ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኢየሱስና የኒቅያ ጉባኤ ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ነጥብ አንድ
እግዚአብሔር ወልድ
እግዚአብሔር ወልድ በግሪኩ ቴኦ ሆ ሁዎስ Θεός ὁ υἱός God the son ሲሆን ባይብል ላይ ይህ አጠራር የለም ነገር ግን በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ ለኢየሱስ የተሰጠ አዲስ ማዕረግ ነው፣ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አብ በግሪኩ ቴኦ ሆ ፓተር Θεός ὁ Πατρὶ God the father የሚል 12 ጊዜ አለ፦
ዮሐንስ 6፥27 ገላትያ 1፥1 ኤፌሶን 6፥23 ፊልጵስዩስ 2፥11 ቆላስይስ 3፥17 1ኛ ተሰሎንቄ 1፥1 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥2 ቲቶ 1፥4 1ኛ ጴጥሮስ 1፥2 2ኛ የዮሐንስ 1፥3 ያዕቆብ 1፥27 ይሁዳ 1፥1
አባት ማለት አስገኚ ማለት ነው፣ ነገር ግን ጉባኤው ያጸደቀው አባት የሆነ አምላክ ሳይሆን ልጅ የሆነ አምላክ ነው፣ ነገሩ በዚህ ቢበቃ መልካም ነበር፣ ወደ ሚቀጥለው ነጥብ እንሂድ።

ነጥብ ሁለት
የተወለደ አምላክ
የአትናቴዎስ አንቀጸ-እምነት በጉባኤው ፦ ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፣ ከአብ ጋር በህላዌ የተስተካከለ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ የአንድ አብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፣ እርሱም ከአምላክ የተገኘ አምላክ ብሎ አውጇል፣ ይህ በዚህ ቢቆም ጥሩ ነበር ነገር ግን ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ በ 330 AD በተዘጋጀው በሳይናቲከስ እደ-ክታብ manuscript እና በ 350 AD በተዘጋጀው በቫቲካነስ እደ-ክታብ ላይ ሞኖጌነስ ቴኦስ μονογενὴς Θεὸς *ብቸኛ የተወለደ አምላክ* the only begotten God ብለው ባይብል ላይ ጨምረዋል፦
John 1:18 No one has seen God at any time; the only begotten God μονογενὴς Θεὸς who is in the bosom of the Father, He has explained Him.
New American Standard Bible, Aramaic Bible in Plain English,

ለምን ቃሉ ላይ ማንሸዋረር አስፈለገ? የተወለደው አምላክ የማይታየውን አምላክ ተረከው ትርጉም ይሰጣል? አምላክ ስንት ሊሆን ነው? አምላክ አምላክ ከወለደ ሁለት አይሆኑምን? ነገር ግን በ 400 AD በተዘጋጀው በአለክሳንድሪየስ እደ-ክታብ እና ከኒቅያ ጉባኤ በፊት በተዘጋጁት በፓፕይረስ 47፣ ፓፕይረስ 115፣ ፓፕይረስ 22፣ ፓፕይረስ 52፣ ፓፕይረስ 90 በመሳሰሉት ላይ *ብቸኛ የተወለደ አምላክ* የሚል የለም፣ ከዚያ ይልቅ ሞኖጌነስ ሁዎስ μονογενὴς υἱός *ብቸኛ የተወለደ ልጅ* the only begotten Son* የሚል አለ፦
John 1:18 No man hath seen God at any time; the only begotten Son μονογενὴς υἱός, which is in the bosom of the Father, he hath declared him.
King James Bible, American King James Version,American Standard Version, English Revised Version.

የተወለደው አምላክ የሚለው የተወለደ ልጅ በሚለው የተተካ መሆኑን የሚታወቀው ሌሎች ጥቅሶች የተወለደ ልጅ ብለው ማስቀመጣቸው ነው፦ ዮሐንስ 1:14 3:16 3:18 1ኛ ዮሐንስ 4:9

ነጥብ ሶስት
ዛሬ ወልጄሃለሁ
ዕብራውያን 1፥5 ከመላእክትስ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ γεγέννηκά፥
*ዛሬ* የሚለው ተውሳከ-ግስ ጊዜን የሚያሳይ ነው፣ ኢየሱስ ከአብ ለመወለዱ ጅማሬ ያለው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ ታዲያ ኢየሱስ ጅማሬ ካለው ወልጄሃለሁ የሚለውስ ቃል ምንን ያመለክታል? ጌኔካ γεγέννηκά ወልጄሃለሁ የሚለው ቃል ለተራራ አገልግሎት ላይ ውሏል፣ ታዲያ ፈጣሪ ተራራን ፈጠረው ወይስ ቃል በቃል የኒቅያ ጉባኤ እንደሚለን ወለደው?
መዝ 90:2 ተራሮች *ሳይወለዱ* γενηθηναι፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።

ተራራ ሆነ ኢየሱስ ተወለዱበት የተባለው ግስ ጌና γίνομαι to cause to be ሲሆን መፈጠርን የሚያሳይ ነው፦
አሞ.4:13፤ እነሆ፥ ተራሮችን *የሠራ*፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ …ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።

ታዲያ ኢየሱስ የተሰራ አይደለምን?
ኢሳይያስ 49.5 ..ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ *የሠራኝ* እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።

የተሰራ አምላክ አለን?
ኢሳይያስ 43:10፤ ከእኔ በፊት *አምላክ አልተሠራም* ከእኔም በኋላ አይሆንም።

እንዴትስ ኢየሱስ ብቻ ተወለደ ይባላል? ሌሎችስ የተወለዱ ልጆች እንዳሉ ያውቃሉ?
1ዮሐ.5:1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር *ተወልዶአል* γεγέννηται ፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ *የተወለደውን* γεγεννημένον ደግሞ ይወዳል።
ሐዋ 17:28-29 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ *ውልደቶቹ* γένος ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን። እንግዲህ የእግዚአብሔር *ውልደቶች* γένος ከሆንን፥

ማጠቃለያ
አምላክ አምላክን ከወለደ አንድ ሳይሆን ሁለት አምላክ ነው የሚሆኑት፣ ሰው ሰውን ሲወልድ ሁለት ሰው ይሆናሉ፦
ኢሳይያስ 51.2 ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፥ ባረክሁትም አበዛሁትም።

አብርሃም አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ እስማኤልንና ይስሃቅን ሲወልድ ተባዝተዋል፣ አምላክ አምላክ ከወለደም እንዲሁ ነው፣ የኒቅያ ጉባኤ ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ አብ አለ ካለ በኋላ ከዚያ ከአንድ አምላክ ከአብ ሌላ ማንነት ያለው አምላክ ከተወለደ አንድ አምላክ የሚለው አስተምህሮት ትርጉም ያጣል፣ ይህ የሃይማኖት መሪዎች የአንድ አምላክ አስተምህሮትን በሰው ትምህርት አደፍርሰው ለህዝቡ ያጠጡት ውሃ ነው፦
ሕዝ 34:19፤ በጎቼም በእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ።
ኤር 50:6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፥
ኤር 23:1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።

ለዚህ ነው አላህ በቁርአን ፦ የተወለደ ልጅ ለአላህ ማድረግ የጎደሎና የነውር ባህርይ አድርጎ ያስቀመጠው፦
18:4 እነዚያንም- አላህ *ልጅን ይዟል* ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው።
112:1-4 በል፦ እርሱ አላህ አንድ ነው። አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለርሱም አንድም ብጤ የለውም።
23:91 አላህ ምንም *ልጅን አልያዘም አልወለደም* ፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
19:35 ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም፤ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፤ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለዉ ኹን ነዉ ውዲያዉም ይኾናል።
25:2 እርሱ ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና የርሱ ብቻ የሆነ *ልጅንም ያልያዘ*፣ በንግሥናውም ተጋሪ የሌለው፣ ነገሩንም ሁሉ የፈጠረና፣ በትክክልም ያዘጋጀው ነው።
17:111፦ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዝነው ለርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው ለርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይግባው፣ በልም ማክበርን አክብረው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዐቂዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه

“ዲን” دِين ማለት “ሃይማኖት” “ፍትሕ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርሕ”Doctrine" ማለት ነው፤ ዲን በግሪክ "ዶግማ" δόγμα ይባላል፤ ስለዚህ ዲን የእምነት መርሕ እና የሥነ-ምግባር እሴት ነው። ዲኑል ኢሥላም ነቢያትን ወንድማማች ያደረገ ዐቂዳህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 113
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፤ እናቶቻቸው ይለያያሉ፤ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَنَا أَوْلَى النَّاسِ بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ، وَالأَنْبِيَاءُ إِخْوَةٌ لِعَلاَّتٍ، أُمَّهَاتُهُمْ شَتَّى، وَدِينُهُمْ وَاحِدٌ ‏

"እናቶቻቸው ይለያያሉ" ማለት በተላኩበት ዘመን ያለውን "ሸሪዓህ" እንደየ ማኅበረሰቡ የእድገት እና የአስተሳሰብ ደረጃ ይለያያል ማለት ነው። “ዲን” ደግሞ ሦስት ደረጃ አሉት፥ እነርሱም፦
1. “ኢሥላም” إِسْلَٰم ፣
2. “ኢማን” إِيمَٰن
3. “ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው።
“ኢማን” إِيمَٰن ማለት "እምነት" ማለት ሲሆን በግል እና በዕውቀት እንደገባህ እና እንደተረዳከው የሚያድግ አሊያ የሚቀንስ ነው። ዲን ግን ከኢማን የሚለየው በተቋም ሕግ እና አንቀጸ-እምነት የያዘ ሥርወ-እምነት ነው።
ኢማን በልብ የምናምነው፣ በምላስ የምንመሰክረው እና በድርጊት የምንገልፀው ነው፤ ኢማንን በልብ ስንቋጥር “ዐቂዳህ” ይባላል። “ዐቂዳህ” عقيدة‎ የሚለው ቃል “ዐቀደ” عَقَدَ ማለትም “ቋጠረ” ወይንም “ዐቅድ” عَقد ማለትም “መቋጠር” ከሚል ቃል የተመዘዘ ነው፤ ለምሳሌ “የተቋጠሩ” ለሚለው ቃል “ዑቀድ” عُقَد ሲሆን ይህ ቃል “ዐቀደ” عَقَدَ ከሚለው ቃል የረባ ነው፦
113፥4 *“በየተቋጠሩ”* ክሮች ላይ ተፊዎች ከኾኑት ደጋሚ ሴቶችም ክፋት፡፡ وَمِن شَرِّ ٱلنَّفَّٰثَٰتِ فِى ٱلْعُقَدِ

ስለዚህ “ዐቂዳህ” ማለት አንድን ነገር በደንብ መቋጠር ወይም እንዳይላላ ማጥበቅ ማለት ነው፤ ለምሳሌ የጋብቻ ቃል-ኪዳን “ዑቅደቱ-ኒካህ” ተብሎ ይጠራል፤ “ላ-ኢላሀ ኢለሏህ” እምነትም በአንድ ሙስሊም ልብ ውስጥ በጠነከረ መልኩ መያዝ ስላለበት “ከሊመቱል-ዐቂዳህ” ተብሎ ይጠራል፤ አንድ ሰው እኔን፦ "ዐቂዳህ ምንድነው? ብሎ ቢጠይቀኝ፤ ትርጉሙ፦ "በልብህ አምነህ የያዝከውና የቋጠርከው ምንድነው? ማለቱ ነው፤ አንድ አማኝ በልቡ ቋጥሮ ያስቀመጠው ዕውቀት “ኢማን” ይባላል።
የኢማን ትልቁ ቅርንጫፍ ከሊመቱል-ዐቂዳህ የሆነው "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፤ ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" ማለት ነው፤ ትንሹ ደግሞ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ነው። ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏"‏ ‏.‏
“ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ ማለት “ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለት ነው፣ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብሎ በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፦
2፥256 *በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
31፥22 *እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُور

“የሰጠ” ለሚለው ቃል የገባው “ዩሥሊም” يُسْلِمْ ሲሆን “ሙሥሊም” مُسْلِم እና “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚሉት ቃላት ከረባበት “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” “ሁሉ ነገሩን ሰጠ” ከሚል የመጣ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰው ሢሠልም ጠንካራን ዘለበት ይጨብጣል፤ ይህም በጣዖት መካድ እና በአላህ ማመን ነው፤ የኢሥላም አስኳሉ ተህሊል ነው፤ “ተህሊል” تهليل‎ ማለት “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” لَا إِلَـٰهَ إِلَّا الله ማለት ነው፤ የዕውቀትን መጀመሪያም “ላ ኢላሀ ኢለሏህን” ማወቅ ነው፤ ይህንን የሚያውቁ ኾነው በእውነት የመሰከሩት እድለኛ ናቸው፦
47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه
43፥86* እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚግገዟቸው እነርሱ የሚያውቁ ኾነው በእውነት ከመሰከሩት በስተቀር* ምልጃን አይችሉም፡፡ وَلَا يَمْلِكُ الَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَن شَهِدَ بِالْحَقِّ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

“ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ዕወቁ በተባሉ ጊዜ የሚኮሩ ዕጣ ፋንታቸው ጀሃነም ነው፦
37፥35 እነርሱ *"ከአላህ ሌላ አምላክ የለም"* በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ፡፡ إِنَّهُمْ كَانُوٓا۟ إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ

ከሊመቱል-ዐቂዳህ “የመጠበቂያዋ ቃል” ስትሆን እርሷን አስይዙ ተብለናል፦
48፥24 *“መጠበቂያይቱንም ቃል አሰያዛቸው”*። በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶቿም ነበሩ። አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው። وَأَلْزَمَهُمْ كَلِمَةَ التَّقْوَىٰ وَكَانُوا أَحَقَّ بِهَا وَأَهْلَهَا ۚ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

ዐቂዳን የተገነዘበ ሰው እብሪትና ትእቢት ያለበት አባይና ወላዋይ ካልሆነ በስተቀር ሚሽነሪዎች ወደዘረጉት ጽርፈት አይገባም። የዚህ መጣጥፍ አላማ እንደ እኔ ጭላንጭል ዕውቀት ያላቸው ልጆች በዚህ የኩፍር ጽርፈት ሰለባ እንዳይሆኑ የቀለም ቀንድ ከነከሱ ምሁራኖቻችን ስንክሳር ዕውቀት ይዘው ልጓም እንዲያበጁ እንዲረዳ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዐረቢኛ ቁርኣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥28 *መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን አብራራነው*፡፡ ሊጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ قُرْآنًا عَرَبِيًّا غَيْرَ ذِي عِوَجٍ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ

ኢሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች፦ "ቁርኣን ውስጥ ዐረቢኛ ያልሆኑ ባዕድ ቋንቋ ቃላት አሉ" ይላሉ፤ እኛ ደግሞ በተቃራኒው ቁርኣን ዐረቢኛ እንጂ የአዕጀሚኛ ቋንቋ ቃላት የለውም ብለን ክፉኛ እንሞግታለን፤ ጥሬውን ከብስል ምርቱን ከእንክርዳር የሚለዩ ሊሂቃን፦ “ ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጡሩ” እንደሚሉት ኢንሻላህ ቁርኣንን ከሥሩ በማስተንተን እንጀምር። አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ አድርጎ አወረደው፤ ቁርኣን በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ነው፦
43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
13፥37 *እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا

"ዐረቢይ" عَرَبِيّ ማለት "ዐረብኛ" ማለት ሲሆን በሥነ-ሰዋስው "ገላጭ" ነው፤ ቁርኣን ዐረቢኛ ሆኖ ነው የወረደው፤ ከዐረቢኛው ቁርኣን ውጪ ያሉት የአማርኛ፣ የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሳይኛ፣ የስውዲንኛ መጽሐፎች ቁርኣን ሳይሆኑ የቁርኣን ትርጉም ናቸው፦
41፥3 አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ *ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው*፡፡ كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
20፥113 *እንደዚሁም ዐረብኛ ቁርኣን ኾኖ አወረድነው*፡፡ አላህንም ይፈሩ ዘንድ ወይም ለእነርሱ ግሣጼን ያድስላቸው ዘንድ ከዛቻ ደጋግመን በውስጡ ገለጽን፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا وَصَرَّفْنَا فِيهِ مِنَ الْوَعِيدِ لَعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ أَوْ يُحْدِثُ لَهُمْ ذِكْرًا
39፥28 *መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን አብራራነው*፡፡ ሊጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ قُرْآنًا عَرَبِيًّا غَيْرَ ذِي عِوَجٍ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
26፥194 *ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ በልብህ ላይ አወረደው*፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنذِرِين
26፥195 *ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ*፡፡ بِلِسَانٍ عَرَبِيٍّ مُّبِينٍ

ቁርኣን የወረደው መዛባት በሌለበት ዐረብኛ ነው፤ ይህም "ሙቢን" ነው፤ "ሙቢን" مُّبِين ማለት "clear" ማለት ነው። "ሙቢን" የሚለው ቃል "ግልጽ ከሓዲ" "ግልጽ ጠላት" "ግልጽ እባብ" "ግልጽ አስጠንቃቂ" "ግልጽ ብርሃን" "ግልጽ ስልጣን" በሚል መጥቷል፦
43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ *"ግልጽ"* ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ
43፥62 ሰይጣንም አያግዳችሁ፡፡ እርሱ ለእናንተ *"ግልጽ"* ጠላት ነውና፡፡ وَلَا يَصُدَّنَّكُمُ الشَّيْطَانُ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
7፥107 በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ *"ግልጽ"* እባብ ኾነች፡፡ فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ
22፥49 «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለእናንተ *"ግልጽ"* አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّمَا أَنَا لَكُمْ نَذِيرٌ مُّبِينٌ
11፥96 ሙሳንም በተዓምራታችንና *"በግልጽ"* ብርሃን በእርግጥ ላክነው፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِآيَاتِنَا وَسُلْطَانٍ مُّبِينٍ
4፥153 ሙሳንም *"ግልጽ"* ስልጣንን ሰጠነው፡፡ وَآتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَانًا مُّبِينًا

"ግልጽ" የሚለውን ቃል "ንጹህ" እያልን ከተረጎምነው "ንጹህ ከሓዲ" "ንጹህ ጠላት" "ንጹህ እባብ" "ንጹህ አስጠንቃቂ" "ንጹህ ብርሃን" "ንጹህ ስልጣን" ትርጉም አይሰጥም። "ንጹህ" ለሚለቅ ቃል ቁርኣኑ ያስቀመጠው "ጠሁር" طَهُور ነው፦
25፥48 እርሱም ያ ነፋሶችን አብሳሪዎች ሲኾኑ ከዝናሙ በስተፊት የላከ ነው፡፡ ከሰማይም *"ንጹህ"* ውሃን አወረድን፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَرْسَلَ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ ۚ وَأَنزَلْنَا مِنَ السَّمَاءِ مَاءً طَهُورًا

ጌታችን አላህ ቁርኣንን በነቢያችን"ﷺ" ጊዜ በወቅቱ በነበረውን "ግልጽ" ዐረቢኛ ነው ያወረደው፤ በሌላ ቋንቋ ሙዳየ-ቃላት በወቅቱ አላወረደም፦
26፥198 *ከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነውም ኖሮ*፤ وَلَوْ نَزَّلْنَاهُ عَلَىٰ بَعْضِ الْأَعْجَمِينَ
26፥199 *በእነርሱ ላይ ባነበበውም በእርሱ አማኞች አይኾኑም ነበር*፡፡ فَقَرَأَهُ عَلَيْهِم مَّا كَانُوا بِهِ مُؤْمِنِينَ
41፥44 *በአዕጀምኛ የኾነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ «በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? ቁርኣኑ አዕጀምኛና መልክተኛው ዐረባዊ ይኾናልን?» ባሉ ነበር"*፤ እርሱ ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያና መፈወሻ ነው፡፡ እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው፤ አይሰሙትም፡፡ እነርሱም በእነርሱ ላይ እውርነት ነው፡፡ እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጥጠሩ ናቸው፡፡ وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَّقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَأَعْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ ۗ قُلْ هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌ ۖ وَالَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ فِي آذَانِهِمْ وَقْرٌ وَهُوَ عَلَيْهِمْ عَمًى ۚ أُولَـٰئِكَ يُنَادَوْنَ مِن مَّكَانٍ بَعِيدٍ
16፥103 እነርሱም፦ *«እርሱን ቁርኣንን የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደ እርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ "አዕጀም" ነው፡፡ ይህ ቁርአን ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው*፡፡ وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّهُمْ يَقُولُونَ إِنَّمَا يُعَلِّمُهُ بَشَرٌ ۗ لِّسَانُ الَّذِي يُلْحِدُونَ إِلَيْهِ أَعْجَمِيٌّ وَهَـٰذَا لِسَانٌ عَرَبِيٌّ مُّبِينٌ
ነቢያችን"ﷺ" ሥርወ-ዘውጋቸው "ዐረቢኛ" ነው፤ እርሳቸውም ዐረባዊ ስለሆነ ቁርኣኑም ዐረቢኛ ነው፤ እርሳቸውም ሆነ ቁርኣን "አዕጀሚይ" አይደሉም፤ "አዕጀሚይ" أَعْجَمِىّ ማለት "ባዕድ"foreign" ማለት ነው። ነቢያችን"ﷺ" ባዕድ የሆነ ነቢይ ቢሆኑ ኖሮ ዐረቦች ለማመን ይቸገሩ ነበር፤ ነቢዩን"ﷺ" ዐረባዊ ቁርኣንን አዕጀሚኛ ቢሆን ኖሮ "በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? ቁርኣኑ አዕጀምኛና መልክተኛው ዐረባዊ ይኾናልን?" ባሉ ነበር፤ ነገር ግን ይህ ቁርኣን ግልጽ ዐረቢኛ ነው። ቁሬሾች ለነቢያችን"ﷺ" ቁርኣንን አስተማረው የሚሉት ዕብራዊ፣ ፋርሳዊ፣ ሮማናዊ ወዘተ ነው፤ እነርሱም፦ " ይህ ቁርኣን እርሱ (ነቢያችንን) የቀጠፈው፥ በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም" አሉ፤ ጭራሽ ስለ ትንሳኤ እሳቤ የሚናገረውን አንቀጽ፦ "የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች" አሉ፤ አምላካችን አላህም፦ "ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው" በላቸው በማለት ምላሽ ሰጠ፦
25፥4 *እነዚያም የካዱት ይህ ቁርኣን እርሱ የቀጠፈው፥ በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት እንጂ ሌላ አይደለም አሉ*፡፡ በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَـٰذَا إِلَّا إِفْكٌ افْتَرَاهُ وَأَعَانَهُ عَلَيْهِ قَوْمٌ آخَرُونَ ۖ فَقَدْ جَاءُوا ظُلْمًا وَزُورًا
25፥5 *አሉም «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች*፡፡» وَقَالُوا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ اكْتَتَبَهَا فَهِيَ تُمْلَىٰ عَلَيْهِ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
25፥6 *«ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው*፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

ግን ይህ ቁርኣን ባዕድ ቋንቋ የለበትም። በዚህ ጊዜ ነው ሚሽነሪዎች፦ "ቁርኣን ውስጥ ዐረቢኛ ያልሆኑ ባዕድ የሆኑ ሙዳያ-ቃላት ጀሃነም፣ አደም፣ ኢብራሂም፣ መርየም፣ ሙሳ ወዘተ ቃላት አሉ" ብለው ይሞግታሉ፤ እነዚህ ቃላት ቁርኣን ከመውረዱ፥ ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ ከመሆናቸው በፊት ዐረቢኛ ውስጥ ገብተው ዐረቢኛ የሆኑ ቃላት ናቸው። ሚሽነሪዎች የሚሉት ዐረቢኛ "ያልሆኑ" ነው፤ እኛም የምንለው ደግሞ ዐረቢኛ "የሆኑ" ነው፤ በሥነ-ቋንቋ ጥናት የዐረቢኛ ቋንቋን መሠረቱ "ግንደ-ሴማዊ ቋንቋ"Central Semitic language" ነው፤ እዚህ ቤተሰብ ውስጥ ያሉት የቋንቋዎች ቃላት ተዋራራሽ ሆነው የቋንቋው ቃላት ይሆናሉ፤ ለዐረቢኛ ቋንቋ ሥረ-መሠረቱ ቅድመ-ዐረቢኛ"proto-Arabic" የሴም እንብርት የሆነው ዐረማይክ ነው። ሴማዊ ቤተሰብ ውስጥ ያሉት ዐረማይክ፣ ዐካድ፣ ዕብራይስጥ፣ ግዕዝ ወዘተ የቃላት መመሳሰል የሚታይባቸው ይህ የቃላት መወራረስ"Nativization" ነው።

