#ሐምሌ19
የፀጥታ ኃይሎች ዝግጅት ምን ይመስላል ?
(ሀዋሳ - ቅዱስ ገብርኤል)
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ጸጥታ እና ፖሊስ መምሪያ ከነገ በስቲያ ሐምሌ 19 የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓልን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የበዓሉን ታዳሚዎች ደህንነት ለማረጋገጥ አስተማማኝ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።
የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሠላም፣ በፍቅርና በመተሳሰብ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ እንዲከበር የህብረተሰቡ ሚና ወሳኝ መሆኑ ገልጿል።
በተለይም በከተማዋ በሚገኙ ሆቴሎች እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ጥብቅ ፍተሻ በማድረግ ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተጠቁሟል።
ሀዋሳ ከነገ በስቲያ በሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ንግስ በዓል እጅግ በጣም ከፍተኛ የሰው ቁጥር ታስተናግዳላቸው ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethiopia

👍483❤86🙏39🥰13👏12😢7
#ሐምሌ19
የፀጥታ ኃይሎች ዝግጅት ምን ይመስላል ?
(ቁልቢ ገብርኤል)
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ፤ በዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ላይ የሚታደሙ ምዕመናንን እና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አስተማማኝ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።
ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የምስራቅ እና የምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፣ የሐረሪ ክልል ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተቀናጅተው በቂ ዝግጅት አድርገዋል።
የንግስ በዓሉ ታዳሚዎች መጨናነቅ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ በተለይ የደብሩ መግቢያና መውጫ በሮች አካባቢ የኪስ ቦርሳቸውን ፣ ሞባይላቸውን እና ሌሎች ንብረቶቻቸውን በጥንቃቄ እንዲይዙ ፖሊስ አሳስቧል።
አሽከርካሪዎች ወደ ንግስ በዓሉ ሲመጡ #ከኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_መለያ ወይንም ከህጋዊው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በስተቀር ሌላ ለፖለቲካ ማራመጃ የሚሆን ዓርማና ምልክት ይዞ መገኘት እንደማይቻል አሳስቧል።
በንግስ በዓል ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ እና የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎች ሲያዙ ውሳኔ ለመስጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።
የበዓሉ ታዳሚዎች አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥማቸው በስልክ ቁጥር 0256665056 መጠቆም እንደሚችሉ ፖሊስ ገልጿል።
የአካባቢው የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ አክብረው በማሽከርከር ከአደጋ እንዲጠበቁ ተብሏል።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ ከባድ መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል።
#ENA

👍949❤111🙏59🥰39👏39😢22
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሐምሌ19
በየዓመቱ ሐምሌ19 የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግሥ በአል በደመቀና በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የምስራቅ ሐረረርጌ ዞን ፖሊስ ገልጿል።
በበዓለ ንግሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከአገር ውስጥና ከወጭ የመጡ ምዕመናን እና ሌሎች አንግዶች ታድመው ነበር።
በዘንድሮ ንግስ በዓል የስርቆት ወንጀል በፈፀመ ተጠርጣሪ ላይ በስፍራው የተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት የሁለት አመት እስራት መወሰኑን ፖሊስ ገልጿል።
ዘንድሮ የተፈፀመው ስርቆት ወንጀል ከባለፉት ዓመታት ከተፈፀሙ የወንጀል ድርጊት እጅግ ማነሱን የፖሊስ ሪፖርት አመልክቷል።
በመንገድ ትራፊክ በኩልም ምንም ዓይነት የትራፊክ አደጋ አልደረሰም።
በሌላ በኩል ፤ በሀዋሳ ሐምሌ19 የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በዓሉ ከወትሮው በተለየ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የተገኘበት ነው።
በበዓሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የመጡ ጎብኚዎች፣ ታላላቅ የሀይማኖት አባቶች እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ የክልልና የሐዋሳ ከተማ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተከበረው።
እንደ ፖሊስ ሪፖርት በዓሉ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሯል።
ከወንጀል ጋር በተያያዘ አንዲት የበዓሉ ታዳሚ ላይ የሞባይል ስርቆት የፈጸመ ተጠርጣሪ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በጊዜያዊነት በተቋቋመው ችሎት ማስረጃ ቀርቦበት የ2 ዓመት እስራት ቅጣት ተላልፎበታል። የተሰረቀውን ሞባይል ለግለሰቧ ማስመለስ መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።
Photo Credit : የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ENA

👍1.42K❤402🙏174👏84🥰64😢46
#ሐምሌ19 #ቁልቢ_ገብርኤል
እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የሚገኝበት ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።
ምዕመናን ከወዲሁ ለንግስ በዓሉ ወደ አካባቢው እየተጓዙ ሲሆን ነገም በስፋት ይጓዛሉ፤ ቁልቢና አካባቢው ገብተውም ያድራሉ።
ፖሊስ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል።
በአካባቢው ዳገት፣ ቁልቁለት እና ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚበዛና ወቅቱም ደግሞ ክረምት ስለሆነ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲሁም የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበር እንዲያሽከረክሩ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ በዓሉ ስፍራ ሲጓዙም ንብረቶቻቸውን በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው ተብሏል። #ENA

❤1.32K🙏159🕊44😡35🥰32😭16👏10🤔9😱1😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa #ማሳሰቢያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ። ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ቅዳሜ ይከበራል። በዓሉን አስታኮ ግን አንዳንድ አገልግሎት ሰጪዎች ከፍ ያለ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ እንደሆነ በግልጽ ታይተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያም " ጥቂት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዓሉን አስታከው በአንዳንድ…
#ሐምሌ19 #ቅዱስ_ገብርኤል
የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓለ ንግስ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ ጀምሮ በከተማይቱ የተወሰኑ መንገዶች ይዘጋሉ።
ሞተር ሳይክሎችና ባጃጆች ከዛሬ ጀምሮ በዓሉ ተከብሮ እስኪያልፍ ከምሽት 3 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድላቸውም።
በየዓመቱ ሐምሌ 19 በሀዋሳ በታላቅ ድምቀት ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ እጅግ በርካታ ምዕመናን ወደ ከተማው ገብተዋል። በነገው እለት እንዲሁም በዕለቱም በርካቶች ወደ ከተማዋ ይገባሉ።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በተለይም በዓሉ ከትራፊክ አደጋ ነጻ ሆኖ እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን ጠቁሟል።
ከሐምሌ 18/2017 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችንም እንዳሉ አመልክቷል።
ለተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ዝግ የሚሆኑት መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?
- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ ሎጊታ
- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ ዳሽን ባንክ ፒያሳ
- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ ማርሲል ቸርች
- ከቅዱስ ገብርኤል /ሱሙዳ/ እስከ ሳዉዝስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል
- ከታቦር መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ ኢንጆሪ ላውንጅ
- ከታቦር ትራፊክ መብራት እስከ ኬራውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል
- ከሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፊት ለፊት እስከ ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ ያሉ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች እንደሁልጊዜው ሁሉ በሀዋሳ ከተማ በሁሉም ክ/ከተሞች ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም አመልክቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ በዓሉ ተከብሮ እስኪያለፍ ማንኛዉም ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችና ባጃጆች ከምሽቱ 3 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይፈቀድላቸው የክልሉ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
እንግዶች ለክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መረጃና ጥቆማ ማድረስ ሲፈልጉ 8295 ነፃ የስልክ መስመር አልያም ለከተማ ፖሊስ 7614 መደወል ይችላሉ ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

❤2.65K🙏229😡77🕊71👏63🥰27🤔18💔17😭8😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሐምሌ19 #ቁልቢ_ገብርኤል እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የሚገኝበት ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል። ምዕመናን ከወዲሁ ለንግስ በዓሉ ወደ አካባቢው እየተጓዙ ሲሆን ነገም በስፋት ይጓዛሉ፤ ቁልቢና አካባቢው ገብተውም ያድራሉ። ፖሊስ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል። በአካባቢው…
ፎቶ፦ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ዛሬ ሐምሌ 19 እየተከበረ ባለው የዓመቱ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ቁልቢ ተገኝቷል።
#ቅዱስገብርኤል #ሐምሌ19
የፎቶ ባለቤት ፦ ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia
ዛሬ ሐምሌ 19 እየተከበረ ባለው የዓመቱ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ቁልቢ ተገኝቷል።
#ቅዱስገብርኤል #ሐምሌ19
የፎቶ ባለቤት ፦ ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia
18❤3.44K🙏346🕊74😡70🥰41👏31😭20🤔14😢14😱8
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ዛሬ ሐምሌ 19 እየተከበረ ባለው የዓመቱ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ቁልቢ ተገኝቷል። #ቅዱስገብርኤል #ሐምሌ19 የፎቶ ባለቤት ፦ ኤፍኤምሲ @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ተገኝቷል።
#ሐምሌ19 #ቅዱስ_ገብርኤል #ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
በዓሉ ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ተገኝቷል።
#ሐምሌ19 #ቅዱስ_ገብርኤል #ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
4❤3.65K🙏399🕊81😡70🥰42💔24😭24🤔19😢18😱6