TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.3K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሃዋሳ⬆️

የኢትዮጵያ ሂሞፊልያ ሶሳይቲ በሀዋሳ የምስረታ ጉባኤው ዛሬ በኬራዊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አደረገ። ሂሞፊልያ ማለት የደም አለመርጋት ችግር ሲሆን በኢትዮጵያ 10,000 ሕሙማን አሉ ተብሎ ይገመታል። ከነዚህ ውስጥ ግን 333 ብቻ ናቸው ሕክምና በማግኘት ላይ የሚገኙት። www.ethiohemophiliayouth.com

Via ፍፁም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ ዋሽንግተን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን የማኅበራዊ ሜዲያ ምንጮች አመልክተዋል፡፡ ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለመቃወም የወጡ ናቸው፡፡ የሰንበት ተማሪዎች በብዛት ተሳታፊ ናቸው፡፡ የሐይማኖቱ አባቶችም ንግግር አድርገዋል፡፡

Via wazemaradio
ፎቶ: ከማህበራዊ ሚዲያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ በትንሹ የ15 ሰዎች ተገደሉ!

የታሊባን ታጣቂዎች በሆስፒታል ላይ ጥቃት አድርሰዋል። በደቡባዊ አፍጋኒስታን በጭነት መኪና ላይ የተጠመደ ቦንብ አንድ ሆስፒታል ደጃፍ በታሊባን ታጣቂዎች በመፈንዳቱ በትንሹ 15 ሰዎች ሞተዋል፡፡

የሃገሪቱ ሚዲያች እንደዘገቡት በኳላት ከተማ በሚገኘው ሆስፒታል በደረሰው ጥቃት ዶክተሮችና ታካሚዎች ሰለባ ሆነዋል፡፡ በሌላ በኩል በሃገሪቱ ምስራቅ አቅጣጫ የአይ ኤስ ታጣቂዎችን ኢላማ ባደረገ የአየር ጥቃት 15 ሲቪሎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡

ባለፈው ወር በተፈጠሩ ግጭቶች 473 ሲቪሎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቢቢሲ አደረኩት ባለው ጥናት ከደረሱ አደጋዎች ሲቪሎች በአምስተኛ ደረጃ ተጎድተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሼር #share

የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት!

ሰሞኑን በላይኛው የተፋሰሱ ክፍል በተካታታይ ቀናት እየጣለ ባለው ካበድ ዝናብ ምክንያት በአዋሽ ወንዝ ላይ ያለው የፍሰት መጠን ጨምሯል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወደ ቆቃ ግድብ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ እየገባ በመሆኑ ወደ ግድቡ የሚገባውንና የሚወጣውን የውሃ መጠን ባገናዘበ መልኩ ግድቡን የማስተንፈስ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሰረት በቆቃ ግድብ አከባቢና በተለይም ከቆቃ ግድብ በታች የሚገኙ ምስራቅ ሸዋ ዞን የአዳማ፣ ቦሰት፣ ፈንታሌ ወረዳ፣ ከአርሲ ዞን መርቲ እና ጀጁ ወረዳ በመካከለኛው አዋሽ ከአፋር ዞን ሶስት የአሚባራ፣ ዱለቻ፣ ገለኣሎ እና ገዋኔ ወረዳዎች በታችኛው አዋሽ ዱብቲ፣ አሳይታ እና አፋምቦ ወረዳዎች ወንዙን ተጠግተው የሚኖሩ ማህበረሰቦችና የመስኖ ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የአዋሽ ተፋሰስ ልማት ጽ/ቤት

📸ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሼር #share

ተጨማሪ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት!

ባለፈው ሰሞን በላይኛው አዋሽ ተፋሰስ ክፍል በጣለው ከባድ ዝናብ እና በዚህ ባለንበት ሳምንት እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በአዋሽ ወንዝ ላይ ያለው የውሃ ፍሰት መጠን በመጨመሩ ሳቢያ ከቆቃ ግድብ በተጨማሪ ወደ ከሰም ግድብ እየገባ ያለው የውሃ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡በተጨማሪም ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከከሰም፣ ከቀበናና ከሌሎች ገባር ወንዞች ወደ አዋሽ ወንዝ እየገባ ባለው ውሃ መጨመር ምክንያት በወንዙ ላይ ያለው የፍሰት ጨምሯል፡፡

በመሆኑም በመካከለኛው አዋሽ አፋር ክልል የአሚባራ፣ ዱለቻ፣ ገለኣሎ እና ገዋኔ ወረዳዎች በታችኛው አዋሽ ዱብቲ፣ አሳይታ እና አፋምቦ ወረዳዎችና በአጠቃላይ በከሰም ግድብ አካባቢና ከግድቡ በታች የአዋሽ ወንዝን ተጠግተው የሚኖሩ ማህበረሰቦችና የመስኖ ልማት ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

የአዋሽ ተፋሰስ ልማት ጽ/ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#REFERENDUM

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ አስቀድሞ ባወጣው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሀ ግብር መሰረት የተለያየ ሀላፊነት ያላቸው የህግ አስፈጻሚ እና የጸጥታ አካላት እና የቦርዱ የስራ አመራር አባላት የህዝበ ውሳኔውን አፈጻጸም ሰላማዊነት ማረጋገጥ አስመልክቶ መስከረም 07/2012 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱም የፌደራል ፓሊስ ተወካዮች ፣ የደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ተወካዮች፣ በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሀላፊ፣ የሃዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ፣ የሲዳማ ዞን ፓሊስ ሀላፊ, የክልሉ የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ ተገኝተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-19-4
#update በአዲስ አበባ ከተማ የዋጋ ንረትን በመጨመር የኑሮ ውድነትን አባብሰዋል የተባሉ 609 ድርጅቶችና የንግድ ሱቆች መታሸጋቸውን የአስተዳደሩ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ። ህግን ከማስከበር ባለፈ ህገወጥ ንግድን ለመከላከል የሚያስችሉ ዘላቂ መፍትሄዎችን ለመስጠት ቢሮው እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን⬆️
#update ኢ/ር ታከለ ከእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ ማህበሩ ኢ/ር ታከለ ከወጣቶች ጋር በተለይም ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር እያሳዩት ያለውን ትብብር አድንቋል።

ወጣቶች በሀገራቸው ሰርተው መኖር እንዲችሉና በሀገራቸው ተስፋ እንዲያደርጉ ኢ/ር ታከለ እያደረጉት ያለውን ጠንካራ ድጋፍ ምስጋናውም ገልጿል። ለዚህ ምስጋና መገለጫ ይሆን ዘንድም የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ለኢ/ር ታከለ ኡማ ሽልማት አበርክቷል።

Via Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
#ARBAMINCH

የትራፊክ አደጋን #ለመቀነስ በሚያስችሉ 58 የተመረጡ ስፍራዎች ላይ ዘመናዊ የፍጥነት መቀነሻና የእግረኛ ማቋረጫ ግንባታ ስራዎችን በከተማዋ እያከናወነ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ትራንስፖርትና መንገድ ጽ/ቤት ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ከመጥራታቸውና ከመቀበላቸው በፊት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቅ ይገባቸዋል፤ በተለይም በተማሪዎች ማደሪያ ላይ በየዓመቱ ቅሬታዎች ይደርሱናል። በዛሬው ዕለትም ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመጣልን መልዕክት ይህ ነው፦

"ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፓሊ ካምፓስ ውስጥ የተመደብኩበት ዶርም ይህን ይመስላል። ጊቢው የክረምት ትምህርት ተማሪዎችን ሳያስወጣ እኛን ጠርቶ ለሁለት ቀናት እየተጉላላን ነው። ማደሪያ እያመቻቸን ነው ገና፣ ከባድ ዝናብ አለ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዮዮ_ጊፋታ_2012

ከመስከረም 14 እስከ መስከረም 18/2012 ዓ.ም ድረስ በሚከበረው የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል ላይ ከመላው ኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦች የተወጣጡ አካላት ይገኙ ዘንድ የወላይታ ሀገር ሽማግሌዎች፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከምሁራንና ከዬላጋ የተወጣጡ የጊፋታ ልዑካን ቡድን በአካል ተገኝተው የክብር ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

የዘንድሮ የ2012 ዓ/ም "የጊፋታ በዓል" ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በUNESCO ለማስመዝገብ የሚደረገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ለማስቀጠል በዓሉን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ጠንካራ የማስተዋወቅ ስራ እንተሰራ ይገኛል። በተጨማሪም ሀገራዊ ለውጡን በሚያንፀባርቅ መልኩ በዓሉን ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት ለማክበር እየተሰራ እንደሚገኝ ሰምተናል።

ለዚህም ሲባል የጊፋታ ልዑክ እስከ ስፍራው ድረስ በመሄድ በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሶማሌ፣ ሀረሪ፣ ድሬዳዋ፣ ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ካፋ፣ ቤንች፣ ማጂ፣ ሸካ፣ የም፣ ጎፋ፣ ዳውሮ፣ ኮንታ፣ ባስኬቶ፣ ደ/ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ጋሞ፣ ደራሼ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ሀዲያ፣ ከምባታ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሲዳማና ጌዲኦ እንዲሁም ከዎላይታ ውጪ ያሉ የወላይታ ልማት ማህበር ቅ/ጽ/ቤቶች ልዑካን ቡድኖች እንዲገኙ የክብር ጥሪ እየቀረበላቸው ይገኛል። በዓሉ ከወትሮው በተለየ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ይከበር ዘንድ ከ10 በላይ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተዋቅረው እየሰሩ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ዘንድሮ በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

#Irrecha2019
@tsegabwoldw @tikvahethiopia
ዮ.ዮ.. ጋሞ ማስቃላ!

እንኳን ለጋሞ ዞን ህዝቦች ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የጋሞ ዞን ሦስቱ ብሔረሰቦች ጋሞ ፣ ዘይሴ ፣ ጊዲቾ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በፍቅርና ሠላም የሚኖሩበት፤የአባያና ጫሞ ሐይቆች ፣ የነጭ ሳርና የማዜ ብሔራዊ ፓርኮች መገኛ፤ የፍራፍሬ ቅርጫት፤ለአለም የሠላም ተምሳሌት ፤ የቱሪስቶች መዳረሻ፣ የጥበብ፣ የጥንታዊ አድባራት፣ የሰዉ ዘር መገኛ ባይራ ምድር ና የቱባ ባህል ባለቤት፤

ዮ….ዮ…. ጋሞ ማስቃላ

የባህልና ቋንቋ ሲምፖዝዬም የሠላም እና የአብሮነት ተምሳሌት በሆነችው አርባምንጭ ከተማ ከመስከረም 12 እስከ 13 / 2012 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡
በዓሉ በአባቶች ምርቃት ደምቆ በባህል ጭፈራ ተውቦ በሕዝብ ውይይት ታጅቦ ይከበራል፡፡ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡

ዮ…ዮ…ጋሞ ማስቃላ!

የጋሞ ዞን አስተዳደር ከአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ጋር በመተባበር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2 ሰው ህይወት አልፏል!

በሀዋሳ ከተማ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ እስካሁን የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል። በበሽታው በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል እየተባለ የሚወራው ሀሰት ነው ሲልም ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍4
እፀገነት አንተነህ⬆️

"የ27 አመቷ የአየር መንገድ ሒሳብ ሰራተኛ እፀገነት አንተነህ ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ወደ ሰራ በምታመራበት ወቅት #ጭካኔ በተሞላበት ወንጀል አቃቂ መንገድ ላይ ተገድላ ተጥላ ተገኘች። ፓሊስ ምርመራ ላይ ነው። ቀብሯ ዛሬ ተፈፅሟል። ቀለበት አድርጋ ሰርግ ለመደገስ ዝግጅት ላይ ነበረች።" ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት/#CAPITAL/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
😢22👍7
#update በወልቂጤ ከተማ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ዛሬ የውል ስምምነት ተፈረመ። የውል ስምምነቱ የተፈራረሙት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ እና  ግንባታውን የሚከናውነው ተቋራጭ ናቸው።

ምንጭ፦ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍2
#update ከባህርዳር ጭስ አባይ የሚወስደውን መንገድ በኮንክሪት አስፓልት ደረጃ ለማስገንባት በ767 ሚሊየን ብር የማስጀመሪያ ፕሮግራም ስራ ዛሬ ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የባህር ዳር-ዘማ ወንዝ-ፈለገብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡

ፕሮጀክቶቹን በተመለከተ:-

ኮንትራት አንድ

የባህርዳር - ዜማ ወንዝ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ፦

* የመንገዱ ርዝመት 92.5 ኪ.ሜ

* የመንገድ ግንባታውን ሲያካሂድ የቆየው የስራ ተቋራጭ ሲኖ ሃይድሮ የተባለ የቻይና ዓለም አቀፍ የስራ ተቋራጭ ድርጅት

* የምህንድስና ቁጥጥርና የማማከር ስራውን ሲያካሂድ የቆየው አማካሪ ድርጅት፡ አገር በቀሉ ኔት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ

* ፕሮጀክቱን ለማካሄድ ወጪ የሆነው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን: 1,292,818,750.99 ብር

* የግንባታ ወጪው የተሸፈነው ሙሉ በሙሉ የግንባታ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኗል።

ኮንትራት ሁለት

ዜማ ወንዝ -ፈለገብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ፦

* የመንገዱ ርዝመት 82.83 ኪ.ሜ

* የመንገድ ግንባታውን ሲያካሂድ የቆየው የስራ ተቋራጭ ሲአርሲጂ

* የምህንድስና ቁጥጥርና የማማከር ስራውን ሲያካሂድ የቆየው አማካሪ ድርጅት አይከን ኢንጂነሪንግ

* ፕሮጀክቱን ለማካሄድ ወጪ የሆነው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን: 1,244,361,000 ብር

* የግንባታ ወጪው የተሸፈነው፡ ሙሉው የግንባታ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኗል፡፡

Via የትራንስፖርት ሚንስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍3
#update ከፀሀይ ብርሀን የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚችል ፕሮጀክት ነገ መስከረም 09/2012 እንደሚመረቅ ተገልጿል፡፡ ፕሮጀክቱ በአቃቂ ወረዳ ቁፍቱ ቀበሌ የተሰራው ሲሆን ወጪው በደቡብ ኮሪያ መንግስት የተሸፈነ ነው፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia