TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ! ትናንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት እንደሚቆይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ገለፁ። ሚኒስትሩ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚከለክላቸው…
· በህዝብ መካከል መጠራጠርና ብጥብጥ ሊያስነሳ የሚችል እንቅስቃሴ ወይም ፅሁፍ ማዘጋጀት፣ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘዴዎች የመልቀቅ እና የማሳተም እንቅቃሴዎችን ያግዳል።
· የአደባባይ ሁከትና ቅስቀሳን የሚያነሳሱ እንቅስቃሴዎችን ያግዳል።
· ሰላማዊ ሰልፍ መካሄድን ይከለክላል።
· ወደ ሁከት ሊያመሩ የሚችሉ ምልክቶችን በመፃፍና በማሳየት በቡድንም ሆነ በነጠላ መንቀሳቀስን ያግዳል።
· ወንጀል የተፈፀመባቸውና ሊፈፀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶችን ለመያዝ ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ ፍተሻ ያደርጋል።
· በሰዓት እላፊ እንቅስቃሴ ወቅት ጥርጣሬን የሚፈጥሩ ግለሰቦችን እና ተሽከርካሪዎችን አስቁሞ ይጠይቃል።
· የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎታቸው እንዳይሰተጓጎል ከለላ ይሰጣል።
· የመሰረታዊ ፍጆታ እቃ ሸቀጦችን እና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል ያደርጋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁን ተከትሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አቶ ሲራጅ ተናግረዋል።
ኮማንድ ፖስቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን፣ የደህንንት ፅህፈት ቤትን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩን እና በየክልሉ ያሉ የጸጥታ ምክር ቤት አባላት እና ሌሎችንም እንደሚያካትት ተናግረዋል።
በመግለጫቸው ላይ እንዳሉትም፥ አዋጁ በ15 ቀናት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርብ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱም እየታየ ይራዘማል።

ሚኒስትሩ “በሀገሪቱ የሽግግር መንግስት ይመሰረት ይሆን” በሚል ለቀረበ ጥያቄም፥ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በህዝብ የተመረጠ በመሆኑ የሽግግር መንግስት ማቋቋም አያስፈልግም ብለዋል።

“የሲቪል መንግስቱን ወታደሩ ይረከባል” በሚል የሚነሳ ስጋትንም አቶ ሲራጅ ውድቅ አድርገዋል።

#FANA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእሳት አደጋ! በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ቦታው ትቅደም ትምህርት ቤት ጀርባ በሚገኘውና ሾላ ገበያ ዶሮ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ።

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠር እና መከላከል ባለስልጣን ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቶ ማሞ እንዳስታወቁት፥ የእሳት አደጋው ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ ነው የደረሰው።

በእሳት አደጋውም በንብረት እና በሰው ላይ ጉዳት ደርሷል ያሉት አቶ ንጋቱ፥ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜም ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠር እና መከላከል ባለስልጣን እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል አምቡላንሶች ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

7 የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች፣ 2 ቦቴዎች እሳቱን የማጥፋት ስራው ላይ ተሰማርተዋል ብለዋል፤ 2 አምቡላንሶችም አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት መሰማራታቸውን በመጥቀስ።

በአሁኑ ጊዜም እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉንም አቶ ንጋቱ አስታውቀዋል።

የእሳት አደጋው መንስኤም እስካሁን አለመታወቁን እና በመጣራት ላይ እንደሚገኝም ነው አቶ ንጋቱ ያስታወቁት።

#FANA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ላይ እየተነሱ #ቅሬታዎች በተመለከተ ከዶክተር አርዓያ ገ/እግዛብሄር ጋር የተደረገ ቆይታ!

#FANA 10 mb
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ"ጳጉሜን በመደመር" የመዝጊያ ስነ ስርዓት ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በብሔራዊ ቤተ መንግስት እየተካሄደ ነው፡፡

#ETV #FANA ---LIVE!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢህአዴግ ውህደት የህዝቦችን እኩል የሀገር ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ነው" - አቶ ሙስጠፌ መሀመድ --- #FANA

https://telegra.ph/ETH-10-02

@tsegabwolde @tikvahethiopia