TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት አረሜናዊ ድርጊት የፈፀመው ተጠርጣሪ " እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም " ሲሉ የትግራይ እንዳስላሰ - ሽረ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። " አሲድ የተደፋባቸው ወገኖች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ይገኛሉ " ሲሉ አክለዋል። አሲድ የተደፋባቸው እንስቶቹ ለተሻለ ህክምና ከእንዳስላሰ - ሽረ ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ሪፈር መባላቸውን…
#Update
ተጠርጣሪው ተይዟል !
በእንዳስላሰ ሽረ በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ጉዳት እንዳደረሰ የተጠረጠረው ተጠርጣሪ ተያዘ።
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የእንዳስላሰ-ሸረ ከተማ ነዋሪ የሆነው ተጠርጣሪ ወላይ ተጠምቀ ሀምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በከተማው በሚገኘው መጠጥ ቤት በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ተጠርጥሮ በፓሊስ ሲፈለግ እንደነበር ተጠቁሟል።
የእንዳስላሰ-ሸረ ከተማ የፀጥታ ፅህፈት ቤት ዛሬ ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጠው መረጃ ፤ ተጠርጣሪው በፀለምቲ ወረዳ አዋሳኝ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ተላልፎ ተሰጥቷል።
በተደፋባቸው አሲድ ክፉኛ ከተጎዱት አንድዋ ፍረይ ተክለሃይማኖት የተባለች እንስት ለከፍተኛ ህክምና በመቐለ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል እንደምትገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

❤738👏230😭93😡55🙏40💔21🤔11😢11🕊11
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጥያቄና ፍላጎታችን በሀይል የፈረሰው አስተዳደራችን እንዲመለሰልን ነው " - ሰላማዊ ሰልፈኞች ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም ጊዚያዊ አስተዳደሩ በሰጠው አቅጣጫ በዞኑ አስተዳደር በአድማ በታኝ ፓሊስ ታጆቦ ይደረጋል የተባለው የስልጣን ሹምሽር በአከባቢው በተለይ በማይጨው ከተማ አለመረጋጋት አስከትለዋል። ከማይጨው ከተማ 195 ኪሎ ሜትር ተጉዘው መቐለ ድረስ የመጡ ተወካዮች ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል)…
#Update
ላለፋት 6 ቀናት ከስራ ገበታ ተስተጓጉለው የሰነበቱት የትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች መልሰው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።
የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዛሬ ሰኞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ-መቐለ በሰጠው መረጃ ዋና አስተዳደሪው አቶ ሃፍቱ ኪሮስ የሚገኙባቸው የስራ አመራሮች ዛሬ በይፋ ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዘዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከህዝብ ተወካዮችና ከዞኑ አመራሮች ተከታታይ ውይይት ሲያካሂዱ ቆይተው መጠነኛ መግባባትና መረጋጋት በመፍጠሩ ምክንያት ነው መንግስታዊ መስሪ ቤቶች ወደ አገልግሎት የተመለሱት።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዘዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የዞኑን ዋና አስተዳደሪ ከሀምሌ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት ማንሳታቸውን ተከትሎ ዞኑ አለመረጋጋት ውስጥ ነው የሰነበተው።
" አስተዳዳሪያችን ከኃላፊነት የተነሱበት አካሄድ ልክ አይደለም " ብለው ያመኑ የዞኑ ነዋሪዎች ወደ መቐለ ተጉዘው ከፕሬዜዳንቱ ከመወያየት በተጨማሪ የተለያዩ ሰላማዊ ተቋውሞዎች አካሂደዋል።
ትናንትና ዛሬ ሀምሌ 20 ና 21/2017 ዓ.ም የራያ ዓዘቦና የአምባላጀ ዓዲሽሁ ወረዳና ከተማ ነዋሪዎች የፕሬዜዳንቱን እርምጃ በመቃወም ሰልፍ ወጥተዋል።
ከሀምሌ 18 -20/2017 ዓ.ም በመቐለና በማይጨው ከፕሬዜዳንቱ ጋር የተካሄዱት ውይይቶች በፈጠሩት ተነፃፃሪ መረጋጋት የተቋረጠው አገልገሎት መልሶ መጀመሩንና ሀምሌ 27/2017 ዓ.ም የቀጠለ ውይይት በማይጨው እንደሚካሄድ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ-መቐለ ተናግሯል።

❤516🕊77👏32😡16🥰5😭5🤔3😢2💔2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" እኔ ስልጣን ላይ እያለሁ ዳግም ግጭትና ጦርነት አይኖርም " ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ተናገሩ።
" በትግራይ በኩል የሚጀመር ጦርነት አይኖርም ፤ እኔ በስልጣን እያለሁኝ የሚነሳ ጦርነት የለም ፤ ዳግም ጦርነትና ግጭት እንዳይቀሰቀስ አቅሜን አሟጥጬ እሰራለሁ " ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል።
ፕሬዜዳንቱ ይህን ያሉት ትንናት ሀምሌ 21/2017 ዓ.ም ወደ መቐለ ትግራይ ከገባዉ የሰላም ልኡክ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
" የትግራይ ህዝብ ጦርነት አይፈልግም " ሲሉ የተናገሩት ፕሬዜዳንቱ " በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮቻችን ወደ ቄያቸው ስላልተመለሱ
ጅምር ሰላሙ ሙሉ መሆን አልቻለም " ብለዋል።
" ሁሉም ልዩነቶች በጠረጴዛ ውይይት ዙሪያ ይፈታሉ " ያሉት የሰላም ልኡካኑ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ለሚደረገው ጥረት ሰላማዊ ድጋፋቸው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
በፌደራል መንግስትና በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር መካከል ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያግዝ የስምምነት ሰነድ በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት ማግኘቱ በውይይቱ የተገለፀ ሲሆን የስምምነት ሰነዱ ዝርዝር ይዘት አስመልክቶ የተባለ የለም።
የሰላም ልኡካኑ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በመጎብኘት የብር 30 ሚሊዮን ዋጋ ያለው እርዳታ ይለግሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

❤880🕊220👏55🤔43🙏39😡19🥰10💔10😭9😱6
TIKVAH-ETHIOPIA
#CustomsCommission " ትልቁ ስህተት የተፈጠረው የጉምሩክ ኮሚሽን 'በርቀትና ኤክስቴንሽን የተመረቃችሁ ተወዳዳሪዎች አትካተቱም' ማለቱ ነው " - ቅሬታ አቅራቢ አመልካቾች ➡️ " የማጣራት ሂደቶች መደረጋቸው አይቀርም። ማንኛውም የቅጥር ማስታወቂያ ሲወጣ ሁሉም የተመዘገበው ያልፋል ማለት አይደለም " - ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን ለሥራ ቅጥር ከ2,000 በላይ ሥራ ፈላጊዎችን ክልሎችና…
#Update
#CustomsCommission
" ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩትን አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉብትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል " - ጉምሩክ ኮሚሽን
የጉምሩክ ኮሚሽን ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ከ200ዐ በላይ ተወዳዳሪዎችን እንዲመለምሉ ለክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በሰጠው ኮታ መሰረት የተመለመሉ አመልካቾች ዝርዝር ከተላከለት በኋላ በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቅነውን " ኮሚሽኑ በቅጥሩ 'አትካተቱም' አለን " የሚል ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበው ነው።
ይህ ቅሬታ ያላቸው የተሰባሰቡት ብቻ ወደ 300 እንደሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ ለምን ይህን እንዳደረገ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጉምሩክ ኮሚሽን ጉዳዩን አጣርቶ ምላሽ ሊሰጥ ቀጠሮ ሰጥቶን ነበር፡፡
ኮሚሽኑ ለቀረበበት ቅሬታ ምን መለሰ ?
የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ዘሪሁን አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ " ኮሚሽኑ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የተማሩት አመልካቾች ብቻ ወደ ቀጣዩ የቅጥር ሂደት መግባት የሚችሉበትን ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል። በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው በዚህኛው ቅጥር የተጋበዙት " ብለዋል።
ማስታወቂያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ፣ በግል ኮሌጆች ተመርቀው ትምህርት ሚኒስቴር ያረጋገጠላቸው ምሩቃን መወዳዳር እደሚችሉ በሚገልጸው መሰረት ካመለከቱ በኋላ " አትካተቱም " እንደተባሉና አሰራሩ ልክ እንዳልሆነ ነው አመልካቾቹ የገለጹት፤ ለዚህ ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል አቶ ዘሪሁንን ጠይቀናቸዋል፡፡
እሳቸውም፣ " ማስታወቂያ ላይ ዝርዝር ጉዳዮች ላይጠቀሱ ይችላሉ " ብለው፣ " ሌሎችን ዲቴይል መስፈርቶችን ኮሚሽኑ በኋላ ላይ ማጣራት አድርጎ ሁሉም ተመሳሳይ አካባቢ በመደበኛና ኤክስቴሽን የተማሩትን፣ ሌሎችን ደግሞ በሌላ መስፈርት ሳይሆን ለሁሉም ወጥ የሆነ ውሳኔ ነው የወሰነው " ብለዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ማስታውቂያው ወጥቶ ተወዳዳሪዎች ካመለከቱ በኋላ ኮሚሽኑ ይህን መወሰኑ ለምንድን ነው ? የገጠማችሁ ችግር ምንድን ነው ? በኢ-መደበኛው መርሃ ግብር የተመረቁት በቅጥሩ የማይካተቱ ከሆነስ ለምን ቀድማችሁ አላሳወቃችሁም ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
አቶ ዘሪሁን፣ " ኮሚሽኑ በኋላ ላይ አጠቃለይ የምልመላ ሂደት ይህን ብቻ ሳይሆን ሌሎች የማጣራት ሂደቶችን አድርጎ ካሉ ዝርዝሮች ውስጥ እነዚህ ወደቀጣዩ ዙር የምልመላ ሂደት ይለፉ ብሎ የወሰነው ወደ ቀጣይ ዙርም የተገባበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን ነው ልገልጽ የምችለው " ሲሉ አስረድተዋል።
ፕሮግራሙ ቢለያይም በሀገሪቱ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ትምህርት ነው የሚሰጠው ስለዚህ መደበኛውን ብቻ ለይቶ ለመቅጠር ህጉ ይፈቅዳል ? ሁሉንም ምሩቃን ማካተት አልነበረባችሁም ? ለሚለው ጥያቄም፤ " ኮሚሽኑ ያስቀመጠው አሰራር ነው፡፡ መደበኛዎቹን ነው በዚህ የቅጥር ሂደት ውስጥ የማካትተው የሚል መስፈርት ወጥቶ ውሳኔ ተሰጥቶበት እየተሰራ ያለ ጉዳይ ነው " የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል፣ በክልሎች በኩል የነበረው የምልመላ ሂደት " በቢሮዎች ዘመድ ላላቸው ቅድሚያ እየተሰጠ ዘመድ የሌላቸው ከመንከራተታቸውም በላይ እድሉን እንዳላገኙ "፣ በአዲስ አበባ ያለው ምልመላም ኦፊሻል ወጥቶ እንዳልተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ያደረሱ እንዳሉ በመግለጽ፤ ለዚሁ ቅሬታ ጉምሩክ ኮሚሽንን ምላሽ ጠይቀናል፡፡
አቶ ዘሪሁን " ቅሬታዎች የሉም ማለት አይደለም፤ እኛ ጋርም የመጡ ቅሬታዎች ነበሩ፤ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻርም ይሁን በግለሰብ 'በዚህ ቀን ተመዝግበን፤ እኔ ማለፍ ሲገባኝ እከሌ/እከሊት ያላግባብ አልፋለች/ፏል' የሚል ቅሬታ አለ " ብለው፤ ፍትሃዊ እንዲሆን ጉዳዩን ወደ ክልል መልሶ ኮሚሽኑ ማጣራት እያደረገ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቅሬታ ያላቸው በክልል በኩል አጽፈው ቅሬታቸውን ቢያቀርቡ ኮሚሽኑ አጣርቶ ማስተካከያ የማያደርግበት ምክንያት እንደማይኖር፣ በዚሁ መሰረትም ምላሽ የተሰጣቸውና በሂደት ላይ ያሉም እንዳሉ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባውን ቅሬታ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ አመልካቾች ተመልምለው እንደተላኩላቸው ተናግረው፣ " አይደለም አዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ መደረጉን ኮሚሽኑ ክትትል ሲያደርግ ነበር " ብለዋል፡፡
በዚህ የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ኮሚሽኑ የሚፈገውን ያህል የሰው ኃይል እንዳገኘና አመልካቾቹ በቀጣይ ስልጠና ወስደው ወደ ስራ የሚገቡበት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘሪሁን፣ በአጠቃላይ ምን ያክል ሰዎች አመልክተው እንደነበር ስንጠይቃቸው ለጊዜው ዳታውን እንዳልያዙና መግለጹ አስፈላጊ እንዳልሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤1.17K😡172😭61🙏46💔37🤔21👏17😢14🕊13🥰12😱7
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia 🇪🇹 #GreenLegacy
የተተከሉ ችግኞች ቆጠራ የሚከናወነው እንዴት ነው ?
በማለዳ በተጀመረው በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ከእቅዱ በላይ መሳካቱን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።
የተተከሉ ችግኞች በሲስተሙ ተመዝግበው ይፋ ስለሚደረጉበት አካሄድ የብሔራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቴክኒክ ኮሚቴ የቴክኖሎጂ ባለሞያ አቶ ቴዎድሮስ ካሳሁን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ቴዎድሮስ ካሳሁን ምን አሉ ?
" የችግኝ መትከያ ቦታዎችን ክልሎች በራሳቸው እቅድ ለይተው አምጥተዋል።
ይህ መገኛው የሚታወቅ የመትከያ ቦታ ከቀደመው መረጃዎች ጋር ተገናዝቦ ማለትም አምና እና ካቻምና የተተከለበት ቦታ ስለመሆኑ እና ዘንድሮ ያልተተከለበት ቦታ መሆኑን ሲረጋገጥ ተመዝግቦ 13 ሺ 84 የመትከያ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል።
እነዚህ መረጃዎች ከተደራጁ በኋላ ለእያንዳንዱ ሳይት ቢያንስ አንድ ሪፖርተር ካልተቻለ ለሦስት የመትከያ ሳይቶች አንድ ሪፖርተር እንዲመደብ ተደርጓል።
ሪፖርተሮቹ በተመደቡበት ቦታ ለዚህ አላማ ተብሎ በተዘጋጀ በ 699 የመልእክት ቁጥር በቴክስት መልእክት እንለዋወጣለን።
የተመደቡት ሪፖርተሮች የስልክ ቁጥራቸው አስቀድሞ በኢትዮጵያ ቴሌኮም የተመዘገበ በመሆኑ የአጭር የመልእክት መቀበያ ቁጥሩ መልእክት የሚቀበለው ከተመዘገቡት ቁጥሮች ብቻ ነው።
አስቀድሞ ሪፖርተሩ የተመደበበት ሳይት ላይ መተከል የሚገባው የችግኝ መጠን የሚታወቅ በመሆኑ ከተሰጠው የችግኝ ቁጥር በላይ መላክ አይችልም።
ከዛ በታች ግን በቦታው የተመደበው ሪፖርተር የተተከሉ ችግኞች ቁጥር ሲልክ ሲስተሙ ይቀበላል የተሰጠው ቁጥር ሲሞላ ሲስተሙ ከዛ የስልክ ቁጥር የተተከሉ ችግኞችን ቁጥር መቀበል ያቆማል።
እስካሁን ባለው ጉዳይ ሲስተሙ ጤናማ ነው ምንም አይነት የኔትወርክ ችግር አላጋጠመም " ብለዋል።
#Update : በአጠቃላይ ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ 714.5 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን ፤ ይህም በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከትል ከታቀደው እቅድ በላይ ሆኗል።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤668😡385🤔93💔16😭13🕊9👏7🥰6😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
#MinistryofAgriculture : ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአቶ አዲሱ አረጋ ተተኩ። ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ አዲሱ አረጋን የግብርና ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል። ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከግብርና ሚኒስትርነት ተነስተዋል። ለምን ከቦታው እንደተነሱ፣ ለሌላ ኃላፊነት ተፈልገው እንደሆነ፣ ወይም ሌላ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው እንደሆነ ለጊዜው የሚታወቅ ነገር የለም። አዲሱ የግብርና ሚኒስትር አቶ…
#Update
የቀድሞው የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት (ጄኔቫ) የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ተሹመዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ግርማ አመንቴን (ዶ/ር) ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት ለመሾም ያሳለፉትን ውሳኔ በአድናቆት እንደምትመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ውሳኔው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች አፍሪካን በመወከል ለምትጫወተው ሚና ሕብረቱ ያለውን ትልቅ ግምት የሚያመላክት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
Via Ministry of Foreign Affairs

3❤1.03K👏195😡80🙏46🤔40🕊26💔26🥰21😭10😱7