TIKVAH-ETHIOPIA
“ አራት አመት ለፍተው ተምረዋል፣ ከተማሩ በኋላ ለፈተና ተቀምጠዋል፣ ውጤታቸውን የማየት ሙሉ መብት አላቸው ” - የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኀበር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ቢቆዩም ሁሉም ተማሪዎች ውጤታቸውን ባለማየታቸው መፍትሄ እንዲሰጣቸው በሰፊው ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኀበርም፣ “የተወሰኑት…
#Update
" በመካከል የ12ኛ ክፍል ፈተና ስንጀምር ወደ አርካይቭ መቀየር ነበረብን ወደ አርካይቭ ስናስገባው ፕላትፎርሙ ተዘጋና ማየት አልቻሉም፤ እኛም ማየት አልቻልንም፤ በቅርብ ይለቀቃል " - ትምህርት ሚኒስቴር
የመውጫ ፈተና ውጤት " ሁሉም ተፈታኞች አላዩም " በሚል እየቀረበ ላለው ቅሬታ ሰሞኑን ምላሽ የጠየቅነው የግል ከፍተኛ ተቋማት ማኀበር ትምህርት ሚኒስቴርንና ክፍያ ያልከፈሉ ተቋማትን ተጠያቂ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ተማሪዎቹ ውጤታቸውን ማየት ያልቻሉት ምን ተፈጥሮ ነው ? ሲል ዛሬ የጠየቀው የትምህርት ሚኒስቴር፣ " ከ12ኛ ክፍል ፈተና በፊት ነው ውጤት የተቀቀው፤ ተቋሙም እንዲያይ ተማሪዎቹም እንዲያዩ አድርገናል " ብሏል።
" ነገር ግን መካከል ላይ የ12 ክፍል ፈተና ስንጀምር ወደ አርካይቭ መቀየር ስለነበረብን ወደ አርካይቭ ስናስገባው ፕላትፎርሙ ተዘጋና ማየት አልቻሉም ሰዎች፤ እኛም ማየት አልቻልንም ለጊዜው። በቅርብ ይለቀቃል፤ እየተነጋገርን ነው " ሲሉ አንድ የተቋሙ አመራር ተናግረዋል።
ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት እንደላኩ አስታውሰው፣ “" አንዳንድ ያላኩላቸውም ክፍያ ላይ የዘገዩ ተቋማት ስለነበሩ እነርሱም አላዩም እንለቀዋለን። ግን 'አላየንም' የሚለው የሚያስኬድ አይደለም ልጆችም ተቋማትም በጊዜ ገብተው ማየት ይችሉ ነበር፤ ያን ማድረግ ስላልቻሉ ነው አሁንም ይለቀቃል " ብለዋል።
ብዙዎች ተቋማት ክፍያ እያጠናቀቁ መሆኑን አስረድተው፣ " በተቀመጠላቸው ጊዜ የኤግዚት ተፈታኝ ስለማይከፍሉ ነው ብዙዎቹ የሚዘገይባቸው። ሁለት፣ ሦስት ተቋማት ናቸው አሁን የቀሩት። ከዛ ውጪ ያሉት ግን ፕላትፎርሙ አክቲቭ ሲሆን ማየት ይችላሉ፤ ያኔም ያላዩት ስለዘገዩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት አይደለም እንዴ ክፍያ መጠናቀቅ የነበረበት ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄም በምላሻቸው፣ ቅድሚያ መክፈል እንደነበረባቸው አምነው፣ " ግን አይከፍሉም። እኛ ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሳይሆን ከዛ በፊት ነው ደብዳቤ የሰጠናቸው፤ ግን ብዙ ከፍተኛ ተቋማት ፈተና ሳይቀመጡ ተማሪዎቹ ከፍለው እንዲጨርሱ ብናሳስባቸውም አያደርጉም " ነው ያሉት።
" እኛም ደግሞ ተማሪዎቹ ለፈተና ተዘጋጅተው ተቋሙ አልከፈለምና አትፈተኑም ማለት አልፈለግንም። ከተፈተኑ በኋላ ተቋማቱ ቢያንስ ከፍለው ውጤቱ እንዲያዩ ነው የምናደርገው፤ ተማሪዎቹም ማገድ አስቸጋሪ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
እንዲህ አይነት ኬዝ ያለበት ውጤትስ ታዲያ መቼ ይለቀቃል ? ለሚለው ጥያቄም '' የመንግስት የግል የሚባል ነገር የለም። አሁን ፕላትፎርሙ አይሰራም " ብለው፣ " ቢበዛ ነገ የሁሉም ይለቀቃል፤ ተነጋግረናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvqhEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

❤426😡33🤔18🕊11👏5😢4🙏4🥰3💔1