መኀደረ ጤና
2.39K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#ፕሮጄሪያ (Progeria)

በሌላ ስሙ (HGPS) በመባል የሚታወቀው የአንድን ልጅ ሰውነት በፍጥነት እንዲያረጅ የሚያደርገው የዘር ውርስ ነው አብዛኛዎቹ ይሄ በሽታ ያለባቸው ህፃናት ከ 13 ዓመት በላይ በህይወት መቆየት አይችሉም በሽታው ሁለቱም ፆታዎች እና ሁሉንም ዘር እኩል ያጠቃል በዓለም ዙሪያ ከ4 ሚልዮን ሕፃናት ውስጥ አንድ ሰው በዚህ በሽታ ይጠቃል

በሰዉ አፈጣጠር ወቅት በአንድ ትክክለኛ ሴል ውስጥ አንድ ስህተት ያልተለመደ ፕሮቲን እንዲፈጥር ያደርገዋል ሴሎቹም Progerin ተብሎ የሚጠራውን ይህን ፕሮቲን ሲጠቀሙ, በቀላሉ ይበሰብሳሉ. የፕሮጀርያ ሕጻናት በሚኖሩባቸው በርካታ ሴሎች ውስጥ progerin ከእድሚያቸዉ ፈጥነዉ በአስቸኳይ እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል

#ምልክቶቹ
አብዛኞቹ ልጆች በሚወለዱበት ወቅት ጤናማ ይመስላሉ ነገር ግን በመጀመሪያ ዓመታቸዉ ውስጥ የበሽታ ምልክት ማሳየት ይጀምራሉ. Progeria ያለባቸው ሕፃናት እድገታቸዉ በጣም ዉስን ነው እንዲሁም ክብደት አይጨምሩም

#የአካል #አቀማመጣቸውም #የሚከተሉትን #ይመስላል
👉ትልቅ ጭንቅላት
👉ትልልቅ ዓይኖች
👉ትንሽ ዝቅተኛ አገጭ
👉ከጫፉ ቀጠን ያለ ቀጭን አፍንጫ
👉ትላልቅ ጆሮዎች
👉የሰዉነታቸው ደም ስሮች በግልፅ ይታያሉ
👉ያልተለመደ የጥርስ አበቃቀል
👉በሚናገሩበት ወቅት ቀጭንና ከፍተኛ ድምፅ ያወጣሉ
👉ሰውነትታቸዉ የቅባት እና የጡንቻ ማጣት ይኖራቸዋል
👉የፀጉር መርገፍ, የዐይን ሽፈሽፍት እና ቅንድብን ጨምሮ
ከ progeria ጋር የሚኖሩ ህፃናት ቶሎ ነው የሚያረጁት ከ 50 አመት በላይ ሊይዙን ይችላሉ በሚባሉ በሽታዎች ይያዛሉ እንደ #የአጥንት መሳሳት #የደም ስሮች በሽታ #የልብ በሽታ
#የኩላሊት በሽታን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች ይጠቃሉ የ Progeria ህመም ያለባቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ በልብ ድካም ወይም በኩላሊት በሽታ ይሞታሉ
በዚህ በሽታ የተጠቁ ልጆችን የማሰብ ችሎታ ወይም የአእምሮ እድገታቸዉ አይጎዳም ችግሩ ያለበት ልጅ ከሌሎች ልጆች ይልቅ በቸለያዩ በሽታዎች የመያዝ ዕድሉ ከፍተኛ ነው.

#Progeria #ምርመራ

የበሽታው ምልክቶቹ በደንብ የሚታዩ ስለሆነ በተለመደው የክትትል ወቅት የልጅዎ የህፃናት ሐኪም ሊያያቸው ይችላል.

በ Progeria ህመም የተያዙ የሚመስሉ ልጆችን የተለያዩ ለውጦችን ከተመለከቱ ከርስዎ ከሀፃናት ሀኪም ጋር መነጋገር የተለያዩ አካላዊ ምርመራ ይደረግላቸዋል, የእይታ ብቃታቸዉ የልብ ምታቸውንና የደም ግፊትን ይለኩእና የልጅዎን ቁመት እና ክብደት እኩዮቹ ተመሳሳይ ዕድሜ ጋር ያወዳድራሉ ከዚያ በኋላ የሕፃናት ሐኪምዎ አሳሳቢ ከሆነ በደም ምርመራ አማካኝነት የምርመራውን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ የሕክምና ባለሙያዎችን ሊያናግር ይችላል.

#ሕክምናዎች

አሁን ባለንበት ግዜ ለ Progeria በሽታ መድኃኒት አልተገኘለትም, ነገር ግን ተመራማሪዎች አንዱን
ለየካንሰር ህመም መድሐኒት የሆነውን በመጠቀምFTI (farnesyltransferase inhibitors), የተጎዱ ሕዋሶችን ሊያስተካክሉ ይችላሉ. #መድሃኒቶች ብዙውን ጊዜ የበሽታውን ምልክቶች ሊያዘገዩ ይችላሉ.
#መድሃኒት የልጅዎ ሀኪም መድሃኒቶች ሊያዝዙ ይችላሉ ዝቅተኛ የኮሌስትሮል መጠን እንዲኖር ወይም የደም መፍሰስን ለመከላከል አነስተኛ መጠን ያለዉ በየቀኑ
#አስፕሪን የልብ ሕመምን ለመከላከል ይረዳል. #የእድገት ሆርሞኖች ይሰጣሉ ቁመት እና ክብደት ለመገንባት ይረዳሉ
#የሰውነት እንቅስቃሴ (ቴራፒ) ህመም ለልጅዎ ጠንካራና የማይተጣጠፍ መገጣጠምያ እንዳይኖረዉ ይረዳዋል
#ቀዶ #ጥገና የአንዳንድ ልጆችን የልብ ሕመምን ለማዘግየት ለመቀነስ የልብ ቀዶ ጥገና ይደረግላቸዋል
#በቤት #ውስጥ #የምናደርግላቸዉ በProgeria በሽታ የተያዙ ልጆች የሰዉነታቸዉ የዉሀ መጠን በጣም ስለሚቀንስ ስለሆነም ብዙ #ውሃ #መጠጣት አለባቸው.
#ምግቦችን በሰአቱ እንዲበሉ ማበረታታት
ልጅዎ ንቁ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ማበረታታት

#መልካም #ጤና
#ግላውኮማ(Glaucoma)

#ግላውኮማ የምንለው የአይን ህመም በአይናችን ነርቭ ላይ ችግር የሚያስከትል ሲሆን በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት መጨመር ምክንያት የሚከሰት ነው። የዚህ ግፊት መጨመር በአይናችን የምናያቸውን ምስሎች ወደ አንጎል የሚውስደውን የአይናችንን ነርቭ ይጎዳል ይህም በቀጣይነት ቋሚ ለሆነ የአይን ብርሃንን እጦት ይዳርጋል።

#የግላኮማ #ዓይነቶች #ምንድ #ናቸው?

🔘ሁለት ዋነኛ ዓይነቶች አሉ

👉Open-angle glaucoma በጣም የተለመደ ዓይነት ነው በዓይናችን ውስጥ ያለውን የውኃ ማስተላለፊያ አካል trabecular meshwork ተብሎ የሚጠራዉ ጤናማ ይመስላል, ግን ፈሳሹ እንደ ልብ አይንቀሳቀስም
👉Angle-closure glaucoma. በምዕራቡ ዓለም በእስያ እንጂ በስፋት የተለመደ አይደለም በአይንዎ መካከል ያለው ፍሰት በጣም ጠባብ ስለሚሆን ዓይንዎ በትክክል አይሰራም. ይህ በአይኑ ውስጥ ድንገተኛ መጨናነቅ ሊያስከትል ይችላል. በተጨማሪም በአይንዎ ውስጥ ያለውን ሌንስ ጭጋግ መሰል ነገር ያለብሰዋል

👉ግላውኮማ በሚጀምርበት ጊዜ የሚያሳየው ቀዳሚ ምልክት ወይንም የህመም ስሜት ስለሌለ ማንኛውም ሰው መደበኛ የሆነ የአይን ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው ይህም አይናችን ለከፋ ጉዳት ከመጋለጡ በፊት ህክምና እንድናደርግለት ይረዳናል። ከ40 አመት እድሜ በላይ ያሉ ሰዎች በአመት አንድ ጊዜ ወደ ሃኪም በመሄድ ምርመራን ማድረግ አለባቸው።

#የአይናችን #ውስጥ #ግፊት #ለምን #ይጨምራል?

🔘ግላውኮማ የሚከሰተው በአይናችን ውስጥ የሚገኘው ግፊት ሲጨምር ነው ያልን ሲሆን ይህደግሞ
👉በኢንፌክሽን
👉በአይን በቀዶ ጥገና ምክንያት በፊተኛው የአይናችን ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ በጤናማ ሁኔታ መንሸራሸር ሲያዳግተው ነው።
ግላውኮማ በአብዛኛው ሁለቱንም አይነቶች የሚያጠቃ ሲሁን የህመሙ ክብደት ግን ሊለያይ ይችላል።
#በግላውኮማ #የሚጠቁ #እነማን #ናቸው?

👉ከአርባ አመት እድሜ በላይ የሆኑ
👉በግላውኮማ የተጠቃ ቤተሰብ ያላቸው
👉የስኳር ህመምተኞች
👉የአይን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች

#የግላውኮማ #ህመም #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው?

🔘በአብዛኛው ግላውኮማ በቅድሚያ የህመም ምልክት ላያሳይ ቢችልም ከጊዜ በሗላ ግን የመጀመሪያ ምልክት የሚሆነው
በጥግ በኩል የሚጀምር የአይን ብርሃን ችግር ነው።
#ከምልክቶቹ #ውስጥ
👉ድንገተኛ የሆነ የአይን ህመም
👉ከፍተኛ የራስ ምታት
👉የአይን ብዥታ
👉ጥርት ያለ እይታ አለመኖር
👉የአይን መቅላት
👉የአይን ብርሃን ማጣት
👉የአይን እይታ ጥበት ናቸው
እነዚህ ሁኔታዎች ሲያጋጥምዎ በአፋጣኝ ወደ አይን ሀኪም መሄድ ይጠበቅቦታል።

#ግላውኮማን #መከላከል #ይቻላል?

🔘ግላውኮማ እንዳይከሰት መከላከል የማንችል ሲሆን ነገር ግን በቶሎ የህመሙ መኖር ከታወቀ ለመቆጣጠርና እንዳይባባስ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።
በግላውኮማ ምክንያት የተከሰተ የአይን ብርሃን ጉዳት ተመልሶ ሊስተካከል የማይችል ሲሆን የነበረው ጉዳት እየተባባሰ እንዳይሄድ ግን የአይን ግፊት መጠኑን መቀነስ ይቻላል። ህክምናቸውን በሚገባ የሚከታተሉ ታካሚዎች የአይን ብርሃናቸውን ማዳን ይችላሉ።

#መልካም #ጤና
#የአፍ #መድረቅ ( Xerostomia)

#የአፍ #መድረቅ #ችግሮች #ምክንያቶችና #መፍትሄዎቻችው

#የአፍ መድረቅ ችግር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ምራቅ አመንጪ እጢዎች (salivary glands) ምራቅን በበቂ ሁኔታ ማመንጨት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት ነው።
ምራቃችን በ አፋችን ውስጥ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የጥርስ መቦርቦር እንዳይፋጠር የሚራዳ ሁኔታን ያመቻቻል። ከዚህም በተጨማሪ ምግብን አላምጦ የመዋጥ ሂደትን እንድናደርግና ለምግብ መፈጨት ሂደት የሚያስፋልጉ ኤንዛየምስ የማመንጨት ተግባርን ያከናውናል።
የምራቅ መመንጨት በሚቀንስ ጊዜ የ አፍ መድረቅ ይከሰትና ጤናችንን ሊያቃውስ ይችላል።

#የአፍ #መድረቅ #ምልክቶች #ምንድን ናቸው?

👉አፋችን ውስጥ የማጣበቅ ስሜት ሲሰማን
👉መጥፎ የአፍ ጠረን
👉ለማላመጥ ፣ ለመዋጥ እና ለመናገር መቸገር
👉የጉሮሮ መሻከር ወይንም ቁስለት
👉የምግብ ጣዕም ማጣት ናቸው።

#የአፍ #መድረቅ #የሚያስከትሉ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?

👉የአፍ መድረቅ የሚመጣው ምራቅ አመንጪ እጢዎች በሚፈለገው መጠን ምራቅን ማመንጨት ሲያቆሙ ነው ለዚህም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እናያለን።
👉 መድሃኒቶች
አብዛኛዎቹ መድሀኒቶች የአፍ መድረቅ የጎንየሽ ጉዳታቸው እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ለመደበት፣ጭንቀት እና አንዳንድ የአለርጂ መድሀኒቶች ይጠቀሳሉ።
👉እድሜ
እድሜአችን በጨመረ ቁጥር የተለያዩ አካላዊ ለውጦችን ተከትሎ የ አፍ መድረቅም የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው።
👉የነርቭ ጉዳት
በጭንቅላት እና አንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች በሚጎዱ ጊዜ የአፍ መድረቅ በተያያዥነት ሊመጣ ይችላል።
👉ሲጋራ ማጨስ፣ የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መውሰድና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን መጠቀም የአፍ መድረቅን ያስከትላል።
👉ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ
ካንሰርን ለማከም የሚሰጡ ህክምናዎች የ አፍ መድረቅን ለጊዜያዊ ወይንም በቋሚነት ሊያስከትሉ ይችላል።
👉ሌሎች የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ፣የስኳር ህመም፣ስትሮክ፣የፈንገስ ኢንፌክሽን የመሳስሉ ህመሞች ለአፍ መድረቅ ችግር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
👉ማንኮራፋትና አፍን ከፍቶ መተንፈስ ሌሎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።

#ከአፍ #መድረቅ #ጋር #በተያያዘ #የሚመጡ #ሌሎች #ችግሮች #ምንድን #ናቸው?

👉የጥርስ መቦርቦር እና የድድ ህመም
👉የከንፈር ቁስለት
👉የፈንገስ ኢንፌክሽን
👉የከንፈር መሰነጣጠቅ
👉የክብደት መጠን መቀነስ ናቸው።
አንድ ሰው የአፍ መድረቅ ሲያጋጥመው ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል። ከዛም እንዳስፈላጊነቱ መድሀኒት እንዲውስዱ ይደረጋል።

#የአፍ #መድረቅ #እንዲቀንስልን #በቤት #ውስጥ #ልንጠቀማቸው #የምንችላቸው #ነገሮች #ምንድን #ናቸው?

👉ውሀን ይጎንጩ
ውሀን መጎንጨት የዘወትር ልማር ማድረግ፣ ምግብ በሚመገቡ ጊዜ ለማላመጥ እና ለመዋጥ እንዳይችሉ በውሃ ማወራረድ።
👉በአፍንጫዎ ብቻ ይተንፍሱ
የማንኮራፋት ችግር ካለብዎና ሌሊት አፍዎን ገጥመው መተኛት ካልቻሉ ለማንኮራፋቱ ሀኪምን ያማክሩ።
👉ከስኳር ነጻ የሆኑ ማስቲካ ወይንም ከረሜላ መጠቀም
👉ከንፈርዎን ቫዝሊን ወይንም የከንፈር ቅባት በመቀባት ያለስለሱ።

እንደተለመደዉ መረጃዉ ከተመቾት ላይክ 👍 ማረጎን አይርሱ

#መልካም #ጤና