TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.3K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሆሳዕና⬆️

"ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ፍቅር ከተማ ወደሆነችው ሆሳዕና ይመጠሉ። አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።"

Via Elias/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GRAPHIC_CONTENT ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ኢትዮጵያዊ ዜጋ በፖሊሶች የተያዘበት መንገድ በርካቶችን አስቆጥቷል፤ በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ እየተቀባበሉት ነው፤ በርካቶችም ድርጊቱን አውግዘዋል።

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ ተጠይቆ ይህን ምላሽ ሰጥቷል፦

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር #ታዬ_ግርማ  ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ችግር እንደተፈጠረ ተደርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ስላለው ምስል በኮሚሽኑ በኩል በትክክል አለመረጋገጡን ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈ ግን ችግሩ በማን እና እንዴት እንደተፈጠረ #እያጣራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት። የክልሉ ፖሊስ ለኦሮሞ ህዝብ አለኝታውና መከታው ሆኖ በርካታ ችግሮችን እየተጋፈጠ ሲታገል የቆየና አሁንም በዚያው ቁርጠኝነት እያገለገለ እንዳለም አስረድተዋል፡፡ ድርጊቱ የክልሉን ፖሊስ ስም ለማጥፋት የተፈጸመ በመሆኑ የፖሊስ ኮሚሽንም ይሁን ሌላ አካል ጉዳዩን በፈጸሙ አካላት ላይ #እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል። በምስሉ ላይ የሚታዩ ግለሰቦችንም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን የደንብ ልብስ ከመልበሳቸው ውጭ ማንነታቸውን ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

ከህጋዊ የንግድ ሥርዓት ውጪ በህገ ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ በ52 አይሱዙ ተሽከርካሪ የተጫነ እህል እና ጥራጥሬ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም በአ/ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ አካባቢ ከእህል በረንዳ ውጪ ያለአግባብ የቆሙ 52 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገው ቁጥጥር የተለያዩ እህል እና ጥራጥሬዎችን በደላሎች ጣልቃ ገብነት ለመሸጥ የተዘጋጁ መሆናቸው መረጋገጡን የክ/ከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት አስታወቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ዋሽንግቶን_ዲሲ

ትላንት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን #ምዕመናን ፣ ዋሺንግተ ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት ተገኝተው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወቃል። በሰልፉ ላይ የተገኙት ሰዎች በቤተክርስቲያኗ እና በምዕመናን ላይ ደረሰ ያሉትን በደል አሰምተዋል፡፡ መንግስት አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል፡፡

ከሰልፉ በኃላ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸውን ይህን ፅፈው አሰራስችተዋል፦

"በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አማኞች ማህበራት አስተባባሪነት ሰላማዊ የሆነ ሰልፍ ተካሄደ፡፡ ከአስተባባሪዎቹም ጋር በኤንባሲው አዳራሽ ውይይት አድርገናል፡፡ ለመንግስት ጥያቄዎችን በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ በአገራችን በቤተ-ክርስቲያን ዙሪያ የሚታየው ጥቃት እንዲቆም፣ አጥፊዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ተማጽነዋል፡፡ ጥያቄዎቹንም ለመንግስት እንደምናደርስ ቃል-የገባን ሲሆን፣ ላሳዩት ሥነ-ሥርዓት የተሞለበት ሰልፍ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡"

ቪድዮ📹VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢሬቻ በዓል ከግል ፍላጎታችን በላይ ነው!" አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኢሬቻ በዓልን ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በጋራ ማክበር ለኦሮሞ ህዝብ ክብር እና ድል ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ በዛሬው እለት የ2012 የኢሬቻ በዓል ዝግጅትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-20-5

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መስከረም 21 በሚከበረው ግሸን ደብረ ከርቤ ንግስ በዓል ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ቅደመ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019

የኢሬቻ በዓል #በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ታዬ ግርማ ኮሚሽኑ በቅርቡ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል እና ከዚያ በፊት ለሚከበሩት ፌስቲቫሎች ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

#ኢሬቻ2012
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሰዓታት በፊት ቅዱስ እስጢፋኖስ አካባቢ በደረሰው የመኪና መገልበጥ አደጋ 41 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንበሳ አውቶብሱ ከሽሮ ሜዳ ወደ ስቴዲየም ይጓዝ ነበር። አደጋው የደረሰበትን አውቶብስ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው።

Via ዋልታ ቴሌቪዥን
ፎቶ: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሙገር ከተማ 1 የፖሊስ አባል ሲገደል ሌላ 1 ሰው ቆስሏል!

በትላንትናው ዕለት ምሽት አንድ ሰዓት ገደማ በሙገር ከተማ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ሳጅን አለማየሁ የተባሉ የፖሊስ አባል ሲገደሉ ሌላ አንድ ሰው ቆስሏል። ግድያውን የፈፀመው አካል ማን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። ለTIKVAH-ETH ጉዳዩን ያስረዱት የከተማው ፖሊስ አባል በማህበራዊ ሚዲያ ቦምብ ተወርውሮ ነው ሰው የተገደለው እየተባለ የሚወራው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba "ማምሻውን ከፈረንሳይ ሌጋሲዮን የተነሳው የአንበሳ አውቶቢስ በደረሰበት አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው ድልድይ ውስጥ በገባው አውቶብስ ለተጎዱት አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገለቸው ይገኛል። በአደጋው እስከአሁን የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በአደጋው ለተጎዱ ሁሉ የተሰማውን ልባዊ ሃዘን ይገልፃል፡፡"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውቶብሱ የተገለበጠው የሰሌዳ ቁጥሩ ይፋ ያልተደረገ ኮድ 3 አ/አ መኪና ለመሸሽ ሲሞክር ነው!

እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ጀርባ በሚገኝው ድልድይ ውስጥ የመውደቅ አደጋ የገጠመው የከተማ አውቶብሱ ምክንያት ለጊዜው የሰሌዳ ቁጥር ይፋ ያልተደረገ ኮድ 3 አ.አ መኪና ለመሸሽ ሲል እንደሆነ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች የኮምንኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለሽገር ራድዮ አስረድተዋል።

አውቶብሱ የተለመደ የመስመር ቁጥር ያልተሰጠው አዲስ ስምሪት እንደሆነም ታውቋል። መነሻውንም ከሽሮሜዳ አድርጎ ወደ ካዛንችስ እየሄደ እንደነበርም ነው ባለሙያው የተናገሩት። አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- አ/አ 68377 እንደሆነ ታውቋል። በዚሁ አደጋም 31 ሰዎች ብርቱ ጉዳት እንደገጠማቸው ተሰምቷል።

ካሰቡበት ለመድረስ #በአውቶብሱ ተሳፍረው አደጋው ያገኛቸው ኢትዮጵያውያንም ወደ ጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ እና አቤት ሆስፒታል መወሰዳቸውን ባለሙያው ተናግረዋል። በደረሰው አደጋ እስካሁን የ2 ሰው ህይወት አልፏል ተብሏል። የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር ይችላል ያሉት የኮምንኬሽን ባለሙያው ናቸው።

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህሌን እጠብቃለሁ ስለ ያሆዴ እሮጣለው!

የያሆዴ ክብረ በዓል ፌስቲቫልን ምክንያት በማድረግ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ በሆሳዕና ከተማ እና በሁሉም ወረዳዎች ባህሌን እጠብቃለሁ ስለ ያሆዴ እሮጣለው በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ዙር መስከረም 11/2012 ዓ/ም በሆሳዕና ከተማ እንደሚደረግ የሀዲያ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሲሳይ እውነቱ ገልፀዋል። ሁሉም ሰው ቲሸርቱን በመግዛት ኢትዮጵያዊነቱን በሚያንፀባርቅ መልኩ የሀዲያን ባህል ለሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ለማስተዋወቅ ስለ ያሆዴ እንዲሮጥ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ Hossana Sport ሆሳዕና ስፖርት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
912 ሺህ 292 ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል!

በ2011 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ወደ ቀጣይ ክፍል የተዘዋወሩት 912 ሺህ 292 ተማሪዎች ሲሆኑ ከተዘዋወሩት ተማሪዎች መካከል 750 ሺ 174 ወንዶች ናቸው፤ 162 ሺ 118 ተማሪዎች ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል። በአጠቃላይ ወደ 11ኛ ክፍል ከተዘዋወሩ ተማሪዎች መካከል የሴቶች ድርሻ 17.77 በመቶ መሆኑን ከአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የባለፈው አመት የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 2.71 እና ለሴቶች 2.57 እንደበር ይታወሳል፡፡ በግል ለተፈተኑት ወንዶች 3.43 እና ለሴቶች 3.14 የማለፊያ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኤጀንሲው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በሀዋሳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ውይይት ተካሄደ!

#VOA
#update የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ዙሪያ ከቤተክርስቲያንቷ ጋር በሃዋሳ ከተማ መከሩ። ቤተክርስቲያኒቷ በክልሉ በተቃጠሉና ጥቃት በደረሰባቸው ቤተ ዕምነት ካሳ እንዲከፈላቸው የክልሉን መንግሥት ጠይቀዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የተቃጠሉ በእምነት፣ ጥቃት የደረሰባቸው ካህናትና ምዕመን መጠንና የጉዳቱ መጠን በጥናት እንዲቀርብና መንግሥትም ጥናቱን ተከትሎ ምላሽ እንደሚስጥ ተናግረዋል።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert ዱከም ቀስተ ዳመና ስፖንጅ ፋብሪካ ላይ የእሳት አደጋ መድረሱን በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል።

Via KOZAK/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ALERT ዱከም በሚገኘው የስፖንጅ ፋብሪካ የእሳት አደጋ ተፈጥሯል። የሚመለከታቹ አካላት እሳቱ ሳይሰፋ ትቆጣጠሩት ዘንድ ቤተሰቦቻችን ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Via KOZAK/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ዱከም አካባቢ የተነሳውን የእሳት አደጋ የሚያሳዩ ተጨማሪ ፎቶዎችን ቤተሰቦቻችን እየላኩ ይገኛሉ። ሁኔታውን እየተከታተልን እናጋራችኃለን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዱከም በሚገኝ የስፖንጅ ፋብሪካ የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር መቻሉን በቦታው የሚገኙ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት አሳውቀውናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ፎቶ📸ኢትዮ ቴሌኮም ከ4500 በላይ ሰራተኞችን በዛሬው ዕለት በጊዮን ሆቴል የምሳ ግብዣ ያደርግላቸዋል። #AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia