YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ጨምሮ የአመራር ሽግሽግ አደረገ።

በትናንትናው እለት በተደረገው በዚህ ሹመትና የአመራር ሽግሽግ፦

1. አቶ መልካሙ ወርቁ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣

2. አቶ ቦንቴ ቦቼ የከተማዋ የደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ፣

3. ኮሌኔል ሮዳሞ ኪአ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ፣

4. ምክትል ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ የፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እና

5. አቶ ሀይለዮሐንስ ነጌሶ የቤቶች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ መስጠቱን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

Via:- Hawassa City Administration
@YeneTube @FikerAssefa
#Reminder - AAU

Regular undergraduate students registration for 2019/20 academic year is on September 16&17,2019(መስከረም 5 እና 6,2012)
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ያረፉትን የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ለማሰብ የሀገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት ዝቅ ብሎ እንዲውለበልብ ትዕዛዝ ሰጡ። ሙጋቤ 95 ዓመታቸው ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው መድሀኒት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡
+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
የድሬዳዋ ፖሊስ 146 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ አቃጠለ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የ2011 ዓ. ም. በከተማዋ የያዘውን 146.53 ኪሎ ግራም የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ ክምችት በዛሬው ዕለት አቃጠለ። የከተማይቱ ፖሊስ እርምጃውን የወሰደው በፍርድ ቤት በተላለፉ ውሳኔያዎች መሠረት ነው ተብሏል። ዛሬ የተቃጠለው አደንዛዥ ዕፅ «በአብዛኛው ወደ ጎረቤት ሃገራት ሊሄድ የተዘጋጀ ነበር» ሲል የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል። «በኅብረተሰብ ጥቆማና ትብብር» እንደተያዘ የተነገረለት አደንዛዥ ዕፅ ክምችት የተቃጠለው ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የዓይን እማኞች በተገኙበት ነው።

በድሬዳዋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተበራከተ ለመጣው የወንጀል ድርጊት «ከተማዋን መናኸርያ ያደረገው የአደንዛዥ ዕፅ ንግድ ድርሻ ከፍተኛ ነው» የሚሉ ነዋሪዎች አሉ። የአደንዛዥ ዕፅ ንግዱ በተለይ በከተማዋ የሚገኘውን ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ቤቶች ተገን ባደረጉት አካባቢዎች በስፋት እንደሚስተዋል ነዋሪዎቹ ይጠቁማሉ። በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ዘርፍ ምክትል ኮምሽነር ማሆ ተሾመ «በአስተዳደሩ እየተበራከተ ያለውን የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ለመግታት ሰፊ ጥረት እየተደረገ» መሆኑን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የቀድሞ የካሜሩን አምባሳደር አስከሬን በክብር ተሸኘ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ. ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና አዳራሽ በተደረገው የቀድሞው በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደር ጃኩዌስ አልፍረድ አስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተገኝተዋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር አምባሳደር ጃኩዌስ አልፍረድ ሰዉ-አክባሪ ከመሆናቸው ባሻገር የኢትየጵያና የካሜሩን ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሰዉ እንደነበሩ ገልጸዋል። በጃኩዌስ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው እንዲሁም ለመላዉ የካሜሩን ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa
የአርቲስት ተዘራ ለማ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ አበረከቱ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ አበረከቱ።ለሰባት ተከታታይ ዙር በዚህ ክረምት በሃዋሳ በአገልጋይ እና በመልካም ወጣት ፕሮጀክት መሪ ዮናታን አስትባባሪነት ሲካሄድ የነበረው መርሃ ግብር የመዝጊያ ስነ ስርዓት በሚሌኒየም አዳራሽ ዛሬ ተካሂዳል።በስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት መልካም ወጣት ማለት ከማስመሰል ወደ መምሰል የሚያድግ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ማለት ወደ እውቀት፣ ጥበብና ፍቅር ወደ መስጠት ማደግ ነው ብለዋል።ሱስ ሀሺሽ ብቻ አደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ዘርን ከዘር እና ሀይማኖትን ከሃይማኖት ማባላትም ሱስ ነው ብለዋል።የውሸት፣ የዘረኝነት እና የዳተኝነት ብዙ ሱሰኛ ባሉበት ሀገር እናንተ ለማስተማሪያነት ተመርጣችኋል ብለዋል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ክብር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አሁን የፖለቲካ እና የዘር አጀንዳችን መጠቀሚያ እያደረግናት ነው ብለዋል።

የፕሮቴስታንት አምነት ተከታዮች የኦሮቶዶክስ ሀይማኖትን ማክበር እና መውደድ የምርጫ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ግዴታችሁም ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።ቤተክርሲያኗ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ አሻራ ማስቀመጧን በማንሳት፥ ቤተክርስቲያኗ ከእነ ክብሯ እንድትቀጥል እንፈልጋለን ብለዋል።
ሲያጠቃልሉም መልካም ወጣቶችም ሆኑ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አገልጋይ ዮናታን አክሉሉ ካሉበት የከፍታ ስፍራ እንዳይለቁ አሳስበዋል።የመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ ሀሳብ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በቅርቡ ኬሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለማዕከሉ ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል።

የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው እንዲህ ዓይነቱ በራስ ተነሳሽነት የነገን ባለ ተስፋዎች እና የሀገር ሀብት የሆኑትን ወጣቶች በማሰባሰብ ከወራት በላይ በጎ መምከር እና በጎ ማስታጠቅ በፈጣሪም በፅድቅ ትልቅ ቦታ እንዳለው እና ለሀገርም ትልቅ ታሪክ ሰሪነት መሆኑን ተናግረዋል።ሁሉም በየደረጃው በዚህ በመቅናት እና በመመኘት የራሱን ሪክ መስራት አለበት ነው ያሉት።እንዲህ ይቅርታና ፍቅርን የሚያስተምሩ ሺዎች ከተሰለፉ ወደ ሚሊዮኖች አድገን በአጭር ጊዜ ራእያችንን እናሳካለን ብለዋል።2009 ዓመተ ምህረት ላይ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በየክረመቱ ሲከናወን ቆይቷል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ለ152 ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች እዉቅና ሰጠ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አንዲት የራያ እናት ዛሬ ለጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮንን የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አቅርበዉ፤ የራያ ባህላዊ ልብስ አልብሰዋቸዋል። ለአዲሱ አመት ያላቸውን የአንድነትና አብሮነት ምኞትም አቅርበዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ 22 ልኳንዳ ቤቶች በዛሬው እለት መታሸጋቸው ተነገረ፡፡

የታሸጉት ልኳንዳ ቤቶቹ፣ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚሰሩ እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ መድሀኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን ተናግሯል፡፡22ቱ ልኳንዳ ቤቶች የታሸጉት የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸው፣ የሰራተኞች የጤና ምርመራ ያደረጉበትን ካርድ ያልያዙ እና ህጋዊ የቄራ ደረሰኝ ያልያዙ በመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡
የክፍለ ከተማው የምግብ መድሀኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን ከሶስት ቀናት በፊት ክትትልና ቁጥጥር አካሂዶ የ24 ሰዓት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበርም ተናግሯል፡፡ ሸገር ያነጋገራቸው የባለስልጣኑ አማካሪ አቶ ጌታቸው ወረቲ ልኳንዳ ቤቶቹ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው በተገኙ ጊዜ ወዲያውኑ ይከፈትላቸዋል ብለዋል፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ፖሊስ ዛሬ በአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ክርስቲያን ታደለ ላይ ተጨማሪ 28 ቀናት ችሎቱ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ተጠርጣሪው ግን ፖሊስ ምንም ማስረጃ ስላላቀረበ፣ በነጻ ልሰናበት ሲሉ ማመልከታቸውን ንቅናቄው በማኅበራዊ ሜዲያ ገጹ አስታውቋል፡፡ ችሎቱ በተጨማሪ ጊዜ ጥያቄው ላይ ጳጉሜ 5 ብይን ይሰጣል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ህብረት ቃል አቀባይ ኤባ ካሎንዶ ከደቂቃዎች በፊት እንዳሳወቀችኝ ህብረቱ ሱዳን ላይ ጥሎ የነበረውን እገዳ ዛሬ አዲስ አበባ አበባ አርጎት በነበረው የፀጥታ ምክር ቤት ስብሰባ አንስቷል።

via:- Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
የየኔቲዩብ ትክክለኛ የፌስቡክ በአማርኛም በእንግሊዝኛ ( YeneTube የኔቲዩብ )
ከ10000 ተከታዮች በላይ ያለሁ ሲሆነ ከዚህ ገፅ ውጪ የኛ አለመሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ይህንን ሊንክ ተጭናችሁ Facebook ላይ ታገኙናላችሁ⬇️⬇️⬇️
https://m.facebook.com/RealYeneTube/
ትምህርት ሚኒስቴር ከሰሞኑ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት በተወሰኑ የትምህርት አይነቶች ላይ ተመስርቶ የሚፈጸም ነው ማለቱ የተማሪዎችን ህልም ያጨለመ ነው ሲሉ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ተፈታኞች አስታወቁ።

ውሳኔው በተለይም ውጤታቸው ውድቅ በተደረጉ የትምህርት አይነቶች ላይ ጥሩ አቀባበልና ልዩ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች ህልም ያሰናከለ ነው ሲል አንድ ተማሪ ተናግሯል።

ይህ የመንግስት ችግር ተማሪዎችን ተስፋ እያስቆረጠ ግዴለሽም እያደረጋቸው ነው ያሉት ላለፉት 15 አመታት ለትምህርት ጥራት ጥናት ያደረጉ ባለሙያ ስርአቱ እምነት የታጣበት በመሆኑ ልዩ አሰራር ሊዘረጋ ይገባል ሲሉ አመልክተዋል።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ❗️

የእግር ኳስ ችሎታ አለን የምትሉ ዕድሜያቹ ከ18-20 አመት የሆናችሁ ወጣቶች የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ክለብ ለምልመላ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ቦታ :- ሲቪል ሰርቪስ

ማስታወሻ❗️ አዲስ አበባ #ከመገናኛ ወደ አያት ታክሲ ይዛቹ Civil service ብላችሁ መውረድ ትችላላችሁ።
@YeneTube @FikerAssefa
የድሬደዋ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች «ጥቅማ ጥቅም» ያሉት ክፍያ እንዲሰጣቸዉ በመጠየቅ ዛሬ የሥራ ማቆም አድማ መቱ።

ከአድመኞቹ አንዱ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት ሠራተኛው ከዚሕ ቀደም የሚያገኘዉ የማነቃቂያ ጉርሻ ወይም ቦነስ እንዲሰጠዉ ከረጅም ጊዜ በፊት ጥያቄ ቢያቀርብም የፋብሪካዉ ኃላፊዎች ተገቢዉን መልስ አልሰጡም።ሠራተኞቹ ዛሬ ጠዋት አድማ መምታታቸዉ እንደተሰማ የድሬዳዋ ፀጥታ አስከባሪዎች ወደ ፋብሪካዉ ቅጥር ግቢ መግባታቸዉን ሠራተኞቹ አስታዉቀዋል። ይሁንና ዛሬ ዉሎዉን ግጭትም ሆነ የፀጥታ መታጎል አልረፈጠረም። የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ የፋብሪካዉን ኃላፊዎች በስልክ ለማነጋገር ቢሞክርም አልተሳካለትም። ነባሩን የድሬደዋ ሲሚንቶ ፋብሪካ ገዝቶ ያስፋፋዉ የድሬደዋ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ በላይ ሠራተኞች አሉት ተብሎ ይገመታል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ድሬደዋ ዩንቨርስቲ !!

ድሬደዋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ከመጥራቱ በፊት #በችኩንጉንያ ወረርሽን የመከላከል ስራ መስራት አለበት ሲሉ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለየኔቲዩብ ተናገሩ።

እንደሚታወቀው ድሬደዋ ከ20000 በላይ በችኩንጉንያ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል። ሆኖም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይህ እንዳሰጋቸው አልደበቁም። ተማሪዎች ወደ ዩንቨርስቲ ከመግባታችን በፊት #አስፈላጊውን_ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ከወዲሁ ጠቁመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa