TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ያልታዩ የማዕከላዊ እስር ቤት ፎቶዎች⬆️

ዛሬም የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት ማዕከላዊን ጎብኝተው በርካታ ፎቶዎችን አጋርተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠ ማሳሰቢያ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2011 ዓ.ም ያስመዘገባቸው ስኬቶች፣ በቀጣይ ዓመት ሊሰራ ያቀዳቸውንና ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች መገናኛ ብዙሃን ጠርቶ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ጥቂት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስም ተጠቅመው አፈፃፀሙን በተመለከተ #ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሀበራዊ ትሰስር ገፆች እያስተላለፉ ይገኛሉ።

ይኸውም የባንኩ ትክክለኛ ገፅ እንደሆነ በማስመሰል የባንኩን ያለፈው ዓመት ክንውን አስመስለው የለቀቁትን ሃሰተኛ መረጃ ላነበበና መረጃውን ለሌሎች ሰላሳ ሰዎች እስከ መስከረም 20 ላጋራ/ሸር ላደረገ/፣ ባንኩ የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጥ የሚያትት ሃሰተኛ መረጃ ነው፡፡

በመሆኑም #የተለቀቀው መረጃ ባንኩን በምንም ሁኔታ እንደማይመለከት እየገለፅን፣ ካሁን በፊት እንዳሳወቅነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃዎች የሚለቀቁት በባንካችን የሬዮና ቴሌቪዠን እንዲሁም በማህበራዊ የትስስር ገፆቻችን ብቻ መሆኑን በድጋሚ እያሰወቅን፣ ህ/ሰቡ ከመሰል ሃሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን፡፡ በቀጣይ ባንኩን በተመለከተ መሰል #ሃሰተኛ መረጃ የሚለቁ ግልሰቦችን ለፍትህ አካል ለማቅረብ ባንኩ እየሰራ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. EBS TV -- በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ስም የተከፈተው እና 5770 subscribers ያሉት የቴሌግራም ቻናል የEBS አይደለም። EBS በይፋ ይህ ነው የኔ ቻናሌ ብሎ ያሳወቀው የቴሌግራም ቻናል የለም።

ፌስቡክ፦

1. National Education Assessment and Examination agency--ይህ 149,000 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ትክክለኛ ገፅ አይደለም። ይህ ብዙ ተከታይ ይለው ገፅ በርካቶችን ያደናግራል ተጠንቀቁ። የኤጀንሲው ትክክለኛው ገፅ 119,000 Like ያለው ነው። ኤጀንሲው ገፁን በፌስቡክ #verify ቢያስደርገው መልካም ነው።

2. Desalegn Chanie Dagnew- ይህ 7,740 ሺህ Like ያለው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በፌስቡክ ላይ Like Page የላቸውም። ጥንቃቄ ይደረግ!

3. BBC news Amharic/አማርኛ--ይህ ከ 4 ሺህ በላይ like ያለው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። ትክክለኛው የBBC አማርኛ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገና ከ300 ሺህ በላይ like ያለው ነው።

4. Jawar mohammed--ይገርማል! ይህ ከ286,000 በላይ ህዝብ የሚከተለው ገፅ ሀሰተኛ ነው። ብዙ የሀሰት መረጃዎች የሚሰራጩበት በመሆኑ ጥንቃቄ ይደረግ። ትክክለኛው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገ ነው። ልብ በሉ like page አይደለም!

#BONUS

DW ትግርኛ/ድምፂ ወያነ የትግርኛው አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ ከ163 ሺህ በላይ ሰዎች የሚከተሉት ነው። የአማርኛው አገልግሎት ገፅ ደግሞ ከ46 ሺህ በላይ Like ያለው ነው።

#ቲክቫህ
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን!

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ #የሕክምናና_ጤና_ሳይንስ ነባር ተማሪዎች የመግብያ ቀን መስከረም 5&6 መሆኑ ኣውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን መጣችሁ እንድትመዘገቡና ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

አቶ ዮሃንስ ከበደ
/የዩኒቨርስቲው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር/


ዩኒቨርሲቲዎች መልዕክት ለመላክ ይሄን አካውንት ብቻ ተጠቀሙ👉@tsegabtikvah

TIKVAH ETH MAGAZINE የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎችን ብቻ በዚህ ተከታተሉ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ ተማሪዎች!

ለወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ። የ2012 የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እንደሚከተለው ተወስኗል። በዚሁ መሠረት :- የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 19-20/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል። የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 26-27/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል። ተጨማሪ መረጃዎችን ወደፊት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች የምናሳውቅ ይሆናል።

ኮርፓሬት ኮሙኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት
_

Simannaan barattoota yuunivarsiitii Wallaggaa ifoomeera. Barattoota buleeyyii fulbaana 19-20/2012 Barattoota haaraa Ful.26-27/2012 ta'uusaa akka bartan isin beeksifna.
_

Dates of Registration for senior and newly assigned Students has been decided the University's Senate ,accordingly :- Registration Date for Senior Students will be from Septemeber 19 upto 20/2012 E.C . Regsitration Date for Newly Assigned students Will be from September 26 up to 27/2012 E.C.
Further annocement will be made in the future by using different Media Outlets.

Corporate Communications Directorate

TIKVAH ETH MAGAZINE የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎችን ብቻ በዚህ ተከታተሉ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው🛫ወደ ሩሲያ ተጉዘዋል!

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ማታ ጳጉሜ 3 ቀን 2011 ዓም ወደ ሩሲያ ተጉዘዋል። ክቡር ሚኒስትሩ በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ለቭሮቭ ጋር ምክክር ያደርጋሉ።ጉብኝቱ የሁለቱን አገሮች የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የልማት ትብብር እንደሚያሳድግ ታምኖበታል፡፡ የሩሲያው የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በፈረንጆቹ 2018 ዓመት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወቃል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert አዲስ አበባ አቃቂ ገበያ #የእሳት_አደጋ መነሳቱን በአካባቢው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰች ጥቆማ አድርሰዋል። ወደአካባቢው የእሳት አደጋ መኪናዎች ደርሰዋል። በአካባቢው የመብራት ኃይልም ተቋርጧል። ለሚመለከተው አካል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቃቂ ገበያ አሁን⬆️

በአካባቢው ያሉ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ተጨማሪ ፎቶዎችን እና መልዕክቶችን እየላኩ ይገኛሉ። እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

#Moti #Yo #Jo
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert የእሳቱ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል፤ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅም እየተሰማ ነው። እሳቱን ለመቆጣጠር ተጨማሪ ኃይል ወደቦታ እንዲላክ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦቻችን ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቃቂ ገበያ⬆️"#እሳቱ መንደድ ከጀመረ 1 ሰዓት ከ54 ደቂቃ ሆኖታል እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም። አካባቢው ላይ ብዙ ሰው አለ እሳቱን ለማጥፋት እየተረባረቡ ነው።" #Alex

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ርብርቡ ቀጥሏል -- አቃቂ ገበያ!

"#እሳቱ መጀመሪያ ከነበረው #ኃይል በመጠኑ ቀንሷል ግን አሁንም ከፍተኛ ነው። የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ህብረተሰቡ በአራቱም አቅጣጫ እሳቱን ለማጥፋት የሚያደረጉት ርብርብ እንደቀጠለ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቃቂ ገበያ የተነሳው እሳት በከፍተኛ ጥረት እና ርብርብ በቁጥጥር ስር ውሏል። እሳቱ መጀመሪያ ከነበረው ኃይልም እጅጉን ቀንሷል። በዚህ ስራ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የእሳት አደጋ ሰራተኞች ርብርብ አድርገዋል፤ የፀጥታ አስከባሪዎችም በስፍራው ተገስኝተው እገዛ ሲያደርጉ ነበር።

የእሳት አደጋው በሰው እና በንብረት ላይ ምን ጉዳት አስከተለ የሚለውን በነገው ዕለት ይዘን እንመለሳለን!!

#Alex

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በግዝፈቱ ከመርካቶ ቀጥሎ የሚታወቀው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የሚገኘው አቃቂ ገበያ እሁድ ሌሊቱን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል። መነሻው ቅመም ተራ እንደሆነ የተነገረው አደጋው በከፍተኛ ተዳርሶ በርካታ ቁጥር ያላቸው ልብስቤቶች እና ጫማ ቤቶችን አውድሟል።

እሳቱ ከምሽቱ 4 ሰአት በሁዋላ መነሳቱን በአካባቢው ያሉ ነጋዴዎች የተናገሩ ቢሆንም እስከ ሊሊቱ 9 ሰአት ድረስ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቢረባረቡም ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ተስኗቸው ቆይቷል። በአደጋው አትክልት ተራ የሚባለውና እንደ ጌሾ እና በርበሬ እንዲሁም ሌሎች ቅመማ ቀመም የሚሸጥባቸው ቦታዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወድመዋል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች ዘግይተው ቢደርሱም ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

Via #WazemaRadio

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ይኖረናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#10ኛ_ክፍል

አቶ አርዓያ ለTIKVAH-ETH ከደቂቃዎች በፊት በስልክ ይህን ብለዋል፦

"ውጤቱን ይፋ ለማድረግ እየሰራንበት ነው በጨረስን ግዜ በይፋ እናሳውቃለን። ዛሬ፣ ነገም፣ ከነገ በስቲያም አንላችሁም ልክ እንደጨረስን ግን እናሳውቃለን። ሁሉም ሰራተኛ እየተሯሯጠ ይገኛል፤ ስራውንም አጥርተን እየሰራን ነው። ተማሪዎች እና ወላጆች ትንሽ ታገሱን በሉልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን!

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አቃቂ ገበያ ትላንት ሌሊቱን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ።

በኮሚሽኑ በአደጋ ምላሽ ዘርፍ የአደጋ መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ አሳዬ ለኢቢሲ እንደተናገሩት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ህብረተሰቡ ባደርጉት ርብርብብ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በአደጋው ወደ 60 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ቢወድምም 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ማዳን ተችሏል። በአደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተገልጿል።

የደረሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጠጣጠር 15 የአደጋ ተሽከሪካሪዎች ተሰማርተዋል፤ አምስት ቦቲ ተሽከርካሪ፣ አምስት ቀላል ተሽከርካሪ፣ ሁለት አምቡላንስ፣ 552 ሺህ ሊትር ውሃ ፣ ወደ 2 ሺህ ሊትር ፎም እንዲሁም 136 ሰራተኞች እና አመራሮች ተሳትፈዋል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia