TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.3K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኛ ኢትዮጵያ ሙስሊም፤ ክርስቲያኑ በፍቅር፣ በመተሳሰብ፣ በመከባበር የሚኖሩባት የሁሉም ዜጎች እኩል ሀገር ናት!!

#ኢትዮጵያ #ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር!

በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ!

በ2011ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት (10ኛ ክፍል) ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

 የመደበኛ፣የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 2.00 እና በላይ ለሴት 1.86 እና በላይ ሆኖ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በማታው ፕሮግራም ይቀጥላሉ።

 ለአካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው ለወንድ 1.86 እና በላይ ለሴት 1.71 እና በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ለወንድ 1.71 ለሴት 1.61 እንዲሆን ተወስኗል።

 ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች፣አርብቶ አደር አካባቢዎች እና የፀጥታ ችግር የታየባቸው አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 1.86 ለሴት 1.71 እንዲሆን መወሰኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ፦

 ሁሉም ወደ 11ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች የሚመርጡት የትምህርት መስክ በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታው በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በምርጫ ተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ ብቻ ይሆናል፡፡

 ከዚህ በፊት የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት 10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 2.00 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያመጡ በማታው ፕሮግራም የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን መቀጠል የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍2
የመደበኛ፣ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 2.00 እና በላይ ለሴት 1.86 እና በላይ ሆኖ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በማታው ፕሮግራም ይቀጥላሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለአካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው ለወንድ 1.86 እና በላይ ለሴት 1.71 እና በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ለወንድ 1.71 ለሴት 1.61 እንዲሆን ተወስኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች፣ አርብቶ አደር አካባቢዎች እና የፀጥታ ችግር የታየባቸው አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 1.86 ለሴት 1.71 እንዲሆን መወሰኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በዛሬው እለት በ2012 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ የትምህርት ዝግጅት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ነው👇
https://telegra.ph/ETH-09-20
#update የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅበላ መርሓ ግብር ይፋ ሆኗል። በዚህ መሰረት ነባር ተማሪዎች #እስከ መስከረም 25 ቀን ድረስ የሚገቡ ሲሆን፥ አዳዲስ ተማሪዎች ደግሞ ከመስከረም 25 እስከ መስከረም 29 ድረስ ምዝገባ ያከናውናሉ ተብሏል፡፡ ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት ይጀምራሉ፡፡ እንዲሁም በዘንድሮው ዓመት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ምደባ እስከ መስከረም 19 እንደሚጠናቀቅ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም አስታውቀዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2012 የተማሪዎች ምደባን በሚመለከት...

በዘንድሮው ዓመት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ምደባ እስከ መስከረም 19 እንደሚጠናቀቅ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም አስታውቀዋል፡

ተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን በTIKVAH-MAGAZINE መከታተል ትችላላችሁ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር ኤሊደአር እና በአማራ ክልል ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች 29 የክላሽንኮቭ ጠመንጃዎችና 3ሺህ 666 ጥይት ሲያጓጉዙ የተገኙ ግለሰቦች መያዛቸው ተገለጸ።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-20-3

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiop
የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚካሄደው ሩጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-20-2
#ኢሬቻ2012 ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶች፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወደ ቄራ
• ከአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ቡልጋሪያ ማዞሪያ
• ከሳርቤቶች አደባባይ ወደ ቄራ
• ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር
• ከቂርቆስ ወደ ገነት ሆቴል
• ከመስቀል ፍላወር ወደ አጎና ሲኒማ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው
• ከኡራኤል ወደ ጦርኃይሎች አደባባይ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ካዛንቺስ->አራት ኪሎ->ሸራተን አዲስ->ሃራም ቤሆቴል->ጎማ ቁጠባ
• ከፒያሳ ወደ ቦሌ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ሃራምቤ ሆቴል->ፍልውሃ->ካዛንቺስ->ኡራኤል->አትላ ስሆቴል->ቦሌ
• ከሳርቤት ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
መካኒሳ አቦ መታጠፊያ->መድሃኒት ፋብሪካ->ሦስት ቁጥር ማዞሪያ->ብስራተ- ገብርኤል አቅጣጫ->በካርል አደባባይ->ቴሌ->ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት
• ከፒያሳ ሳሪስ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ቸርችል ጎዳና->ጥቁር አንበሳ->ኦርማ ጋራዥ->በዘውዲቱ ሆስፒታል->በፍልውሃ->በኡራኤል
• እንዲሁም ከፒያሳ እስከ ብሄራዊ ቲያትር ያለውን መንገድ በአማራጭነት መጠቀም ይቻላል።

አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመሮች 991 ፣6727 ፣816 እና በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ011-1-01-02-97

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
#update የዓለም መንግስታት ለአየር ንብረት ለውጥ ድርጅት ስብሰባን መሰረት በማድረግ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ሰልፍ መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡

እየተስተዋለ ያለውን የዓለም የአየር ንብረት መዛባት ጉዳይ ጉዳዬ ያሉ የተለያዩ ሀገራት ተማሪዎች “ተለዋጭ ፕላኔት የለንም’’ በሚል ሃሳብ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡

በጎርፍ እየተጥለቀለቁ ያሉ የፓስፊክ ደሴቶች፣ ኒው ዚላንድ፣ የአውስትራሊያ፣ የባንኮክ እና የታይላንድ ሰልፈኞች የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስን ለማቃለል የዓለም መንግስታት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-20-4

Via አልጀዚራ/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ባልቻ ሬባ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለ ቴሌኮሙዩኒኬሽን በጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1148/2011 መሰረት፥ የቴሌኮም ዘርፉን በመቆጣጠር በዘርፉ ለሚሰማሩ የግል ተቋማት የውድድር ሜዳውን ምቹ ለማድረግ የተቋቋመ ነው። አቶ ባልቻ ሬባም ተቋሙን ከመስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተሾመዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚካኤል አፅብሃ ገብሩ⬆️ በአራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በተለምዶ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገደለው ሚካኤል አፅብሃ ገብሩ ካላይ በፎቶው የምትመለከቱት ነው። ከካናዳ/ቶሮንቶ/ ወደኢትዮጵያ የመጣውም በቅርቡ ነበር። አቶ ሚካኤል ከአመት በፊት በካናዳ ሀገር የሎተሪ እድለኛ ሆኖ እንደነበር ወዳጆቹ ገልፀዋል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
በአቶ #ሚካኤል_አፅብሃ_ገብሩ የግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተሰምቷል!

በአራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በተለምዶ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

መስከረም 3 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 6 ሰዓት ሲሆን በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፒያሳ ልዩ ቦታው መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአቶ ሚካኤል አጽበኻ ገብሩ ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራመ ሆኑን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ እንደገለፀው ብዛታቸው 3 የሆኑ ተጠርጣሪዎች በዕለቱ ሟች ሚካኤል አፅበኻ ከጓደኛቸው ጋር እየተዝናኑ ከቆዩ በኋላ ወደ ማደሪያቸው ለመሄድ ታክሲ እየጠበቁ በነበሩበት አጋጣሚ ንብረት ለመዝረፍ በማሰብ ጉዳት አድርሰውባቸው ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት እንደደረሰው ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር ቀንና ሌሊት ባደረገው ብርቱ ጥረት 48 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ሁለቱን በ05/01/2012 ዓ.ም ማምሻውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑንና ቀሪውን አንድ ተጠርጣሪ ለመያዝ ክትትሉ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ወንጀልፈፃሚዎቹ እንዲያዙ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋናውን በማቅረብ ወንጀልን የመከላከል ስራ ላይ የሚሰጠውን ድጋፍና ተሳትፎን አጠናክሮ አንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ አ/አ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
የአዲስ አበባና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በ2012 ዓ.ም ለሚቀበሏቸው አዲስ ተማሪዎች የቅድመ መግቢያ ፈተና ዛሬ መስጠት ጀመሩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አለም ከተማ የደረሰ የመኪና አደጋ ነው። በአደጋው ጉዳት የደረሰበት አሽከርካሪ ወደ አምቦ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል።

አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እያደረጋችሁ አሽከርክሩ!

Via Fire/TIKVAH-ETH - ከአምቦ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ደግሞ ከ10 ደቂቃ በፊት አዲስ አበባ እስጢፋኖስ ድልድይ ውስጥ የገባ አንበሳ አውቶብስ ነው። በአካባቢው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት አምቡላስ ወደአካባቢው እንዲመጣ ጠይቀዋል። በአደጋው የተጎዱ ሰዎች እንዳሉም ነግረውናል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል!
ፎቶ:TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
በአሁን ሰዓት እስጢፋኖስ አካባቢ በርካታ አምቡላንሶች እንዲሁም የፖሊስ አባላት እንደሚገኙ ቤተሰቦቻችን ገልፀውልናል። ከመስቀል አደባባይ ወደ 4 ኪሎ የሚወስደው መንገድ ለጊዜው ተዘግቷል።

ፎቶ: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍2
ይህ ባነር የተለጠፈው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ ነው

"የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ እንኳን ደህና መጡ! ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እያበረከቱት ላለው ጉልህ አስተዋፆ #እናመሰግናለን!" ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

Via AB/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአ/አ እስጢፋኖስ አከባቢ...

"አሁን አንበሳ አውቶብስ #የተገለበጠበት ቦታ እገኛለሁ አደጋው በጣም አስከፊ ይመስላል። እስካሁን ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጫለሁ። ሌሎች የተጎዱ ሰዎች ደግሞ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ተወስደዋል።" D/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia