TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በወላይታ ዞን ለ182 የፖሊስ  አባላት የማዕረግ እድገት መሰጠቱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ። የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኤፌሶን ላካይቶ እንደገለጹት ለ182 የፖሊስ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት የተፈቀደላቸው ከሀምሌ ወር ጀምሮ መሆኑን ገልጸዋል። የማዕረግ እድገት ካገኙት ውስጥ 18ቱ የሙሉ ኮማንደርነት ማዕረግ ሲሆን ቀሪዎቹ ከረዳት እስከ ዋና ሳጅንነት ያደጉ ናቸው ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ7 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው አሳዛኝ አደጋ!

በትናንትናዉ ዕለት በዳዉሮ ዞን በማረቃ ወረዳ በያማላ ሜሶ ቀበሌ እና በሎማ ወረዳ ሃልአኒ አይሺ ቀበሌ በተከሰተዉ የመሬት መንሸራተት የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በዕለቱ ከጥዋት ጀምሮ ሲጥል በነበረዉ ኃይለኛ ዝናብ መነሻ ስድስት ሰዓት አከባቢ በተከሰተዉ የመሬት መንሸራተት በማረቃ ወረዳ ያማላ ሜሶ ቀበሌ ሁለት ልጆች የአደጋዉ ሰለባ የሆኑ ሲሆን የአንዲት ሴት ልጅ አስክሬን ተገኝቶ የወንዱ በነጋታዉ ተገኝቷል። ከአደጋዉ ምሶሶ ይዛ የአትርፉኝ ጩኸት በማሠማት የተረፈችዉ በአሁኑ ሰዓት በህክምና ላይ ትገኛለች። በተመሣሣይ በሎማ ወረዳ ሃልአኒ አይሺ ቀበሌ አንድ አባት አንድ እናት እና ሦስት ልጆች የአደጋዉ ሰለባ ሆነዋል።

ሌሎች በህይወት የተረፉት በጋሣ መጀመሪያ ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸዉ ይገኛል። በሁለቱ ወረዳዎች እስካሁን በደረሰነዉ መረጃ 15 ሄክታር ማሣ ላይ የሚገኝ ቋሚ እና ተነሽ አትክልት ዕና አዝርዕት ሁለት ቆርቆሮ ቤት ከነ ኩሽናዉ አንድ ሣር ቤት በግምት 25 የሚጠጋ የቤት እንስሣት ላይ አደጋ ደርሷል። የዞኑ አደጋ እና ቅድመ መስጠንቀቂያ ሥራ ሂደት በሁለቱም ቀበሌ ተገኝተዉ ሙሉ መረጃ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

የዳዉሮ ዞነ መንግስት በደረሰዉ የሞትና የንብረት አደጋ የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን ገልጾ እንደ ዞኑ ተጨባጭ ሁኔታ በዘንድሮ ክረምት መጠኑ እየበዛ ባለዉ ዝናብ ምክንያት አደጋዉ እንዳይሰፋ ተዳፋታማ አከባቢ የሚገኙ ህዝቦች ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ምንጭ፦የዳዉሮ ዞን ህዝብ ግኑኝነት ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍2
#HappeningNow

31 የቻይና ዩኒቨርሲቲዎች በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ለአንድ ቀን የሚቆይ ኤግዚቢሽን እያካሄዱ ይገኛሉ። በኤግዚቢሽኑ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን ሁለንተናዊ ትሥሥር በትምህርት ዘርፉም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጁዋን በበኩላቸው ቻይና በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንምትቀጥል ቃል ገብተዋል።

Via #ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በሰማይ ያለው ያዝንላችሁ ዘንድ በምድር ላሉት እዘኑ" [ረሱል ሰ.ዐ.ወ] የNESRA ሀዋሳ ሙስሊም ጀመአ አቅም የሌላቸው ቤተሰብ ልጆች የደብተር ማሰባሰብስ ስራን በመስራት ለማገዝ እየሰሩ ይገኛሉ። 0911964838 0932639747 0935519489

@tsegabwolde @tijvahethiopia
እሁድ ኮምቦልቻ ላይ በመልካም ስራ እያለፈ ነው!

"አርሂቡ ኮምቦልቻወች የከተማውን ወጣት በማስተባበር የአረጋዊያን እና የአቅመ ደካሞችን ቤት በመጠገን ላይ ይገኛሉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምቦ ወጣቶችን አመስግኑልን!

#የአምቦ_ወጣቶች_ማህበር ለወላጅ አልባ ለሆኑና እና ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል። ማህበሩ ከሰሞኑን በአምቦ ከተማ የትምህርት ቁሳቁስ ሲያሰባስብ እንደነበር በTIKVAH-ETH አሳውቀናችሁ ነበር።

"Paakko Tokko Barataa Tokkof"
/አንድ እሽግ ለአንድ ህፃን/
#አምቦ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመኪና ስርቆት ተበራክቷል!

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆነ ወንድማችን ዛሬ አለም ባንክ ኪዳነምህርት አካባቢ የታርጋ ቁጥሩ26313 የሆነ ላዳ ታክሲ ጠፍቶበታል። እንደው ያያችሁ ሰዎች ካላችሁ 0920890310 ወይም 0913795818 ደውሉለት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠንቀቁ የመኪና ስርቆቱ ተበራክቷል!

🚖በአዲስ አበባ ከተማ የመኪና ስርቆቱ መበራከቱን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እየገለፁ ይገኛሉ። ከሶስት ቀን በፊት ካዛንቺስ አካባቢ ያቆሙት መኪና እንደተሰረቀባቸው የነገሩን አንድ የቤተሰባችን አባል እኛን የግጠመን እንዳያጋጥማችሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፖሊስ!?
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወራቤ ከተማ ወጣቶችን አመስግኑልን!

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አልከሶ 01 ቀበሌ ውስጥ የተደረገ የት/ት ቁሰስ ድጋፍ ነው። ወጣቶቹ #የአረጋዊያን ቤቶችንም አድሰዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድን በበጎ ስራ በሻሸመኔ⬆️

"እኛ የሻሸመኔ ከተማ ተምሳሌት የበጎ አድራጎት ማዕከል አዲሱን አመት ከተቸገሩ ነዲያን ጋር በጋራ ለማክበር ዛሬ የሻሸመኔ አራዳ ገቢያ በመዞር ከ35-40kg የሚሆን የሽንኩርት ልገሳ፣ ጤፈ ከ25 kg፣ በርበሬ 5kg፣ ነጭ ሸንኩርት እንዲሁም ገንዘብ ልገሳን አድገናል፡፡ የተለያዩ ነገሮች ዘይት፣ ስጋ ስለሚቀሩን መተባበር ለሚፈልጉ ሰዎች 0926940304 ይደወሉልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አመስግኑልን!

"#በሻሸመኔ ከተማ የሚገኘው ኢንስፓየር የልማት እና የመረዳጃ ማህበር "አንተ ለኔ እኔ ላንተ ልማር" በሚል መሪ ቃል የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ አደም ከማል እንዲሁም የኢንስፓየር ልዩ አባል የሆነው የቀድሞ የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ደስታ ቡኩሉ እና ሌሎች የከተማችን አመራሮች በተገኙበት በ(Cinima9) ከ500 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አበርክተናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርሂቡ ኮምቦልቻ!

አርሂቡ ኮምቦልቻ ከኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለአቅመ ደካሞች የብርድልብስ እና አንሶላ ድጋፍ አድርገዋል በተጨማሪም የትምህርት ቁሳስ ለተማሪዎች አበርክተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እባካችሁ ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ!

ወቅቱ #የበዓል መዳረሻ በመሆኑ ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴው ይጨምራል እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች የትራፊክ መጨናነቅ ስለሚኖር ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ።

ፎቶ፡ ዛሬ አባይ በረሀ የደረሰ አደጋ ነው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰቆጣ ከተማ በተፈጸመ የተኩስ ልውውጥ የአንድ ግለሰብ ህይወት አለፈ!

በሰቆጣ ከተማ በስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ትላንት ሌሊት ከአንድ ግለሰብ ጋር በስህተት በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ የግለሰቡ ህይወት መጥፋቱን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

በከተማው ፖሊስ የጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደባሽ ጌታሁን እንደገለጹት ችግሩ የተፈጠረው በከተማው 02 ቀበሌ ማይ ቡሊት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጳጉሜን 2/2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ላይ ነው።

በጸጥታ ስራ ላይ የተሰማሩ ፖሊሶች እና በግል መሳሪያ የታጠቀ አንድ ግለሰብ መካከል “ማነህ? ማነህ?” በሚል በተካሄደ የተኩስ ልውወጥ በግለሰቡ ላይ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል።

ጉዳት የደረሰበት ግለሰብም ወዲያውኑ ወደ ተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱ መትረፍ እንዳልቻለ ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ችግሩን የፈጠሩት የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-08-2

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 12 የመማር ማስተማር ስራ ይጀምራል!

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተር ዶ/ር አብድልዋሴ ሁሴን #በድጋሚ ለTIKVAH-ETH በስልክ እንዳሳወቁት ተማሪዎች ከመስከረም 5 ጀምሮ ወደ ግቢው መምጣት እንደሚችሉ ጠቁመው ከመስከረም 7-10 ባሉት ቀናት ምዝገባቸውን አከናውነው መስከረም 12 ትምህርት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል።

TIKVAH-ETH ዶክተር አብልዋሴ ሁሴንን ለቀና ትብብራቸው ሊያመሰግናቸው ይወዳል!

TIKVAH ETH MAGAZINE የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎችን ብቻ በዚህ ተከታተሉ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በ2012 ዓ/ም #ስራ የሚጀምረው አዲሱ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ኲሓ የሚገኘው መለስ ካምፓስ #MekUniETH

TIKVAH ETH MAGAZINE የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎችን ብቻ በዚህ ተከታተሉ👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
እሁድ በአዳማ⬆️

"በአዳማ ዛሬ ሴዴቅያስ አረጋውያን መርጃ ማዕከል ወጣቶች ተገኝተን ለአረጋውያን የሚጠቅሙ እቃዋችንን አበርክተናል እንዲሁም የጥበብ ምሽትም በማዘጋጀት አብረናቸው እንኳን አደረሳችሁ ብለናል።"

የመጣችሁ ታዳሚ ተመስግናችኀል! መምጣት እና አረጋውያንን መጎብኘት ለሚፈልጉ ትችላላችሁ ተብሏል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ በመቂ⬆️

"እኛ የ"መልክአ ሰናይ ስለ መቂ አረጋውያን" ህብረት ዛሬ 1ኛ አመት አክብረናል ህብረቱ 23 አረጋውያንን ይዞ የተነሳ ሲሆን ለወደፊቱ ተስፋ የተጣለበት ማህበር ነው።" አሌክ ነኝ ከ መቂ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተበራከተው የመኪና ስርቆት በሸገር!

"እኔም መኪና #ተሰርቆብኝ 1 ወር ሆኖኛል። አስኮ አዲስ ሰፈር ነው የተሰረቀብኝ TOYOTA COROLLA 2003/A85253/እስካሁን አልተገኘም። በጣም ከባድ ሆኗል ከተማችን ውስጥ ያለውን ነገር።" የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia