TIKVAH-ETHIOPIA
ሰኞ ሀምሌ 7/2017 ዓ.ም በትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ሁለት እንስቶች አሲድ ተደፍቶባቸው ጉዳት እንደደረሰባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል። ለጊዜው ስሙ ይፋ ያልተደረገ አንድ ግለሰብ በከተማዋ በሚገኘው አንድ መጠጥ ቤት በሚሰሩ ሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ከባድ የአካል ጉዳት አድርሶባቸዋል። ድርጊቱ በርካቶችን አስደንግጧል። የተፈጠረው ምንድነው ? በማለት ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ…
#Update
በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት አረሜናዊ ድርጊት የፈፀመው ተጠርጣሪ " እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም " ሲሉ የትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።
" አሲድ የተደፋባቸው ወገኖች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ አክለዋል።
አሲድ የተደፋባቸው እንስቶቹ ለተሻለ ህክምና ከእንዳስላሰ - ሽረ ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ሪፈር መባላቸውን ገልጸዋል።
ባለፈው ሀምሌ 7/2017 ዓ/ም እስካሁን ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአንድ መጠጥ ቤት በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ማድረሱ ይታወሳል።
የድርጊቱ ፈፃሚ ግለሰብና ? አስቃቂ ተግባር የተፈፀመባቸው እንስቶች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ለማጣራት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ኣባል ዛሬ ሀምሌ 10/2017 ዓ.ም ወደ ከተማዋ ፓሊስ ስልክ ደውሎ ነበር።
ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የከተማዋ ፓሊስ አመራር " በአካል ወደ ከተማችን ካልመጣችሁ በስቀር በስልክ መረጃ አንሰጥም " በማለት መረጃውን ከልክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማዋ ነዋሪ ከሆኑ ታማኝ ምንጮቹ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የጭካኔ ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የሚታወቅ የከተማዋ ነዋሪ ሆኖ እያለ እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋሉ ሁኔታውን አሳሳቢ አድርጎታል።
" ተጠርጣሪ ወንጀለኛው እስካሁን በከተማዋ ተደብቆ እንደሚገኝ የሚሰሙ ጭምጭምታዎች አሉ " ያሉት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ፤ ፓሊስ የጭካኔ ድርጊቱ የፈፀመው ግለሰብ አድኖ በመያዝ ህግ እንዲያስከብር አደራ ብለዋል።
የከተማዋ ነዋሪ ተጥርጣሪውን ለፓሊስ አሳልፎ በመስጠት ዜግነታዊ ሃላፊነቱ እንዲወጣም ነዋሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የእንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ፓሊስ ለሚድያ የሚፈቀድ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር እየጠየቀ ጉዳዩ ተከታትሎ መዘገቡ እንደሚቀጥል ቃል ይገባል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamliyMekelle
@tikvahethiopia

❤551😢155😭104😡59🙏19🕊15💔14🤔7👏5😱5🥰4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
#አርባምንጭ
ተከሳሾች ያቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ ዉድቅ ተደርጓል።
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት ባካሄደዉ ችሎት የብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ የግድያ ወንጀል የተጠረጠሩት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል ያቀረቡትን የመከላከያ ማስረጃ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ በማድረግ የፍርድ ዉሳኔ ለመስጠት ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ችሎቱን ለመታደም ፍርድ ቤት መጥተዉ የነበረ ቢሆንም የችሎት አደራሽ ከልክ በላይ በመሙላቱ አብዛኛዉ ሰው ከግቢ ዉጪ በመሆን የፍርድ ውሳኔውን በመጠባበቅ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው ተገኝቶ ችሎቱን እየተከታተለ ያለ ሲሆን መረጃዎችን ተከታትሎ የሚያደርስ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch

❤1.02K🙏71😢52🕊47👏32😭27🤔18😱18😡16🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ፍርድ ቤቱ አለልኝ አዘነ በሰዉ እጅ ስለመገደሉ አረጋግጦ ባለቤቱንና የባለቤቱን እህት ባል ጥፋተኛ ብሎ ብይን ሰጥቷል።
በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ ላይ ዛሬ በሁለት ፈረቃዎች የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት እና 2ኛ ተከሳሽ የባለቤቱ እህት ባል መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለዉ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር ' ሃይላንድ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 አመቱን ወጣት አለልኝ አዘነን በመግደል እራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግዲያ ወንጀል መፈፀማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ ጥፋተኛ እንዳላቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጃውን ልኳል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ የፍርድ ድሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት የዐቃቤ ሕግና የተከሳሾችን ጠበቃ የቅጣት አስተያየት ካደመጠ በኋላ ዉሳኔዉን ወደ ሀምሌ 15/2017 ዓ/ም አሸጋግሯል።
ምን የሚሉ የቅጣት አስተያየቶች ተሰጡ ?
የተከሳሾች ጠበቃ (የቅጣት ማቅለያ) ፦
👉 ተከሳሾች የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን
👉 የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸዉንና
👉 1ኛ ተከሳሽ የሟች አለልኝ አዘነ ባለቤት የአስም ታማሚ መሆኗ በቅጣት ማቅለያነት አቅርቧል።
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ (የቅጣት ማክበጃ) ፦
ዐቃቤ ሕግ የወንጀል አወሳሰን መመሪያ ማንዋል 03/2017ዓ/ም እና የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 84 (1) ለ፣ ሐ፣ ሠ በመጥቀስ
➡️ የአገዳደሉ አደገኛነት
➡️ ወንጀል ፈፃሚዎች ለወንጀል ድርጊቱ የመረጡት ሰዓት አሳቻና ሰዎች የማይደርሱበትን ሰዓት መሆኑን
➡️ በዘመድ ላይ የተፈፀመ የጭካኔ ወንጀል መሆኑን በመግለፅ እንዲሁም ሟቹ አለልኝ አዘነ ለብሔራዊ ቡድኑ (ለሀገር) ሲሰጥ የነበረዉን ግልጋሎት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲያከብድ ጠይቋል።
የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ያደመጠዉ ፍርድ ቤት የፍርድ ቅጣት እርከኑን ለመወሰን ለሀምሌ 15/2017 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከስፍራው መረጃውን ልኳል።

❤1.79K😭677💔139🙏67😡62👏32🕊30😱19😢17🤔12🥰8
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ #ለሚመለከታችሁ_አካላት " ይሄ የመብራት ፖል የመኖሪያ ቤት ላይ ወድቆ ጉዳት ሳያደርስ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት " - ነዋሪዎች ከላይ የተያያዘው ቪድዮ አዲስ አበባ፣ እንጦጦ ማርያምን በተለምዶ ' ሀሙስ ገበያ ' እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ከሚኖሩ ነዋሪዎች የተላከ ነው። በቪድዮው ላይ እንደሚታየው የመብራት ፖሉ ቤት ላይ ተንጋዶ ይገኛል። አንድ የአካባቢው ነዋሪና የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ…
#Update
ነዋሪነታቸው እንጦጦ ማርያም በተለምዶ ' ሀሙስ ገበያ ' የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መኖሪያ ቤት ላይ የመብራት ፖል ተንጋዶ መተኛቱን በመጠቆም በክረምቱ ንፋስና ዝናብ ጉዳት ሳይደርስ በፊት የሚመለከታቸው አካላት እንዲያስተካክሉላቸው ትላንት ጠቁመው ነበር።
ጥቆማው የደረሰው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሞያዎቹን በመላክ ጥገና አደርጎ ማስተካከሉን አገልግሎቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።
" ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለሚዲያችሁ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በቀጣይም በአገልግሎታችን ላይ ለሚሰጡን ጥቆማዎችና ቅሬታዎች በወቅቱ ለመፍታት እንሰራለን " ሲል ገልጿል።
ጥቆማውን ያደረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ዛሬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች መጥተው ችግሩን ማስተካከላቸውን ገልጸው ምስጋናን አቅርበዋል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ ከጋርመንት ወደ ጀሞ 1 መሄጃ መንገድ ላይ ' ዘመን ማደያ ' አካባቢ በመኪና የተገጨ እና በክረምቱ ዝናብና ንፋስ ቢወድቅ ጉዳት የሚያደርስ ኮንክሪት ፖል ጥቆማ በደረሰ ቀን እስከ ምሽት 4 ሰዓት በመስራት መቀየሩ ይታወሳል።
#EthiopianElectricUtility
#TikvahEthiopiaFamliyAA

❤1.45K🙏364👏203😭23🥰11🕊10🤔7😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
“ ተራራው እየተደረመሰ ወደ ታች ወደ እሳተ ገሞራው እየገባ ነው፡፡ በፍንዳታው የሚወጣው ሰልፈርዳይ ኦክሳይድም የመተንፈሻ አካል ላይ ክፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ” - ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
የአፋር ክልሉ የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ፍንዳታ እንዳልቆመ፣ እሳተ ገሞራው ሲወጣ መሬቱ እየተደረመሰ ወደ ውስጥ እየገባ ከመሆኑም ባሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑን በቦታው ተገኝቶ የነበረው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጅ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ኖራ ያኒሚኦ ጉዳዩ ያለበትን ሁኔታውን ሲያስረዱን፣ “ትላንት በቦታው ነበርን፤ በኤርታሌ በጣም ከፍተኛ የሆነ አቧራ እየወጣ ነው፡፡ በሁለት ቦታዎች ላይ ደግሞ ትንሽ ጭስና እሳት ታይቷል፡፡ ግን ትንሽ ጭስ ከመውጣት ውጪ ሌላ ነገር የለውም” ብለዋል፡፡
“በፎቶ የተሰራጨው በጣም ከፍተኛ አቧራ ሲወጣበት የነበረው ቦታ ግን ትላንት ራሱ ከቀኑ 11 እስከ ማታ 2 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ አቧራ እየወጣበት ነው የነበረው፡፡ አቧራው ከመውጣቱ በፊት ዝቅተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር፡፡ መሬት መንቀጥቀጡ ከእሳተ ገሞራ ፍናዳታው ጋር የተያያዘ ነው” ሲሉም አስረድተዋል፡፡
አክለው፣ “የሚወጣው አቧራ ደግሞ ሰርፈርዳይ ኦክሳይድ ኮንቴነቱ ከፍተኛ ስለሆነ ከፍተኛ የሰልፈር ሽታ አለው፡፡ መሬቱም እተሰነጠቀ ነው፡፡ አስቸጋሪ ሆነ ሁኔታ ነው ያለው” ብለዋል፡፡
“እየተሰነጠቀ ያለው መሬት ደግሞ የእሳተ ገሞራው ላቫ ወደ መሬት በሚወጣት ወቅት ሶሊድፋይድ ይሆናል፤ ስለዚህ ሶሊድፋይ የሆነውና ላቫና ክቧ ተራራ የሚገናኙት ቦታ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ተራራው እየተደረመሰ ወደ ታች ወደ እሳተ ገሞራው እየገባ ነው” ሲሉም የአደጋውን በአሳሳቢነት አስረድተዋል፡፡
ተመራማሪው፣ “በፍንዳታው የሚወጣው ሰልፈርዳይ ኦክሳይድ የመተንፈሻ አካል ላይ ክፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በዓይንም ሆነ አፍንጫ ሲገባ በጣም ነው የሚያቃጥለው” ብለው፣ በኤርታሌ በጣም በቅርበት የሚኖሩ ነዋሪዎች ባይኖሩም ብናኝ የሚድርሰባቸው ነዋሪዎችም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል፡፡
ርቀት ቦታ ላይ በሚገኙ እንደ አፍዴራ ባሉ አካካቢዎች ብናኙ እየደረሰ መሆኑን ጠቁመው፣ “የሚወጣው አቧራ የመተንፈሻ አካል ላይ ጉዳት ሊያስከትል ስልሚችል ማህበረሰቡ የአፍንጫ ጭምብል ሊጠቀም ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በኤርታሌ ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት አደጋ አጋጥሞ እንደማያውቅ ገልጸው፣ “ አሁን ግን ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ወደ ኤክስክሎሲቭ ኢራፕሽን እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ብዙም ኤርታሌ ላይ የተለመደ አይደለም፡፡ እስከዛሬ ማግማው ወደ ላይ ከመምጣት ውጭ የኤክስክሎሲቭ ምልክት አያሳይም ነበር ” ነው ያሉት፡፡
ፎቶ ለማንሳትና ቪዲዮ ለመቅረጽ ወደ ቦታው የሚሄዱ ሰዎች እንዳሉ ገልጸው፣ እሳተ ገሞራው በሚወጣበት ወቅት ከፍትኛ የሆነ መሬት መንቀጥቀጥ ስላለ፣ ተራራውም እየተናደ ስለሆነ (ትላንት የነበሩበት ቦታ እንደተናደ ጠቁመዋል) በርቀት ካልሆነ በስተቀር ሰዎች ወደ ቦታው ቀርቦ ከመቅረጽ እንዲታቀቡ በአጽንኦት አስጠንቅቀዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiafamilyAA
ፎቶ፦ ፋይል

❤1.49K🙏214😭131🕊71🤔32💔31😱27😢24🥰11😡9👏2
TIKVAH-ETHIOPIA
#EFFORT " ነባሩ ቦርድ ህጋዊ ነው ፤ በትእምት ስም የተካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " የሚል ውሳነ መሰጠቱ ተሰማ። የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታማኝ ምንጮች በላኩት መረጃ ነባሩ የትእምት ኢንቨስትመንት አመራር " ህገ-ወጥ የምክር ጉባኤ አካሂዶ ህገ-ያልተከተሉ አመራሮች መርጦ በተቋሙ ላይ የጀመረው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ይታገድልኝ " ሲል ለክልሉ የፍትህ ቢሮ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት…
#Update
#EFFROT
እነ አዲስአለም ባሌማ (ዶ/ር) ፣ ደብረጽዮን ገ/ማካኤል (ዶ/ር) ጨምሮ 12 ሰዎች እግድ ተጣለባቸው።
በትእምት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ቀደም ሲል በፍትህ ቢሮ " ህጋዊ አይደላችሁም " የተባሉ አካላት ፍርድ ቤትም እንዳገዳቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል መረጃውን ልኳል።
የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት እግድ የጣለው በኣዲስ ኣለም ባሌማ (ዶ/ር) የሚመራውና ባለፈው የካቲት ወር 2017 ዓ.ም ጉባኤ አካሂዶ የትእምት አመራር ለሚለው አካል ነው።
የትግራይ ፍትህ ቢሮ ነባሩ የትእምት አመራር በፅሁፍ ያቀረበለት " በኣዲስ ኣለም ባሌማ (ዶ/ር) የሚመራው አካል ያካሄደው ጉባኤ 'ህገ-ወጥና ቅቡልነት እንደሌለው ይረጋገጥልኝ " የሚል ክስ ከ10 ቀናት ማጣራት በኋላ ተቀባይነት ማግኘቱ መዘገባችን ይታወሳል።
የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም በፃፈው ትእዛዝ በስም የጠቀሳቸው ኣካላት ተለዋጭ ቀጠሮ እስኪሰጥ ድረስ በትእምት ኢንቨስትመንት ስም ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የአግድ ትእዛዝ ጥሎባቸዋል።
ተከሳሾቹ እነማን ናቸው ?
1. ኣረጋዊ ገ/ሚካኤል(ዶ/ር)
2. ጀነራል ክንፈ ዳኘው
3. ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)
4. ኣብራሃም ተኸስተ (ዶ/ር)
5. ወ/ሮ ኪሮስ ሓጎስ
6. አምባሳደር ሃይለኪሮስ ገሰሰ
7. ፃድቕ ኪ/ማርያም (ዶ/ር)
8. አቶ ሰናይ ካሓሰ
9. ኮ/ል ካሕሳይ ተኽሉ
10. ወ/ሮ ሸዊት አዲሱ
11. አቶ አታኽልቲ ገ/ሂወት
12. አምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ (ዶ/ር)

❤874👏114🕊35😡34🙏28🤔24🥰8😱6😢4😭3💔1
TIKVAH-ETHIOPIA
“ አራት አመት ለፍተው ተምረዋል፣ ከተማሩ በኋላ ለፈተና ተቀምጠዋል፣ ውጤታቸውን የማየት ሙሉ መብት አላቸው ” - የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኀበር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ቢቆዩም ሁሉም ተማሪዎች ውጤታቸውን ባለማየታቸው መፍትሄ እንዲሰጣቸው በሰፊው ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኀበርም፣ “የተወሰኑት…
#Update
" በመካከል የ12ኛ ክፍል ፈተና ስንጀምር ወደ አርካይቭ መቀየር ነበረብን ወደ አርካይቭ ስናስገባው ፕላትፎርሙ ተዘጋና ማየት አልቻሉም፤ እኛም ማየት አልቻልንም፤ በቅርብ ይለቀቃል " - ትምህርት ሚኒስቴር
የመውጫ ፈተና ውጤት " ሁሉም ተፈታኞች አላዩም " በሚል እየቀረበ ላለው ቅሬታ ሰሞኑን ምላሽ የጠየቅነው የግል ከፍተኛ ተቋማት ማኀበር ትምህርት ሚኒስቴርንና ክፍያ ያልከፈሉ ተቋማትን ተጠያቂ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ተማሪዎቹ ውጤታቸውን ማየት ያልቻሉት ምን ተፈጥሮ ነው ? ሲል ዛሬ የጠየቀው የትምህርት ሚኒስቴር፣ " ከ12ኛ ክፍል ፈተና በፊት ነው ውጤት የተቀቀው፤ ተቋሙም እንዲያይ ተማሪዎቹም እንዲያዩ አድርገናል " ብሏል።
" ነገር ግን መካከል ላይ የ12 ክፍል ፈተና ስንጀምር ወደ አርካይቭ መቀየር ስለነበረብን ወደ አርካይቭ ስናስገባው ፕላትፎርሙ ተዘጋና ማየት አልቻሉም ሰዎች፤ እኛም ማየት አልቻልንም ለጊዜው። በቅርብ ይለቀቃል፤ እየተነጋገርን ነው " ሲሉ አንድ የተቋሙ አመራር ተናግረዋል።
ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት እንደላኩ አስታውሰው፣ “" አንዳንድ ያላኩላቸውም ክፍያ ላይ የዘገዩ ተቋማት ስለነበሩ እነርሱም አላዩም እንለቀዋለን። ግን 'አላየንም' የሚለው የሚያስኬድ አይደለም ልጆችም ተቋማትም በጊዜ ገብተው ማየት ይችሉ ነበር፤ ያን ማድረግ ስላልቻሉ ነው አሁንም ይለቀቃል " ብለዋል።
ብዙዎች ተቋማት ክፍያ እያጠናቀቁ መሆኑን አስረድተው፣ " በተቀመጠላቸው ጊዜ የኤግዚት ተፈታኝ ስለማይከፍሉ ነው ብዙዎቹ የሚዘገይባቸው። ሁለት፣ ሦስት ተቋማት ናቸው አሁን የቀሩት። ከዛ ውጪ ያሉት ግን ፕላትፎርሙ አክቲቭ ሲሆን ማየት ይችላሉ፤ ያኔም ያላዩት ስለዘገዩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት አይደለም እንዴ ክፍያ መጠናቀቅ የነበረበት ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄም በምላሻቸው፣ ቅድሚያ መክፈል እንደነበረባቸው አምነው፣ " ግን አይከፍሉም። እኛ ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሳይሆን ከዛ በፊት ነው ደብዳቤ የሰጠናቸው፤ ግን ብዙ ከፍተኛ ተቋማት ፈተና ሳይቀመጡ ተማሪዎቹ ከፍለው እንዲጨርሱ ብናሳስባቸውም አያደርጉም " ነው ያሉት።
" እኛም ደግሞ ተማሪዎቹ ለፈተና ተዘጋጅተው ተቋሙ አልከፈለምና አትፈተኑም ማለት አልፈለግንም። ከተፈተኑ በኋላ ተቋማቱ ቢያንስ ከፍለው ውጤቱ እንዲያዩ ነው የምናደርገው፤ ተማሪዎቹም ማገድ አስቸጋሪ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
እንዲህ አይነት ኬዝ ያለበት ውጤትስ ታዲያ መቼ ይለቀቃል ? ለሚለው ጥያቄም '' የመንግስት የግል የሚባል ነገር የለም። አሁን ፕላትፎርሙ አይሰራም " ብለው፣ " ቢበዛ ነገ የሁሉም ይለቀቃል፤ ተነጋግረናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvqhEthiopiaFamilyAA

❤420😡33🤔18🕊11👏5😢4🙏4🥰3💔1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" እስካሁን አስክሬኖቹን ማግኘት አልተቻለም፤ ፍለጋው እንደቀጠለ ነዉ " - የደቡብ አሪ ወረዳ አስተዳደር
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ከመር ቀበሌ በደረሰዉ የመሬት ናዳ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ሰዎች ከመሬት በታች ናዳዉ ተጭኖባቸዉ ለማዉጣት ዛሬ
ቀኑን ሙሉ ቢሞከርም እስካሁን አለመቻሉን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛዉ ሃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" የአስክሬን ፍለጋዉ ሂደት በሰው ሃይል መሆኑ ፍለጋዉን ከባድ አድርጎታል " ያሉት ዋና አስተዳዳሪው " ከክልሉ መንግስትና ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የማሽን ድጋፍ ብንጠይቅም እስካሁን አልደረሰልንም " ሲሉ አስረድተዋል።
የመሬት ናዳዉ ከ3 ሄክታር በላይ በሆነ ቦታ መከሰቱን አንስተው በናዳዉ እስካሁን የተለዩ አራት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መዋጣቸዉን ገልፀዋል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸዉንና በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ አደጋ ዉስጥ ናቸዉ ብለዋል።
" የፍለጋዉ ሂደት እንደ ጎፋዉ አከባቢ ሌላ ናዳ እንዳያስከትል ሕብረተሰቡን ብናስጠነቅቅም ከአቅማችን በላይ ሆኗል " ያሉት አስተዳዳሪዉ " እስከ ምሽት ድረስ የአስክሬን ፍለጋዉ ሂደት በሰዉ ሃይል እየተካሄደ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስራትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋምኣ ደዉሎ የነበረ ሲሆን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መረጃ ማግኘት ሳይቻል ቀርቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamliyHawassa

😭461❤371💔40😢30🙏19🕊11👏6😱5🥰4
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፍርድ ቤቱ አለልኝ አዘነ በሰዉ እጅ ስለመገደሉ አረጋግጦ ባለቤቱንና የባለቤቱን እህት ባል ጥፋተኛ ብሎ ብይን ሰጥቷል። በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ ላይ ዛሬ በሁለት ፈረቃዎች የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት እና 2ኛ ተከሳሽ የባለቤቱ እህት ባል መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ…
#Update
የእግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።
በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈው መጋቢት 17/2016 ዓ/ም በተጋቡ በ15ኛ ቀን አለልኝ አዘነን ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል መግደላቸውን በሰዉና በሰነድ ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጃውን ከአርባ ምንጭ ልኳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch
@tikvahethiopia
የእግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።
በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈው መጋቢት 17/2016 ዓ/ም በተጋቡ በ15ኛ ቀን አለልኝ አዘነን ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል መግደላቸውን በሰዉና በሰነድ ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጃውን ከአርባ ምንጭ ልኳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamliyArbaminch
@tikvahethiopia
😡1.38K❤351😭133👏77💔73😢48🙏25🤔15😱14🕊6
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ትእዛዝ በሰጠው አድማ በታኝ ፓሊስ የተደገፈ የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል። ከትናንት ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ከመቐለ ወደ ማይጨው ከተማ በተላከ የአድማ ብተና ፓሊስ ጥብቅ ቁጥጥር ስር የስልጣን ሹምሽር እየተካሄደ ያለው። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄ) የስልጠን ሹም ሽሩ " ሰላማዊ…
#Update
" ወታደር ስላሰማራህ አስተዳድረሀል ማለት አይደለም " - የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ
" እኔን የወከለ አስተዳዳሪ የለም ፤ ህጋዊ የዞኑ አስተዳዳሪ እኔ ነኝ ፤ አላስፈላጊ ግጭትና ደም መፋሰስ ለማስቀረት በማሰብ ፅህፈት ቤቴን ለቅቄ ወጥቻለሁ " አሉ የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ።
ዋና አስተዳዳሪው በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እውቀና ትእዛዝ ከትናንት ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም " ሰላማዊ ሹምሽር ነው " የተባለው በዞኑ እየተከናወነ ያለው የአመራር ለውጥ ተቃውመዋል።
" በዞኑ የሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ቀይ መስመር ነው ፤ ወታደር ስለአሰማራህ አስተዳድረሀል ማለት አይደለም " በማለት ገልፀዋል።
ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ በሰጡት ቃል ፥ ከትናንት ሀምሌ 14 ከምሽቱ 3፡30 ጀምሮ የአድማ ብተና ፖሊስና ታጣቂ ሰራዊት ወደ ዞኑ መሰማራቱ አረጋግጠዋል።
" ለረጅም ጊዚያት እቅድና ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ የዞኑ አስተዳደር የማፍረስ ተግባር እየተፈፀመ ነው " ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ፕሬዜዳንት ጀነራል ታደሰ የሰጡት ቃለመጠይቅ " እርስበራሱ የሚጋጭ አዲስ ቀውሰ አዋላጅ " በማለት አብጠልጥለውታል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ " ኃላቀርና ቆሞ ቀር " ሲሉ የገለፁት የህወሓት አመራር ቡድን መሳሪያ ሆኗል ሲሉም ከሰዋል።
ባለፈው የሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ወደ የአከባቢውን አስተዳደር በራሱ ሰዎች ለመተካት መወሰኑን ተከትሎ ማይጨውና አላማጣ ጨምሮ በመላ የዞኑ ከተሞች የተቃውሞ ህዝባዊ ሰልፍ መካሄዱ አይዘነጋም።

❤783🕊92🤔32😡32👏23😭18😢13🙏11😱4🥰2💔2
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ #ለሚመለከታችሁ_አካላት አዲስ አበባ አስኮ አዲስ ሰፈር ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ የእንጨት ኤሌክትሪክ ፖል ተንጋዶ ለመውደቅ እጅጉን መቃረቡን የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመዋል። " ሰፈሩ የነዋሪዎች መግቢያ መውጫ፣ ህጻናትም ያሉበት ፣ መኪኖች የሚመላለሱበት ስለሆነ ወድቆ አደጋ ከመድረሱ በፊት መፍትሄ ይሰጠው " ብለዋል። ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ከፍተኛ ዝናብና ንፋስ ስላለ ፈጣን…
#Update
ተስተካክሏል !
አዲስ አበባ አስኮ አዲስ ሰፈር ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ የእንጨት ኤሌክትሪክ ፖል ተንጋዶ ለመውደቅ እጅጉን መቃረቡን የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቁመው ነበር።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ በጥቆማው መሰረት " የዘመመውን ምሰሶ አቃንተን ከአደጋ ነፃ አድርገናል " ሲል ገልጾልናል።
#እናመሰግናለን

❤998👏543🙏128🤔34🕊18😡16😢6😭6😱3🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ከዞኑ ተነስተው የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር
➡️ " ጥያቄያችን ለግለሰቦች ስልጣን ስለመስጠትና መንሳት አይደለም። ጥያቄያችን ስለ ህዝብ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ነው ። ስለሆነም የተሰጠኝ ኃላፊነት አልቀበለውም " - የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ
ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም በጊዚያዊ አስተዳደሩ ትእዛዝ በፀጥታ ኃይል በመታገዝ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት አመራሮች አንዱ የሆኑት ሃፍቱ ኪሮስ በማህበራዊ የትስስር ገፅ በተሰራጨው ደብዳቤ ከዞን አስተዳዳሪነት ተነስተው ወደ ክልል ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊነት መሾማቸው ያትታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ተፅፎ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ሲዘዋወር የተስተዋለው ደብዳቤ ትክክለኝነት አረጋግጧል።
አቶ ሃፍቱ የተሰጣቸው ተለዋጭ የስልጣን ቦታ በማስመልከት በሰጡት መልስ ኃላፊነቱን እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።
አቶ ሃፍቱ ኪሮስ " ጥያቄያችን ለግለሰቦች ስልጣን ስለመስጠትና መንሳት አይደለም። ጥያቄያችን ስለ ህዝብ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ነው። ለኔ ስልጣን የከፍታና የዝቅታ መግለጫ ሳይሆን መንግስታዊ ኃላፊነት በተገቢዉ ከመውጣትና ከህዝብ አገልጋይነት አንፃር ነው የመምዝነው " ብለዋል።
" ስለሆነም ክቡር ፕሬዜዳንት መንግስታዊ መዋቅር የማስተካከል ስልጣን እንዳላቸው በመርህ ደረጃ ባምንም ተገቢ መግባባት ያልተደረገበት፣ አንገብጋቢና የሚያመርቅዝ የህዝብ ጥያቄ ባልተመለሰበት የሚሰጥን ኃላፊነት ከምስጋና ጋር አልቀበለውም " ሲሉ የተሰጣቸውን ሹመት ውድቅ አድርገዋል።
አቶ ሃፍቱ ለሰላም ሲሉ ከፅህፈት ቤታቸው መውጣታቸው ገልፀው " እኔን የወከለ አስተዳዳሪ የለም ፤ ህጋዊ የዞኑ አስተዳዳሪ እኔ ነኝ ፤ አላስፈላጊ ግጭትና ደም መፋሰስ ለማስቀረት በማሰብ ፅህፈት ቤቴን ለቅቄ ወጥቻለሁ " ማለታቸው ይታወሳል።
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በዞኑ የተካሄደው በፓሊስ የተደገፈ የስልጣን ሹምሽር በመቃወም በማይጨው ከተማ ለሀምሌ 18 ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዟል።

❤908🕊73👏44🤔40🙏28😡27🥰12😱12😭12💔7😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" ቀሪዎቹ 2 አስክሬኖች ተገኝተዉ የ5ቱም ስርዐተ ቀብር ተፈፅሟል " - የደቡብ አሪ ዞን አስተዳዳሪ
በአሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ኮመር ቀበሌ ሀምሌ 13/2017 ዓ/ም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ 5 የአንድ ቤተሰብ አባላት አስክሬን ፍለጋ በማሽንና በሰዉ ሃይል ሲካሄድ ቆይቶ የ3 ሰዎችን አስክሬን ትላንት የተገኘ ሲሆን የቀሪዎቹ 2 ሰዎችም አስክሬን ዛሬ ተገኝቶ የቀብር ስነ ስርዓት እንደተፈፀመላቸዉ የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛዉ ሃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በመሬት ናዳዉና በከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ናቸዉ ተብለዉ ከተለዩ አከባቢዎች ከ1,019 የሚሆኑ ነዋሪዎች ተፈናቅለዉ በድንኳንና በሃይማኖት ተቋማት ተጠልለው ይገኛሉ ያሉት አስተዳዳሪዉ " ቀጣይ ትኩረታችን የተጎዱትን ማገዝና ተፈናቃዮችን መልሶ የማቋቋም ስራ ይሆናል " ብለዋል።

😭648❤321💔70🕊32😢29🙏22🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mesebo የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ከሁለት ወራት በላይ ከስራ ገበታ ውጪ ሆኗል። ስራ ባቆመባቸው ቀናት 400 ሺህ ቶን ስሚንቶ ሳያመርት ቀርቷል። ፋብሪካው ከማምረት ውጪ ሊሆን የቻለው ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር ማህበረሰብ ጋር በተፈጠረ አለመስማማት ነው። የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ክብረኣብ ተወልደ ምን አሉ ? " የላይምስቶን ጥሬ እቃ የሚያገኝበት አከባቢ የሚኖረው ህዝብ በተደጋጋሚ…
#Update
የመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ዛሬ ሀምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጠው አጭር መግለጫ ከ75 ቀናት በላይ አቋርጦት የነበረውን ስሚንቶ የማምረት ስራ መልሶ መጀመሩን አስታውቋል።
ስራ ባቆመባቸው ቀናት ከ400 ሺ ቶን በላይ ስሚንቶ ሳያመርት ቀርቷል።
መሰቦ ሲመንቶ ከሁለት ወራት ተኩል በላይ ስራውን እንዲያቋርጥ ምክንያት የሆነው ችግር በዘላቂነት በመፈታቱ መልሶ ወደ ማምረት እንደገባ አመልክቷል።
ፋብሪካው ጥሬ እቃ ከሚያገኝበት አከባቢ ከሚኖር ማህበረሰብ ጋር በተፈጠረ አለመስማማት የማምረት ስራውን አቁሞ እንደነበር መግለጹ ይታወሳል። #DW

2❤546🙏65👏52🕊37🤔18😡10😢8🥰5💔5😭3
TIKVAH-ETHIOPIA
" ነጻ፤ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያለ ሰላምና መረጋጋት ውጪ ሊታሰቡ አይችልም " - የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል ጉዳይ ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ የውይይት መድረክ ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። በዚህ መድረክ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት…
#Update
የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ ሲያካሂድ የነበረውን የሰላም ኮንፈረንስ ' የቢሾፍቱ ቃልኪዳን ' መግለጫ በማውጣት አጠናቋል።
ይህ ቢሾፍቱ ቃልኪዳን መግለጫ 7 አንቀጾችን የያዘ ነው።
ቃልኪዳኑ ምን ይላል ?
አንቀጽ 1. ሠላማዊና የሠለጠነ የፖለቲካ አካሄድ የመከተል ቃል ኪዳን።
" የፖለቲካ ዓላማችንን በዲሞክራሲያዊ እና በሕግና በስርዓት እናከናወናለን " ብለዋል።
" ጸጥታን በማደፍረስ፣ የስም ማጥፋትና ጥላቻ እንዲሁም ለሰዉ ህይዎትና ንብርት መጥፋት ምክንያት ባላመሆን ለሰላም እንተጋለን " ሲሉ ገልጸዋል።
አንቀጽ 2 ፦ ለዲሞክራሲ ተቋማትና እሴቶች ክብር የመስጠት ቃል ኪዳን።
" ሕግና ሥርዓት፣ የህዝብ ውሳኔ ወሳኝነት፣ የምርጫ ሂደቶችና ዉጤት እንዲከበሩ " እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
" በውሳኔዎች ላይ ልዩነት ቢኖር እንኳ ህጋዊነትን በማክበር አቋማችንን እናራምዳለን " ብለዋል።
አንቀጽ 3 ፦ ለአካታችነት፣ ለሀገራዊ መግባባትና ብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም ኪዳን።
" ያሉንን ልዩነቶችን ክብርና ልዩ ትኩረት በመስጠት ለህብረብሄራዊነት እሳቤ ግንባታ ለመስራት ተስማምተናል " ሲሉ አሳውቀዋል።
የወጣቶች፣ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እንድያድግ በትኩረት እንደሚሰሩና ለብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም የፖለቲካ ባህል እንደሚገነቡ ገልጸዋል።
አንቀጽ 4 ፦ ለዲሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደር መስፈን የመስራት ቃል ኪዳን።
" በአጀንዳ፣ በፖሊሲ፣ በችሎታ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት ለመገንባት እንሰራለን። የተለያዩ የፖለቲካ አስተሰሰብና ፍላጎት መኖር እንደ ጤናማ ዲሞክራሲ ምልክት እንቀበላለን " ብለዋል።
አንቀጽ 5 ፦ የግጭት አያያዝ እና የሰላም ግንባታ ዉጤታማነት የመስራት ቃል ኪዳን፡፡
" በየፓርቲዎቻችን ውስጥና በሌሎች ፓርቲዎች መካከል ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ የመፍትሄ ሥርዓቶችን እንገነባለን " ያሉ ሲሆን " በማህበረሰብ፣ በአካዳሚያ፣ በተለያዩ መድረኮች እና ከፖለቲካ አመራሮች ጋር በሚካሄዱ የሰላም ውይይቶች በአጋርነት እንሳተፋለን " ብለዋል።
አንቀጽ 6 ፦ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የመዳበር ቃል ኪዳን፡፡
" በመንግስት እንዲሁም በፓርቲያችን ውስጥ ግልጽነት፣ የሐሳብ ነጻነትና መተማመን እንዲጎለብት እንተጋለን። የህዝብ ተሳትፎ የሚገድብ ሥራ እና ተቋማዊነት የሚጎዳ የፖለቲካ አካሄድ በጋራ አንታገላለን " ሲሉ በቢሾፍቱ ቃልቂዳን ላይ አስፍረዋል።
አንቀጽ 7 ፦ ለብሄራዊ ጥቅም እና ለዲሞክራሲ ስርዓት የመጽናት ቃል ኪዳን፡፡
" በሰላም፣ በዉጫዊ ችግሮች፣ በብሄራዊ ምርጫ እና በመንግሥት ልማት አካል እንደአንድ አካል እንሰራለን። በኢትዮጵያ የዜጎችና ህዝቦች ክብር እና በሀገራች የጋራ ዕጣ ፋንታችን ላይ በጋራ በመቆም ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ለማጽናት እንሰራለን " ብለዋል።
#EthiopianPoliticalPartiesJointCouncil
#MinistryofPeace

❤451😡119🤔23😭14🕊13🙏9😱6😢5🥰4💔4
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የተከሰተው የእሳት አደጋ በህዝቡ ብርቱ ጥረት በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደተቻለ ተገልጿል። በአደጋው የሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና ፣ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና ተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል። መንስኤው እየተጣራ ነው ተብሏል። #WolaitaZoneAdministration #TikvahEthiopiaFamilyWolaitaSodo…
#Update
" በርካታ ታካሚዎች የተኙባቸው ክፍሎች ስለነበሩ ያሉት ሠራተኞች በሙሉ ታካሚ ማውጣት ላይ ትኩረት ስላደረጉ በርካታ ንብረቶች ተቃጥለው ወድመዋል " - የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከሰተው የእሳት አደጋ በሰዎች ጉዳት ባያደርስም በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)፣ " በርካታ ታካሚዎች የተኙባቸው ክፍሎች ስለነበሩ ሠራተኞች በሙሉ ታካሚ ማውጣት ላይ ትኩረት ስላደረጉ በውስጥ የነበሩ በርካታ ንብረቶች ተቃጥለው ወድመዋል " ሲሉ ነግረውናል።
ፕሬዚዳንቱ፣ " የተጎዳ ሰው የለም። ታካሚ የነበረበት ክፍል ነበር አደጋው የደረሰው እሳቱ መቀጣጠል ከጀመረበት ጊዜ ጅምሮ ታካሚዎቹን ወደ ሌላ ክፍል አውጥተናል። ታካሚ አልተጎዳም " ብለዋል።
" በእርግጥ እሳት በማጥፋት ላይ እያለ አንድ ሠራተኛ መስታወት የቆረጠው አለ ሌላ የተጎዳ የለም " ሲሉም አክለዋል።
መንስኤው ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ "ገና ነው አልታወቀም። መንስኤው እየተጣራ ነው። እሳቱ በጣም ከጎበዘ በኋላ ስለሆነ የደረስነው እሩጫ ላይ ስለነበርን መንስኤውን አላገኘንም" ሲሉ መልሰዋል።
የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ከአደጋው ጋር በተያያዘ አጣዳፊ ሥራ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ ሲያጠናቅቁ ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጡን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤544😢161😭54🙏29💔29🥰6🤔3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት አረሜናዊ ድርጊት የፈፀመው ተጠርጣሪ " እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም " ሲሉ የትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። " አሲድ የተደፋባቸው ወገኖች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ አክለዋል። አሲድ የተደፋባቸው እንስቶቹ ለተሻለ ህክምና ከእንዳስላሰ - ሽረ ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ሪፈር መባላቸውን…
#Update
ተጠርጣሪው ተይዟል !
በእንዳስላሰ ሽረ በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ጉዳት እንዳደረሰ የተጠረጠረው ተጠርጣሪ ተያዘ።
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የእንዳስላሰ-ሸረ ከተማ ነዋሪ የሆነው ተጠርጣሪ ወላይ ተጠምቀ ሀምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በከተማው በሚገኘው መጠጥ ቤት በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ተጠርጥሮ በፓሊስ ሲፈለግ እንደነበር ተጠቁሟል።
የእንዳስላሰ-ሸረ ከተማ የፀጥታ ፅህፈት ቤት ዛሬ ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጠው መረጃ ፤ ተጠርጣሪው በፀለምቲ ወረዳ አዋሳኝ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ተላልፎ ተሰጥቷል።
በተደፋባቸው አሲድ ክፉኛ ከተጎዱት አንድዋ ፍረይ ተክለሃይማኖት የተባለች እንስት ለከፍተኛ ህክምና በመቐለ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል እንደምትገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

❤708👏226😭91😡54🙏39💔20😢11🕊11🤔9
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥያቄና ፍላጎታችን በሀይል የፈረሰው አስተዳደራችን እንዲመለሰልን ነው " - ሰላማዊ ሰልፈኞች ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም ጊዚያዊ አስተዳደሩ በሰጠው አቅጣጫ በዞኑ አስተዳደር በአድማ በታኝ ፓሊስ ታጆቦ ይደረጋል የተባለው የስልጣን ሹምሽር በአከባቢው በተለይ በማይጨው ከተማ አለመረጋጋት አስከትለዋል። ከማይጨው ከተማ 195 ኪሎ ሜትር ተጉዘው መቐለ ድረስ የመጡ ተወካዮች ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል)…
#Update
ላለፋት 6 ቀናት ከስራ ገበታ ተስተጓጉለው የሰነበቱት የትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች መልሰው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።
የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዛሬ ሰኞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ-መቐለ በሰጠው መረጃ ዋና አስተዳደሪው አቶ ሃፍቱ ኪሮስ የሚገኙባቸው የስራ አመራሮች ዛሬ በይፋ ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዘዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከህዝብ ተወካዮችና ከዞኑ አመራሮች ተከታታይ ውይይት ሲያካሂዱ ቆይተው መጠነኛ መግባባትና መረጋጋት በመፍጠሩ ምክንያት ነው መንግስታዊ መስሪ ቤቶች ወደ አገልግሎት የተመለሱት።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዘዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የዞኑን ዋና አስተዳደሪ ከሀምሌ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት ማንሳታቸውን ተከትሎ ዞኑ አለመረጋጋት ውስጥ ነው የሰነበተው።
" አስተዳዳሪያችን ከኃላፊነት የተነሱበት አካሄድ ልክ አይደለም " ብለው ያመኑ የዞኑ ነዋሪዎች ወደ መቐለ ተጉዘው ከፕሬዜዳንቱ ከመወያየት በተጨማሪ የተለያዩ ሰላማዊ ተቋውሞዎች አካሂደዋል።
ትናንትና ዛሬ ሀምሌ 20 ና 21/2017 ዓ.ም የራያ ዓዘቦና የአምባላጀ ዓዲሽሁ ወረዳና ከተማ ነዋሪዎች የፕሬዜዳንቱን እርምጃ በመቃወም ሰልፍ ወጥተዋል።
ከሀምሌ 18 -20/2017 ዓ.ም በመቐለና በማይጨው ከፕሬዜዳንቱ ጋር የተካሄዱት ውይይቶች በፈጠሩት ተነፃፃሪ መረጋጋት የተቋረጠው አገልገሎት መልሶ መጀመሩንና ሀምሌ 27/2017 ዓ.ም የቀጠለ ውይይት በማይጨው እንደሚካሄድ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ-መቐለ ተናግሯል።

❤474🕊73👏32😡15🥰5🤔3😢2💔2😭2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" እኔ ስልጣን ላይ እያለሁ ዳግም ግጭትና ጦርነት አይኖርም " ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ተናገሩ።
" በትግራይ በኩል የሚጀመር ጦርነት አይኖርም ፤ እኔ በስልጣን እያለሁኝ የሚነሳ ጦርነት የለም ፤ ዳግም ጦርነትና ግጭት እንዳይቀሰቀስ አቅሜን አሟጥጬ እሰራለሁ " ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንቱ ይህን ያሉት ትንናት ሀምሌ 21/2017 ዓ.ም ወደ መቐለ ትግራይ ከገባዉ የሰላም ልኡክ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
" የትግራይ ህዝብ ጦርነት አይፈልግም " ሲሉ የተናገሩት ፕሬዜዳንቱ " በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮቻችን ወደ ቄያቸው ስላልተመለሱ
ጅምር ሰላሙ ሙሉ መሆን አልቻለም " ብለዋል።
" ሁሉም ልዩነቶች በጠረጴዛ ውይይት ዙሪያ ይፈታሉ " ያሉት የሰላም ልኡካኑ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ለሚደረገው ጥረት ሰላማዊ ድጋፋቸው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
በፌደራል መንግስትና በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር መካከል ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያግዝ የስምምነት ሰነድ በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት ማግኘቱ በውይይቱ የተገለፀ ሲሆን የስምምነት ሰነዱ ዝርዝር ይዘት አስመልክቶ የተባለ የለም።
የሰላም ልኡካኑ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በመጎብኘት የብር 30 ሚሊዮን ዋጋ ያለው እርዳታ ይለግሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

❤816🕊203👏53🤔39🙏36😡18💔10😭8🥰7😱6
TIKVAH-ETHIOPIA
#CustomsCommission " ትልቁ ስህተት የተፈጠረው የጉምሩክ ኮሚሽን 'በርቀትና ኤክስቴንሽን የተመረቃችሁ ተወዳዳሪዎች አትካተቱም' ማለቱ ነው " - ቅሬታ አቅራቢ አመልካቾች ➡️ " የማጣራት ሂደቶች መደረጋቸው አይቀርም። ማንኛውም የቅጥር ማስታወቂያ ሲወጣ ሁሉም የተመዘገበው ያልፋል ማለት አይደለም " - ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን ለሥራ ቅጥር ከ2,000 በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ክልሎችና…
#Update
#CustomsCommission
" ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩትን አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉብትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል " - ጉምሩክ ኮሚሽን
የጉምሩክ ኮሚሽን ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከ200ዐ በላይ ተወዳዳሪዎችን እንዲመለምሉ ለክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በሰጠው ኮታ መሰረት የተመለመሉ አመልካቾች ዝርዝር ከተላከለት በኋላ በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቅነውን " ኮሚሽኑ በቅጥሩ 'አትካተቱም' አለን " የሚል ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበው ነው።
ይህ ቅሬታ ያላቸው የተሰባሰቡት ብቻ ወደ 300 እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ ለምን ይህን እንዳደረገ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጉምሩክ ኮሚሽን ጉዳዩን አጣርቶ ምላሽ ሊሰጥ ቀጠሮ ሰጥቶን ነበር፡፡
ኮሚሽኑ ለቀረበበት ቅሬታ ምን መለሰ ?
የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ " ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩት አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉበትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል። በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው በዚህኛው ቅጥር የተጋበዙት " ብለዋል።
ማስታወቂያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ፣ በግል ኮሌጆች ተመርቀው ትምህርት ሚኒስቴር ያረጋገጠላቸው ምሩቃን መወዳዳር እደሚችሉ በሚገልጸው መሰረት ካመለከቱ በኋላ " አትካተቱም " እንደተባሉና አሰራሩ ልክ እንዳልሆነ ነው አመልካቾቹ የገለጹት፤ ለዚህ ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል አቶ ዘሪሁንን ጠይቀናቸዋል፡፡
እሳቸውም፣ " ማስታወቂያ ላይ ዝርዝር ጉዳዮች ላይጠቀሱ ይችላሉ " ብለው፣ " ሌሎችን ዲቴይል መስፈርቶችን ኮሚሽኑ በኋላ ላይ ማጣራት አድርጎ ሁሉም ተመሳሳይ አካባቢ በመደበኛና ኤክስቴሽን የተማሩትን፣ ሌሎችን ደግሞ በሌላ መስፈርት ሳይሆን ለሁሉም ወጥ የሆነ ውሳኔ ነው የወሰነው " ብለዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ማስታውቂያው ወጥቶ ተወዳዳሪዎች ካመለከቱ በኋላ ኮሚሽኑ ይህን መወሰኑ ለምንድን ነው ? የገጠማችሁ ችግር ምንድን ነው ? በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቁት በቅጥሩ የማይካተቱ ከሆነስ ለምን ቀድማችሁ አላሳወቃችሁም ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
አቶ ዘሪሁን፣ " ኮሚሽኑ በኋላ ላይ አጠቃለይ የምልመላ ሂደት ይህን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የማጣራት ሂደቶችን አድርጎ ካሉ ዝርዝሮች ውስጥ እነዚህ ወደቀጣዩ ዙር የምልመላ ሂደት ይለፉ ብሎ የወሰነው ወደ ቀጣይ ዙርም የተገባበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን ነው ልገልጽ የምችለው " ሲሉ አስረድተዋል።
ፕሮግራሙ ቢለያይም በሀገሪቱ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ትምህርት ነው የሚሰጠው ስለዚህ መደበኛውን ብቻ ለይቶ ለመቅጠር ህጉ ይፈቅዳል ? ሁሉንም ምሩቃን ማካተት አልነበረባችሁም ? ለሚለው ጥያቄም፤ " ኮሚሽኑ ያስቀመጠው አሰራር ነው፡፡ መደበኛዎቹን ነው በዚህ የቅጥር ሂደት ውስጥ የማካትተው የሚል መስፈርት ወጥቶ ውሳኔ ተሰጥቶበት እየተሰራ ያለ ጉዳይ ነው " የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል፣ በክልሎች በኩል የነበረው የምልመላ ሂደት " በቢሮዎች ዘመድ ላላቸው ቅድሚያ እየተሰጠ ዘመድ የሌላቸው ከመንከራተታቸውም በላይ እድሉን እንዳላገኙ "፣ በአዲስ አበባ ያለው ምልመላም ኦፊሻል ወጥቶ እንዳልተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ያደረሱ እንዳሉ በመግለጽ፤ ለዚሁ ቅሬታ ጉምሩክ ኮሚሽንን ምላሽ ጠይቀናል፡፡
አቶ ዘሪሁን " ቅሬታዎች የሉም ማለት አይደለም፤ እኛ ጋርም የመጡ ቅሬታዎች ነበሩ፤ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻርም ይሁን በግለሰብ 'በዚህ ቀን ተመዝግበን፤ እኔ ማለፍ ሲገባኝ እከሌ/እከሊት ያላግባብ አልፋለች/ፏል' የሚል ቅሬታ አለ " ብለው፤ ፍትሃዊ እንዲሆን ጉዳዩን ወደ ክልል መልሶ ኮሚሽኑ ማጣራት እያደረገ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቅሬታ ያላቸው በክልል በኩል አጽፈው ቅሬታቸውን ቢያቀርቡ ኮሚሽኑ አጣርቶ ማስተካከያ የማያደርግበት ምክንያት እንደማይኖር፣ በዚሁ መሰረትም ምላሽ የተሰጣቸውና በሂደት ላይ ያሉም እንዳሉ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባውን ቅሬታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ አመልካቾች ተመልምለው እንደተላኩላቸው ተናግረው፣ " አይደለም አዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ መደረጉን ኮሚሽኑ ክትትል ሲያደርግ ነበር " ብለዋል፡፡
በዚህ የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ኮሚሽኑ የሚፈገውን ያህል የሰው ኃይል እንዳገኘና አመልካቾቹ በቀጣይ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ የሚገቡበት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘሪሁን፣ በአጠቃላይ ምን ያክል ሰዎች አመልክተው እንደነበር ስንጠይቃቸው ለጊዜው ዳታውን እንዳልያዙና መግለጹ አስፈላጊ እንዳልሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

❤398😡72😭31🙏19💔19🤔9🥰7👏7😢5🕊5😱3