TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FakeNews በጅማ ከተማ አንድ አባት ታርደው ወንዝ ዳር ተጥለው ተገኙ ተብሎ በፌስቡክ እና በቴሌግራም የሚሰራጨው መረጃ #ከእውነት_የራቀ ነው። ይህንን ያረጋገጡልንም የጅማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ናቸው።

ሼር የምታደርጉትን መረጃ በቅድሚያ አጣሩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

ጅማ ዩኒቨርሲቲ -- የተማሪዎች መግቢያ ቀን ይፋ ተደርጓል!

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናትን እና ሌሎች መረጃዎችን በTIKVAH-MAGAZINE ታገኛላችሁ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
@tikvahethmagazine
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተላለፈ መልዕክት!

ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፦

#የጎንደር_ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2012 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ የ2012 የትምህርት ዘመን መግቢያ ጊዜ በዮኒቨርሲቲያችን ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ በፌስቡክ እና ሊንክድኢን ገጾቻችን በቅርቡ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጎንደር ዩኒቨርስቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ!

በአርባ ምንጭ ከተማ ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡ በጫንጮ ከተማም 456 ኪሎ ግራም ቅቤ ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዳንኤል አረጋ ለኢዜአ እንዳሉት ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ ነበሩ ሁለት ግለሰቦች የተያዙት በትናንትናው ዕለት ነው፡፡ ግለሰቦቹ የተያዙት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የከተማው ፖሊስ ለነዋሪው አስቀድሞ በፈጠረው ግንዛቤ መሰረት ከነዋሪዎች ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ ነው። “ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ የጀመረ ሲሆን ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ይደጋል” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-11-3

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሀገር መከላከያ ሠራዊት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ድሪባ መኮንን ተናገሩ። ሜጀር ጄነራል ድሪባ ይህን ያሉት በሰላም  ማስከበር ማዕከል ሁርሶ የተጠባባቂ ኃይል ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለዘጠነኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የሠራዊት አባላት ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ10,000,000 ብር ባለዕድለኛ ማን ይሆን??

እንቁጣጣሽ ሎተሪ በዛሬው ዕለት /ጳጉሜ 6/ ይወጣል።/የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር/

ከሰዓታት በኃላ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት የIS አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል!

የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሞኑን የተወሰኑ የአይኤስ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ያልተያዙትም በጥብቅ ክትትል ውስጥ መሆናቸውን የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ጀነራል ብርሀኑ ጁላ አስታወቁ፡፡

ሰራዊቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሀገርና ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ ጀነራሉ እንዳስታወቁት፤ አይ ኤስ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ በተደጋጋሚ ጥረት አድርጎ ቢመክንበትም በአገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የመለመላቸው፣ ስልጠና የወሰዱና የተጠመቁ ሰዎች እንዳሉ መንግስት በሚገባ እንደሚያውቅ ተናግረዋል፡፡

‹‹በአሁኑ ወቅት የአይኤስ አባላት ምን እያደረጉ እንዳሉ፣ የት የት ቦታ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ፣ ከእነማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው፣ በከተሞች ውስጥ ያሉት ሰዎቻቸው እነማን እንደሆኑ፣ ምን እየሰሩ እንዳሉ፣ እቅዳቸው ምን እንደሆነና ሌሎች መግለጽ የማያስፈልጉ ጉዳዮችም እጅግ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው ነው››ብለዋል ጀነራሉ፡፡

‹‹ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከየትኛውም አደጋ ለመጠበቅና ለመከላከል ባለብን አደራና ከባድ ኃላፊነት የተነሳ ቀን ከሌት አንተኛም›› ያሉት ምክትል ጠቅላይ ኢታማጆሩ፤ ‹‹ሰራዊቱ እረፍት የሚባል ነገር አያውቅም፤ ያረፍንበት ጊዜም የለም›› ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

እንደ ጀነራሉ ማብራሪያ፤ አንዳንድ ጊዜ የሆነ ሰው እንደተገኘ ሄዶ መያዝና መቆጣጠር ተገቢ አይደለም፤ ምክንያቱም ለአንድ ሰው ተብሎ ብዙ ነገር እንዳይታጣና እንዳያመልጥ በማድረግ በጥንቃቄና በሕግ አግባብ መቆጣጠር ስለሚቻል ሁኔታው አስቸጋሪ አይሆንም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-11-2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሁን በኃላ ግን ዝም አንልም...

የጦር ኃይሎች ም/ኢ/ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፦

"የመከላከያ ሰራዊታችን እኩሪ ታሪክ ያለው ሰራዊት ነው። በህገ መንግስት ዙሪያ የተገነባ ነው። ከራስ በፊት ለህዝብ የሚል ነው። ከሀገሪቱ ዜጎች የተሻለ የማይከፈለው ነው። ራሱን አሳልፎ ለህዝብ የሰጠ ነው። ችግር መፍታት የሚችል ሰራዊት ነው። ሌሎች መፍታት ያቃታቸውን ችግሮች መፍታት የሚችል ነው። feedback ማግኘት አለበት። feedback ማለት ሰራዊታችን ገንዘብ ስጡኝ፤ ቁርበት አንጥፉልኝ አይልም። ክብሩ ግን መጠበቅ አለበት። መመስገን አለበት! ከተመሰገነ ይበቃዋል። ህዝቡ በሰራዊቱ "አመሰግናለሁ" ካለ የሰራዊታችን የሞራል ምንጭ እሱ ነው። "አንዲት ኢትዮጵያ" እያለ የሚዘምረው ከኛ በላይ የሚዘምረው፤ እኛማ ጦር ሜዳ ውለን ህይወታችንን ሰጥተን፤ ተቷክሰን፣ አሸንፈን ጓዶች ገብረን ፣ ሀገር ጠብቀን፣ እዚህ አድርሰናል። ለዚህች ሀገር ጠጠር ያልወረወረ መሸታ ቤት የሚውል እየወጣ ሰራዊቱን እያብጠለጠለ ነው። የዴሞክራሲ ምህዳር ይስፋ ስለተባለ እያብጠለጠለን ዝም ብለናል። ከአሁን በኃላ ግን ዝም አንልም።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር፦

1662862 --የ1ኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል
0022646--2ኛ እጣ ቁጥር ሆኗል
1231149--የ3ኛ አሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል
0018527--የ4ኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል
1703425--የ6ኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር ሆኗል

ባለዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እንቁጣጣሽ ሎተሪ ጳጉሜን 06/2011 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር-----1662862

2ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር------0022646

3ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር ----1231149

4ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር ----0018527

5ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር -----1774633

6ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር ------1703425

7ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር ------- 36808

8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------- 89196

9ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር--------7889

10ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------3883

11ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------788

12ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 250 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-- ----657

13ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-----52

14ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 50 የሚያስገኘው (የማስተዛዘኛ) ዕጣ ቁጥር----1 በመሆን ወጥቷል፡፡

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ሀሰተኛ መረጃዎች⬆️

በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

TIKVAH-ETHIOPIA ሰዎች በሰውነታቸው ተከባብረው የተሳባሰቡበት ቤት ነው። ቤተሰባችን ውስጥ ፈፅሞ መሰዳደብ አይቻልም፤ የሰዎችን አመለካከት ማንቋሸሽ አይቻልም፤ በብሄራቸው፣ በእምነታቸው ላይ አፀያፊ ቃላትን መናገር አይቻልም። የቤተሰባችን አባልት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ከተለያዩ ውጭ ሀገራት የተሰባሰቡ ናቸው።

ይህ ገፅ ትልቁ ስራው አባላቱ መረጃዎችን እርስ በእርስ መለዋወጥ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት ነው። የቤተሰቡ አባላት በያሉበት ሆነው የሚያዩትን ነገር ከማጋራት በተጨማሪ ከተለያዩ ሚዲያዎች ዜናዎች #ተመርጠው የሚጋሩበት መድረክ ነው። አንዳዶች TIKVAH-ETHን እንደትልቅ ሚዲያ፣ ከጀርባው ደጋፊ እንዳለው ወይም የፖለቲካ ድርጅት ድምፅ አድርገው ይቆጥሩታል። ይህ በጣም ስህተት ነው ገፁ የሁላችንም ነው። የባለስልጣኑም፣ ፓለቲከኛውም፣ አርቲስቱም፣ ጋዜጠኛውም፣ አክቲቪስቱም፣ የግል ሰራተኛውም፣ ተቀጣሪውም፣ ተማሪውም፣ የህዝብ አሰተዳዳሪውም፣ የሀይማኖት መሪውም፣ የሀገር ሽማግሌውም ...የሁሉም ቤት ነው TIKVHA-ETH! ከጀርባው ሆኖ የሚደግፈውም የለውም!

ወደዋናው ጉዳይ ስገባ...

ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ አሳዝኖናል። ያሰራጩ አካላትም እርምት ይወስዳሉ ብለን እጠብቃለን። ሀይማኖታዊ ጉዳዮች sensitive ናቸው። የሚሰራስጩ መረጃዎችም ጥንቃቄ ካልታከለባቸው እልቂትን የሚፈጥሩ ሊሆኑ ይችላሉ። /የማይናማር ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ እንዴት እንደዋለ ከዚህ በፊት ነግሬያችሁ ነበር/። ይህ ማለት ግን መረጃ ይደበቅ፣ ይታፈን፤ ተድበስብሶ ይቅር፣ ፖለቲከኞሽ በሚዲያ እየወጡ ይዋሹ ማለት አይደለም።

የሚሰራጩ መረጃዎች ግን መዘዛቸው ምንድነው፣ ሌላ ቦታ ተጨማሪ እልቂት ይፈጥራሉ ወይ?፣ የሰዎች ስሜት ላይስ ምን ይፈጥራል፣ ማህበረሰቡ ላይስ የሚፈጥረው ምንድነው? የሚሉትን ነገሮች ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለባቸው። መረጃዎች እውነት እንኳን ቢሆኑ በምን መልኩ ይቅረቡ፣ የሚለው ሊታሰብበት ይገባል። ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ያሉበትን ሁኔታ የምታውቁት ነው። መረጃዎችን መደበቅ አያስፈልግም ነገር ግን ሲሰራጩ ተጨማሪ ችግር በሚፈጥር እና በማጋጋል ወይም ደግሞ ሌሎችን ለጥፋት በሚያነሳሳ መልኩ ሊሆን አይገባም።

መቼም የተሳሳቱ መረጃዎች በሀገራችን ውስጥ ያመጡትን መዘዞች ከናተ የሚደበቅ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም በሀይማኖት ጉዳዮች በፖለቲካው የሚሰራጩ መረጃዎች ያመጡትን መዘዝ አይተናል። እኛ መረጃዎችን እንደወረደ የምንቀበልበት አቅም ያለን ህዝቦች መስሎ አይሰማኝም፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል በተለይ አሁን ያለንበት ሁኔት። ያለችን ትንሽ ሰላም በእጃችን ከወጣች እመኑኝ ዳግም አናገኛትም!! እናንተም አስተዋይ ናችሁና ሲሰራጩ የምታገኟቸው መረጃዎች ማጣራት እንዳትዘነጉ ከማን? ለምን? ተላለፉ፤ እኔ ሼር ሳደርገው ምን ይፈጠራል? አላማው ምን ይሆን ብለን እንጠይቅ። አንዳንዶች በውጭ ሀገር ስላሉ ምናልባት እኛ ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ላያውቁት ይችላሉ፤ ማህበረሰቡም የሚሰማውን ነገር ሁሉ እንዴት እንደሚቀበለው ብዙም የተረዱት አይመስለኝም።

ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳያረጋግጡ እና ሆንብለው የሚያሰራጩትም ልቦና ይስጣቸው ከማለት ውጭ ምንም ማለት አይቻልም!!

በመጨረሻም...

/TIKVAH-ETH/ ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ በርካታ #የሚያሳዝኑ ልብ የሚሰብሩ መረጃዎች ሲጋሩበት ነበር። እዚሁ ሀገራችን የኦርቶዶክስም፣ የወንጌላውያን አማኞች ቤተ እምነቶች ሲቃጠሉ፤ ካህናት ሲገደሉ፣ መስጊድ ሲቃጠል፣ አባቶች ሲገደሉ...ብቻ በምድር ላይ አሉ የሚባሉ መጥፎ ነገሮች ሁሉ ቀርበውበታል። አዲሱ አመት ግን ክፉ ማንሰማበት፤ የሰላም፤ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ፣ መስጊድ ፈረሰ፣ መስጊድ ተቃጠለ፣ ሰዎች በብሄራቸው ጥቃት ደረሰባቸው፣ በሃይማኖታቸው ተጠቁ፣ የሚሉ ዜናዎችን የማንሰማበት ሰላማዊ፣ የፍቅር እብሮነታችን የሚጠነክርበት ዓመት እንዲሆን በእውነት ከልብ ከልብ እመኛለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ"ጳጉሜን በመደመር" የመዝጊያ ስነ ስርዓት ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በብሔራዊ ቤተ መንግስት እየተካሄደ ነው፡፡

#ETV #FANA ---LIVE!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በርካታ የሺሻ ዕቃዎች እና ሀሰተኛ ሰነዶች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያና በስሩ የሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ከህዝብ በደረሳቸው ጥቆማ መሰረት ትናንት ምሽት በ43 መኖሪያ ቤቶች ላይ ባደረጉት ፍተሻ 475 የሺሻ ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ ሀሰተኛ ማህተሞች እና ሰነዶች ተይዘዋል፡፡ ሺሻ የማስጨስ ህገወጥ ተግባር ሲያከናውኑ የነበሩና ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የይቅርታ ሰዓት!

እውነትን ተናግረን ፈጣሪን ይቅርታ ጠይቀን፤ የበደልነውን፣ ያስቀየምነውን ይቅርታ ጠይቀን ወደ አዲሱ ዓመት እንሸጋገር...

በ2011 ዓ/ም ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሜ ሰዎችን ስድብ ነበር፣ የሰዎችን ስብእና ስነካ ነበር፤ ሰዎችን በህብሄራቸው፤ በእምነታቸው ስጣላ ነበር፣ ሰዎችን በብሄራቸው፣ በእምነታቸው እና በአመለካከታቸው ሳንቋሽሽ ነበር፤ የጥላቻ ንግግርን ሳሰራጭ ነበር፣ ሳላውቀውም አውቄውም የሀገሬ ሰላም እንዲደፈርስ በማህበራዊ ሚዲያ አስተዋፆ ሳደርግ ነበር፣ የሌሎች ወገኖቼን ስሜት የሚጎዱ መልዕክቶችን ሳጋራ ነበር፣ በቅጡ በማላውቃቸው ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ሳደርግ ነበር፣ ሀሰተኛ መልዕክቶችን ለወገኖቼ ሳሰራጭ ነበር፣ የእድሜ ታላቆቼን ስድብና ሳንቋሽሽ ነበር፣ የሰው ልጅ ሁሉ ጉዳት ሳይሆን የኔ ምለው ወገን ጉዳት ብቻ ይሰማኝ ነበር፣ ለተጎዳው ሁሉ ማዘን አቅቶኝ ነበር....ጨምሩበት!

ስለሆነም....ላደረኩት ነገር ሁሉ ፈጣሪ ይቅር እንዲለኝ እየተማፀንኩ፣ በእኔ የተከፋችሁም ይቅር እንድትሉኝ እለምናለሁ፤ ይቅርታዬንም ተቀበሉኝ፤ ያናተንም እቀበላለሁ። አዲሱን አመት ንፁህ ልቤን ይዤ እቀበለሁ፣ ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ የምትሉ ወገኖች ሁሉ👉❤️

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert ጅማ ከተማ ዳሸን ባንክ /መርካቶ/ አካባቢ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች በሚገኙበት ቦታ የእሳት አደጋ መድረሱን በቦታው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የእሳቱ መነሻ ለጊዜው አልታወቀም። በአካባቢው የእሳት አደጋ ሰራተኞች ደርሰዋል/ብዙ ንብረት ከወደመ በኃላ/፣ በስፍራው የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል የፖሊስ አባላት እንደሚታዩም የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል።

ፎቶዎች እንደደረሱኝ አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዋዜማ ምሽት መርሃ ግብር እያከናወነ ነው፡፡ በምሽት መርሃ ግብሩ ሃገራዊ አንድነትና ፍቅርን የሚጠናክሩ የተስፋ መልዕክቶች ይተላለፋሉ፡፡ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዝግጅቱ ተገኝተው ልዩ የበአል የመልካም ምኞት መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተለይም ከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ አድርጎት መረሃ ግብር በትምህርት፣ በጤናና በአቅመ ደካሞች ቤት መጠገን ስራ ሙሉ ጊዜና ገንዘባቸውን ለሰጡ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia