፅ/ቤት እንዲቋቋም በመጠየቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክተርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስን በመጠየቅ የሰጠው መግለጫ ጥፋት ነው በማለት የኮሚቴው አባላት ይቅርታ እንዲጠይቁ ብፁሃን አባቶች ለማስገደድ ብሞክሩም የኮሚቴው አባላት ያጠፋነው ነገር የለም በማለት ይቅርታ መጠየቅ አይገባንም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምክኒያቱም መግለጫ የተሰጠው፡-

1⃣ኛ. የቤተ ክርስትያኗን ቀናኢ ልጆችን ብሶትና ፍላጎትን ለመግለፅ ነው

2⃣ኛ. ላለፉት 27 አመታትና ከዚያ በፊት ባሉ ጊዜያት ለህዝቡ በተለይም ለኦሮሞ ህዝብ ተደራሽ ያልሆነ መዋቅርና የአገልግሎት አሰጣጠት ችግር ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ

3⃣ኛ. ቋሚ ሲኖዶሱ መግለጫ እንዳይሰጥ ከልክሏል ብለን ስለማናምን

4⃣ኛ. ህዝቡ መግለጫውን በከፍተኛ ተነሳሽነት የሚጠብቅ ስለሆነ መግለጫው በመቅረቱ ምክኒያት የሀገሪቱ ሰላም እንዳይደፈርስ

5⃣ኛ. እንዲያውም ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ከሆነ መጠየቅ ያለባቸው ላለፉት አመታት ስር የሰደደውን የቤተ ክርስትያኗን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ ቤተ ክርስትያኗን የፖሊትካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶቻቸው ሎሌ ያደረጉ ብፁሃን አባቶች በመሆናቸው ህዝቡን ይቅርታ በይፋ ጠይቀው ህዝቡን እንዲክሱ በትህትና በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን:: በአጠቃላይ በእነዚህና አያሌ አሳማኝ ምክኒያቶች ያለጥፋታችን ይቅርታ ጠይቁ የተባልነውን አስገዳጅ ኣካሄድ አልተቀበልንም፡፡

የኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ
ጳጉሜ 2፣ 2011 ዓ.ም

@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
የኢ/ኦ/ተ/ቤ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

#ELU
@YeneTube @FikerAssefa
ከስንፈት እንዴት መላቀቅ እንችላለን አስተማሪ ቪዲዮ ነው ይመልከቱት⬇️⬇️

https://www.youtube.com/watch?v=Ye4PYTkdGpE
የሹመት ዜና!

አቶ ጌትነት ይርሳው ቦጋለ ከጳጉሜ 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት አስታወቀ።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
#Fact_check
አቶ ጌትነት የክልሉ ቃል አቀባይ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትን አሳማህኝ አስረስን በመተካት ነው የተሾሙት። አቶ ጌትነት "የጀንበር ዕድሜ ስንቅ" የተሰኘ መጽሐፍ ደራሲ ናቸው።
@YeneTube @FikerAssefa
የሲኖዶሱ ምልኣተጉባኤ እንኳ ሳያሟላ በሲኖዶስ ስም ለውሳኔ መቻኮል አግባብነት የለውም ብሏል የኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ፡፡

ከኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ ጋር በስፋት በቀጣይነት መወያየት ኣለብን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ አንሰጥም ያሉ የሲኖዶስ አባላት ስብሰባውን #ለቀው_እንደወጡ ምንጮች ኣረጋግጧል፡፡

የሲኖዶሱን ስብሰባ ትተው ከወጡት መካከል #የሰሜን_ሸዋ_ደብረብርሃንሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡና #ቄሌሜንጦስ#የአርሲ ሀገረስብከት ልቀጳጳስና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ #አቡነ_ያሬድ፤ የደቡባዊ #ትግራይ መህጮህ ሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡነ ዲዎስቆሮስ፤ የኢሉ አባቦር ሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡነ ሚካኤል ይገኙበታል ተብሏል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ብዙ የሲኖዶስ አባላት ስብሰባው ላይ እንዳልተገኙ ነው ምንጮች የገለፁት፡፡የቦረና ዞን ሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ፤ የደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን ሀገረስብከት አቡነ ሳዊሮስና ብዙ የሲኖዶሱ አባላት ከሀገር ውስጥም ከውጭ ሀገርም አልተሳተፉም ተብሏል፡፡

Via OMN
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ርዕሰ-መስተዳድሩ በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢ ስለሚንቀሳቀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የኦሮሚያ ቤተ-ክሕነት ለማቋቋም ከቀረበው ጥያቄ በኋላ ከቤተ-ክርስቲያኗ ጋር ስላደረጉት ውይይት ንግግር አድርገዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa