TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CustomsCommission

" የጀመርነውን እርምጃ አጠናክረን እንቀጥላለን " - የጉምሩክ ኮሚሽን

የጉምሩክ ኮሚሽን ፥ የግል መገልገያ እቃዎችን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ለማስገባት ለመንገደኞች የተፈቀደውን መመሪያ ተገን አድርገው ከመመሪያው ውጭ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተመላላሽ መንገደኞች በመንግስት ገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ ጫና እያደረሱ በመሆኑ የተጀመረው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኮሚሽነር ደበሌ ፥ የዓለም አቀፍ መንገደኞች ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ይዘዋቸው ስለሚመጡ እና ከቀረጥ ነጻ ስለተፈቀዱ ብሎም ስላልተፈቀዱ የግል መገልገያ እቃዎችን ለመወሰን ከዚህ በፊት መመሪያ ቁጥር 51/2010 ጸድቆ ስራ ላይ መዋሉን ጠቅሰዋል፡፡

ኮሚሽኑ ባደረገው ጥናት መሰረት ከመመሪያው ዓላማ ውጭ አንዳንድ ተመላላሽ መንገደኞች በህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው መንግስት በዘርፉ የሚያገኘውን ገቢ እንዲያጣ እና በንግድ ስርዓቱም ላይ ፍትሀዊ ውድድር እንዳይኖር እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

እነዚህ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተመላላሽ መንገደኞች የሚያደርጉት የገንዝብ ዝውውር በህጋዊ የፋይናንስ ተቋማት የሚከወን ባለመሆኑም ህገወጥ የገንዝብ ዝውውር እንዲስፋፋ፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስና የንግድ ስርዓቱ እንዲታወክ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

መመሪያውን ተላልፈው የተገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እና ወደ ህጋዊ የንግድ መረብ እንዲገቡ ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አለመቻላቸውን ኮሚሽነር ደበሌ ገልጸው በእነዚህ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ከሌሎች የጸጥታ አካላትም ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

@tikvahethiopia
👍4
#NBE #CustomsCommission #LC

የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ባንክ፣ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጥያቄ መሠረት አስመጪና ላኪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ወደ አገር ቤት እንዳያስገቡም ሆነ ወደ ውጪ እንዳይልኩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ እንደሚለው ፤ ኮሚሽኑ በወሰነው ውሳኔ አንዳንድ ላኪዎችና አስመጪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያየ ጊዜ ምርቶችን መላክና ማስመጣት የሚፈቅደውን ሕግ፣ የአገርን ጥቅም በሚያሳጣና በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀሙበት በመሆኑ አንድ LC (LETTER OF CREDIT) ለአንድ ምርት ብቻ እንዲሆን ሊያደረግ ነው።

ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚሆነው ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. እነድሆነ ተገልጿል።

አስመጪና ላኪዎች ትዕዛዙ በአሁኑ ሰዓት በክፍልፋይ (Partial Shipment) መሠረት ስምምነት ያደረጉ ድርጅቶችን ያካተተ መሆን የለበትም ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

እኚሁ አስመጪና ላኪዎች አንዳንድ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያሰሩትን ስምምነት መቀየር እንደማይችሉና ትዕዛዙ ተግባራዊ መሆን ያለበት አዲስ ስምምነት ለሚያደርጉ ድርጅቶች መሆን እንደሚገባ ለብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በባንኮች በኩል የሚከፈተው LC (LETTER OF CREDIT) በገዥና በአቅራቢ ድርጅት መካከል የሚደረግ ጠንካራ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል፡፡

የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) ማለት ገዥውና አቅራቢ በስምምነታቸው መሠረት በአንድ ጊዜ ሁሉንም ምርት በተለያየ ምክንያት መላክ ስለማይቻል ከሥር ከሥር እየተመረተ ለመላክ የሚስማሙበት አካሄድ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በኮንቴይነር እጥረት፣ ገዥው በቂ ማከማቻ ቦታ ከሌለው፣ የክፍልፋይ ስምምነት ይደረጋል፡፡ ይህ ስምምነት ጥሬ ዕቃዎቹ በወቅቱ እንዲገቡ ያደርጋል እንጂ አገርን የሚጎዳ አይደለም ሲሉ አስመጪ ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡

የአስመጪዎች ትልቅ ሥጋት የሆነው የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) መሠረት የታዘዙት ዕቃዎች ጂቡቲ የሚደርሱት የጉምሩክ ኮሚሽን ውሳኔ ከሚጀመርበት ቀን በኋላ ነው፡፡

በአዲሱ ትዕዛዝ ቀድሞ ስምምነት የነበራቸውን በማካተቱ ምርቶቹ መጥተው ወደብ ላይ መዘግየት፣ የባንክ  ብድር መክፈል አለመቻል፣ የቀረጥ ክፍያ አለመስተናገድና ለተጨማሪ " ዴሜሬጅ " ክፍያ እንደሚያወጡ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ዕገዳው ቀድሞ ስምምነት የተደረገባቸውን ሳያካትት ከኅዳር 10 ቀን በኋላ ለሚደረግ አዲስ ስምምነት ፈቃድ መከልከል አለበት ብለዋል፡፡

በክፍልፋይ ጊዜ በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያዩ ወቅቶች ምርቶችን ማስገባት መፈቀዱ፣ አስመጪዎቹ ባንክ ከፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ በላይ የሚያወጡ ምርቶችን የማስገባት ዕድሎችን እንደመፍጠሩ፣ በዚህም ባንኩ ከፈቀደላቸው ውጪ ጥቅም ላይ ያዋሉት ገንዘብ ከጥቁር ገበያ የተገኘ ነው የሚለውን ጥርጣሬ ከማሳደጉ ባለፈ፣ አሠራሩም ሕገወጥ ገበያን አበረታቷል በሚል የተላለፈ ትዕዛዝ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ  ማብራሪያ የሰጡት የዘርፉ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነ የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) አገርን ችግር ውስጥ የሚከት አይደለም ብለዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን ሕገወጥ ተግባርን ለመከላከል የሚፈልግ ከሆነ በቀላሉ ሕገወጦቹን በመለየት በሕግ መጠየቅ እንጂ በትክክለኛ አካሄድ የሚሠሩትንም በአንድ ላይ በማገድ መፍትሔ አይመጣም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
242😡125👏31🙏26😢19😱12🥰11😭11🕊10
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጉምሩክ

(አስመጪዎች)

" በኢንቮይስ ያልተከፈሉ አሉ። ብዙ እቃዎች ናቸው ያሉት። እቃዎቹ አንድ ላይ ጉምሩክ የገቡ ናቸው።

የነዛና የነዚህ ልዩነት በጣም ሰፊ ነው። ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን በኮንቴነር ጭማሪ የሚያመጡ ናቸው።

እነዚህም አብረው የሚስተናገዱበት መንገድ መኖር አለበት።

እቃዎቹ ሰሞኑን የታሪፍ ፣ የቀረጥ ለውጥ ሁሉ ተደርጎባቸው ነበር። በአንድ አይተም እስከ 10 ዶላር ጭምር ተደርጎ ነበር ከሬት ውጭ እሱ ላይ ብዙ ቅሬታ አልነበረም ሁሉም አንድ ላይ ስለጨመረበት።

አሁን ላይ እቃው አብሮ ገብቷል። እነዚህ ኢንቮይስ ከፍለዋል። እኛ በኢንቮይስ አልከፈልንም። ተመሳሳይ እቃዎች ናቸው።

የእነሱ ይውጣ ፤ እናተ ደግሞ በአዲሱ ሬት ክፈሉ ብንባል በጣም ትልቅ ልዩነት ይኖራል። በአንድ ገበያ ላይ ተወዳድሮ ለመስራት የሚቻል አይደለም።

ጉምሩክ ይኔንም ስጋታችንን ቢይይልን።

ሁለት ቦታ ተከፍለናል ፤ በኢንቮይስ የከፈሉ አሉ በኢንቮይስ ያልከፈልን አለን። ልዩነቱ ብዙ ነው በሚሊዮኖች ነው።

አንድ ገበያ ላይ  ነው የምንሰራውና እኛንም ከገበያ እንዳያስወጣን ይሄም ይታይልን። "

#CustomsCommission

@tikvahethiopia
😡9069🙏13🕊10🥰8🤔4😭4😱3😢2
#CustomsCommission

" ትልቁ ስህተት የተፈጠረው የጉምሩክ ኮሚሽን 'በርቀትና ኤክስቴንሽን የተመረቃችሁ ተወዳዳሪዎች አትካተቱም' ማለቱ ነው "  - ቅሬታ አቅራቢ አመልካቾች

➡️ " የማጣራት ሂደቶች መደረጋቸው አይቀርም። ማንኛውም የቅጥር ማስታወቂያ ሲወጣ ሁሉም የተመዘገበው ያልፋል ማለት አይደለም " - ጉምሩክ ኮሚሽን


የጉምሩክ ኮሚሽን ለሥራ ቅጥር ከ2,000 በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች መልምለው እንዲልኩለት በሰጠው ኮታ መሠረት የተመለመሉ ከ270 በላይ አመልካቾች መስፈርቱን ካሟሉ በኋላ " ኮሚሽኑ አልተካተታችሁም' አለን " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቀረቡ።

ለውድድሩ በቀረቡት 14 መስፈርቶች መሠረት በየወረዳ እንደተመለመሉ የገለጹት አመልካቾቹ፣ " ትልቁ ስህተት የተፈጠረው ጉምሩክ ኮሚሽን ' በርቀትና ኤክስቴንሽን የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች አትካተቱም ' ማለቱ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" በኮሚሽኑ የሥራ ማስታወቂያ ላይ በማንኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተመረቀ፣ በግል ኮሌጆች ተመርቀው ትምህርት ሚኒስቴር ያረጋገጠላቸው መወዳደር እንደሚችሉ ተጠቅሶ እያለ በዚያ መሠርት ተመለመልን ስማችን ከተላከ በኋላ እየደወሉ አትካተቱም እያሉ ነው የነገሩን " ነው ያሉት።

ጉዳዩን ሲያጣሩ፣ " በመደበኛ ፕሮግራም የተመረቁ ብቻ ለፈተና እና ቅጥር ታሳቢ እንደሚደረጉ" መረዳታቸውን ገልጸው፣ "በመንግስትም ሆነ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኢ-መደበኛው ፕሮግራም (በእሁድና ቅዳሜ፣ በክረምት፣ በማታና በርቀት ፕሮግራሞች) የተመረቅን እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪ ያጠናቀቅን (በመንግስትና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) ከውድድር ውጪ ሆነናል " ሲሉ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቅሬታውን በዝርዝር በመግለጽ ምላሽ የጠየቅናቸው የጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ያነሱት አጠቃላይ ሂደቱ ትክክል እንደሆነ፣ ሆኖም " አልተካተትንም " ማለታቸውን በተመለከተ ግን ጉዳዩን በደንብ ማጣራት እንዳለባቸው (እሳቸው ኮሚሽኑን) የሚመለከት ምላሽ ሰጥተዋል። 

" የማጣራት ሂደቶች መደረጋቸው አይቀርም። ማንኛውም የቅጥር ማስታወቂያ ሲወጣ ሁሉም የተመዘገበው ያልፋል ማለት አይደለም። ተቋሙ ያስቀመጣቸው መስፈርቶች ይኖራሉ። ያን መሠረት ተደርጎ ምልመላ ይደረጋል " ብለው፣ በመዋቅራቸው በኩል የተቀጣሪዎችን መልምለው እንዲልኩ በዋናነት ተግባሩ ለክልሎች እንደተሰጠ አስታውሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አመልካቾቹ፣ ለውድድር ተመልምለው የክልል ኃላፊዎች ፈርመውበት ለፌደራሉ ጉምሩክ መላኩ እንደተነገራቸው፣ ሆኖም ከኮሚሽኑ ተደውሎ " በመደበኛው ለተመረቁ ነው ቅጥሩ” እንደተባሉ ነው የገለጹት፤ አሁን ትልቁ ነገር ኮሚሽኑ ይህን አድርጓል ? ለምን ? የሚል ጥያቄ አቅርቧል።

አቶ ዘሪሁን በምላሻቸው፣ መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት መርሃ ግብሮች ተመርቀው የተወዳደሩ ሰዎች በውድድሩ ያቀረቡትን ቅሬታ በተመለከተ መረጃ ማጣራት እንዳለባቸውና የሚመለከተውን ክፍል ጠይቀው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ቀጠሮ ሰጥተዋል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
714😡55🙏27😭23🕊21😢9🤔6💔5😱4🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#CustomsCommission " ትልቁ ስህተት የተፈጠረው የጉምሩክ ኮሚሽን 'በርቀትና ኤክስቴንሽን የተመረቃችሁ ተወዳዳሪዎች አትካተቱም' ማለቱ ነው "  - ቅሬታ አቅራቢ አመልካቾች ➡️ " የማጣራት ሂደቶች መደረጋቸው አይቀርም። ማንኛውም የቅጥር ማስታወቂያ ሲወጣ ሁሉም የተመዘገበው ያልፋል ማለት አይደለም " - ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን ለሥራ ቅጥር ከ2,000 በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ክልሎችና…
#Update
#CustomsCommission

" ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩትን አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉብትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል " - ጉምሩክ ኮሚሽን

የጉምሩክ ኮሚሽን ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከ200ዐ በላይ ተወዳዳሪዎችን እንዲመለምሉ ለክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በሰጠው ኮታ መሰረት የተመለመሉ አመልካቾች ዝርዝር ከተላከለት በኋላ በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቅነውን " ኮሚሽኑ በቅጥሩ 'አትካተቱም' አለን " የሚል ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበው ነው።

ይህ ቅሬታ ያላቸው የተሰባሰቡት ብቻ ወደ 300 እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ ለምን ይህን እንዳደረገ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጉምሩክ ኮሚሽን ጉዳዩን አጣርቶ ምላሽ ሊሰጥ ቀጠሮ ሰጥቶን ነበር፡፡

ኮሚሽኑ ለቀረበበት ቅሬታ ምን መለሰ ?

የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ " ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩት አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉበትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል። በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው በዚህኛው ቅጥር የተጋበዙት " ብለዋል።

ማስታወቂያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ፣ በግል ኮሌጆች ተመርቀው ትምህርት ሚኒስቴር ያረጋገጠላቸው ምሩቃን መወዳዳር እደሚችሉ በሚገልጸው መሰረት ካመለከቱ በኋላ " አትካተቱም " እንደተባሉና አሰራሩ ልክ እንዳልሆነ ነው አመልካቾቹ የገለጹት፤ ለዚህ ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል አቶ ዘሪሁንን ጠይቀናቸዋል፡፡

እሳቸውም፣ " ማስታወቂያ ላይ ዝርዝር ጉዳዮች ላይጠቀሱ ይችላሉ " ብለው፣ " ሌሎችን ዲቴይል መስፈርቶችን ኮሚሽኑ በኋላ ላይ ማጣራት አድርጎ ሁሉም ተመሳሳይ አካባቢ በመደበኛና ኤክስቴሽን የተማሩትን፣ ሌሎችን ደግሞ በሌላ መስፈርት ሳይሆን ለሁሉም ወጥ የሆነ ውሳኔ ነው የወሰነው " ብለዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ማስታውቂያው ወጥቶ ተወዳዳሪዎች ካመለከቱ በኋላ ኮሚሽኑ ይህን መወሰኑ ለምንድን ነው ? የገጠማችሁ ችግር ምንድን ነው ? በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቁት በቅጥሩ የማይካተቱ ከሆነስ ለምን ቀድማችሁ አላሳወቃችሁም ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

አቶ ዘሪሁን፣ " ኮሚሽኑ በኋላ ላይ አጠቃለይ የምልመላ ሂደት ይህን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የማጣራት ሂደቶችን አድርጎ ካሉ ዝርዝሮች ውስጥ እነዚህ ወደቀጣዩ ዙር የምልመላ ሂደት ይለፉ ብሎ የወሰነው ወደ ቀጣይ ዙርም የተገባበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን ነው ልገልጽ የምችለው " ሲሉ አስረድተዋል።

ፕሮግራሙ ቢለያይም በሀገሪቱ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ትምህርት ነው የሚሰጠው ስለዚህ መደበኛውን ብቻ ለይቶ ለመቅጠር ህጉ ይፈቅዳል ? ሁሉንም ምሩቃን ማካተት አልነበረባችሁም ? ለሚለው ጥያቄም፤ " ኮሚሽኑ ያስቀመጠው አሰራር ነው፡፡ መደበኛዎቹን ነው በዚህ የቅጥር ሂደት ውስጥ የማካትተው የሚል መስፈርት ወጥቶ ውሳኔ ተሰጥቶበት እየተሰራ ያለ ጉዳይ ነው " የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል፣ በክልሎች በኩል የነበረው የምልመላ ሂደት " በቢሮዎች ዘመድ ላላቸው ቅድሚያ እየተሰጠ ዘመድ የሌላቸው ከመንከራተታቸውም በላይ እድሉን እንዳላገኙ "፣ በአዲስ አበባ ያለው ምልመላም ኦፊሻል ወጥቶ እንዳልተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ያደረሱ እንዳሉ በመግለጽ፤ ለዚሁ ቅሬታ ጉምሩክ ኮሚሽንን ምላሽ ጠይቀናል፡፡

አቶ ዘሪሁን " ቅሬታዎች የሉም ማለት አይደለም፤ እኛ ጋርም የመጡ ቅሬታዎች ነበሩ፤ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻርም ይሁን በግለሰብ 'በዚህ ቀን ተመዝግበን፤ እኔ ማለፍ ሲገባኝ እከሌ/እከሊት ያላግባብ አልፋለች/ፏል' የሚል ቅሬታ አለ " ብለው፤ ፍትሃዊ እንዲሆን ጉዳዩን ወደ ክልል መልሶ ኮሚሽኑ ማጣራት እያደረገ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቅሬታ ያላቸው በክልል በኩል አጽፈው ቅሬታቸውን ቢያቀርቡ ኮሚሽኑ አጣርቶ ማስተካከያ የማያደርግበት ምክንያት እንደማይኖር፣ በዚሁ መሰረትም ምላሽ የተሰጣቸውና በሂደት ላይ ያሉም እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባውን ቅሬታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ አመልካቾች ተመልምለው እንደተላኩላቸው ተናግረው፣ " አይደለም አዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ መደረጉን ኮሚሽኑ ክትትል ሲያደርግ ነበር " ብለዋል፡፡

በዚህ የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ኮሚሽኑ የሚፈገውን ያህል የሰው ኃይል እንዳገኘና አመልካቾቹ በቀጣይ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ የሚገቡበት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘሪሁን፣ በአጠቃላይ ምን ያክል ሰዎች አመልክተው እንደነበር ስንጠይቃቸው ለጊዜው ዳታውን እንዳልያዙና መግለጹ አስፈላጊ እንዳልሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
1.13K😡168😭60🙏45💔37🤔21👏16😢14🥰12🕊12😱6