ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.4K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ለምሳሌ፦
አንደኛ በ 50-138 AD የማቲያስ ተማሪ የነበረው ባስሊዲስ በ 117 AD ላይ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የቀሬናን ስምዖንን እንደሰቀሉት ይናገራል፤ ይህንን ወንጌል በኃላ ላይ የመጡት አበው በ 130-200 AD ይኖር የነበረ ኢራኒየስ፣ በ 150-215 AD ይኖር የነበረ የአሌክሳንድሪያው ክሌመንት ተቃወሙት፤ ብዙ ጊዜ ከባስሊዲስ ወንጌል ላይ 260-340 AD ይኖር የነበረው የቂሳሪያው አውሳቢዮስ ይጠቅስ ነበረ።

ሁለተኛ በ 60-135 AD ይኖር የነበረው በርናባስ የበርናባስን ወንጌል፣ የበርናባስን መልእክት እና የበርናባስ ሥራ በ 100–131 AD አዘጋጅቷል፤ በሳይናቲከስ ኮዴክስ ላይ ፓሊካርፕ ለፊሊጵስዩስ በጻፈው ፓሊላርፕ 1፥1 ቀጥሎ የበርናባስ መልእክት 5፥7 ይቀጥልል። እዚህ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደሰቀሉት ይናገራል።

ሦስተኛ በ 85-160 AD ይኖር የነበረው የሲኖፕ ማርኮይን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የማርኮናይት ወንጌል በ 1740 AD ከተገኙት የሙራቶሪያን ብጥስጣሽ"Muratorian fragment" አንዱ ነው፤ የካርቴጅ ጉባኤ ከማርኮናይት ግሩፕ ውስጥ የዮሐንስን አፓልካሊፕስ"ራእይ" ተቀብላ በእነርሱ የነበረውን የጳውሎስን አፓልካሊፕስ፣ የጴጥሮስን አፓልካሊፕስ፣ የቶማስን አፓልካሊፕስ፣ የእስጢፋኖስን አፓልካሊፕስ፣ የያዕቆብን አፓልካሊፕስ ደብቃቸዋለች።
በማርኮናይት ወንጌል ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ እና እርሱን እንሰቅላለን ብለው የሮማ ወታደር እንደሰቀሉት ይናገራል።

አራተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ኤቦን ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የኤቦናይት ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። በ 347-420 AD ይኖር የነበረው ጄሮም ኤቦን በዮሐንስ ዘመን ይኖር እንደነበረ መስክሯል። ነገር ግን ኤቦንን በ 36-115 AD ይኖር የነበረው የቆሮጵሮሱ ኤጵፋኒየስ አውግዞቷል።
አምስተኛ በ 36-115 AD ይኖር የነበረው ሰርቲዩስ ወንጌል አዘጋጅቷል፤ ይህ የሰርቲዩስ ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል።

ስድስተኛ በ 36 AD ጀምረው ይኖሩ የነበሩት ናዝራውያን ወንጌል አዘጋጅተዋል፤ ይህ የናዝራውያን ወንጌል ላይ፦ "ኢየሱስ ሳይሰቀል ወደ ሰማይ እንዳረገ ይናገራል። ናዝራውያን የሙሴን ሕግ ይቀበላሉ፤ የኢየሱስን በድንግና መወለድ ይቀበላሉ፣ የሌሎችን ወንጌላት አይቀበሉም።

በግሪክ ኮይኔ የተዘጋጁት ወንጌሎች የትዬለሌ ናቸው፤ እነርሱም፦ የቶማስ ወንጌል፣ የይሁዳ ወንጌል፣ የባስሊዲስ ወንጌል፣ የበርናባስ ወንጌል፣ የማርኮናይት ወንጌል፣ የኤቦናይት ወንጌል፣ የሰርቲዩስ ወንጌል፣ የናዝራውያን ወንጌል፣ የጴጥሮስ ወንጌል፣ የያዕቆብ ወንጌል፣ የፊሊጶስ ወንጌል፣ የበርተሎሜዎስ ወንጌል፣ የመቅደላዊት ማርያም ወንጌል፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ የማርቆስ ወንጌል፣ የሉቃስ ወንጌል፣ የዮሐንስ ወንጌል የመሳሰሉት ናቸው፣ በቁጥር ወደ 47 ይደርሳሉ፣ ዛሬ የቀኖና ወንጌሎች የተባሉት ኦርጅናል አራቱ ወንጌሎች የለም፣ አራቱ ወንጌላት ተጻፉ የሚባሉት ከ 60-100 AD ሲሆን የእነርሱ የቅጂ ቅጂ ብጥስጣሽ"fragments" እና ደንገሎቹ"papiruses" የሚያሳዩት ግን ከ 200-250 AD ነው፦ የማቴዎስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የማርቆስ ወንጌል ደንገል 45 የሚባለው በ 250 AD፣ የሉቃስ ወንጌል ደንገል 75 የሚባለው በ 250 AD፣ የዮሐንስ ወንጌል ደንገል 46 የሚባለው በ 200 AD ነው፣ ዛሬ ያሉት 5800 ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት ኢየሱስ ካስተማረ ከሶስት መቶ አመት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው፤ ዋና ዋናዎቹ ሳይናቲከስ ጥራዝ በ 330 AD፣ ቫቲካነስ ጥራዝ 350 AD፣ አሌክሳንድሪየስ ጥራዝ 400 AD፣ ኤፍሬማይ ጥራዝ 450 AD ላይ የተዘጋጁ ናቸው።

ይህ እንዲህ በእንዲህ እንዳለ በ 397 AD የካርቴጅ ጉባኤ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን የቅጂዎች ቅጂዎች የሆኑትን አራቱን ወንጌሎች ብቻ ቀኖና"canon" አድርጋ ሌሎችን ወንጌሎች "አፓክራፋ" አድርጋለች፤ "አፓክራፋ" የሚለው ቃል "አፓክራፈስ" ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ድብቅ" ማለት ነው፤ ለዛ ነው አምላካችን አላህ፦ "የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?" ብሎ የተናገረው፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ

“ከብዙውም የሚተው ሲኾን” ማለት የመጽሐፉ ባለቤቶች ከደበቋቸው ሁሉንም አልተናገሩም ማለት ነው፤ በቀኖና ያላካተቷቸው ግን የሸሸጓቸውን እንዳለ ይህ አንቀጽ ይጠቁማል፤ በወንጌሎች ታሪካዊ ዳራና ፍሰት ዋቢ መጽሐፍት ያደረኩት የአዲስ ኪዳን ምሁር የሆኑትን የፕሮፌሰር ባርት ሄርማን መጽሐፍት ነው፦
1. The Other Gospels: Accounts of Jesus from Outside the New Testament. Oxford University Press, USA. 2013 by Bart D. Ehrman
2. The Orthodox Corruption of Scripture: The Effect of Early Christological Controversies on the Text of the New Testament. Oxford University Press, USA. 2011
3. Lost Scriptures: Books that Did Not Make It into the New Testament. Oxford University Press, USA. 2003

ኢንሻላህ በክፍል ሥስት እንቀጥላለን....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጥያቄአችን!

የቱ ነው ትክክል?

A. ""ጆሬዬን ግን ከፈትክ""
አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕብራይስጡ በቀጥታ እንዲህ አስቀምጦታል፦
መዝሙር 40፥6 መሥዋዕትንና ቍርባንን አልፈለግህም፤ """ጆሬዬን ግን ከፈትክ""፤
ዕብራይስጡ፦ זֶבַח וּמִנְחָה, לֹא-חָפַצְתָּ-- אָזְנַיִם, כָּרִיתָ לִּי;

B. ""ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ""
ጳውሎስ ደግሞ ከየት እንዳመጣው ባይነግረንም በተቃራኒው ""ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ"" ብሏል፦
ዕብራውያን 10፥5 ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ""ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ""፤
ግሪኩ፦ τὸν κόσμον λέγει, Θυσίαν καὶ προσφορὰν οὐκ ἠθέλησας, σῶμα δὲ κατηρτίσω μοι:

ሲኮረጅ እንኳን በትክክል ለምን አይኮረጅም? ይህ ነው በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተጻፈው? ለመሆኑ የቱ ነው ትክክል ""ጆሬዬን ግን ከፈትክ"" ወይስ ""ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ""?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጥያቄ ለህዝበ ክርስቲያኑ

1ኛ. እንደ ባይብሉ ፉሲካ የሰንበት ዋዜማ ላይ ከሆነ ይህንን ፋሲካ ኢየሱስ ሀሙስ ፀሀይ ከጠለቀች በኃላ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አክብሯል፦
ዘሌዋውያን 23፥5 በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን #ሲመሽ የእግዚአብሔር #ፋሲካ #ነው
ዘኁልቅ 28፥16 በመጀመሪያው ወር ከወሩም ""በአሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ"" ነው።
ማቴዎስ 26፥19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ ፋሲካንም አሰናዱ።
ማርቆስ 14፥16 በዚያም አሰናዱልን። ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፥ ፋሲካንም አሰናዱ።
ሉቃስ 22፥13 ሄደውም እንዳላቸው አገኙና ፋሲካን አሰናዱ።

ጥያቄአችን ፋሲካ ከሀሙስ ማታ እስከ አርብ መአልት ከነበረ ፋሲካ እሁድ የሚከበርበት ቀን ከየት አመጣችሁት?
መረጃዋን ከባይብል ቁጭ ቁጭ አርጓት።

2ኛ. እንደ ባይብሉ ከሆነ ሶስት ቀንና ሌሊት የሚሸፍነው በምድር ልብ ማለትም በመቃብር ውስጥ ነው፦
ማቴዎስ 12፥40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ #በምድር #ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።

እንደ ባይብሉ ከሆነ ወደ መቃብር የገባው አርብ ምሽት የቅዳሜ ሌሊት ከሚጀምርበት ነው፦
በማለት በመቃብር ያለውን ጊዜ የሚሸፊን መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ መቃቢር የገባው ደግሞ በምሽት ነው፦
ማርቆስ 15፥42-46 አሁንም """#በመሸ #ጊዜ""" የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። ጲላጦስም አሁኑን እንዴት ሞተ ብሎ ተደነቀ፥ የመቶ አለቃውንም ጠርቶ ከሞተ ቆይቶአልን? ብሎ ጠየቀው፤ ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው። በፍታም ገዝቶ አውርዶም በበፍታ ከፈነው ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው፥ በመቃብሩ ደጃፍም ድንጋይ አንከባለለ።

""በመሸ ጊዜ""" የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ አይሁድ የሚያከብሩት በኣል ከ 12 ሰኣት በኃላ የነገው ነው፤ ቀኑም የሚጀመረውም ከሚሽቱ 12 ነው፤ ምሽት የሌሊት መጀመሪያ ነው፤ ሲመሽ ደግሞ ፀሀይ ትጠልቃለች ቀጣዩ ቀን በሌሊት ይጀመራል፦
ዘጸአት 12፥18 በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን "በመሸ ጊዜ" ከወሩም እስከ ሀያ አንድ ቀን #በመሸ #ጊዜ የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።
ማርቆስ 1፥32 "#ፀሐይም #ገብቶ #በመሸ ጊዜ"፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤

እንግዲህ ከዚህ ከሰንበት ማለት ከቅዳሜ ዋዜማ ምሽቱ የቅዳሜ ከሆነ ከዚያ ጀምራችሁ ቁጠሩት። ሰኞ ማታ ለማክሰኞ ለማክሰኞ ጅማሬ ላይ ይመጣል። ጥያቄአችን ሶስት መአልትና ሌሊት በመቃብር ከነበረ ሰኞ ማታ ለማክሰኞ ጅማሬ ትንሳኤ ከሆነ እንዴት እሁድ ሌሊት ተነሳ ይባላል?
መረጃዋን ከባይብል ቁጭ ቁጭ አርጓት።

3ኛ. ኢየሱስ የአላህ ነብይ ነው አይዋሽም፤ መቼም አራቱ ወንጌላት ላይ ያሉት ቃላት አይደለም የኢየሱስ ይቅርና የመጀመሪያዎቹ ፀሃፊያን ያልሆኑ ንግግሮች በእማኝነትና በአስረኝነት ማቅረብ ይቻላል፤ ነገር ግን ነጥባችን እርሱ አይደለም፤ ኢየሱስ ተናገረ ተብሎ የተቀጠፈበት ነገር እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ እንደ ማርቆስ ዘጋቢ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በኃላ” የሚለው መስተዋድድ በአራተኛው ቀን አሊያም በአምስተኛው ቀን ሊሆን ይችላል፤ ግን ሶስኛውን ቀን አይጨምርም፦
ማርቆስ 8፥31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ሊነሣ” እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።

የማቴዎ ዘጋቢ ደግሞ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በ” የሚለው መስተዋድድ ሶስተኛውን ቀን ብቻ የሚያመለክት ነው፦
ማቴዎስ 16፥21 ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ “”በሦስተኛውም ቀን” ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ነው ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ነው ብሎ የሚተርከው የማቴዎስ ዘጋቢ?
መረጃዋን ከባይብል ቁጭ ቁጭ አርጓት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
አልገደሉትም

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥157 *«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَـٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

ነጥብ ሁለት
"አልገደሉትም"
በነጥብ አንድ ስንመለከት በኢየሱስ ሁኔታ ዙሪያ ተገድሏል ወይስ አልተገደለም የሚለውን እሳቤ በወንጌሎች ዙሪያ የተለያዩ አመለካከቶች እንዳሉ አይተን ነበር፤ በወንጌሎች ውስጥ የተዘገበው ታሪክ ፈጣሪ የሚናገረው የፈጣሪ ንግግር ሳይሆን በቦታው ያልነበሩ ታሪክ ጸሐፊዎች የዘገቡት ነው፤ በቦታው ያልነበሩ ሰዎች የጻፉትን ይዞ መሞገት ስሁት ሙግት ነው፤ "ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ" ይባል የለ፤ አምላካችን አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር ሁሉ የሚያውቀው ነው፤ የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀተ ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን አያውቅምን? በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው? ማንም የለም፦
25፥6 *«ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና»* በላቸው፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ ٱلَّذِى يَعْلَمُ ٱلسِّرَّ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا
67፥14 *የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀተ ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን አያውቅምን?* أَلَا يَعْلَمُ مَنْ خَلَقَ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ
4፥87 አላህ ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም፡፡ ወደ ትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ *በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?* اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ ۗ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا

የመጸሐፉ ሰዎች አይሁድና ክርስቲያኖች የአላህን ንግግር ከሰው ንግግር ጋር በመቀላቀል በርዘውታል፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
“እውነት” የተባለው ከአላህ የወረደው ሲሆን “ውሸት” የተባለው ደግሞ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ነው፦
2:79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው*፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

የነብያችን”ﷺ” ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባስ”ረ.ዐ.” የሱረቱል በቀራ 2:79 አንቀጽ ሲፈስረው እንዲህ ይላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 46:
ኢብኑ አባስ ሲናገር፦ ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ የተወረደው ወቅታቂ ንግግርና የምትቀሩት እያለ? *መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል*። حَدَّثَنَا يَحْيَى بْنُ بُكَيْرٍ، حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ عُبَيْدِ اللَّهِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُتْبَةَ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ.

እውነት የሆነው የአላህ ንግግር ከሰው ንግግር ጋር ስለተቀላቀለ እውነትን ከሐሰት ለመለየት አምላካችን አላህ ቁርአንን አውርዷል፤ “ፉርቃን” فُرْقَان ማለት "እውነትን ከሐሰት የሚለይ" ማለት ነው፦
25፥1 ያ *ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا
3፥4 ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ *”ፉርቃንንም አወረደ”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ ٱلْفُرْقَانَ

ቁርኣን ፉርቃን ነው፤ እውነትን ከሐሰት ለመለየት ወርዷል፤ ይህንን ካየን ዘንዳ በዒሳ ጉዳይ ላይ እንግባ፤ የእስራኤልንም ልጆች ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልእክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ፤ ከፊሉንም ይገድላሉ፤ ነቢያትንም ያለ አግባብ በመግደላቸው ምክንያት ረገማቸው፦
2፥87 َ*ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልክተኛ በመጣላችሁ ቁጥር ከመከተል ትኮራላችሁን? ከፊሉን አስተባበላችሁ፤ ከፊሉንም ትገድላላችሁ*፡፡ أَفَكُلَّمَا جَآءَكُمْ رَسُولٌۢ بِمَا لَا تَهْوَىٰٓ أَنفُسُكُمُ ٱسْتَكْبَرْتُمْ فَفَرِيقًۭا كَذَّبْتُمْ وَفَرِيقًۭا تَقْتُلُون
5፥70 የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዝንባቸው፡፡ ወደ እነርሱም መልክተኞችን ላክን፡፡ *ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልእክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ፤ ከፊሉንም ይገድላሉ*፡፡ لَقَدْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَأَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمْ رُسُلًۭا ۖ كُلَّمَا جَآءَهُمْ رَسُولٌۢ بِمَا لَا تَهْوَىٰٓ أَنفُسُهُمْ فَرِيقًۭا كَذَّبُوا۟ وَفَرِيقًۭا يَقْتُلُونَ
4፥155 ቃል ኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው፣ በአላህም አንቀጾች በመካዳቸው፣ *ነቢያትንም ያለ አግባብ በመግደላቸው* እና «ልቦቻችا ሽፍኖች ናቸው» በማለታቸው ምክንያት ረገምናቸው፡፡ فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَٰقَهُمْ وَكُفْرِهِم بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَقَتْلِهِمُ ٱلْأَنۢبِيَآءَ بِغَيْرِ حَقٍّۢ وَقَوْلِهِمْ قُلُوبُنَا غُلْفٌۢ ۚ بَلْ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَيْهَا بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًۭا
በመቀጠል ሁሉም አይሁዳውን ዒሳ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከዝሙት የተወለደ ነው የሚል አቋም አላቸው፤ ፅንሱ ያለ አባት መወለዱን በምን ያውቃሉ? ማንስ ነግሮአቸዋል? ያ ነገር ታምር ቢሆንም መርየም አመንዝራ እንደሆነች በማሰብ በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን ቀጥፈዋል፤ ይህንን በማለታቸው አላህ ኮንኗቸዋል፦
4፥156 በመካዳቸውም *በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን በመናገራቸውም* ምክንያት ረገምናቸው፡፡ وَبِكُفْرِهِمْ وَقَوْلِهِمْ عَلَىٰ مَرْيَمَ بُهْتَٰنًا عَظِيمًۭا

አላህ ሆን ብሎ ከዝሙት እንደተወለደ ቢያስመስልባቸው ኖሮ ስለቀጠፉ መርገሙ ትርጉም አይኖረውም፤ ግን አይሁዳውያን አሁንም ሁሉም የዝሙት ልጅ ነው የሚል አቋም አላቸው። አንቀጹ እንዲህ ይቀጥላል፦
4፥157 *እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም ረገምናቸው*፡፡ وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا ٱلْمَسِيحَ عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ ٱللَّهِ

ይህንን ቅጥፈት የእራሳቸው ባይሆን ኖሮ ሰቀልንና ገደልን በማለታቸው ይረግማቸው ነበርን? ሁለቱንም ማለትም ዲቃላ ልጅ ማለታቸውና ሰቀልን ማለታቸው ስለመሰላቸው ነው፤ ግን ሁለቱንም አላህ በግልፅ ነግሯቸዋል፤ እየነገራቸው በመቅጠፋቸው ረገማቸው። እርግማን የበረከት ተቃራኒ ነው፦
4፥157 *አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነርሱ ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም*፡፡ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ لَفِى شَكٍّۢ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا ٱتِّبَاعَ ٱلظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًۢا

ሰቀልን፣ ገደልን እና ተሰቀለ፣ ተገደ የሚል ስላለ "አልገደሉትም አልሰቀሉትም" የሚለው ይህንን ያሳያል፤ "ሹብ" شُبِّ ማለት "መምሰል" ማለት ነው፤ የሰቀሉትና የገደሉት መስሏቸዋል፤ በእርግጥም አልገደሉትም፤ "ሊገድሉህ ሲያስቡህ ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ በዚህ ባህርያቸው ዒሳ በተአምራት በመጣባቸውና ከእነርሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ብለው ሊገድሉት ሲያስቡህ አላህ ወሰደው፤ አይሁዶችም ሊገሉት አደሙ አላህም ወደራሱ በመውሰድ አድማቸውን መለሰባቸው፤ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው፦
5፥110 አላህ በሚል ጊዜ አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ የዋልኩላችሁን ጸጋዬን አስታውስ፡፡ ... *የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣህባቸውና ከእነርሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ባሉ ጊዜ፣ ሊገድሉህ ሲያስቡህ ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ كَفَفْتُ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ عَنكَ إِذْ جِئْتَهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ فَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌۭ مُّبِينٌۭ
3፥54 *አይሁዶችም አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው፡፡ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው*፡፡ وَمَكَرُوا۟ وَمَكَرَ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

"መከረ" مَكَرَ ማለት "አቀደ" "አሴረ" ማለት ነው፤ "ማኪሪን" مَٰكِرِين ማለት "ሴረኞች" አቃጂዎች" እና "አድመኞች" ማለት ነው፤ አላህ ከማኪሪን ሁሉ በላጭ ነው አለ እንጂ "ማኪር" مَٰكِرِ አልተባለም። "መክር" مَكْر ማለት "ምክር" "እቅድ" "ሴራ" ማለት ነው፤ ለምሳሌ አላህ፦ እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያወጡህ በአንተ ላይ *"በመከሩብህ"* ጊዜ" ምክራቸውን በመመለስ መለኮታዊ ጥበቃ ለነብያችን አርጎላቸዋል፦
8፤30 እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያወጡህ በአንተ ላይ *"በመከሩብህ"* ጊዜ አስታውስ፡፡ *"ይመክራሉም"* አላህም *"ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል"*፡፡ አላህም *"ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው"*፡፡ وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

ሙፈሲሪን ማለትም የቁርአን አብራሪዎች ይህንን አንቀፅ በማስመልከት የተለያየ ትንተና ስጥተዋል፤ ይህንን ትንተና መነሻ ያደረጉት ቁርኣንን እና ሐዲስን መሰረት አድርገው ሳይሆን ኢስራኢልያት ሪዋያ መሰረት አድርገው ነው፤ በነጥብ አንድ ላይ ያሉትን የወንጌሎች ታሪካዊ ዳራ መሰረት ያደረገ አፈሳሰር ነው፤ ከኢስራኢልያት የሚገኙ ሪዋያ ሙሉ ለሙሉ ትክክል ነው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አንድ ተፍሲር ስሙር አፈሳሰር ነው የሚባለው አንደኛ ከሐዲስ በሚገኘው ሰሒህ ሪዋያ፣ ሁለተኛ ቁርአን በቁርአን ሲፈሰር፤ ሥስተኛ ዐውዱ ላይ የሚገኘው ነጥብ፣ አራተኛ የቁርኣኑ ቋንቋና ሰዋሰዉ በተቀመጠው ነጥብ ነው። ኢንሻላህ ይቀጥላል……

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አላህን መርዳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

47:7 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሃይማኖቱን) ብትረዱ ይረዳችኋል፤ ጫማዎቻቸሁንም ያደላድላልል።

ነጥብ አንድ
*ተብቃቂው*
አላህ ተብቃቂ ነው፣ በሰማያት ውስጥ ያለውና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉም ፍጥረት የራሱ ነው፣እኛ ፍጥረቱ ከእርሱ ከጃዮች እንጂ እርሱ ከእኛ ጥገኛ አይደለም፦
60፥6፡-አላህ *ተብቃቂው* ምስጉኑ እርሱ ብቻ ነውና፡፡
22፥64፡- በሰማያት ውስጥ ያለውና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ አላህም እርሱ *ተብቃቂው* ምስጉኑ ነው፡፡
35፥15፡- እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ *ከጃዮች* ናችሁ፡፡ አላህም እርሱ *ተብቃቂው* ምስጉኑ ነው፡፡

ነጥብ ሁለት
*እርዳታ*
ኢስላም ዲኑ የአላህ ስለሆነ ዲኑን መርዳት አላህን መርዳት ነው፣ አላህን መርዳት የሚለው ቃል ሃይማኖቱን መርዳት በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
22:40 አላህም *ሃይማኖቱን የሚረዳውን* ሰው፣ በእርግጥ ይረዳዋል፤
47:7 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ሃይማኖቱን) ብትረዱ ይረዳችኋል፤
57:25አላህም *ሃይማኖቱንና መልክተኞቹን* በሩቁ ሆኖ *የሚረዳውን* ሰው ሊገልጽ አወረደው፤

ዒሳ *ረዳቶቼ* እነማን ናቸዉ? ሲል ሃዋርያቱ፡- እኛ የአላህ *ረዳቶች* ነን አሉ፣ ምክንያቱም መልእክተኛውንና ዲኑን መርዳት አላህ መርዳት ነውና፡-
3:52 ዒሳ ከነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ ፡-ወደ አላህ *ረዳቶቼ* እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት፡- እኛ የአላህ *ረዳቶች* ነን፤ በአላህም አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መሆናችንን፥ መስክር፥ አሉ።
3:81 ከዚያም ከእናንተ ጋር ላለዉ መጽሐፍ የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላቸዉ፣ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም *እንድትረዱት* ሲል በያዘ ጊዜ አስታዉስ፤
59:8 ለነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉ *አላህንና መልክተኛውንም የሚረዱ* ሆነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡት ስደተኞች ድሆች ይሰጣል፤
ለዲኑ በገንዘባችን መርዳት ለአላህ ሰጥቶ በእጥፍ ይነባበርልናል፦
5:12 አላህም የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው። ከነሱም ዐሥራ ሁለትን አለቆች አስነሣን፤ አላህም አላቸው፤ እኔ ከናንተ ጋር ነኝ፤ ሶላትን ብታስተካክሉ ግዴታ ምጽዋትንም ብትሰጡ በመልክተኞቼም ብታምኑ፣ *ብትረዱአቸውም*፣ ለአላህም መልካም *ብድርን ብታበድሩ* ኃጢአቶቻችሁን ከናንተ በእርግጥ አብሳለሁ፤
35:29 እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱ, *ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም ሆነ በግልጽ *የለገሱ*፣ በፍጹም የማትከስርን *ንግድ* ተስፋ ያደርጋሉ።
73:20 ዘካንም ስጡ፤ ለአላህም መልካም *ብድርን አበድሩ*፤ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ፣ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ አላህ ዘንድ *ታገኙታላችሁ*፤
57:11 ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድር ለርሱም *የሚያነባብርለት* ሰው ማነው? ለርሱም መልካም ምንዳ አለው።

በተለይ *ለአላህም መልካም ብድርን ብታበድሩ እና በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ* የሚለው ሃረግ ይሰመርበት፣ አላህ ከሰጠን ሲሳይ ላይ ስንሰጥ በትርፍ ይመልስልናል፣ ይህ መንፈሳዊ ንግድ ነውና የሰጠነውን በሌላ እጥፍ አርጎ ይተካዋል፦
34:39 ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ *ይተካዋል*፤ እርሱም ከሲሳይ ሰጭዎች ሁሉ በላጭ ነው በላቸው።
8:60 ከማንኛውም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱትም ምንዳው *ወደ እናንተ በሙሉ ይሰጣል*፤ እናንተም አትበደሉም።
2:261 የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች ልግስና ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ቅንጣት ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንደ አበቀለች አንዲት ቅንጣት ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው ከዚህ በላይ ያነባብራል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡
2:265 የእነዚያም የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ለነፍሶቻቸው ለማረጋገጥ ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
57:18 የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህም መልካምን ብድር ያበደሩ ለነርሱ ይደራረብላቸዋል፤ብድሩን ለነርሱ ይደራረብላቸዋል፤ ለነርሱም መልካም ምንዳ አላቸው።
64:17 ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩ ምንዳውን ለናንተ ይደራርበዋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህ አመስጋኝ ታጋሽ ነው።

መቼም መበደር የሚለው ቃል ሰው ለሰው በሚበደርበት ስሌት ለአላህም ከተረዳነው መስጠት የሚለውን ቃልስ እንዴት ልንረዳው ነው? ምክንያቱም አንድ ሰው ለሌላ ሰው የሚሰጠው ነገር እርሱ ጋር የሌለና የራሱ ያልሆነውን ነው፤ ለአላህ የምንሰጠው ግን ከሰጠን ላይ የራሱ የአላህ ሲሆን የፍቅራችን መገለጫ ብቻ ነው፤ አላህ ተብቃቂ ነው፦
24:64 ንቁ፣ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፤
31:26 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው።

ሌላ አንድ ናሙና ማየት እንችላለን፦
2:152 “አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና” ለኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡

ምእመን አላህ ማስታውሱ አላህ ምእመኑን በሚያስታውስበት ሂሳብ እንዳልሆነ ሁሉ ምእመን አላህን መርዳትና አላህ ምእመንን መርዳት አንድ አይደለም።
መደምደሚያ
አይ ማገዝ በሰውኛ ካሰባችሁት፣ መበደር በሰውኛ ያጣ ሰውን አይነት ብርድ ካሰባችሁት እንግዲያውስ በራሳችሁ መጽሐፍ ለእግዚአብሔር ማበደር እንዳለ መረዳት አላባችሁ፣ እግዚአብሔር ይበደራልን?
መጽሐፈ ምሳሌ 19፥17 ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ *ለእግዚአብሔር ያበድራል*፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።

አስራት ከአስር አንድ ለፈጣሪ የሚሰጥ ነው፣ ስጡ ይሰጣችኋል ይላል፣ ያ ማለት ሰው ለፈጣሪ መስጥቱና ፈጣሪ ለሰው መስጠቱ አንድ ነውን?
ሉቃስ 6፥38 “ስጡ ይሰጣችሁማል”፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥
ዘሌዋውያን 27፥30 የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።

እግዚአብሔር ያከበሩኝን አከብራለሁ ይላል፣ ያ ማለት ሰው እግዚአብሔርን ማክበሩና እግዚአብሔር ሰውን ማክበሩ አንድ ነውን?
1ኛ ሳሙኤል 2፥30 አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ያከበሩኝን አከብራለሁና”፥

እግዚአብሔር ሰውን አከበረናና ለሰው ሰጠ የሚለው ቃላትና ሰው እግዚአብሔርን አከበረና ለእግዚአብሔር ሰጠ የሚሉት ቃላት ሁለት የተለያየ ደረጃ እንደሆነ ሁሉ አማኞች አላህን እርዱ ሲባልና አላህ አማኞችን መርዳቱ ሁለት ለየቅል የሆኑ ደረጃዎች ናቸው፣ ሆን ብሎ ጥመት ካልሆነ በስተቀር ይህንን እንኳን ህሊና ያውቀዋል፣ የራስንም መጽሃፍ በቅጡ ካለመፈተሽ የሚመጣ ጥያቄ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሙት ማስነሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ማርታ የሞተውን ወንድሟን አልአዛርን ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለምኖ ከሞት እንደሚያስነሳላት ጠንቅቃ ታውቅ ነበር፤ ለዚህ ነው “አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር” ያለችው፦
ዮሐንስ 11፥21-25 ማርታም ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ “”አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም”” ነበር፤ አሁንም “”ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ”” አለችው። 

ኢየሱስ አብን ለምኖ ሰዎች እግዚአብሔር እንዳላከው እንዲያምኑበት የተሰጠው ስራ እንደሆነ መናገሩ ነው፦
ዮሐንስ 11፥41-44 ድንጋዩንም አነሡት። ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። “አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ” አወቅሁ፤ ነገር ግን “አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ” በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ። ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ። አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ። የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም። ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው።

ብሉይ ኪዳን ላይ የነበሩት ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች በፀሎት ህይወት በመስጠት አስነስተዋል፦
1. ኤልያስ
1ኛ ነገሥት 17፥21-23 በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ ተዘረጋበት፥ ወደ እግዚአብሔርም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም “የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች”፥ እርሱም ዳነ፤ ኤልያስም ብላቴናውን ይዞ ከሰገነቱ ወደ ቤት አወረደው፥ ኤልያስም። እነሆ፥ “ልጅሽ በሕይወት ይኖራል” ብሎ ለእናቱ ሰጣት።
2. ኤልሳዕ
1ኛ ነገሥት 4፥32-34 ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ “ሕፃኑ ሞቶ” በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። ገብቶም በሩን ከሁለቱ በኋላ ዘጋ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ “አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ”፤ ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ።

