TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳትደናገጡ!

🎆በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው #የዋዜማ ዝግጅት ለአዲሱ አመት ስጦታ ከቻይና መንግስት የተበረከተው ርችት አምባሳደር አካባቢ እየተገነባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግዙፍ ህንፃ ላይ #ይተኮሳል፡፡ በዚህም ህብረተሰቡ #በርችቱ ድምፅ እንዳይደናገጥ ከተማ አስተዳደሩ አስገንዝቧል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አልሞትኩም፤ ሞቴን ለተመኛችሁ እንሆ አልተሳካላችሁም" አባ ወ/ሰንበት ገ/ሚካኤል

በጅማ ከተማ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎችን ያሳተፈ የሰላም ኮንፍረንስ ተካሂደዋል። በዛሬው ዕለት በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች አንገታቸው #ተቆርጦ ሞተው ተገኙ ተብልው ሲናፈስ የነበረው አባ ወ/ሰንበት ገ/ሚካኤል ኮንፍረንሱ ላይ በመገኘት "እኔ አልሞትኩም! ሞቴን ላለማችሁ እንሆ አልተሳካላችሁም" በማለት የሀሰት ወሬ አራጋቢዎች ብሎም የግጭት እና ውድቀት ናፋቂዎች አላማ እንደማይሳካ እና ጅማ በምታወቅበት ፍቅር እና አንድነትዋ እንደ ምትዘልቅ አስገንዝበዋል። የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች ጅማ ለህዝቦችዋ ፍቅርን እንጂ መከፋፈልን የምትለግስ ከተማ አይደለችም በማለት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሰላማችንን በአንድነት ጠብቀን ለዘላቂ ልማት እንተጋልን ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1