"...የጥላቻ ሀሳብ ንግግር መሆን የሚጀምረው በተለያዩ ሚዲያዎች #መሰራጨት ሲጀምር ነው። ንግግሩ ቀስ እያለ #ወደመጠፋፋት ደረጃ የመራል። የቃላት ጉልበት የሚገለጠውም እዚህ ደረጃ ላይ ነው። ቃላት እንደሚያድኑት፤ እንደሚያፅናኑት ሁሉ ቃላት ለማጥፋትም ስሜትን መቀስቀስ ይችላሉ። ስለዚህ በእኔ እሳቤ መዋጋትና ማስቆም ካለብን የጥላቻን ሀሳብ ነው፤ የጥላቻ ንግግር ተብሰልስሎ ወደ ውጪ የወጣ የጥላቻ ሀሳብ መገለጫ ነው።" ዶክተር ፀደይ ወንድሙ /በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH መድረክ ላይ የተናገሩት/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዛሬ በተካሄደ የህገ-ወጥ ንግድ ድንገተኛ አሰሳ በ26 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ የነበረ የአትክልትና ኢንዱስትሪ ምርት መያዙን የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስታወቀ። በግብረኃይል የተወሰደው የኦፕሬሽን ስራ ያለደረሰኝ ግብይት በሚፈፅሙ፣ያለንግድ ፍቃድ የሚነግዱ፣ ከአድራሻና መደብር ውጪ በሚነግዱ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላቸው የዋጋ ጭማሪባደረጉ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑም ተገልጿል።

«ግብፆች የኅዳሴ ግድብ በየአመቱ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሐ የመልቀቅ ስምምነት እንዲደረስ ይፈልጋሉ። ይኸ ደግሞ ተገቢ አይሆንም። ያንን ያህል ውሐ ወደ ታች የማስተላለፍ ግዴታ ልንስማማ አንችልም» የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር #ስለሺ_በቀለ
Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
"የሀዋሳ ከተማ ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ ደርሷል!" የሆቴል ባለሀብቶችና ስራ አስኪያጆች
.
.
የሀዋሳ ከተማ #ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ በመድረሱ ተጠቃሚነታቸው እየጨመረ መምጣቱን በሀዋሳ የሆቴል ባለሀብቶችና ስራ አስኪያጆች ገለፁ።
በቱሪስት አገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ #ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ የሆቴል ባለሀብቶችና ስራ አስኪያጆች ጋር በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በመሩት በዚህ መድረክ የተሳተፉት የሆቴል ባለሀብቶች እና ስራ አስኪያጆች ቀድሞ የነበረውን የከተማዋን ሰላም ጠብቆ የማቆየት እና አስተማማኝ ደረጃ የማድረስ ኃላፊነት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለቱሪዝም ዘርፉ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በጋራ ለመፍታት እንሰራለን ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች የከተማዋ ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ ተጠቃሚነታችን ተረጋግጧልም ብለዋል፡፡
አቶ ጥራቱ በየነ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ በበኩላቸው አስተዳደሩ ሰላምን በማረጋገጥ እና ሁሉን አቀፍ ለውጥ በማምጣት የከተማዋን የቱሪስት መስህብነት ከምንጊዜውም በላይ እውን ለማድረግ እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡
Via Hawassa City Administration Public Relation Office

#GrandEthiopianRenaissanceDam
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ግንባታን በተመለከተ አንዳንድ የውጪ ሚዲያዎች የተዛባ መረጃ እያቀረቡ መሆናቸውን የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ እነዚህ ሚዲያዎች ግድቡን በተመለከተ ያለበቂ መረጃ የሚሰሯቸው ዘገባዎች ህብረተሰቡን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዝ የሚያደርጉ እንደሆነም በመግለጫው ተጠቁሟል።
የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተን ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ አንዳንድ የውጪ ሚዲያዎች ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ እያሰራጩ ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዳይኖረው ማድረጋቸው ሃላፊነት የጎደለው አሰራር ነው።
በተለይ በአንዳንድ የግብፅ ሚዲያዎች ላይ የሚተላለፉ ዘገባዎች የተዛቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ኢንጅነሩ አሁን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ሚዲያዎችን በማስተባበር ታላቁን የህዳሴ ኃይል ማመንጫ ግድብን ቦታ ድረስ ተገኝተው እውነታውን እንዲረዱ ለማድረግ የመስክ ምልከታ ፕሮግራም ያዘጋጃል ብለዋል። እንደሚኒስትሩ ገለጻ የመስክ ምልከታ ፕሮግራሙ ዋንኛ ዓላማ ጋዜጠኞች እውነታ ላይ ተመስርተው መረጃን ለህዝብ ማድረስ እንዲችሉ ለማድረግ በመሆኑ ሁሉም ሚዲያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ።
Via ኢፕድ

😱1
በTIKVAH-ETHIOPIA|ተስፋ ኢትዮጵያ| ስር የሚገኙ ሌሎች ትክክለኛ ቻናሎች እኚህ #ብቻ ናቸው፦
•ለዓመታት የቆየው የቤተሰባችን የመተጋገዣ መድረካችን-- የታመሙትን የምናግዝበት፤ ጠያቂ ያጡትንም የምንጠይቅበት TIKVAH-AID https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFL4FSDwsNhb0sVn3Q
•በዋናው ቻናል ብዙም የማይዳሰሱ የቱሪዝም፣ የባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች፣ የተማሪዎች፣ የወላጆች፣ የመምህራን ጉዳዮች የሚዳሰስበት TIKVAH-MAGAZINE https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
•ስፖርታዊ ጉዳዮች TIKVAH-SPORT https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
•ይህ ደግሞ የቤተሰባችን አባላት የአፋን ኦሮሞ የመረጃ መለዋወጫ ቻናላችን ነው TIKVAH-AFAAN OROMOO https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFEzH7Ywz6n7V8mzcQ
•ይህ የቋንቋ መማማሪያ ቻናላችን ብዙ ለመስራት የታቀደበት ነገር ግን ከሁኔታዎች አለመመቻቸት ጋር እንደታሰበው ያልተገለገልንበት ቻናላችን ነው። በቅርቡ ግን የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንዲሳተፉበት በማድረግ የቆሙት የትግርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ የግዕዝ ትምህርቶች እንዲቀጥሉ ለማድረግ ይሰራል። ተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎችን ለማስተማር መምህራኖችን ካገኘን ተጨማሪ ትምህርቶች ይካተቱበታል TIKVAH-EDUCATION -- https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEWA_-Jt2zIM5COJqw
#ማሳሰቢያ፦ ከላይ ከተገለፁት ውጭ TIKVAH-ETH ሌላ ምንም ቻናል የለውም፤ በተጨማሪ TIKVAH-ETH ፌስቡክ ላይ ምንም ገፅ የለውም።

😢1
#update የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄነራል ሀማድ መሃመድ ታኒ አል ራቱኒ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ነው የተነገረው። ሌተናል ጄነራል ሀማድ መሃመድ ታኒ አል ራቱኒ የተመራ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ወታደራዊ ልኡክ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የጉብኝቱ ዋነኛ አላማም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊ ትብብር በምን ደረጃ ላይ አንደሚገኝ ለመገምገም እና በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ውይይቶችን ለማድረግ እንደሆነም ተነግሯል።
Via #FBC

አሳዛኝ ዜና!
በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አንድ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ተገልብጦ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ20 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድርሱን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ሳጂን አዳነ አሰፋ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ በወረዳው ዋሙራ በሚትባል የገጠር ቀበሌ አካባቢ ተገልብጦ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ ነው።
የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 4147 ደ.ህ የሆነው ይህ አውቶብስ ከአረካ ወደ ማዞሪያ 29 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ከሟቾቹ በተጨማሪ ሶስቱ ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው አሽከርካሪውን ጨምሮ ሌሎች 17ቱ ደግሞ ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።
ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ በደረሰው በዚህ አደጋ የቆሰሉ መንገደኞች በዱቦ ማሪያም ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ገልጸው የሟቾቹ አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱን ተናግረዋል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የገለጹት ሳጅን አዳነ አካባቢው ቁልቁለታማ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የመንገድ አጠቃቀም ስርዓትን አክብረው በጥንቃቄ ሊጓዙ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
ፎቶ: መአዛ/TIKVAH-ETH/

#update መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ያደረገው ‹‹ተስፋ አይ ኤል ጂ›› የተሰኘ ድርጅት በስዊዘርላንድ ‹‹ስታንዳርድ›› የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል በኢትዮጵያ የመገንባት እቅድ እንዳለው ይፋ አደረገ፡፡ ‹‹ተስፋ አይ ኤል ጂ›› በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ጀማሪዎችን በተለያየ መልክ ለመደገፍ የሚያችለውን ስምምነት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል፡፡ ድርጅቱ በስዊዘርላንድ የቴክኖሎጂ ጀማሪዎችን የቴክኖሎጂ ሃሳቦቻቸውን ከመነሻ ጀምሮ ወደ ገበያ እስኪገቡ ድረስ የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርግ ነው፡፡
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RIDE
"የምንሠራው በቴክኖሎጂ ዘርፍ ፍቃድ አውጥተን ነው። ፍቃድ እያለን ተጨማሪ ፍቃድ ማውጣት ለምን አስፈለገ?" የራይድ ሥራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ
የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ስምሪትን በተመለከተ ያወጣው መመሪያ እንደ ራይድ ካሉ በቴክኖሎጂ ታግዘው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ቅሬታ አስነስቷል።
በመመሪያው ከተካተቱ ነጥቦች አንዱ የሆነውና ሰሌዳቸው ኮድ 3 የሆኑ ተሽከርካሪዎች የኪራይ አገልግሎት ፍቃድ ካላወጡ በስተቀር የመጓጓዣ አገልግሎት መስጠት አይችሉም የሚለው የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
በመመሪያው፤ በዘርፉ የታክሲ አገልግሎት ለመስጠት የሚሰማሩ አሽከርካሪዎች ሰሌዳቸውን ወደ ኮድ 1 እንዲቀይሩ እንዲሁም መኪናቸውን ቀለም እንዲቀቡ ተወስኗል። በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በድርጅት መታቀፍ አለባቸው ተብሏል።
Via BBC
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-19

❤1
ሚካኤል አፅብሃ ገብሩ⬆️
በአራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በተለምዶ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገደለው ሚካኤል አፅብሃ ገብሩ ካላይ በፎቶው የምትመለከቱት ነው። ከካናዳ/ቶሮንቶ/ ወደኢትዮጵያ የመጣውም በቅርቡ ነበር። አቶ ሚካኤል ከአመት በፊት በካናዳ ሀገር የሎተሪ እድለኛ ሆኖ እንደነበር ወዳጆቹ ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በተለምዶ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገደለው ሚካኤል አፅብሃ ገብሩ ካላይ በፎቶው የምትመለከቱት ነው። ከካናዳ/ቶሮንቶ/ ወደኢትዮጵያ የመጣውም በቅርቡ ነበር። አቶ ሚካኤል ከአመት በፊት በካናዳ ሀገር የሎተሪ እድለኛ ሆኖ እንደነበር ወዳጆቹ ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
❤1
#update ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እየተካሄዱ ያሉት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትና የኢዩቤልዩ ቤተመንግስት እድሳት ዙሪያ ዛሬ መስከረም 8 ቀን 2012 ጠዋት ከፈረንሳዩ የባህል ሚንስትር ፍራንክ ራይስተር ጋር ተገናኝተው ተወያዩ።
የኢትዮጵያና የፈረንሳይን ጠንካራ ግንኙነትና የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ጥልቅ የትብብር ፍቃደኝነት ያነሱት ጠ/ሚር ዐቢይ እድሳቱን ማፋጠን እንዲቻል አበረታትተዋል። ራይስተር በበኩላቸው የዛሬው ጉብኝታቸውፕሬዝዳንት ማክሮን ለሁለቱም ሀገራት የሚበጅ የቅርስ ጥበቃ ላይ ለመተባበር ያላቸውን ፍቃደኝነት ማሳያ ነው በማለት የቴክኒክና የልምድ ልውውጥም ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢዩቤልዩ ቤተመንግስትን እድሳት በተመለከተ አስፈላጊው ጥናት እየተጠናቀቀ ሲሆን እድሳቱ በጥቂት ወራት ውስጥ ተጀምሮ በፍጥነት ለቱሪስት ጉብኝት የሚከፈት ይሆናል።
Via #PMOEthiopia

የታቆረ ውሃ ውስጥ የሰጠመው ግለሰብ አክስሬን ከ22 ሰዓታት በኋላ ተገኘ!
በአያት ሪል ስቴት የግንባታ ሳይት ላይ በሚገኝ የታቆረ ውሃ ውስጥ የሰጠመው ግለሰብ አክስሬን ከ22 ሰዓታት በኋላ ተገኘ፡፡ አደጋው የተፈጠረው መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም ሰባት ሰዓት ላይ ነበር፡፡
አደጋው የደረሰበት የጉልበት ሠራተኛ ሲሆን ህይወቱ ሊያልፍ የቻለውም ለመዋኘት በገባበት ወቅት መሆኑን የአይን እማኞች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ የጉልበት ሠራተኛው ህይወቱ ያለፈበት የታቆረ ውሃ ሲሆን ከ1 ሺ ካሬ ሜትር በላይ ስፋት እና ከ3-8 ሜትር የሚደርስ ጥልቀት አለው፡፡
በጊዜው ህይወቱ ካለፈው ግለሰብ ጋር አብሮ ወደታቆረው ውሃ ለመዋኘት የገባው ግለሰብ እንደ ነገረን ከሆነ የእሱም ህይወት ሊተርፍ የቻለው ሌሎች ሠራተኞች ረዥም እንጨት ልከውለት እንደሆነ ገልጿል፡፡ አስክሬኑን ለማውጣት ሁለት ዋናተኞች በትላንትናው እለት ከቀኑ ከ9-12 ሰዓት ፍለጋ ቢያደርጉም አስክሬኑን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 5 ሰዓት አስክሬኑ ሊገኝ ችለዋል፡፡
ምንጭ፦ አሃዱ ሬድዮ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንደራሴ የሁሉም 12 ክፍል ተማሪዎች የምረቃ እና የመዝናኛ ዝግጅት እሁድ መስከረም 11 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ!
መግቢያ በነፃ!
የበዓሉ ተሳታፊ ተማሪዎች የመግቢያ ካርዶችን ከየትምህርት ቤታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግቢያ በነፃ!
የበዓሉ ተሳታፊ ተማሪዎች የመግቢያ ካርዶችን ከየትምህርት ቤታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1st GADAA FESTIVAL
የመጀመሪያው የገዳ ፌስቲቫል ከፊታችን መስከረም 20 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቶ ሆራ ሀርሰዴ የሚከበሩ የኢሬቻ በዓላት መስከረም 24 እና 25 2012 እንደሚበሩ ይታወቃል።
የመጀመሪያው የገዳ ፌስቲቫል እና ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ የዚሁ በዓል አካል መሆናቸው ተገልጿል። በዚሁ መሰረት መጀመሪያው የገዳ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማእከል እንደሚካሄድ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስተባባሪነት የሚዘጋጀው የገዳ ፌስቲቫል ከፊታችን መስከረም 20 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 2012 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳልም ተብሏል።
በፌስቲቫሉ ላይ በኢሬቻ በዓል እንዲሁም የገዳ ስርዓት በአንድነት፣ በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ዝርፍ ያለው ፋይዳ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል። እንዲሁም የሙዚቃ ኮንሰርት እና የኦሮሞ ባህል አውደ ርዕዮችም የፌስቲቫሉ አካል እንደሆኑም ነው አዘጋጅ ኮሚቴው በመግለጫው ያስታወቀው።
ታላቁ የኢሬቻ ሩጫም የፊታችን መስከረም 11 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ እና በሩጫው ላይም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚካፈሉ ይጠበቃል መባሉ ይታወሳል።

❤2
#update በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በቦልቪያናዊዉ ናማኒ ቺንቼ ኢቬሊን የፓስፖርት ቁጥር AE57255 ከብራዚል ሳዖ ፖሎ አዲስ አበባ የገባዉ 8 ኪሎ ግራም የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ የጉምሩክ ፈታሾች በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡
ዕፁን ይዞት ይጓዝ በነበረዉ ግለሰብ ላይ ከብራዚል ሳኦ ፖሎ ጀምሮ በጉምሩክ ኮሚሽን ኢንተለጀንስ ቡድን ባደረገዉ የተቀናጀና ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊዉል መቻሉ ተገልጿል፡፡
ይህንን አድካሚና የተቀናጀ ስራ በመስራት እፁን መያዝ ለቻሉ የቦሌ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራር አካላትና ሰራተኞች የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል፡፡ ባለፈዉ ሳምንትም 20 ሚሊየን ብር የሚገመት 10.8 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ መያዙ የሚታወስ ነዉ፡፡
Via #ethiofm

የከፍተኛ ትምህት ተማሪዎች የመጓጓዣ ችግር እንዳይገጥማቸው ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ!
ተማሪዎች በጉዞ ወቅት መጨናነቅና እንግልት ካጋጠማቸው መናኸሪያ ውስጥ ላለ የትራንስፖርት ቡድን መሪ ማሳወቅ እንዳለባቸው ተነገረ፡፡
ከሰሞኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ለመጀመር ተማሪዎቻቸውን ጠርተዋል፡፡ በአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ስምሪት ተወካይ ዳይሬክተር ጌታቸው መርሻ ወቅቱ የበዓል ጊዜ በመሆኑ እና የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ንግሥ የሚከበረው በዚህ ወቅት በመሆኑ የትራንስፖርት እጥረትና መጨናነቅ ሊኖር እንደሚችል ጠቅሰው ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል መፍትሔ እንደተቀመጠ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-19-2

5ሺ ዶላር የሚየሸልም ውድድር ይፋ ተደረገ!
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 5ሺ የአሜሪካን ዶላር የሚያሸልም ውድድር ይፋ አደረገ። ሚኒስቴሩ ከአይቢኤ ኢትዮጲያ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22ቀን 2012 ድረስ በአዲስ አበባ አካሂዳለሁ ብሏል፡፡
ስለሆነም ችግር ፈቺ፤ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላችሁ በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችሁን ወክላችሁ እንድትወዳደሩና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፤ ለቬንቸር ካፒታል ተቋማት እና ለሌሎች የፋይናስ ምንጮች በማስተዋወቅ ወደ ምርትና አገልግሎት እንድትቀላቀሉ ይጋብዛል፡፡ በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ አምስት ከፍተኛ የፈጠራ ወይም የምርምር ስራዎች እያንዳንዳቸው 5ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ #ሽልማቶች እንደሚበረከትላቸው በተገለጸው በዚህ ውድድር ላይ ለመካፈል ዘመናዊ ከተሞች እና አዳዲስ የመኖሪያ ቴክኖሎጂዎች፤ ዲጂታላይዜሽን፤ የኢንተርኔት ንግድ ስርዓት፤ የግብርና፤ የጤናና የህክምና ቴክኖሎጂ፤ መስተንግዶና ቱሪዝም፤ የማምረቻና እና የማዕድን ኢንደስትሪ አመልካቾች የፈጠራ ስራ ፕሮፖዛላችሁን ስከ መስከረም 16ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብላችኋል።
በዚህ ውድድር ላይ የመወዳደሪያ ሀሳባችሁን Registration@africaninnovationweek.com ላይ በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።
Via #ETHIO_FM

ውድ ቤተሰቦቻችን ስራ፤ ትምህርት እንዴት ነው? ቀኑስ እንዴት እየለፈ ነው? በአጋጣሚ ወደቤታችሁ TIKVAH-ETH ጎራ ካላችሁ ባለፉት ሰዓታት በሀገራችን የተሰሙ አዲስ ጉዳዮችን ታነቧቸው ዘንድ ሰብስበንላችኃል፦
•ከባህር ዳር-ጀማ ወንዝ–ፈለገ ብርሃን የተገነባው 175 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ግንባታ የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ተመርቋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች መንገዱን ጎብኝተዋል፡፡
•የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ዛሬ በርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት ባደረጉት ውይይት በክልሉ የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
•የክብር ዶ/ር አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ በኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ሥራዎች ላበረከተው አስተዋፅኦ የፈረንሳይ መንግሥት በባህል ዘርፍ የሀገሪቱን ከፍተኛ ሽልማት አበርክቶለታል።
•ሜቴክ ከ108 ሚሊየን ብር በላይ ያወጣበትን ህንጻ ከ2 ወር በኋላ እንዲለቅ ሊደረግ መሆኑን ገለጸ። በተለምዶ ኢምፔሪያል ሆቴል ተብሎ የሚጠራውን ህንጻ በሽያጭ ሂደቱ ወቅት 32 ሚሊየን ብር የገቢዎች ክፍያ ባለመፈጸሙ ነው ሜቴክ ህንጻውን እንዲለቅ እግድ የወጣበት።
•ቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባኤ ዛሬ በአሶሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድር እንደገለጹት ለአንድ ቀን የሚቆየው ጉባኤ በክልላዊና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ በውይይቱ አጃንዳ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ FANA RADIO, EBC, ENA