ይህን ካየን ዘንዳ በጥንት ጊዜ ቁርኣን ከመውረዱ፥ ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ ከመሆናቸው በፊት ዐረቢኛ ውስጥ ገብተው ዐረቢኛ የሆኑ ቃላት በሥነ-ቋንቋ ጥናት "ሙዐረብ" مُعَرَّب ማለትም "ዐረቢኛ የሆኑ" ይባላሉ፤ አንድ ቃል ከዐረቢኛ ግስ መደብ እና ከዐረቢኛ ስም መደብ ሲረባ “ሙሽተቅ” مُشتَق ሲባል ነገር ግን አንድ ቃል ከዐረቢኛ ግስ መደብ እና ከዐረቢኛ ስም መደብ የማይረባ ከሆነ “ጃሚድ” جامِد ይባላል፤ ሙዐረብ ቃላት ጃሚድ ናቸው። ስለዚህ ቁርኣን በሚወርድበት እና ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ በሆኑበት ጊዜ ከዐረቢኛ ውጪ የሆኑና ዐረቢኛ "ያልሆኑ" ቁርኣን ውስጥ የገቡ የባዕድ ቋንቋ ሙዳየ-ቃላት አንዳች የሉም ብለን በሙሉ ልብ እንናገራለን። አለ የሚል ተሟጋች ካለ የታሪክ፣ የሥነ-ቅርፅ፣ የቋንቋ እና የሰዋስው መረጃና ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

ለምሳሌ ወሒድ ንጹህ አማርኛ ነው የሚናገረው ቢባል ዐረቢኛ፣ ፈረሳይኛ፣ ስውዲንኛ እና እንግሊዝኛ አልቀላቀለም ማለት ነው እንጂ ወሒድ ከመፈጠሩ ከረጅም ዓመታት በፊት አማርኛ የሆኑ ሥርና መሠረታቸው ሌላ የሆኑ የአማርኛ ቃላት አይጠቀም ማለት አይደለም። ለምሳሌ ፈረሳይኛ የነበሩ ቃላት ኦፊሴል፣ ሞኖፖል፣ ሌጋሲዮን፣ ኦፕራሲዮን፣ ቡፌ፣ ካፌ ወይም ጣሊያንኛ የነበሩ ቃላት ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ላዛኛ፣ ስልስ፣ አሮስቶ፣ ፋብሪካ፣ ጋዜጣ፣ ፉርኖ፣ ፍሬን፣ ፒንሳ ወዘተ አማርኛ የሆኑ ቃላት አይጠቀምም ማለት አይደለም። ከላይ ያለውን የቀርኣን ሙዐረብ በዚህ መልክና ልክ፥ ስሌትና ቀመር መረዳት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቴኦክራሲ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥48 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّه

ኢሥላም አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ ይዟል፤ ይህም ዘይቤ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘይቤ ነው። “ፓለቲካ” πολιτικά የሚለው የግሪክ ቃል “ፓሊቲኮስ” πολιτικός ማለትም “ዜግነት”citizen” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ፓሊስ” πόλις ማለትም “ከተማ” እና “ፓሊተስ” πολίτης ማለትም “ፓሊስይ” ያቀፈ የአስተዳደር ጥበብ ነው፤ በጥንቷ ሄለናዊ ግሪክ ከተማ የምትመራበት ፓሊሲይ ፓለቲካ ይባል ነበር። በጥቅሉ ፓለቲካ ማለት በፓሊስይ ማለትም በመርሕ ዜጎችም የሚመራ ሥነ-መንግሥት ጥናት ነው፤ ሕገ-መንግሥት”constitution” ማለት ደግሞ የመንግሥት መርሕ፣ ሕግ እና መመሪያ ነው፤ “መንግሥት” አገዛዝ” “ኃይል” “ሥልጣን” በግሪክ “ክራቶስ” κράτος ይባላል፤ “ክራሲ” የሚለው ቃል “ክራቶስ” ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን የመንግሥት ቅርፅ መዳረሻ ቅጥያ ሆኖ ሲመጣ የተለያየ የመንግሥት እርከን ይሆናል፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ፕሉቶ-ክራሲ”
“ፕሉቶ-ክራሲ” ማለት “የሃብት አገዛዝ” ማለት ነው፤ “ፕሉቶስ” πλοῦτος ማለት “ሃብት” ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ ሃብት ያላቸው ሃብታሞች ሃብት ስላላቸው በሃብታቸው የሚገዙበት ሥርዓት ነው፤ ይህ እሳቤ በድህረ ዘመነ አብርሆት ውድቅ ሆኗል።

ነጥብ ሁለት
“አርስቶ-ክራሲ”
“አርስቶ-ክራሲ” ማለት “የልዕልና አገዛዝ” ማለት ነው፤ “አርስቶስ” ἄριστος ማለት “ልዕልና” ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ ልዕልና ያላቸው ልዑላን በልዕልናቸው የሚገዙበት ሥርዓት ነው፤ እኛ ምርጥ ዘር ነን የሚል አቋም አላቸው፤ ይህ እሳቤ በድህረ ዘመነ አብርሆት ውድቅ ሆኗል።

ነጥብ ሥስት
“አውቶ-ክራሲ”
“አውቶ-ክራሲ” ማለት “የኃይል አገዛዝ” ማለት ነው፤ “አውቶስ” αὐτός ማለት “ኃይል” ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ ኃይል ያላቸው ኃያላን በኃይላቸው የሚገዙበት ሥርዓት ነው፤ ይህ እሳቤ በተለይ የሞናርኪስም እሳቤ በሳውዲ፣ በዖማን፣ በሲዊዘርላድ፣ በደቡብ ኮርያ ወዘተ ያለ እሳቤ ነው፤ ይህ እሳቤ እየወደቀ ነው፤ ቅርብ ቀን ኢንሻላህ ሙሉ ለሙሉ ይወድቃል።

ነጥብ አራት
“ዲሞ-ክራሲ”
“ዲሞ-ክራሲ” ማለት “የሕዝብ አገዛዝ” ማለት ነው፤ “ዴሞስ” δημο ማለት “ሕዝብ” ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ በሕዝብ ምርጫ በተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤት ውስጥ የተመረጠው ሰው የሚገዛበት ሥርዓት ነው፤ ሕገ-መንግሥቱን የሚያረቁት ከአእምሮ አፍልቀው ነው።

ነጥብ አምስት
“ቴክኖ-ክራሲ”
“ቴክኖ-ክራሲ” ማለት “የሙያ አገዛዝ” ማለት ነው፤ “ቴክኖስ” τέχνη ማለት “ሙያ”skill” ወይም “እደ-ሙያ”craft” ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ በእያንዳንዱ ሚኒስትሪ ሚኒስቴ መሆን ያለበት የሙያው ባለቤት ነው የሚል እሳቤ ነው፤ ለምሳሌ በጤና ሚኒስትሪ ሜዲካል ያጠና ዶክተር፤ በትምህርት ሚኒስቴር ፔዳጎጂ ያጠና ሚኒስተር፣ በግብርና ሚኒስትሪ ግብርና ያጠና ሚኒስቴር ወዘተ የሚመራበት እሳቤ ነው። “ሚንስትሪ” ማለት “አገልግሎት” ማለት ሲሆን “ሚንስተር” ማለት “አገልጋይ” ማለት ነው፤ ይህ እሳቤ በአንጻራዊ ተመራጭ ነው።

ነጥብ ሥድስት
“ቴኦ-ክራሲ”
“ቴኦ-ክራሲ” ማለት “የአምላክ አገዛዝ” ማለት ነው፤ “ቴኦስ” θεός ማለት “አምላክ” ማለት ነው፤ ከአንድ እስከ ስድስት ያየናቸው የአገዛዝ ቅርጽ ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን ሕገ-መንግሥት የሚያረቁት ከሰው አእምሮ ነው፤ ነገር ግን በቴኦክራሲ ቅርጽ መመሪያው መለኮታዊ ብቻ ነው። “መጅሊስ” مجلس‎ የሚለው የዐረቢኛ ቃል “ሲኖዶስ” σῠ́νοδος የሚለው የግሪክ ቃል ትርጉማቸው “ምክር ቤት”council” ማለት ነው፤ እዚህ ምክር ቤት ውስጥ ሕገ-መንግሥቱ ሸሪዓህ ነው፤ “ሸሪዓህ” شَرِيعَة የሚለው ቃል “ሺርዓህ” شِرْعَة ማለትም “ሕግ” ከሚለው የስም መደብ የመጣ ሲሆን “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው፦
45፥18 *ከዚያም ከነገሩ ከሃይማኖት “በትክክለኛይቱ ሕግ” ላይ አደረግንህ*፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ
5፥48 *ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን*፡፡ لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا

አላህ ለሁሉም መልእክተኞች “ሕግ” እና “መንገድ” አድርጓል፤ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ማለትም “ፋና” ማለት ሲሆን “መንሃጅ” منہاج የሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይህ ሕግ የሚዋቀረው ውቅር አራት ሲሆኑ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ቁርኣን” قرآن‌‎ ማለትም የአላህ ቃል፣
2ኛ. “ሡናህ” سنة የነብያችን”ﷺ” ሰሒህ ሐዲስ፣
3ኛ. “ቂያሥ” قياس‌‎ “ማመጣጠን”Analogy”
4ኛ. “ኢጅማዕ” إجماع‌‎ ማለትም የዐሊሞች ስብስብ ናቸው።
ስለዚህ ፍርድ ከአላህ በወረደው ሕግ ይፈረዳል፦
5፥48 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّه
“ፍረድ” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፈሕኩም” فَاحْكُمْ ሲሆን “ሑክም” ለሚለው የግስ መደብ ነው፤ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፤ “አሕካም” أحكام ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ነው፤ በኢስላም “ሕጎች” በአምስት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فرض ማለትም “የታዘዘ”
2ኛ. “ሙሥተሐብ” مستحب” ማለትም “የተወደደ”
3ኛ. “ሙባሕ” مباح ማለትም “የተፈቀደ”
4ኛ. “መክሩህ” مكروه” ማለትም “የተጠላ”
5ኛ. “ሐራም” حرام” ማለትም “የተከለከለ” ናቸው።
“ፊቅህ” فقه ማለት “ጥልቅ መረዳት” ማለት ሲሆን የሥነ-ሕግ ጥናት”the study of law” ነው፤ ሕግ አዋቂ ደግሞ “ፈቂህ” فقيه ይባላል፤ “ፊቅህ” ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ “መረዳት” ማለት ነው፦
6፥98 *”ለሚያወቁ” ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን*፡፡ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَفْقَهُونَ

“ሚያወቁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የፍቀሁነ” يَفْقَهُونَ ሲሆን “ሚረዱ” ማለት ነው። ሙስሊሙ የስልጣን ባለቤቶች ለሆኑት ለአሚሮቻችን ይታዘዛል፤ የሚያወዘግብ ነገር ካለ ወደ አላህ ቁርኣን እና ወደ መልእክተኛው ሐዲስ መረጃ እና ማስረጃ ማግኘት ነው፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ መልክተኛው እና *ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ*፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ *የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት*፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

ነጥብ ስድስት ኢስላም የያዘውን ፓለቲካዊ ዘይቤ ቴኦ-ክራሲ ነው። እንደሚታወቀው የመጨረሻው ዘመን ጥናት”Eschatology” በኢስላም “አል-አኺሩል ዘማን” لَلْآخِر لَلْزَمَان ይባላል፤ የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች በሁለት ይከፈላሉ፤ አንዱ ንዑሣን ምልክቶች ሲሆኑ ሁለተኛ ዐበይት ምልክቶች ናቸው፤ የኺላፋህ ሥርዓት ተመልሶ መምጣት ከንዑሳን ምልክቶች አንዱ ሲሆን በነብያችን”ﷺ” ትንቢት ውስጥ እንዲህ ተቀምጧል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 14, ሐዲስ 163
ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ነብይነት አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በነብይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ይጀመርና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም ዘውዳዊ ንግሥና ቦታውን ይይዝና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም የአንባገነን ንግሥና ይነሳልና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በስተመጨረሻም በነብይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ከእንደገና ይመጣል*። فَقَالَ حُذَيْفَةُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ – صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -: « تَكُونُ النُّبُوَّةُ فِيكُمْ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةٌ عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا عَاضًّا فَيَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا جَبْرِيَّةً فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةً عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ

የነብያችን”ﷺ” ነብይነት ቆይታው እንደ ጎርጎሮሳውን አቆጣጠር ከ 610-632 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያም በነብያችን”ﷺ” ፋና አል-ኺላፈቱ አር-ረሺዳህ ከ 632-661 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያ የበኑ ኡመያድ ሥርወ-መንግሥት እና የበኑ ዐባሥ ሥርወ-መንግሥት ዘውዳዊ ንግሥና ሆኖ ከ 661-1258 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያም ከ 1258 ድህረ-ልደት እስከ ዘመናችን የአንባገነኖቹ ነገሥታት ጊዜ ውስጥ ነን፤ ከዚያም ኢንሻላህ በነብያችን”ﷺ” ፋና እንደገና የኺላፋህ ሥርዓት ይመለሳል፤ አላህ ቴኦክራሲን ያምጣልን! አሚን።

الإسلام هو الحل

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሴቶች በባይብል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ክርስትና በአውሮፓ ላይ የተሸመነበት ድርና ማግ እንደሆነ ሁሉ የተዋረደበት ማቅ፣ የተገነዘበት በፍታ፣ የተከፈነበት ግምዣ ነው ብዬ ብናገር እብለትም ወይም ግነትም አሊያም ቅጥፈትም አይደለም። ሚሽነሪዎችም ማንኛውም ነገር ሲለኩ እና ሲመዝኑ ከባይብል ህግ ይልቅ ሰው ሰራሹን የምዕራባውያንን ህግ ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ የኢስላም ህግ ስህተት እንዳለው ቧጦና ጓጦ ከመፈለግ ይልቅ የራሳቸውን ባይብል ላይ ስለ ሴቶች የተቀመጠውን ነገር ቅድሚያ ቢመለከቱ አባጣና ጎርባጣ ይሆንባቸዋል፤ ለዛ ነው ምዕራባውያን የክርስትና አህጉር የነበረው ዛሬ ተገልብጦ ከመቶ 65% አይደለም ሃይማኖት ሊኖረው ይቅርና በፈጣሪ መኖር እንኳን አይቀበልም። ምክንያቱም የክርስትና ሃይማኖት ህግ በጊዜው እንደጎረበጣቸው ይናገራሉ። ታዲያ ሚሽነሪዎች ሥርወ እምነታቸው ላይ የአውሮፓን ሥርወ መንግሥት ከለላ አድርገው ሂስ ከመስጠጣቸው በፊት በእማኝነትና በአስረጂነት ሴቶች በባይብል ያለባቸውን ደረጃና መብት ነጥብ በነጥብ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
"ሴትና ደረጃዋ"
ሚስት ባልዋን "ጌታዬ" እያለች እንድትገዛ "ህጉ" ማለትም ኦሪት እርሱም *ገዥሽ* ነው ብሎ ያዛል፣ ለወንድ እንድትገዛ እንጂ እንድትናገር አልተፈቀደላትም፤ በዝግታ ትኑር እንጂ በወንድ ላይ ልትሰለጥን አይፈቀድም፤ በማህበር ማለትም ሰዎች በተሰበሰቡበት ልታስተምር ወይም ልትናገር አይፈቀድላትም፦
ዘፍጥረት3፤16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም *ገዥሽ* ይሆናል።
1ኛ ቆሮንቶስ 14፥34 ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።
1ኛ ጴጥሮስ 3፤5-6 እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ *ለባሎቻቸው ሲገዙ* ተሸልመው ነበርና፤ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ *ጌታ* ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፤11-12 ሴት በነገር ሁሉ *እየተገዛች* በዝግታ ትማር፤ ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ *ልታስተምር* ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።

ሚስት ባልዋን እንዴት ነው የምትገዛው ሲባል ልክ እንደ ፈጣሪ መገዛት አለባት። ሚስት ለፈጣሪዋ አምልኮ፣ ስግደት፣ ምስጋና፣ ውዳሴ፣ ማህሌት፣ የቀልብ፣ የነቢብ፣ የገቢር መገዛት የምታቀር ከሆነ ለባልዋም ማቅረብ አለባት፣ ምክንያቱም ሚስት ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ ተብሏልና፦
ኤፌሶን 5፣22 ሚስቶች ሆይ፥ ""ለጌታ እንደምትገዙ"" ለባሎቻችሁ ""ተገዙ""፤

ጥያቄአችን ሚስት ለባልዋ የምትገዛው እንደ ጌታዋ "ጌታዬ" እያለች ከሆነ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይሆንምን?
ማቴዎስ 6፤24 ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤

ምክንያቱም ሴት ማለት ከሞት ይልቅ የመረረች፣ ልብዋ ወጥመድና መርበብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ናት፤ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርስዋ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል ይለናል፦
መክብብ 7፥26 እኔም #ከሞት ይልቅ #የመረረ #ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መርበብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ #ሴት #ናት፤ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርስዋ #ያመልጣል#ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።

ሴት በተፈጥሮዋ ደካማ እና የኃጢያትም ምንጭ እርሷ እንደሆነች እና የተታለለች እርሷ እንጂ ወንድ አይደለም ይለናል፦
1ኛ ጴጥሮስ 3፥7 እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ""ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ"" ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤
ሲራክ 42:13-14 ከልብስ ብል ይገኛል፤ኃጢያትም ሁሉ
ከሴቶች ይገኛል።
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥14 የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤
ነጥብ ሁለት
"ሴትና ጋብቻ"
በሙሴ ህግ አንድ ወንድ አንድ ሴት መፍታት የሚችለው የፍችዋን ወረቀት በመስጠት ነው፦
ዘዳግም 24፥1 ሰው ሴትን ወስዶ ቢያገባ፥ የእፍረት ነገር ስላገኘባት በእርሱ ዘንድ ሞገስ ባታገኝ፥ ""የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ይስጣት፥ ከቤቱም ይስደዳት""።
ዘዳግም 24፥3 ሁለተኛውም ባል ቢጠላት፥ ""የፍችዋንም ጽሕፈት ጽፎ በእጅዋ ቢሰጣት""፥ ከቤቱም ቢሰድዳት፥ ወይም ሚስት አድርጎ ያገባት ሁለተኛው ባልዋ ቢሞት፥

ነገር ግን በአዲስ ኪዳን አንድ ወንድ አንድ ሴት መፍታት የሚችለው ዝሙት ስትሰራ ብቻ ነው፦
ማቴዎስ 5: 31-32 ሚስቱን የሚፈታት ሁሉ የፍችዋን ጽሕፈት ይስጣት ተባለ። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ #አመንዝራ #ያደርጋታል#የተፈታችውንም #የሚያገባ #ሁሉ #ያመነዝራል
ማቴዎስ 19:9 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥ #የተፈታችውንም #የሚያገባ #ያመነዝራል አላቸው።"

አንዲት ሴት በባህርይ አለመግባባት ቢኖር ወይም የፍቅር አለመጣጣም ቢኖር በዝሙት ካልሆነ መፈታት አትችልም። ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ አመንዝራ መባሉ ብቻ ሳይሆን የተፈታችው ሴት እርሱ በፈታት ሌላ ሰው እንዳያገባት እቀባ ተጥሎባታል። የተፈታች ሴት ሌላ ወንድ ካገባት አመንዝራ ይባላል።ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፥ "የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል አላቸው" የሚለው ይሰመርበት። እና ምን ትሆናለች? ሲባል ባልዋ እስኪሞት ድረስ ምንን ማግባት አትችልም፦
ሮሜ 7፥2-3"""ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና""፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች። """"ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች""""፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም።

ልብ አድርጉ ""ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች"" ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ሌላ ወንድ ማግባት ትችላለች። በተለይ የኢስላምን ህግ በምዕራባውያን ሚዛን ለሚመዝኑ ክርስቲያኖች ምን ይውጣቸው ይሆን? ዛሬስ በአገራችን ይህ የአዲስ ኪዳን ህግ ይኖር ይሆን? ፍርድ ቤቱን ያጨናነቀው የክርስቲያኑን ፍቺ ያለ ዝሙት ነው። ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ኢየሱስ ባል ሚስቱ ያለ ዝሙት ምክንያት ከፈታ አመንዝራ ነው ሲል ጳውሎስ ደግሞ ሚስት ከባልዋ መለያየት ትችላለች ግን ሌላ ወንድ ሳታገባ ትኑር በማለት ይቃረናል፦
1ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:10-11 " ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ """ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር"""" ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥ ባልም ሚስቱን አይተዋት ብዬ የተጋቡትን አዛቸዋለሁ፥ እኔ ግን አላዝም፥ ጌታ እንጂ።
ሲጀመር ""ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር" ማለት "ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል" ከሚለው ጋር አይጋጭም? ሲቀጥል "ሳታገባ ትኑር" ፍትሃዊ ብይን ነውን? ሲሰልስ """ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች"" መባሉስ አግባብ ነውን?
ባሏ ከሞተስ? ትሉ ይሆናል፤ ባሏ ሲሞት ደግሞ መከራዋ አላለቀም የባሏን ወንድም ታግባ የሚል ወፍራም ትእዛዝ ይጠብቃታል፦
ዘዳግም 25፥5-10 ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ ""የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ""፥ ከእርስዋም ጋር ይኑር። የምዋቹ ስም ከእስራኤል ዘንድ እንዳይጠፋ ከእርስዋ የሚወለደው በኵር ልጅ በሞተው በወንድሙ ስም ይጠራ። ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳይቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔ ጋር ሊኖርም አልወደደም ትበላቸው። የከተማውም ሽማግሌዎች ጠርተው ይጠይቁት፤ እርሱም በዚያ ቆሞ፦ አገባት ዘንድ አልወድድም ቢል፥ ዋርሳይቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል ስትል ጫማውን ከእግሩ ታውጣ፥ በፊቱም እንትፍ ትበልበት። በእስራኤልም ዘንድ ስሙ የጫማ ፈቱ ቤት ተብሎ ይጠራ።

""""ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ""" ስሙ የጫማ ፈቱ ቤት ተብሎ ይጠራ እንጂ በግድ አግባ አይባልም። እርሷን ግን እርሷ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ ተብሎ ታዟል እንጂ እንደ ወንዱ የፈለገችውን ማግባት አትችልም። ይህ እኩልነት ነውን? ከዚያም አልፎ ሴቶች ምንም ባልሰሩት በባሎቻቸው ወንጀል ምክንያት ለሌላ ወንዶች ይሰጡ ነበር፦
ኤርሚያስ 8:10 ሰለዚህ ሚሰቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ።
2ኛ ሳሙኤል 12፥8 የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ ""የጌታህንም ሚስቶች"" በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።
2ኛ ሳሙኤል12፥11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ""ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል""።

በዝሙት የተገኘች የካህንም ልጅ የቅጣቱ ብይን በእሳት መቃጠል ነው፦
ዘሌዋውያን 21፡9 የካህንም ልጅ ራስዋን በግልሙትና ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ በእሳት ትቃጠል።

ይህ የባይብል ስለ ሴቶች አስተምህሮቱ መገለጥ ወይስ መጋለጥ?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https//t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አምስት ወቅት ሶላት በቁርአን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

4:103 “ሶላት” በምእመናን ላይ “በጊዜያት” የተወሰነች ግዴታ ናትና፤

መግቢያ
ብዙ ጊዜ ሚሽነሪዎሽ ፦”አምስት ወቅት ሶላት ቁርአን ላይ የለም” ብለው በማያውቁት ነገርና ባላነበቡት ጉዳይ እንደ በቀቀን በመደጋገም ሲዘላብዱ ሰንበትበት አለ፤ ይህን መጣጥፍ ልፅፍ የቻልኩበት ምክንያት ለሙስሊሞች አምስት ወቅት ሶላት የቱ ጋር እንዳለ ለማሳየት ሳይሆን የሚሽነሪዎችን ቅጥፈት ለማጋለጥ ነው፤ በእርግጥም አምስት ወቅት ሶላት በቁርአን አላህ ነግሮናል፤ ሶላት በምእመናን ላይ “በጊዜያት” የተወሰነ ፈርድ ነው፤ ይህን አንድ በአንድ እንይ፦

1. “ሶላተል ፈጅር”
“ፈጅር” فَجْر ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጎህ” ሲሆን አምላካችን አላህ ይህን የጎህ ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
17:78 ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፤ “የጎህ” الْفَجْرِ ሰላት ስገድ፣ “የጎህ” الْفَجْرِ ሶላት መላእክት የሚጣዱት ነውና።
24:58 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው፣ እነዚያም ከናንተ ለአካለ መጠን ያልደረሱት፣ “ከጎህ” الْفَجْرِ ሶላት በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ፣ ከምሽት ሶላትም በኃላ ሦስት ጊዜያት ያስፈቅዷችሁ።

አላህ ፈጅርን ለማመልከት “በምታነጉም ጊዜ”፣ “ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት”፣ “በማለዳም”፣ “በቀን ጫፍ”፣ “በምትንነሳ ጊዜ” በማለት በአፅንኦትና በአንክሮት ይናገራል፦
30:17-18 አላህንም፣ በምታመሹ ጊዜ፣ “በምታነጉም ጊዜ”፣ አጥሩት ።
20:130 በሚሉትም ላይ ታገስ፤ ጌታህንም “ፀሃይ ከመውጣትዋ በፊት” ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው፤
50:39 በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር “ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት” ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡
40:55 በቀትር “በማለዳም” ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው።
11:114 ሶላትንም “በቀን ጫፎች”፤ ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፤
52:48-49 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፤ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፤ ጌታህንም “በምትንነሳ ጊዜ” ከማመስገን ጋር አወድሰው።

2 . “ሰላት አዝሁር”
“ዝሁር” ظهر በቁርአን “ዘሂረት” ظَّهِيرَة በሚል ስም የመጣ ሲሆን “ቀትር” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ይህን የቀትር ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
24:58 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው፣ እነዚያም ከናንተ ለአካለ መጠን ያልደረሱት፣ ከጎህ ሶላት በፊት፣ “በቀትርም” الظَّهِيرَةِ ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ፣ ከምሽት ሶላትም በኃላ ሦስት ጊዜያት ያስፈቅዷችሁ።
30:18 ምስጋናም በስማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ የተገባው ነው። በሠርክም “በቀትር” تُظْهِرُونَ ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ አጥሩት።
3. “ሶላተል አስር”
“አስር” عَصْ ማለት “ጊዜ” ወይም “ሰርክ” ማለት ሲሆን የዓለማቱ ጌታ የማለበት ወቅት ነው፤ ይህቺ የሰርክ ሰላት በቁርአን የመካከለኛይቱ ሶላት ትባላለች፦
103:1″በጊዜያቱ እምላለሁوَالْعَصْرِ ፤
2:238 “በሶላቶች” الصَّلَوَاتِ “እና” በተለይ “በመካከለኛይቱም ሶላት” وَالصَّلَاةِ الْوُسْطَىٰ ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡

“መካከለኛይቱም ሶላት” የተባለችው ከሌሎች ሶላቶች ለመለየትና ለማያያዝ “ወ” وَ የሚል መስተፃምር ይጠቀማል፤ ታዲያ መካከለኛነቷ ለማን ነው? ስንል ለሁለት ሶላቶች ቢሆን ኖሮ ሙተና”dual” ያለው “ሷላተዪን” صلاتين በመንሱብና በመጅሩር”በተሳቢና በአገናዛቢ” አሊያም “ሷላታን” صلاتان በመርፉ”በባለቤት” ይጠቀም ነበር ነገር ግን መካከለኝነቷ ለሁለት ሳይሆን ጀመዕ”plural” ያለው “ሰለዋት” الصَّلَوَات የሚል ነው፣ ይህ የሚያሳየው ከፊቷ ሁለት ከኃላዋ ሁለት ያላት መካከለኛይቱ ሰላተል አስር ናት፤ ይህቺ ሶላት “ሰርክ”፣ “ፀሐይ ከመግባቷም በፊት”፣ “ከፀሐይ መዘንበል” ትባላለች፦
30:17 ምስጋናም በስማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ የተገባው ነው። “በሠርክም” በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ አጥሩት።
50:39 በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት “ከመግባቷም በፊት” አወድሰው፡፡
20:130 በሚሉትም ላይ ታገስ፤ ጌታህንም ፀሃይ ከመውጣትዋ በፊት “ከመግባትዋም በፊት” የምታመሰግን ሆነህ አጥራው፤ ስገድ፤
17:78-79 ሶላትን “ከፀሐይ መዘንበል” እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፤

4. “ሶላተል መግሪብ”
“መግሪብ” مَغْرِب “ምዕራብ” ማለትም “የጸሃይ መጥለቂያ” ማለት ነው፣ ይህ ሌላኛው የቀን ጫፍ ይባላል፦
11:114 ሶላትንም በቀን “ጫፎች” طَرَفَيِ ፤ ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፤ መልካም ሥራዎች ኅጢአቶችን ያስወግዳሉና፤ ይህ ለተገሣጮች ግሣጤ ነው።
20:130 በሚሉትም ላይ ታገስ፤ ጌታህንም ፀሃይ ከመውጣትዋ በፊት ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው፤ ስገድ፤ ከሌሊት ሰዓቶችም “በቀን “ጫፎች” طَرَفَيِ አጥራው በሚሰጥህ ምንዳ ልትወድ ይከጀላልና።

“ተረፍ” طَرَف ማለት “ጫፍ” ማለት ሲሆን እዚህ ጋር የተጠቀመው ቃል ሙተና”dual” ሆኖ “ተረፈዪ” طَرَفَيِ ነው፤ የቀን ጫፍ አንዱ ጎህ ሲሆን ሌላው ምሽት ነው፤ ይህ “ምሽት” በቁርአን “በምታመሹ ጊዜ”፣ “በከዋክብት መደበቂያ ጊዜም” ይባላል፦
30:17-18 አላህንም፣ “በምታመሹ ጊዜ”፣ በምታነጉም ጊዜ፣ አጥሩት ።
52:48-49 ጌታህንም በምትንነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው። ከሌሊቱም አወድሰው፤ “በከዋክብት መደበቂያ ጊዜም አወድሰው” ።

5. “ሶላተል ኢሻአ”
“ኢሻአ” عِشَآء ማለት “ማታ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ይህን የማታ ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
24:58 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው፣ እነዚያም ከናንተ ለአካለ መጠን ያልደረሱት፣ ከጎህ ሶላት በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ፣ “ከማታ” الْعِشَاءِ ሶላትም በኃላ ሦስት ጊዜያት ያስፈቅዷችሁ።
40:55 ታገስም፤ የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፤ ለስሕተትህም ምሕረትን ለምን፤ “በማታ” بِالْعَشِيِّ
በማለዳም ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው።
18:28 ነፍስህንም፤ ከነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጧትና “በማታ” وَالْعَشِيِّ ከሚግገዙት ጋር አስታግሥ፤

“ዙልፈ” زُلْفَة ” ፊተኛው የሌሊት ክፍል” ሲሆን የሌሊቱ ክፍል ኢሻአ ነው፦
11:114 ሶላትንም በቀን ጫፎች፤ ከሌሊትም “ክፍል وَزُلَفًا مِنَ اللَّيْلِ ፈጽም፤ መልካም ሥራዎች ኅጢአቶችን ያስወግዳሉና፤ ይህ ለተገሣጮች ግሣጤ ነው።

ማጠቃለያ
አሏህ ስለ ሶላት የነገረን በጊዜ የተወሰነና በአምስት ወቅት መሰገድ እንዳለበት ብቻ ሳይሆን “የተስተካከለ ደንብ” እንዳለውም ጭምር ነው፦
29:45 ከመጽሐፉ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ ሶላትንም “ደንቡን” ጠብቀህ ስገድ፤
4:77 ሶላትንም “ደንቡን” ጠብቃችሁ ስገዱ፣
2:43 ሶላትንም “ደንቡን” ጠብቃችሁ ስገዱ፤
30:31 ሶላትም “አስተካክላችሁ” ስገዱ፤
22:78 ሶላትንም “አስተካክላችሁ” ስገዱ፤
24:56 ሶላትንም “አስተካክላችሁ” ስገዱ፤

የሰላት ደምብ ደግሞ በውስጡ ተክቢራ፣ ተህሊል፣ ተስቢህ፣ ተሸሁድ፣ ተስሊም ወዘተ የመሳሰሉትን ያቅፋል፤ ይህን የተስተካከለ ደንብ የምናገኘው ደግሞ በነብያችን ሱና ነው፤ ስለዚህ ሱና አላህ ይናገራል፦
2:231 የአላህንም ጸጋ በናንተ ላይ ያደረገውን “ከመጽሐፍ” እና “ከጥበብም” በእርሱ የሚገስጻችሁ ሲኾን በእናንተ ላይ “ያወረደውን” አስታውሱ፡፡

“መጽሐፍ” የተባለው የአሏህ ንግግር ቁርአን ሲሆን “ጥበብ” የተባለው ደግሞ የረሱል “ንግግር” ነው፤ ሁለቱም የተወረዱ መሆናቸው ይሰመርበት፤ ስለዚህ የሶላት ዝርዝርና አፈፃፀም የነብያችን ሱና ላይ ተገልፃል።

አሏህ ሶላት ላይ ቆመው ከሚሞቱ ባሮቹ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዘጠኙ ታምራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17:101 ለሙሳም “ግልጽ” የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” በእርግጥ ሰጠነው።

አምላካችን አላህ ሙሳን ወደ ፊርዖንና ወደ መማክርቶቹ በታምራት ልኮታል፤ እነዚህም ታምራት ዘጠኝ ናቸው፦
7:103 ከዚያም ከበኋላቸው ሙሳን ወደ ፊርዖንና ወደ መማክርቶቹ “በታምራታችን” ላክነው፤ በእርሷም ካዱ፤ የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት።
17:101 ለሙሳም “ግልጽ” የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” በእርግጥ ሰጠነው።

1ኛ. ታምር
“ግልጽ እባብ”
7:106-107 ፈርኦንም፦ “በታምር” የመጣህ እንደሆንክ ከእውነተኞቹ ከሆንክ እርሷን አምጣት አለው። በትሩንም ጣለ፤ እርሷም ወድያውኑ “ግልጽ እባብ” ሆነች።
26:32 በትሩንም ጣለ፡፡ እርሷም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች፡፡

2ኛ. ታምር
“እጁንም ነጭ መሆን”
7:108 እጁንም አወጣ፤ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካች ነጭ ሆነች።
20:22 እጅህንም ወደ ብብትህ አግባ፣ “ሌላ ታምር” ስትሆን ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና።

እጁን ወደ ብብቱ አስገብቶ ያለ ነውር ነጭ ሆና መውጣት እና ከላይ በትሩ ወደ እባብ መቀየሩ “”ሁለት አስረጅዎች”” ናቸው፦
28:32 እጅህን በልብስህ ውስጥ አግባ፡፡ ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፡፡ ክንፍህንም ከፍርሃት ለመዳን ወደ አንተ አጣብቅ፡፡ እነዚህም ከጌታህ የሆኑ ወደ ፈርዖንና ወደ መኳንንቶቹ የሚደርሱ “”ሁለት አስረጅዎች”” ናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡»

3ኛ. ታምር
“ድርቅ”
7:130 የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ “በድርቅ” አመታት እና ከፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ ያዝናቸው።

ይህ ታምር ለአመታት ከፍሬዎችም በመቀነስ ድርቅ መምጣቱ ሲሆን እነዚህ ሶስት ታምራት መጥተውላቸው በማንኛይቱም ታምር በእርሷ ልትደግምብን ብትመጣብን እኛ ለአንተ የምናምንልህ አይደለምን አሉ፦
7:131-132 ደጊቱም ነገር በመጣላችሁ ጊዜ ይህች ለኛ ተገቢ ናት ይላሉ፤ ክፋትም ብታገኛቸው በሙሳና አብረውት ባሉት ገደቢስነት ያመካኛሉ፤ ንቁ፤ ገደቢስነታቸው አላህ ዘንድ ብቻ ነው፤ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም። ለሙሳም
፦ “”በማንኛይቱም ታምር በእርሷ ልትደግምብን ብትመጣብን እኛ ለአንተ የምናምንልህ አይደለምን”” አሉ፤

ያንን ሶስት ታምራት ሲያስተባብሉ ወዲያውም፦ የውሃን ማጥለቅለቅ፣ አንበጣንም፣ ነቀዝንም፣ እንቁራሪቶችንም፣ ደምንም “የተለያዩ ታምራት” ሲኾኑ በእነርሱ ላይ ተላከ፦
7:133 ወዲያውም፦ የውሃን ማጥለቅለቅ፣ አንበጣንም፣ ነቀዝንም፣ እንቁራሪቶችንም፣ ደምንም “የተለያዩ ታምራት” ሲኾኑ በእነርሱ ላይ ላክን፤ ኮሩም፤ ተንኮለኞችም ሕዝቦች ነበሩ።

እነዚህም አራት ተከታታይ ታምራት፦
4ኛ. ታምር
“የውሃን ማጥለቅለቅ”
5ኛ. ታምር
“አንበጣን”
6ኛ. ታምር
“ነቀዝን”
7ኛ. ታምር
“እንቁራሪቶች”
8ኛ. ታምር
“ደም”

9ኛ. ታምር
“ባህሩ መከፈሉ”
አላህ ስምንቱን ታምራት ሲያስተባብሉ በባህር ውስጥ አሰጠማቸው፦
7:136 እነርሱ “በታምራታችን” ስለአስተባበሉም ከእርሷ ዘንጊዎች ስለኾኑም፤ ከእነርሱ ተበቀልን፤ በባሕርም ውስጥ አሰጠምናቸው።

ይህንን ያደረገው ቅድሚያ በሙሳ ባህሩን በበትር እንዲመታ አስደርጎ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ በማድረግ ሙሳንም ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም ካዳነ በኃላ ያስተባበሉትን ሌሎቹን አሰጠመ፤ ይህ ታላቅ ታምር ነው፦
26፥63-67 ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ መታውና ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡ እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን፡፡ ሙሳንም ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳንን፡፡ ከዚያም ሌሎቹን “አሰጠምን”፡፡ በዚህ ውስጥ “”ታላቅ ታምር”” አለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም አማኞች አልነበሩም፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እራስን ማጥፋት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

4፥29 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ፡፡ ግን ከእናንተ በመዋደድ የኾነችውን ንግድ ብሉ፡፡ *"እራሳችሁንም አትግደሉ"*፡፡ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

አምላካችን አላህ ነፍስን መግደል አውግዟል፦
4፥33 *ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“ነፍስ” نَفْس ማለት “ራስነት”own self-hood” ነው፤ ይህ ነፍስ መግደል ሐራምነቱ በእናት ማህጸን ውስጥ ያለ ሽልንም ሆን ብሎ እንዲጨነግፍ ማድረግም ጭምር ነው፦
4፥31 *ልጆቻችሁንም ድኽነትን ለመፍራት አትግደሉ፡፡ እኛ እንመግባቸዋለን፡፡ እናንተንም እንመግባለን፡፡ እነርሱን መግደል ታላቅ ኃጢኣት ነውና*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا أَوْلَادَكُمْ خَشْيَةَ إِمْلَاقٍ ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُهُمْ وَإِيَّاكُمْ ۚ إِنَّ قَتْلَهُمْ كَانَ خِطْئًا كَبِيرًا

ይህ ነፍስን መግደል ሐራምነቱ እራስንም መግደል ያጠቃልላል፤ "አንፉሠኩም" أَنفُسَكُمْ ማለት "እራሳችሁን" ማለት ነው፦
4፥29 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ፡፡ ግን ከእናንተ በመዋደድ የኾነችውን ንግድ ብሉ፡፡ *"እራሳችሁንም አትግደሉ"*፡፡ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا
2፥195 በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ *በእጆቻችሁም ነፍሶቻችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ*፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

"እራስን ማጥፋት"Suicide" በኢሥላም ይህ ያህል ሐራም እንደሆነ ጥልልና ጥንፍፍ ያለ አስተምህሮት እንዳለ ካወቅን ዘንዳ ሚሽነሪዎች፦ "ነቢያችሁ"ﷺ" ለምንድን ነው እራሳቸውን ሊያጠፉ የሞከሩት?" ብለው ጥያቄ ያቀርባሉ፤ እኛ ሙሥሊሞች፦ "ነቢያችን"ﷺ" እረ በፍጹም እንዲህ ያለ ሙከራ አላደረጉም" ብለን ክፉኛ እንሞግታለን፤ ለማንኛው ይህ ጥያቄ ያስነሳበትን ሐዲስ በሰከነና በሰላ አእምሮ እናስተንትን፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 1
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ ........፦ከዚያም ወረቃህ ከሞተ ከጥቂት ቀናት በኃላ ወሕይ ለተወሰነ ጊዜ ያህል በተቋረጠ ጊዜ ነቢዩ"ﷺ" እጅግ አዝነው ነበር፤ *"እንደሰማነውም"፦ "እርሳቸው ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ከትልቅ ተራራ ላይ ለመጣል ያስቡ ነበር"*።
ثُمَّ لَمْ يَنْشَبْ وَرَقَةُ أَنْ تُوُفِّيَ، وَفَتَرَ الْوَحْىُ فَتْرَةً حَتَّى حَزِنَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فِيمَا بَلَغَنَا حُزْنًا غَدَا مِنْهُ مِرَارًا كَىْ يَتَرَدَّى مِنْ رُءُوسِ شَوَاهِقِ الْجِبَالِ،

ሐዲሱ እረጅም ስለሆነ ለመጻፍ ጊዜና ቦታ እንዳይፈጅ እና ለአንባቢያንም እንዳይሰለች በአጭሩ አስቀምጬዋለው፤ ሙሉውን የሚፈልግ መረጃው ስላለ ገብቶ ማየት ይችላል። እዚህ ሐዲስ ላይ "እንደ ሰማነው" ተብሎ የተቀመጠው የዐረቢኛው ቃል "ፊማ በለገና" فِيمَا بَلَغَنَا እንጂ "ፊማ ሠሚዕና" فِيمَا سَمِعْنَا አይደለም። ምንድን ነው ልዩነቱ? ከተባለ "ፊማ ሠሚዕና" فِيمَا سَمِعْنَا ማለት "እንደ ሰማነው" ማለት ሲሆን ይህ መስማት ከላይ ከተራኪው በሰንሰለት የተላለፈ ትክክለኛ ትረካ ሲሆን "ፊማ በለገና" فِيمَا بَلَغَنَا ማለት ደግሞ ከአሉባልታ የሚሰማ ወሬ ነው፤ "ሙበሊግ" مـُبـَلّـِغ ማለት "አሉባልተኛ" ማለት ሲሆን "መብለግ" مـَبلـَغ ማለት ደግሞ "አሉባልታ" ማለት ነው። ይህንን የሥነ-ቋንቋን ሙግት ይዘን ስለ ነቢያችን"ﷺ"፦ "እርሳቸው ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ከትልቅ ተራራ ላይ ለመጣል ያስቡ ነበር" የሚል ሃይለ-ቃል ከጠላት አሉባልተኛ የተገኘ አሉባልታ ወሬ እንጂ ከባልደረቦቻቸው የተገኘ ስንክሳር በፍጹም አይደለም። ሲቀጥል "ፊማ በለገና" فِيمَا بَلَغَنَا ያለው በዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እና በዘጋቢው መካከል ያለ አስተላላፊ "አዝ-ዙህሪይ" الزُّهْرِيّ ነው፤ ይህንን ነጥብ ሀፊዝ ኢብኑ ሐጀረል አስቀላኒ"ረሒሙሁላህ" እንዲህ ይሉናል፦
ፈትሑል ባሪ ፊ ሸርሕ 19/449 ኪታቡል ተዕቢር
*"ፊማ በለገና" فِيمَا بَلَغَنَا ብሎ የተናገረው አዝ-ዙሁሪይ ነው። ይህም ማለት ስለ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ከሚያወራው ጥቅል ትረካ ውስጥ "ፊማ በለገና" የአዝ-ዙሁሪይ ንግግር ብቻ እንጅ ከዘገባው ጋር የተያያዘ አይደለም"*። إِنَّ الْقَائِل فِيمَا بَلَغَنَا هُوَ الزُّهْرِيّ ، وَمَعْنَى الْكَلَام أَنَّ فِي جُمْلَة مَا وَصَلَ إِلَيْنَا مِنْ خَبَر رَسُول اللَّه صَلَّى اللَّه عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي هَذِهِ الْقِصَّة وَهُوَ مِنْ بَلَاغَات الزُّهْرِيّ وَلَيْسَ مَوْصُولًا
እኛም ዞር ብለን ባይብል ላይ ተመሳሳይ ባይሆንም ስለ እራስን ማጥፋት ጥያቄ እናቀርባለን፤ የዕብራዊያን ጸሐፊ በእምነት ድል ስላደረጉ የብሉይ ኪዳን ሰዎች ሲተርክን እንደ ደመና በዙሪያቸው ካሉት ምስክሮች አንዱ ሶምሶን ነበር፦
ዕብራውያን 11፥32-33 እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ *"ስለ ሶምሶንም"* ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። *"እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ"*፥
ዕብራውያን 12፥1 እንግዲህ *እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን*፥

እንደሚታወቀው ሶምሶን እራሱን አጥፍቶ ሌሎችን ያጠፋ ሰው ነው፦
መሣፍንት 16፥30 ሶምሶንም፦ *"ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት አለ፤ ተጎንብሶም ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ"*።

እና እራሱን ያጠፋ ሰው እንዴት በእምነት ድል ነሳ፥ ምስክር ነው ይባልለታል? ይህንን የሚመልስ አንዳች ሰው የለም። አሉባልታው የሚለው፦ "ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ከትልቅ ተራራ ላይ ለመጣል ይሞክሩ ነበር" አሊያም "ራሳቸውን ከትልቅ ተራራ ላይ አጥፍተው ነበር" ሳይሆን "ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ከትልቅ ተራራ ላይ ለመጣል ያስቡ ነበር" ነው።
ማሰብ እና መሞከር አሊያም ማሰብ እና ማድረግ ሁለት ለየቅል የሆኑ ትርጉሞች ናቸው። ይህ የሶምሶን ድርጊት ግን እራስን ለማጥፋት ማሰብ አሊያም መሞከር ሳይሆን እራሱን ማጥፋት ነው። ይህንን ጉድ ይዞ ከላይ ያቀረብነውን ሐዲስ መተቸት ማለት ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሽዋን ምች መታት እንደማለት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ አለይኩም
የአላህ ዘለበት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥103 *የአላህንም ገመድ ሁላችሁም ያዙ*፡፡ አትለያዩም وَٱعْتَصِمُوا۟ بِحَبْلِ ٱللَّهِ جَمِيعًۭا وَلَا تَفَرَّقُوا۟ ۚ ፡፡

መግቢያ
"ሐብል" حَبْل ማለት "ዘለበት" ወይም "ገመድ" ማለት ሲሆን ሙፈሲሪን የአላህ ዘለበት የተባለው የአላህ መጽሐፍ፣ ኪዳን፣ ሃይማኖት ነው ብለው አስቀምጠውታል፤ ይህንን ጠቅለል ስናደርገው "ኢስላም" ይሆናል፦
3፥102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፡፡ እናንተም *ሙስሊሞች* ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ أَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ ፡፡
3፥103 *የአላህንም ገመድ ሁላችሁም ያዙ*፡፡ አትለያዩም وَٱعْتَصِمُوا۟ بِحَبْلِ ٱللَّهِ جَمِيعًۭا وَلَا تَفَرَّقُوا۟ ۚ ፡፡

ይህንን ዘለበት የያዘ ሰው ልዩነት ውስጥ አይገባም፤ አላህም "አትለያዩ" ብሎ አስጠንቅቋል፤ ከቁርአን መውረድ በፊት የነበሩት ህዝቦች እንደተለያዩት እና እንደተከፋፈሉት አትለያዩ ብሎናል፦
30:32 ከነዚያ *ሃይማኖታቸውን ከለያዩት እና ክፍልፍሎችም ከኾኑት አትኹኑ*፤

አምላካችን አላህ ስለ "አንድንት" ብዙ ጊዜ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይናገራል፤ ኢስላም ማለት አላህ ኑሕን፣ ኢብራሂምን፣ ሙሳንና ዒሳንም ያዘዘበትን ሃይማኖት እንደሆነ ይናገራል፤ ይህ ሃይማኖት በመያዝ በኢስላም "አትለያዩ ይለናል፦
42:13 ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፤ ያንንም በርሱ ኢብራሂምን፣ ሙሳንና ዒሳንም ያዘዘበትን፣ ሃይማኖትን በትክክል አቋቋሙ፣ *በእርሱም አትለያዩ* ማለትን ደነገግን።

ነጥብ አንድ
""ዉስቃ"
"ዉስቃ" وُثْقَىٰ "ገመድ" ወይም "ዘለበት" ማለት ሲሆን ይህ ዘለበት በቁርአን "ጠንካራ ዘለበት" ተብሏል፦
31:22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ "ፊቱን" وَجْهَهُ ወደ አላህ "የሚሰጥም" يُسْلِمْ ሰው፣ "ጠንካራ ገመድ" بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፤ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው።
2:256 በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ "የሌላትን ጠንካራ" بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

ይህ ጠንካራ ዘለበት “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ “ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም” የሚለው ቃለ-ምስክርነት ነው፤ በዚህ ቃል ማንኛውንም ጣኦታትን ክደን "ሌላ አምላክ የለም" ብለን የምናፈርስበትና አንዱን አምላክ አላህ አምነን የምናፀናበት ጠንካራ ዘለበት ነው፤ በዚህ ዘለበት እራሳችንን መሉ ለሙሉ ለአላህ በአምልኮ የምንታዘዝበት ነው፤ "ፊት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ወጅህ" وَجْه ሲሆን "ሁለንተና" ማለት ነው፦
3:20 ቢከራከሩህም :- "ፊቴን" وَجْهِيَ "ለአላህ ሰጠሁ"፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ በላቸዉ፤
4:125 እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ "ፊቱን" وَجْهَهُ "ለአላህ ከሠጠ" እና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን፣ ከተከተለ ሰው፣ ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ሰው ማነው?

"ለአላህ ሰጠሁ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል ይሰመርበት፤ "ሰጠሁ" ተብሎ የተቀመጠበት ግስ "አስለምቱ" أَسْلَمْتُ ሲሆን "ታዘዝኩ" ማለት ነው፤ ስለዚህ የዚህ የመታዘዝ እንብርቱና አስኳሉ የአላህ ዘለበት ነው፤ "ኢስላም" እነዚህን ሁሉ የሚጠቀልል ስም ነው፤ እስቲ የሚቀጥለውን ነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ ሁለት
"ኢስላም"
"ኢስላም" إِسْلَٰم ማለት "መታዘዝ" ማለት ሲሆን የአላህ ሃይማኖት ነው፦
አላህ ዘንድ ሃይማኖት "ኢስላም" الْإِسْلَامُ ብቻ ነው፡፡
110፥2 ሰዎችንም ጭፍሮች እየኾኑ፤ በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ሲገቡ ባየህ ጊዜ وَرَأَيْتَ ٱلنَّاسَ يَدْخُلُونَ فِى دِينِ ٱللَّهِ أَفْوَاجًۭا ፤
2:139 እኛም "ለእርሱ ፍጹም ታዛዦች" ስንኾን "በአላህ ሃይማኖት" ትከራከሩናላችሁን? በላቸው፡፡

ሁለንተናውን አላህን ለማምለክ "ታዛዥ" የሆነው ግለሰብ ደግሞ "ሙስሊም" مُسْلِم ይባላል፤ አንድ የአላህ ዘለበት የጨበጠ ሰው "ለእርሱ ታዛዥ" ነው፦
29:46 በሉም ፦ በዚያ ወደኛ በተወረደው፣ ወደናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፤ እኛም "ለእርሱ ታዛዦች" مُسْلِمُونَ ነን።
2:136 እኛም "ለእርሱ ታዛዦች" مُسْلِمُونَ ነን» በሉ፡፡
3፥84 እኛ "ለእርሱ ታዛዦች" مُسْلِمُونَ ነን፣ በል።
21:108 ያ ወደኔ የሚወረደው፣ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም "ታዛዦች" مُسْلِمُونَ ናችሁን? በላቸው።

"ታዛዦች" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሙስሊሙን" مُسْلِمُونَ ሲሆን የሙስሊም ብዙ ቁጥር ነው፤ "በሉ" የተባልነው ስማችን "ሙስሊም" እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህን ስም ያወጣው የጉባኤ ስብስብ ሳይሆን የዓለማቱ ጌታ ነው፤ ከዚህ ስም ውጪ ያማረ ቃል የት አለ? አላህ ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ ብሎናል፦
22፥78 በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ፤ እርሱ አላህ መርጧችኋል፤ በእናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፤ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፤ እርሱ አላህ ከዚህ በፊት "ሙስሊሞች" الْمُسْلِمِينَ ብሎ ሰይሟችኋል፡፡
41:33 ወደ አላህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ፣ እኔ "ከሙስሊሞች" الْمُسْلِمِينَ ነኝ ካለም ቃሉ ያማረ ማነው?
3፥102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፡፡ እናንተም "ሙስሊሞች" مُّسْلِمُونَ ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ ፡፡

አላህ ሙስሊም ሳትሆኑ እንዳትሞቱ፣ ሙስሊም ከሚለው ስም ያማረ ስም የለም እያለን እኛ ማን ነንና ነው ታፔላ እየለጠፍን በማንፈልግበት ስም የምንጠራራው? "አልቃብ" أَلْقَٰب ማለት "ቅፅል ስም"nickname" ነው፤ በዚህ ስም መጠራራት ሆነ እርስ በእርሳችን አንዱ ሌላውን ማነወር፣ መንቀፍ፣ መዝለፍ ሃራም ነው፦
49:11እላንተ ያመናችሁ ሆይ .. እራሳችሁንም አታነውሩ፤ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ وَلَا تَلْمِزُوا أَنْفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ ፤
ነጥብ ሶስት
"ኡማ"
“ኡማ” أُمَّة የሚለው ቃል “ህዝብ” “ማህበረሰብ” ማህበር” “ሃማኖታዊ ጉባኤ” የሚል ፍቺ አለው፤ ይህ የሙስሊም ኡማ አንድ ኡማ ነው፦
21:92 ይህች አንዲት ኡማ ስትኾን በእርግጥ ኡማችሁ ናት إِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً ፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ።
Dr. Laleh Bakhtiar translation፦ Truly, this, your community, is one community and I am your Lord so worship Me
23:52 ይህችም አንድ ኡማ ስትኾን ኡማችሁ ናት وَإِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً ፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፡፡
Dr. Laleh Bakhtiar translation፦ And, truly, this, your community is one community and I am your Lord so be Godfearing.

ይህ የሙስሊሙ ኡማ ምርጥ እና ሚዛናዊ ኡማ ነው፦
2፥143 እንደዚሁም በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልክተኛውም በእናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ “ምርጥ” “ኡማ” أُمَّةً አደረግናችሁ፡፡
3፥110 ለሰዎች ከተገለጸች “ኡማ” أُمَّةٍ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ፤ በአላህም ታምናላችሁ፡፡

ይህ ኡማ አንድነቱን ሊያደፈርስ የሚችለው ልዩነት ጭቅጭቅ ነው፤ መጨቃጨቅ ፍርሃት ያመጣል፣ ሃይል ያጠፋል፣ አላህ ዘንድ ታላቅ ቅጣት አለው፤ ከአላህ ጋር እተሰሰባለው ብሎ በአላህ የሚያምን እና በመጨረሻው ቀን ወሮታና አፀፌታ አለ ብሎ በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚያከራክር ጉዳይ ካለ ወደ አላህ ቁርአን እና ወደ መልእክተኛው ሐዲስ በመመለስ አላህና መልእክተኛውን ይታዘዛል፤ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፦
3:105 እንደነዚያም ግልጽ ታምራት ከመጣላቸዉ በኋላ *እንደተለያዩት እና እንደ "ተጨቃጨቁት አትሁኑ"፤ እነዚያም ለእነርሱ "ታላቅ ቅጣት" አላቸዉ።
8:46 *አላህንና መልክተኛውንም* ታዘዙ፤ አትጨቃጨቁም፤ "ትፈራላችሁና" "ኃይላችሁም" ትኼዳለችና፤
4:59 በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኑ የተከራከራችሁበትን ነገር *ወደ አላህና ወደ መልክተኛው* መልሱት ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው።

አላህም ይህ የሙስሊም ኡማ በእርሱ ላይ ምንም የማያጋሩ ሆነው ያመልኩኛል ብሏል፤ በተረፈ አላህ እና መልእክተኛውን ከመታዘዝ ወዲያ ሌላው ነገር ሁሉ አመፅ ነው፤ ሰውዬውም "አመጸኛ ነው፦
24፥55 *በእኔ* ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል፤ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئً ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡

አላህ የእርሱ ዘለበት ይዘን ሳንለያይ ሙስሊም ሆነው ከሚሞቱት ባሮቹ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የምርኮ ገንዘብ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

8፥1 ከአንፋል ይጠይቁሃል፡፡ በል፦ «አንፋል የአሏህ እና የመልእክተኛው ናቸው፡፡» يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَنفَالِ ۖ قُلِ الْأَنفَالُ لِلَّهِ وَالرَّسُولِ

የግጭት አዙሪት እና የጭቅጭቅ ቀለበት አባዜ የተጠናወታቸው ሚሽነሪዎች "ቁርኣን ዝረፉ ይላል" በማለት መጥኔ የሌለው ሥርዋጽ ሲለቁ እያየን ነው፥ የመካከለኛው ምሥራቅ ትኩሳት ተስታኮ ለማሳጣት ሾርኔ መሆኑ ነው። "ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል" ነውና ነገሩ መስመር የሳተ አስተሳሰብ ቢሆንም ጥሩ የውይይት ማሳለጫ ነው፥ ከከርሞ ዘንድሮ ለያዥ ለገናዥ በማያመች መልኩ ቅሌቱ ቢያገረሽባቸውም እኛ ደግሞ "ከፋህም ከረፋህም" ሳንል መልስ እንሰጣለን።
"ነፈል" نَفَل የሚለው ቃል"ነፈለ" نَفَلَ ማለትም "ማረከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ምርኮ" ማለት ነው፥ የነፈል ብዙ ቁጥር ደግሞ "አንፋል" أَنفَال ሲሆን "ምርኮዎች" ማለት ነው፦
8፥1 ከአንፋል ይጠይቁሃል፡፡ በል፦ «አንፋል የአሏህ እና የመልእክተኛው ናቸው፡፡» يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَنفَالِ ۖ قُلِ الْأَنفَالُ لِلَّهِ وَالرَّسُولِ

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ ትርጉም ላይ "የጦር ዘረፋ" "የዘረፋ ገንዘብ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አል አንፋል" الْأَنفَال ሲሆን በቀላሉ ከጦነት በኃላ የሚገኙ "ምርኮዎች" ናቸው፥ 8ኛ ሡራህ እራሱ ስሙ "ሡረቱል አንፋል" سُورَة الْأَنفَال ነው። ይህም ምርኮ አንድ አምስተኛው ለአሏህ፣ ለመልእክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለመንገደኛ የተገባ ነው፦
8፥41 ከማንኛውም የምርኮ ገንዘብ የዘረፋችሁትም አንድ አምስተኛው ለአሏህ እና ለመልእክተኛው፣ የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ። وَاعْلَمُوا أَنَّمَا غَنِمْتُم مِّن شَيْءٍ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ

በቁርኣን ስለ አንፋል እዚህ ድረስ አጥለን እና አጠንፍፈን ከተረዳን ዘንዳ መጅ እና ወፍጮ ይዘን ስለ ምርኮ በባይብል የተነገሩት በቅጡ አድቅቀን እናያለን። ነቢዩ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከነገሥታቱ የዘረፈውን ለሳሌም ንጉሥ ለመልከ ጼዴቅ ሰጥቶታል፦
ዕብራውያን 7፥4 የአባቶች አለቃ አብርሃም "ከዘረፋው" የሚሻለውን አስራት የሰጠው ይህ ሰው እንዴት ትልቅ እንደ ነበረ እስኪ ተመልከቱ።

"ከዘረፋው" የሚለው ይሰመርበት! አብርሃም በጦርነት ምርኮን ስለዘረፈ ሌባ ነውን? መዝረፉስ ሌብነት ነውን? ጉድ ፈላ፥ ይህ ከድጡ ወደ ማጡ ነው። የያዕቆብ ልጆች እኅታቸው ዲና ስለተደፈረች ደፋሪዎችን ገድለው በከተማይቱ ያሉትን በጎቻቸውን፣ ላሞቻቸውን፣ አህዮቻቸውን፣ በውጭም ያለው፣ ሀብታቸውን ሁሉ፣ ሕፃናቶቻቸውን፣ ሴቶቻቸውንም እና በቤት ያለውንም ሁሉ ዘረፉ፦
ዘፍጥረት 34፥27-29 የያዕቆብም ልጆች እኅታቸውን ዲናን ሰለ አረከሱአት ወደ ሞቱት ገብተው ከተማይቱን "ዘረፉ"፤ በጎቻቸውንም ላሞቻቸውንም አህዮቻቸውንም በውጭም በከተማም ያለውን ወሰዱ። ሀብታቸውን ሁሉ ሕፃናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውንም ሁሉ ማረኩ፥ በቤት ያለውንም ሁሉ "ዘረፉ"።

"ዘረፉ" የሚለው ይሰመርበት! ይህንን ስታነቡ ሰኔ እና ሰኞ ይሆንባቸዋል። በዚህ ቢቆም ጥሩ ነበር፥ እስራኤላውያንም ከግብፅ ሲወጡ የግብፅ ንብረት በዝብዘው ነበር። ይህንን ያደረጉት ከተማይቱን በማቃጠል ነው፥ ይህንን ያዘዛቸው የእስራኤል አምላክ እንደሆነ ባይብሉ ይናገራል፦
ዘጸአት 3፥22 ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር ዕቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም "ትበዘብዛላች"።
ዘጸአት 12:36 እግዚአብሔርም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት የፈለጉትን እንዲሰጡአቸው ሞገስን ሰጠ። እነርሱም ግብፃውያንን "በዘበዙ"።

"ትበዘብዛላች" የሚለው መጻኢ ግሥ እና "በዘበዙ" የሚለው አላፊ ግሥ ይሰመርበት! በትእዛዙ መሠረት በመንገድ ላይም ያደረጉት ይህንን ተግባር ነው ፦
ዘኍልቍ 31፥9-11 የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን "ማረኩ"፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ "በዘበዙ"። የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። "የሰውን እና የእንስሳን ምርኮና ብዝበዛ ሁሉ ወሰዱ"።
ዘኍልቍ 31፥53 ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ "ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ"።
ኢያሱ 8፥27 ነገር ግን ያህዌህ ኢያሱን እንዳዘዘው ቃል የዚያችን ከተማ ከብት እና ምርኮ እስራኤል ለራሳቸው "ዘረፉ"።
ኢያሱ 11፥14 የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው "ዘረፉ"።

"የምርኮ ገንዘብ ለአሏህ ምን ያደርግለታል" የምትሉ ግን በጤናችሁ ነውን? የምርኮ ገንዘብ ከአምስት መቶ አንድ ለያህዌህ ነው፦
ዘኍልቍ 31፥28 ከእነዚያም ከተዋጉት ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ፥ ከሰዎችም ከበሬዎችም ከአህዮችም ከመንጎችም ከአምስት መቶ አንድ ለያህዌ ግብር አውጣ።

ከአምስት መቶ አንድ ለያህዌህ ግብር ምን ያረግለታል? በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። ስለ ዘረፋ በባይብል ልቀጥል ብል ቦታ አይበቃኝም፥ አንባቢንም ማሰልቸት ነው። መቼም ሚሽነሪዎች የኢሥላም ትምህርት ጥንብ እኩሱን ቢወጣ እና ዶግ አመድ ቢሆንላቸው ደስታቸው እጥፍ ድርብ ነው፥ ይህ ጡዘቱ ጣራ የነካና ዙሪያ ገባ ምኞች ስለማይሳካ በቁጭ ይሙቱ! ከእነርሱ ቅንነት የተሞላው ትምህርት መጠበቅ ማለት ከጅብ አፍ ላይ ሥጋ እንደመጠበቅ ነው። እነርሱ የሚሰጡት ትችት እኛ ሙሥሊሞችን የሚያፍረከርክ ሳይሆን ከእለት ወደ እለት የሚያጀግን ነው፥ ለማንኛውም የተነሳውን ትችት አብጠርጥረን እና አንጠርጥረን መልስ ሰተናል። አሏህ ለእነርሱ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መርየም እና ልጇ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

3፥36 *በወለደቻትም ጊዜ*፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሴት ኾና ወለድኋት፡፡» አላህም የወለደችውን ዐዋቂ ነው፡፡ «ወንድም እንደ ሴት አይደለም፡፡ እኔም መርየም ብዬ ስም አወጣሁላት፡፡ እኔም *እስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ*» አለች፡፡ فَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّي وَضَعْتُهَا أُنثَىٰ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنثَىٰ ۖ وَإِنِّي سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

ብዙ ክርስቲያኖች ይህንን የሐዲስ ዘገባ ይዘው የኢየሱስን ከሸይጧን መጠበቅ ለአምላክነት መስፈርት አድርገው ይጠቀሙበታል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60 , ሐዲስ 102:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ” ከአደም ልጅ መካከል አንድ የለም ሸይጣን የሚነካው ቢሆን እንጂ፤ አንድ ህጻን ጮክ ብሎ ያለቅሳል በውልደት ጊዜ ሸይጣን ስለሚነካው ከመርየም እና ከልጇ በስተቀር፤ ከዛም አቢ ሁረይራህ፦ 3፥36 እኔም እርስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» የሚለውን አለ። حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنِ الزُّهْرِيِّ، قَالَ حَدَّثَنِي سَعِيدُ بْنُ الْمُسَيَّبِ، قَالَ قَالَ أَبُو هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ مَا مِنْ بَنِي آدَمَ مَوْلُودٌ إِلاَّ يَمَسُّهُ الشَّيْطَانُ حِينَ يُولَدُ، فَيَسْتَهِلُّ صَارِخًا مِنْ مَسِّ الشَّيْطَانِ، غَيْرَ مَرْيَمَ وَابْنِهَا ‏”‌‏.‏ ثُمَّ يَقُولُ أَبُو هُرَيْرَةَ ‏{‏وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ ‏}‌‏.‏

ሲጀመር ያላስተዋሉት ነገር ግን ከሸይጧን መጠበቅ የኢየሱስ ብቻ ሳይሆን የእናቱም የማርያምም ጉዳይ ነው፤ ታዲያ ማርያም አምላክ ነችን? አይ ከተባለ ታዲያ ማርያምና ልጇ እንዴት ሸይጧን ሳይነካቸው ቀረ? ከተባለ መልሱ የመርየም እናት ልጇን መርየምን እና የልጅ ልጇን ከሸይጧን ለመጠበቅ ኢስቲዓዛ አድርጋ ነበር፤ አቢ ሁረይራህም ያስቀመጠው በዚህ መልኩ ነው፦
3፥36 *በወለደቻትም ጊዜ*፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሴት ኾና ወለድኋት፡፡» አላህም የወለደችውን ዐዋቂ ነው፡፡ «ወንድም እንደ ሴት አይደለም፡፡ እኔም መርየም ብዬ ስም አወጣሁላት፡፡ እኔም *እስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ*» አለች፡፡ فَلَمَّا وَضَعَتْهَا قَالَتْ رَبِّ إِنِّي وَضَعْتُهَا أُنثَىٰ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا وَضَعَتْ وَلَيْسَ الذَّكَرُ كَالْأُنثَىٰ ۖ وَإِنِّي سَمَّيْتُهَا مَرْيَمَ وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

ሲቀጥል እዚህ ሐዲስ ላይ “ከመርየም እና ከልጇ በስተቀር” በሚለው ቃል ላይ “ኢልላ” إِلَّا ማለትም “በቀር” የሚለው ቃል “ኢስቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም “ግድባዊት”Exceptional” አለ፤ ይህ “ኢልላ” የሚለው ቃል በፍጹማዊ ግድብነት“Absolute Exception”” ሲመጣ “ሙጥለቅ” مطلق ይባላል፤ በአንጻራዊ ግድብነት“Relative Exception”” ሲመጣ ቀሪብ” قريب ይባላል፤ እዚህ ሐዲስ ላይ የመጣው ቀሪብ መሆኑ ይህ ሐዲስ ያሳየናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 92:
ኢብኑ አባስ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “ከእናንተ መካከል ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ሲያደርግ፦ “አላህ ሆይ ከሸይጧን ጠብቀኝ፤ ሸይጧንን ወደ ረዘቅከን ከመቅረብ አግድልን” ይበል፤ ሴቲቱም ልጅ ቅሪት ከሆነች ሸይጧን አይጎዳውም በእርሱም ላይ ሃይል የለውም። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَوْ أَنَّ أَحَدَكُمْ إِذَا أَتَى أَهْلَهُ قَالَ ‏{‏اللَّهُمَّ‏}‏ جَنِّبْنِي الشَّيْطَانَ، وَجَنِّبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنِي‏.‏ فَإِنْ كَانَ بَيْنَهُمَا وَلَدٌ لَمْ يَضُرُّهُ الشَّيْطَانُ، وَلَمْ يُسَلَّطْ عَلَيْهِ ‏”‌‏

ከእነዚህ ሐዲሳት የምንረዳው የመርየም እናት ልጇን መርየምን እና የልጅ ልጇን ከሸይጧን ለመጠበቅ ኢስቲዓዛ እንዳደረገች ሁሉ እኛም ልጆቻችን ከሸይጧን ለመጠበቅ ኢስቲዓዛ እናደርጋለን፤ ያ ማለት ልጆቻችን አማልክት ይሆናሉ ማለት አይደለም። ስለዚህ የኢየሱስን ከሸይጧን መጠበቅ ለአምላክነት መስፈርት አድርጎ መጠቀም ስሁት ሙግት ነው። በትንሳኤ ቀን ሁሉም ስህተተኛ ሆነው ይመጣሉ ከየህያ ኢብኑ ዘከርያ በስተቀር ተብሏል። ያ ማለት የሕያ አምላክ ነው ማለት አይደለም፦
ሙስነድ አህመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 2294
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ስህተተኛ ሆነው ይመጣሉ ከየህያ ኢብኑ ዘከርያ በስተቀር*። عن رسول الله صلى الله عليه وسلم أنه قال: ” كُلُّ بَنِي آدَمَ يَأْتي يَوْمَ القِيامَةِ وَلَهُ ذَنْبٌ إلا ما كانَ مِنْ يَحْيَى بنِ زَكَريَّا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዒሣ ሞቷልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥55 አላህም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ “ዒሣ ሆይ! እኔ *”ወሳጂህ”* እና ወደ እኔም *”አንሺህ”* ነኝ”፡፡ إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ

ክርስትና በአውሮፓ ላይ የተሸመነበት ድርና ማግ እንደሆነ ሁሉ የተዋረደበት ማቅ፣ የተገነዘበት በፍታ፣ የተከፈነበት ግምዣ ነው ብዬ ብናገር እብለትም ወይም ግነትም አሊያም ቅጥፈትም አይደለም። ሚሽነሪዎች፦ "ቁርኣን፦ ዒሣ ሞቷል" ይላል ብለው የአሕመድያን ጽርፈት ሲያስተጋቡ ይታያል። የአሕመድያን ጽርፈት ቧጦና ጓጦ ቁርኣን ላይ መፈለግ አባጣና ጎርባጣ የሆነ የሥነ-አፈታት ጥናት"hermeneutics" ነው። ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት። ለናሙና ያክል አንዳንድ የቋንቋ ሙግት እንመልከት፦
“ፊ” فِي ማለት “ውስጥ” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል እና “ፈውቅ” فَوْق ማለትም “በላይ” በሚል ይመጣል።
“ወ” وَ ማለት “እና” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል ይመጣል።
“ላ” َلَا ማለት “አይደለም” ማለት ቢሆንም “ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” በሚል ይመጣል።
“ማ” مَا ማለት “አይደለም” ማለት ቢሆንም “አለዚ” الَّذِي ማለትም “ያ” በሚል ይመጣል።
“በአሠ” بَعَثَ ማለት “አስነሳ” ማለት ቢሆንም “አርሰለ” أَرْسَلَ ማለትም “ላከ” በሚል ይመጣል።
“ጀንብ” جَنب ማለት “ጎን” ማለት ቢሆንም “ሚን” مِن ማለትም “በኩል” በሚል ይመጣል።
“ተእዊል” تَأْوِيل ማለት “ትርጉም” ማለት ቢሆንም “አኺር” آخِر ማለትም “መጨረሻ” በሚል ይመጣል።
ይህንን በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ካየን ዘንዳ "ወፋ" وَفَّىٰٓ የሚለውም ግስ "ሞላ" "ተኛ" "ሞተ" "ወሰደ" በሚል ይመጣል፦

ነጥብ አንድ
"ሞላ"
"ወፋ" وَفَّىٰٓ ማለት "ሞላ" የመጣበት አንቀጽ ለምሳሌ ይህ ነው፦
2፥272 እነርሱን ማቅናት በአንተ ላይ የለብህም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል፡፡ ከገንዘብም የምትለግሱት ምንዳው ለራሳችሁ ነው፡፡ የአላህንም ውዴታውን ለመፈለግ እንጂ አትለግሱም፡፡ ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ ምንዳው ወደ እናንተ *"ይሞላል"*፡፡ እናንተም አትበደሉም፡፡ لَّيْسَ عَلَيْكَ هُدَاهُمْ وَلَـٰكِنَّ اللَّهَ يَهْدِي مَن يَشَاءُ ۗ وَمَا تُنفِقُوا مِنْ خَيْرٍ فَلِأَنفُسِكُمْ ۚ وَمَا تُنفِقُونَ إِلَّا ابْتِغَاءَ وَجْهِ اللَّهِ ۚ وَمَا تُنفِقُوا مِنْ خَيْرٍ يُوَفَّ إِلَيْكُمْ وَأَنتُمْ لَا تُظْلَمُونَ

"ይሞላል" የሚለው የወደፊት ግስ "ዩወፈ" يُوَفَّ ሲሆን "ይሞታል" ብለን ከተረጎምነው ከዐውደ-ንባቡ ጋር ክፉኛ ይላተማል፦
3፥185 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም *የምትሞሉት* በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ

"የምትሞሉት" ለሚለው ቃል የመጣው "ቱወፈውነ" تُوَفَّوْنَ ነው። "የምትሞሉት" የሚለው "የምትሞቱት" ብለን ብንተረጉመው "ምንዳዎቻችሁንም *የምትሞቱት* በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው" ትርጉም አይሰጥም።

ነጥብ ሁለት
"ተኛ"
ወፋ" وَفَّىٰٓ ማለት "ተኛ" በሚል የመጣበት አንቀጽ ለምሳሌ ይህ ነው፦
6፥60 እርሱም ያ በሌሊት *”የሚያስተኛችሁ”* በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ *”የሚቀሰቅሳችሁ”* ነው፡፡ ከዚያም *”መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው”*፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰٓ أَجَلٌۭ مُّسَمًّۭى ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

አንቀፅ ላይ “የሚያስተኛችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው።

ነጥብ ሦስት
"ሞተ"
"ወፋ" وَفَّىٰٓ ማለት "ሞተ" በሚል የመጣበት አንቀጽ ለምሳሌ ይህ ነው፦
2፥234 እነዚያም ከእናንተ ውስጥ *"የሚሞቱ"* እና ሚስቶችን የሚተዉ ሚስቶቻቸው በነፍሶቻቸው አራት ወሮች ከዐስር ቀናት ከጋብቻ ይታገሱ፡፡ وَالَّذِينَ يُتَوَفَّوْنَ مِنكُمْ وَيَذَرُونَ أَزْوَاجًا يَتَرَبَّصْنَ بِأَنفُسِهِنَّ أَرْبَعَةَ أَشْهُرٍ وَعَشْرًا

"የሚሞቱ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ዩተወፈውነ" يُتَوَفَّوْنَ ነው።