TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

#ቁልቢ_ገብርኤል_ንግስ_በዓል

የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከነገ ታኅሣሥ 15/2013 ጀምሮ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ድረስ ባለው ዋናው መንገድ ላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች አቁሞ መሄድ እና መተላለፍ አይቻልም ተብሏል።

መልዕክት ለምእመናን ፦

ማንኛውም ዓይነት ወንጀል ሲፈጸም እንዲሁም ወድቆ የተገኘ ንብረትና ገንዘብ ሲገኝ ቁልቢ ገብርኤል ገዳም ለሚገኘው ጊዜያዊ የፖሊስ ጣቢያ በስልክ ቁጥር 0253390335 ደውለው ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብር እንድታደርጉ ከወዲሁ መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሐምሌ19 #ቁልቢ_ገብርኤል

እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የሚገኝበት ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

ምዕመናን ከወዲሁ ለንግስ በዓሉ ወደ አካባቢው እየተጓዙ ሲሆን ነገም በስፋት ይጓዛሉ፤ ቁልቢና አካባቢው ገብተውም ያድራሉ።

ፖሊስ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል።

በአካባቢው ዳገት፣ ቁልቁለት እና ጠመዝማዛ መንገድ ስለሚበዛና ወቅቱም ደግሞ ክረምት ስለሆነ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲሁም የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበር እንዲያሽከረክሩ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ በዓሉ ስፍራ ሲጓዙም ንብረቶቻቸውን በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው ተብሏል። #ENA

@tikvahethiopia
1.32K🙏159🕊44😡35🥰32😭16👏10🤔9😱1😢1