የዕብራውያን ጸሐፊ ይህንን ጉዳይ በማስታወስ በኤልያስ እና በኤልሳዕ ዘመን የነበሩት ሁለት ሴቶሽ ሙታን ልጆቻቸውን በትንሳኤ ተቀበሉ ይለናል፦
11፥35 ሴቶች ሙታናቸውን “በትንሣኤ” ተቀበሉ፤

ሰዎች ይደነቁ ዘንድ አብ ለኢየሱስ ሙታንን እንዲያነሣ ሕይወትም እንዲሰጥ አድርጎታል፤ ይህንን የአብን ስራ ኢየሱስ በአብ ስም ይሰራል፦
ዮሐንስ 10፥25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። ነገርኋችሁ አታምኑምም “”እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል””፤”
ዮሐንስ 10:37 እኔ “”የአባቴን ሥራ”” ባላደርግ አትመኑኝ፤”
በኢየሱስ ይህንን ስራ የሚሰራው አብ ነው፤ ኢየሱስ የሰራውን ስራ በእርሱ መልእክተኝነት ያመኑ ሰዎችም ኢየሱስ ከሰራው ስራ ሊሰሩ እንደሚችሉ እራሱ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 14፥10-13 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን “”በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል””፤ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ “ስለ ራሱ ስለ ሥራው”” እመኑኝ፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን “”እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል””፥

በዚህ መሰረት ኢየሱስ ነብይነት ያመኑት ሃዋርያትም ኢየሱስ የሰራውን ስራ ማለትም ሰው ከሞት ማስነሳት ሰርተውቷል፦
ማቴዎስ 10፥8 “ድውዮችን ፈውሱ፤ “”ሙታንን አስነሡ””፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።
የሐዋርያት ሥራ 9:40 ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ “”ሬሳውም”” ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ “”ተነሺ”” አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።”

እንደ ባይብሉ ኢየሱስ ሙት አስነስቶ ህይወት መስጠት አብ ለኢየሱስ መልክተኛነት በስጦታ የሰጠው ስራ እንደሆነ ኢየሱስ ፍትንውና ቁልጭ ባለ መልኩ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 17:4 እኔ ላደርገው “የሰጠኸኝን ሥራ” ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
ዮሐንስ 5:36 እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክር የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ ልፈጽመው “የሰጠኝ ሥራ”፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ “”አብ እንደ “”ላከኝ” ስለ እኔ ይመሰክራልና””።
ዮሐንስ 11፥42 ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን “”አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ”” ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።

ኢየሱስ ሙት በማስነሳት ህይወት የሰጠው በላከው ፈቃድ እንጂ በራሱ ፈቃድ አይደለም፤ ከራሱማ ምንም ማድረግ አይችልም፤ የኢየሱስ ተአምራት፣ ድንቆች እና ምልክቶችም እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ያደረገው ነው፤ በተጨማሪም የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው መሆኑን አበክሮና አዘክሮ የሚያሳይ ነው፦
ዮሐንስ 5:30 “”እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም””፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ “”የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና”:።
የሐዋርያት ሥራ 2:22 “”የእስራኤል ሰዎች”” ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ “”በእርሱ”” በኩል ባደረገው “”ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም” ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ “”ሰው”” ነበረ፤”

በተለይ “ራሴ”my self” የሚለው ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ስጋን፣ አጥንት አሊያም ደምን ሳይሆን የሚያመለክተው ሙሉ ማንነትን ነው፤ ይህ ከሆነ ኢየሱስ በሙሉ ማንነቱ አብ ከሰጠው ስልጣን ውጪ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም።

የዓለማቱ ጌታ አላህ ከፊሉን መልእክተኛ በከፊሉ ላይ በደረጃ አብልጧል፤ ለድንግል ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ግልፅ የሆነ ታምራት ሰጥቶታል፦
2፥87 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክትኞችን አስከታተልን፤ የመርየምን ልጅ ዒሳንም “ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው”፡፡
2፥253 እነዚህን መልክተኞች “”ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን””፤ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፤ “”ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ””፤ የመርየምን ልጅ ዒሳንም “”ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው””፡፡

አምላካችን አላህ ለነቢዩ ኢየሱስ ነብይነት ከሰጠው ታምራት አንዱ የሆነው ሙታንን በአላህ ፈቃድ ከሞት ማስነሳት እንደሆነ ኢየሱስ በተልእኮው ተናግሯል፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ “”በተዓምር”” ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ “”በአላህም ፈቃድ”” ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ “”ሙታንንም አስነሳለሁ””፡፡

አላህም ለኢየሱስ ካደረገው ከውለታ አንዱ በአላህ ፈቃድ ሙታንን ከመቃብር ማስነሳት እንደሆነ ይናገራል፦
5፥110 አላህ በሚል ጊዜ አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ የዋልኩላችሁን ጸጋዬን አስታውስ፡፡ በሕፃንነትና በከፈኒሳነት ሰዎችን የምትናገር ስትኾን በቅዱስ መንፈስ ባበረታሁህ ጊዜ፤ ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ባስተማርኩህ ጊዜ፣ ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ብጤ በፈቃዴ በምትሠራና

በውስጧ በምትነፋ በፈቃዴም ወፍ በምትኾን ጊዜ፣ ዕውርም ኾኖ የተወለደንና ለምጻምንም በፈቃዴ በምታሽር ጊዜ፣ “”ሙታንንም በፈቃዴ ከመቃብራቸው በምታወጣ ጊዜ”፣ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ፡፡

“”በአላህም ፈቃድ”” ..””ሙታንንም አስነሳለሁ”” እና “”ሙታንንም በፈቃዴ ከመቃብራቸው በምታወጣ ጊዜ” የሚሉት ቃላት ይሰመርበት፤ ስለዚህ ኢየሱስ በአላህ ፈቃድ ሙት ማስነሳቱ ለእርሱ መልእክተኛነት ማስረጃ መሆኑን እንረዳለን እንጂ ጭራሽ ለአምላክነት ሸርጥ ነው ብሎ እንደ ደሊል መረጃ ማቅረብ እጅግ በጣም ሲበዛ ቂልነት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አልገደሉትም

ገቢር አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥55 አላህም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ "ዒሳ ሆይ! እኔ *"ወሳጂህ"* ወደ እኔም *"አንሺህ"* ነኝ"፡፡ إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ

ነጥብ ሦስት
"አርጓል"
አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፤ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፦
39፥42 አላህ ነፍሶችን *በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል*፡፡ ያችንም ያልሞተችውን *በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል”*፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

"በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል" ማለት አላህ መልአከ ሞትን ልኮ ነፍስን በሞታቸው ጊዜ “ይወስዳታል፤ አሁንም “ይወስዳችኃል” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፦
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
7፥37 የሞት መልክተኞቻችንም *”የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ”* «ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሃዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوٓا۟ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ ۖ قَالُوا۟ ضَلُّوا۟ عَنَّا وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِين

"ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል" በእንቅልፍ ጊዜ ማስተኛትን ያመለክታል፤ “ይወስዳል” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፈ” يَتَوَفَّى ሲሆን በሌላ አንቀፅ ላይ “የሚያስተኛችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፦
6፥60 እርሱም ያ በሌሊት *”የሚያስተኛችሁ”* በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ *”የሚቀሰቅሳችሁ”* ነው፡፡ ከዚያም *”መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው”*፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰٓ أَجَلٌۭ مُّسَمًّۭى ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
ስለዚህ “መውሰድ” እና “ማሞት” ይለያያል፤ "ያሞታችኃል" ለሚለው ቃል የተጠቀመበት "ዩሚቱኩም" يُمِيتُكُمْ ነው፦
22፥66 *እርሱም ያ ሕያው ያደረጋችሁ ነው፡፡ ከዚያም ያሞታችኋል፡፡ ከዚያም ሕያው ያደርጋችኋል*፡፡ ሰው በእርግጥ በጣም ከሓዲ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَحْيَاكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ۗ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ

ተፍሲሩል ኢብኑ ከሲር እና ተፍሲሩል አት-ታባሪ፦ "አላህ ዒሳን እንዲያንቀላፋ አድርጎታል" ብለው አስቀምጠውታል፤ "እንዲያንቀላፋ አድርጎታል" ለሚለው ቃል የተጠቀሙበት "ሙተወፊይሃ" مُتَوَفِّيهَا ሲሆን ዒሳ ባንቀላፋበት ጊዜ አላህ ወደ ራሱ ወሰደው፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ማለትን እንጂ ለነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ በነርሱ ላይ *"ምስክር"* ነበርኩ፡፡ *"በወሰድከኝም"* ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ *"ተጠባባቂ"* ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ شَهِيدٌ
3፥55 አላህም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ "ዒሳ ሆይ! እኔ *"ወሳጂህ"* ወደ እኔም *"አንሺህ"* ነኝ"፡፡ إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ

"በወሰድከኝ" ለሚለው ቃል "ተወፈይተኒ" تَوَفَّيْتَنِى ሲሆን "ወሳጂህ" ለሚለው ደግሞ "ሙተፈፈይከ" مُتَوَفِّيكَ ነው፤ አይሁዳውያን በእርግጥም አልገደሉትም፤ ሊገድሉት ሲሉ አላህ ወሰደው፤ "ራፊዑከ" َرَافِعُكَ ማለትም "አንሺህ" ማለት ሲሆን ወደ ላይ ማረጉን ያሳያል፦
4፥158 ይልቁኑስ፣ *አላህ ዒሳን ወደ እርሱ አነሳው*፤ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው። بَل رَّفَعَهُ ٱللَّهُ إِلَيْهِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًۭا

"ረፈዐሁ" رَفَعَهُ ማለትም "አነሳው" የሚለው ቃል "ረፈዐ" رَفَعَ ማለትም "አነሳ" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ይህም ቃል አላህ ሰለ ኢድሪስ እርገት በሚናገርበት አንቀፅ ላይ በተመሳሳይ "ረፈዕናሁ" رَفَعْنَاهُ ማለትም "አነሳነዉ" ይላል፤ ስለዚህ በቁርአን ያረገው ዒሳ ብቻ ሳይሆን ሄኖክንም እንደሆነም ጭምር ነው፦
19፥56 በመጽሐፉ *ኢድሪስንም አዉሳ* እርሱ እዉነተኛ ነቢይ ነበርና፣ وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ إِدْرِيسَ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ صِدِّيقًۭا نَّبِيًّۭا
19፥56 *ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነዉ*። وَرَفَعْنَٰهُ مَكَانًا عَلِيًّا

ያረገ አካል ደግሞ መሞቱ አይቀርምና ዒሳ ወደ ፊት መጥቶ ይሞታል፤ ኢንሻላህ በመጨረሻው ክፍል ይህንን ነጥብ እንዳስሳለን…………

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አልገደሉትም

ገቢር አምስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥61 *እርሱም ዒሳ ለሰዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው*፡፡ «በእርሷም አትጠራጠሩ፡፡ ተከተሉኝም፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው፡፡ وَإِنَّهُ لَعِلْمٌ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمْتَرُنَّ بِهَا وَاتَّبِعُونِ ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ነጥብ አራት
"ይሞታል"
አምላካችን አላህ ዒሳ አልተገደሉትም ብቻ ሳይሆን ከመነሻው አልሰቀሉትም ነው ያለን፤ መገደል በስቅላት ብቻ ሳይሆን በመውገርም ሊሆን ይችላል፤ መሞት ተገድሎም ብቻ ሳይሆን ታሞም ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ዒሳ አልተገደለም ማለት ወደፊት መጥቶ አይሞትም ማለትን አይዝም፤ "ቀትል" قَتْل ማለት "መገደል" ማለት ሲሆን "መውት" مَوْت ደግሞ "ሞት" ነው፤ በሁለቱ መካከል ልዩነቱን ለማሳየት "አው" أَوْ ማለትም "ወይም" የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፦
3፥144 ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፤ ታድያ *”ቢሞት ወይም ቢገደል”* ወደኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ۚ أَفَإِن مَّاتَ أَوْ قُتِلَ انقَلَبْتُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ ۚ وَمَن يَنقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَن يَضُرَّ اللَّهَ شَيْئًا ۗ وَسَيَجْزِي اللَّهُ الشَّاكِرِينَ
22፥58 እነዚያም በአላህ ሃይማኖት የተሰደዱ፣ *ከዚያም የተገደሉ ወይም የሞቱ* አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይስጣቸዋል፣ አላህም እርሱ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው። وَالَّذِينَ هَاجَرُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ ثُمَّ قُتِلُوا أَوْ مَاتُوا لَيَرْزُقَنَّهُمُ اللَّهُ رِزْقًا حَسَنًا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَهُوَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ
33፥16 *"ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም*፡፡ ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም" በላቸው፡፡ قُل لَّن يَنفَعَكُمُ الْفِرَارُ إِن فَرَرْتُم مِّنَ الْمَوْتِ أَوِ الْقَتْلِ وَإِذًا لَّا تُمَتَّعُونَ إِلَّا قَلِيلًا

የማይሞት አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ የሚያሞትም በትንሳኤ ቀን ሕያው የሚያደርግ እርሱ ነው፦
25፥58 በዚያም *በማይሞተው ሕያው አምላክ* ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا
3፥185 *ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት*፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
22፥66 *እርሱም ያ ሕያው ያደረጋችሁ ነው፡፡ ከዚያም ያሞታችኋል፡፡ ከዚያም ሕያው ያደርጋችኋል*፡፡ ሰው በእርግጥ በጣም ከሓዲ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَحْيَاكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ۗ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ

ዒሳ ለትንሳኤ ቀን ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው፤ ዒሳ የትንሳኤ ቀን ሲቃረብ በምድር ላይ 40 ዓመት ይቆያል፤ ከዚያም ይሞታል፦
43፥61 *እርሱም ዒሳ ለሰዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው*፡፡ «በእርሷም አትጠራጠሩ፡፡ ተከተሉኝም፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው፡፡ وَإِنَّهُ لَعِلْمٌ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمْتَرُنَّ بِهَا وَاتَّبِعُونِ ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ቁጥር 34
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ" እንደተረከው፤ ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ "በእኔ እና በዒሳ መካከል ነቢይ የለም። እርሱ ዒሳ ወደፊት ይወርዳል፤ ባያችሁት ጊዜ ታውቁታላችሁ፤ መካከለኛ ቁመት፣ ቀያማ ጸጉር፣ ሁለት ቀለል ያሉ ቢጫ ልብሶችን ይለብሳል፤ እይታል ልክ ነጠብጣብ ከግንባሩ እንደሚወርድ ግን እንደማይረጥብ ነው፤ በኢስላም መንገድ ህዝቦችን ይታገላል፤ መስቀልንም ይሰባብራል፣ አሳማዎችንም ይገድላል፣ ግብርንም ይተዋል፤ አላህም ከኢስላም በስተቀር ሁለንም ሃይማኖቶች ያጠፋል፤ ዒሳ መሲሑል ደጃልን ያስወግዳል፤ *በምድር ላይ 40 ዓመት ይቆያል፤ ከዚያም ይሞታል*፤ ሙስሊሞች ይሰግዱበታል። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لَيْسَ بَيْنِي وَبَيْنَهُ نَبِيٌّ - يَعْنِي عِيسَى - وَإِنَّهُ نَازِلٌ فَإِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَاعْرِفُوهُ رَجُلٌ مَرْبُوعٌ إِلَى الْحُمْرَةِ وَالْبَيَاضِ بَيْنَ مُمَصَّرَتَيْنِ كَأَنَّ رَأْسَهُ يَقْطُرُ وَإِنْ لَمْ يُصِبْهُ بَلَلٌ فَيُقَاتِلُ النَّاسَ عَلَى الإِسْلاَمِ فَيَدُقُّ الصَّلِيبَ وَيَقْتُلُ الْخِنْزِيرَ وَيَضَعُ الْجِزْيَةَ وَيُهْلِكُ اللَّهُ فِي زَمَانِهِ الْمِلَلَ كُلَّهَا إِلاَّ الإِسْلاَمَ وَيُهْلِكُ الْمَسِيحَ الدَّجَّالَ فَيَمْكُثُ فِي الأَرْضِ أَرْبَعِينَ سَنَةً ثُمَّ يُتَوَفَّى فَيُصَلِّي عَلَيْهِ الْمُسْلِمُونَ ‏"‏ ‏.‏
መስቀል እንጨት፣ ብር፣ ወርቅ፣ ብረት ነው፤ መስቀሉን ለስግደት ስለሚጠቀሙበት ያኔ መስቀሎችን ይሰባብራቸዋል። ለጤና ጠንቅ የሆኑትን አሳማዎች የምዕራባውያን ምግብ ነው፤ አሳማዎችን እንዳይበሉ በማድረግ ያጠፋል። አህለ ዚማህ ማለት በሙስሊም ሸሪዓ ሕገ-መንግሥት የሚኖሩ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች የሚከፍሉትን ጂዝየ ማለትም ግብር ያስቀራል፤ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ሙስሊም ስለሚሆን፤ ከመጽሐፉ ሰዎች አይሁዳውያን ሆኑ ክርስቲያኖች ወለም ዘለም ውልፍጥ ዝልፍጥ ሳይሉ ዒሳ ከመሞቱ በፊት በእርሱ ነብይነት ብቻ የሚያምን እንጅ አንድም አይገኝም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 118
ከአቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ" እንደተላለፈው፤ የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ነፍሴ በእጁ በኾነችው ይሁንብኝ! በእናንተ ላይ የመርየም ልጅ እንደ ፍትሐዊ ዳኛ ኾኖ ሊወርድ ይቃረባል፤ መስቀልንም ይሰባብራል፣ አሳማዎችንም ይገድላል፣ ግብርንም ይተዋል፤ ገንዘብንም የሚቀበለው ሰው እስኪጠፋ ድረስ ይበራከታል፤ ለአላህ የሚደረግ አንድ ሱጁድ ዱንያ እና በውስጧ ከያዘችው ኹሉ የበለጠና የተሻለ ይኾናል"
ከዚያም አቡ ሁረይራህ፦ "ከፈለጋችሁ ይህን አንቀጽ አንብቡ" አለ፦
4፥159 *"ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ በዒሳ በእርግጥ የሚያምን እንጅ አንድም የለም፤ በትንሣኤም ቀን በእነርሱ ላይ መስካሪ ይኾናል"* سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَيُوشِكَنَّ أَنْ يَنْزِلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ حَكَمًا عَدْلاً، فَيَكْسِرَ الصَّلِيبَ، وَيَقْتُلَ الْخِنْزِيرَ، وَيَضَعَ الْجِزْيَةَ، وَيَفِيضَ الْمَالُ حَتَّى لاَ يَقْبَلَهُ أَحَدٌ، حَتَّى تَكُونَ السَّجْدَةُ الْوَاحِدَةُ خَيْرًا مِنَ الدُّنْيَا وَمَا فِيهَا ‏"‌‏.‏ ثُمَّ يَقُولُ أَبُو هُرَيْرَةَ وَاقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ ‏{‏وَإِنْ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ إِلاَّ لَيُؤْمِنَنَّ بِهِ قَبْلَ مَوْتِهِ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا‏}‌‏.‏

በዚያ በተወለደበት ቀን ሰላም በእርሱ እንደሆነ ሁሉ በሚሞትበት በዚህ ጊዜ ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ ሕያው ኾኖ በሚቀሰቀስበትም በትንሳኤ ቀን ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ በዚያ ቀን ከመምጣቱ በፊት በነበሩት ደረጃውን ዝቅ ባደረኩት አይሁዳውያን እና ደረጃውን ከፍ ባደጉት ክርስቲያኖች ላይ መስካሪ ይኾናል፦
19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ *በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን*፡፡» وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا
4፥159 *"ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ በዒሳ በእርግጥ የሚያምን እንጅ አንድም የለም፤ በትንሣኤም ቀን በእነርሱ ላይ መስካሪ ይኾናል"*። وَإِن مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا لَيُؤْمِنَنَّ بِهِۦ قَبْلَ مَوْتِهِۦ ۖ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا

በእርግጥም አምላካችን አላህ ሁሉን ዐዋቂ ስለሆነ የነገረን ነገር ሁሉ እውነት ነው፤ ቁርኣንም የእርሱ ንግግር ነው፤ የብዙዎችን ልብ ማርኮ ያሸነፈ አሸናፊ መጽሐፍ ነው፤ እነዚያ አሸናፊ መጽሐፍ ሲኾን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት ጠፊዎች ናቸው፦
41፥41 እነዚያ በቁርኣን እርሱ *አሸናፊ መጽሐፍ ሲኾን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት ጠፊዎች ናቸው*፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِٱلذِّكْرِ لَمَّا جَآءَهُمْ ۖ وَإِنَّهُۥ لَكِتَٰبٌ عَزِيزٌۭ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አላህ አይረሳም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

አምላካችን አላህ ሁሉን ዐዋቂ ነው፤ ወደ ኃላው የተደረጉት ነገሮች ሁሉ አይረሳም፦
20፥52 ሙሳም፦ «ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ የተመዘገበ ነው፡፡ *ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም*» አለው፡፡ قَالَ عِلْمُهَا عِندَ رَبِّى فِى كِتَٰبٍۢ ۖ لَّا يَضِلُّ رَبِّى وَلَا يَنسَى
19፥64 ጂብሪል አለ፦ «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ *ጌታህም ረሺ አይደለም*፡፡ وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّۭا

አምላካችን አላህ ሰዎችን እንደሚገናኝ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ወሕይን ያወርዳል፤ በዚህ ወሕይ የመገናኛውን ቀን* ያጠነቅቅ ዘንድ ነብይ ይልካል፦
40፥15 እርሱ ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፡፡ *የመገናኛውን ቀን* ያጠነቅቅ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ መንፈስን ያወርዳል፡፡ رَفِيعُ ٱلدَّرَجَٰتِ ذُو ٱلْعَرْشِ يُلْقِى ٱلرُّوحَ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ لِيُنذِرَ يَوْمَ ٱلتَّلَاقِ

ይህንን ቀን መገናኘት ሆን ብሎ የረሳ ማለትም የተወ ልክ እርሱ እንደረሳው አላህ በዚያን ቀን ለጀነት አያስታውሰውም ይረሳዋል፦
45፥34 «ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን *እንደ ረሳችሁ* ዛሬ *እንረሳችኋለን*፡፡ መኖሪያችሁም እሳት ናት፡፡ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም» ይባላል፡፡ وَقِيلَ الْيَوْمَ نَنْسَاكُمْ كَمَا نَسِيتُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا وَمَأْوَاكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُمْ مِنْ نَاصِرِينَ
7፥51 «እነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙ የቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸው ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን *እንደ እረሱ* በተአምራታችንም ይክዱ እንደነበሩ ዛሬ *እንረሳቸዋልን*፡፡ الَّذِينَ اتَّخَذُوا دِينَهُمْ لَهْوًا وَلَعِبًا وَغَرَّتْهُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۚ فَالْيَوْمَ نَنْسَاهُمْ كَمَا نَسُوا لِقَاءَ يَوْمِهِمْ هَٰذَا وَمَا كَانُوا بِآيَاتِنَا يَجْحَدُونَ

መቼም አንድ አስተባባይ የመገናኛውን ቀን ተነግሮት ረሳ ማለት ተወ ማለት እንጂ በዐቅሉ ዘነጋ ማለት አይደለም። ምክንያቱም ዐቅልን ስቶ መዘንጋት አያስጠይቅምና፤ ግን ሆን ብሎ በማስተባበል መተው ያስጠይቃል፤ ከሃዲያን ሆን ብለው የመገናኛውን ቀን እንደረሱት እንደዚሁ አላህም የዚያን ቀን ይረሳቸዋል፤ “ከማ” كَمَا ማለትም “እንደ” የሚል መስተዋድድ ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ ነው።
በተጨማሪ “ነሢይ” نَسِيّ የሚለው ቃል “ተሪክ” تَارِك ማለትም “መተው” በሚል ቃል ይመጣል፤ ኢማም ቁርጡቢ ሱረቱል አዕራፍ 7፥51 ላይ ያለውን አንቀጽ ሲፈስሩ እንዲህ ይላሉ፦ “ዛሬ እንረሳቸዋልን” ማለት “በእሳት እንተዋቸዋለን” ማለት ሲሆን “ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን እንደ እንደረሱት” ማለት ደግሞ “ይህንን ስራቸውን እንደ እንደተዉትና እንዳስተባበሉት” ማለት ነው። فَالْيَوْمَ نَنْسَاهُمْ أي نتركهم في النار كَمَا نَسُوا لِقَاءَ يَوْمِهِمْ هَذَا أي تركوا العمل به وكذبوا به
በጌታውም አንቀጾች ከተገሠጸና ከእርሷ ከዞረ እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር “የተወውን” ሰው “ረሳ” ይባላል፤ ያንን አስተባባይ አላህ በዚያ በመገናኛው ቀን “ይተወዋል”፦
18፥57 በጌታውም አንቀጾች ከተገሠጸና ከእርሷ ከዞረ እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር *ከረሳ ሰው*፣ ይበልጥ በዳይ ማነው? وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ فَأَعْرَضَ عَنْهَا وَنَسِىَ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ
32፥14 «ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን *በመርሳታችሁ* ምክንያት ቅጣትን ቅመሱ! እኛ *ተውናችሁ*፡፡ ትሠሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ” ይባላሉ ፡፡ فَذُوقُوا بِمَا نَسِيتُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا إِنَّا نَسِينَاكُمْ ۖ وَذُوقُوا عَذَابَ الْخُلْدِ بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ
20፥126 ነገሩ እንደዚሁ ነው፡፡ «ታምራታችን መጣችልህ፡፡ *ተውካትም*፡፡ እንደዚሁም ዛሬ *ትተዋለህ*» ይለዋል፡፡ قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتْكَ ءَايَٰتُنَا فَنَسِيتَهَا ۖ وَكَذَٰلِكَ ٱلْيَوْمَ تُنسَىٰ
19፥67 መናፍቃንና መናፍቃት ከፊሎቻቸው ከከፊሉ ናቸው፡፡ በመጥፎ ነገር ያዛሉ ከደግም ነገር ይከለክላሉ፡፡ እጆቻቸውንም ከልግስና ይሰበስባሉ፡፡ አላህን *እረሱ*፤ ስለዚህ እርሱ *ተዋቸው*፡፡ መናፍቃን አመጸኞቹ እነሱ ናቸው፡፡ ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتُ بَعْضُهُم مِّنۢ بَعْضٍۢ ۚ يَأْمُرُونَ بِٱلْمُنكَرِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ ٱلْمَعْرُوفِ وَيَقْبِضُونَ أَيْدِيَهُمْ ۚ نَسُوا۟ ٱللَّهَ فَنَسِيَهُمْ ۗ إِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ

“እንረሳችኋለን” የሚለው ቃል *ነሢናኩም” نَسِينَاكُمْ ማለትም “ተውናችሁ”፣ “ቱንሣ” تُنْسَىٰ ማለትም “ትተዋለህ”፣ “ነሢተሃ” نَسِيتَهَا ማለትም “ተውካት” በሚል ተለዋዋጭ ቃል እንደመጣ አንባቢ ልብ ይለዋል። ከምንም በላይ አላህን መርሳት ሆን ተብሎ አመጽ ነው፤ አላህ ማስታወስ ግን አላህም በመገናኛውን ቀን ያስታውሰዋል፦
59፥19 እንደነዚያም *አላህን እንደረሱት እና እራሳቸውን እንዳስረሳቸው* አትኹኑ፡፡ እነዚያ እነርሱ *አመጸኞቹ* ናቸው፡፡ وَلَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ نَسُوا۟ ٱللَّهَ فَأَنسَىٰهُمْ أَنفُسَهُمْ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
2:44 እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን? *እራሳችሁንም ትረሳላችሁን?* የሥራችሁን መጥፎነት አታውቁምን? أَتَأْمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ ٱلْكِتَٰبَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
2፥152 *አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና* ለኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡ فَٱذْكُرُونِىٓ أَذْكُرْكُمْ وَٱشْكُرُوا۟ لِى وَلَا تَكْفُرُونِ
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 55, ሐዲስ 22
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አላህ እንዲህ ይላል አሉ፦ “እኔን እንደረሳኸኝ እረሳካለው” فَيَقُولُ أَفَظَنَنْتَ أَنَّكَ مُلاَقِيَّ فَيَقُولُ لاَ ‏.‏ فَيَقُولُ فَإِنِّي أَنْسَاكَ كَمَا نَسِيتَنِي

ከእነዚህ አናቅጽ የምንረዳው አላህ ረሳቸው ማለት እነርሱ ችላ እንዳሉት ችላ አላቸው ማለትን ያስገነዝባል፦
19፥72 ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ አመጸኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ *እንተዋቸዋለን*፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

መደምደሚያ
እኛስ የሰዋስው፣ የቋንቋ፣ የዐውድ ሙግት አቅርበናል። በአማርኛችንም ምህዋር፣ አውታርና ምህዳርም ከሄድን አንድ ጊዜ ሚስት ለሽማግሌዎች ስለ ባሏ አቤቱታ ስታቀርብ፦ “ባሌ እረስቶኛል አለች፤ ከሽምጋዮቹ አንዱ ለባሏ ለምን እረሳሃት ስሟ ማን ነው? ብሎ አለው፤ ባልም፦ “እከሌ” ብሎ መለሰ፤ ሚስትም፦ “እረስቶኛል ስል ስሜን ዘንግቶታል ማለቴ ሳይሆን ትቶኛል ወይም ችላ ብሎኛል ማለቴ ነው” ብላ መለሰች አሉ፤ ይህ መርሳት ያወቀውን ነገር መዘንጋት”subjective ignorance” ሳይሆን እያወቀ ችላ ማለትን”Objective ignorance” ያመለክታል። አሁን ነው ጉድ የሚፈላው፤ መቼም አላህ ያለፈውን ክስተት አይረሳም፤ በተጨማሪ ወደ ፊት በአንቀጾቹ ያስተባበሉትን ሰዎች የመገናኛው ቀን ይተዋቸዋል። ሚሽነሪዎች፦ አላህ “ይረሳቸዋል” ማለት ግን “ይዘነጋቸዋል” ማለት ነው ካላችሁ የማትወጡበት እረመጥ ውስጥ ትገባላችሁ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንደሚረሳ እራሱም ሆነ ነብያቱ ስለሚናገሩ፤ “ሸካህ” שָׁכַח ማለት በዕብራይስጥ “መርሳት” ወይም “መዘንጋት” ማለት ሲሆን ይህ ቃል ለእግዚአብሔር መርሳት አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ሆሴዕ 4:6 ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ *ረስተሃልና* וַתִּשְׁכַּח֙ እኔ ደግሞ ልጆችህን *እረሳለሁ* אֶשְׁכַּ֥ח ።
ኤርምያስ 23:39 የእግዚአብሔር ሸክም ብላችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ “ፈጽሜ *እረሳችኋለሁ* וְנָטַשְׁתִּ֣י እናንተንም ለእናንተና ለአባቶቻችሁም የሰጠኋትን ከተማ ከፊቴ እጥላለሁ።
ሰቆቃው ኤርምያስ 5:20 ስለ ምን ለዘላለም *ትረሳናለህ?* תִּשְׁכָּחֵ֔נוּ ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
መዝሙር 13:1 አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ *ትረሳኛለህ?* תִּשְׁכָּחֵ֣נִי እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?”
መዝሙር 42፥9 እግዚአብሔርን፡— አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ለምን *ረሳኸኝ?* שְׁכַ֫חְתָּ֥נִי ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።
መዝሙር 44:24 ለምንስ ፊትህን ትሰውራለህ? መከራችንንና ችግራችንንስ ለምን *ትረሳለህ?* תִּשְׁכַּ֖ח

የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ ወይም ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት አሉ፤ ትችት እና ሻወር ከራስ ነው የሚጀመረው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም