መኀደረ ጤና
2.59K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#የአፍ #መድረቅ ( Xerostomia)

#የአፍ #መድረቅ #ችግሮች #ምክንያቶችና #መፍትሄዎቻችው

#የአፍ መድረቅ ችግር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ምራቅ አመንጪ እጢዎች (salivary glands) ምራቅን በበቂ ሁኔታ ማመንጨት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት ነው።
ምራቃችን በ አፋችን ውስጥ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የጥርስ መቦርቦር እንዳይፋጠር የሚራዳ ሁኔታን ያመቻቻል። ከዚህም በተጨማሪ ምግብን አላምጦ የመዋጥ ሂደትን እንድናደርግና ለምግብ መፈጨት ሂደት የሚያስፋልጉ ኤንዛየምስ የማመንጨት ተግባርን ያከናውናል።
የምራቅ መመንጨት በሚቀንስ ጊዜ የ አፍ መድረቅ ይከሰትና ጤናችንን ሊያቃውስ ይችላል።

#የአፍ #መድረቅ #ምልክቶች #ምንድን ናቸው?

👉አፋችን ውስጥ የማጣበቅ ስሜት ሲሰማን
👉መጥፎ የአፍ ጠረን
👉ለማላመጥ ፣ ለመዋጥ እና ለመናገር መቸገር
👉የጉሮሮ መሻከር ወይንም ቁስለት
👉የምግብ ጣዕም ማጣት ናቸው።

#የአፍ #መድረቅ #የሚያስከትሉ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?

👉የአፍ መድረቅ የሚመጣው ምራቅ አመንጪ እጢዎች በሚፈለገው መጠን ምራቅን ማመንጨት ሲያቆሙ ነው ለዚህም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እናያለን።
👉 መድሃኒቶች
አብዛኛዎቹ መድሀኒቶች የአፍ መድረቅ የጎንየሽ ጉዳታቸው እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ለመደበት፣ጭንቀት እና አንዳንድ የአለርጂ መድሀኒቶች ይጠቀሳሉ።
👉እድሜ
እድሜአችን በጨመረ ቁጥር የተለያዩ አካላዊ ለውጦችን ተከትሎ የ አፍ መድረቅም የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው።
👉የነርቭ ጉዳት
በጭንቅላት እና አንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች በሚጎዱ ጊዜ የአፍ መድረቅ በተያያዥነት ሊመጣ ይችላል።
👉ሲጋራ ማጨስ፣ የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መውሰድና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን መጠቀም የአፍ መድረቅን ያስከትላል።
👉ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ
ካንሰርን ለማከም የሚሰጡ ህክምናዎች የ አፍ መድረቅን ለጊዜያዊ ወይንም በቋሚነት ሊያስከትሉ ይችላል።
👉ሌሎች የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ፣የስኳር ህመም፣ስትሮክ፣የፈንገስ ኢንፌክሽን የመሳስሉ ህመሞች ለአፍ መድረቅ ችግር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
👉ማንኮራፋትና አፍን ከፍቶ መተንፈስ ሌሎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።

#ከአፍ #መድረቅ #ጋር #በተያያዘ #የሚመጡ #ሌሎች #ችግሮች #ምንድን #ናቸው?

👉የጥርስ መቦርቦር እና የድድ ህመም
👉የከንፈር ቁስለት
👉የፈንገስ ኢንፌክሽን
👉የከንፈር መሰነጣጠቅ
👉የክብደት መጠን መቀነስ ናቸው።
አንድ ሰው የአፍ መድረቅ ሲያጋጥመው ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል። ከዛም እንዳስፈላጊነቱ መድሀኒት እንዲውስዱ ይደረጋል።

#የአፍ #መድረቅ #እንዲቀንስልን #በቤት #ውስጥ #ልንጠቀማቸው #የምንችላቸው #ነገሮች #ምንድን #ናቸው?

👉ውሀን ይጎንጩ
ውሀን መጎንጨት የዘወትር ልማር ማድረግ፣ ምግብ በሚመገቡ ጊዜ ለማላመጥ እና ለመዋጥ እንዳይችሉ በውሃ ማወራረድ።
👉በአፍንጫዎ ብቻ ይተንፍሱ
የማንኮራፋት ችግር ካለብዎና ሌሊት አፍዎን ገጥመው መተኛት ካልቻሉ ለማንኮራፋቱ ሀኪምን ያማክሩ።
👉ከስኳር ነጻ የሆኑ ማስቲካ ወይንም ከረሜላ መጠቀም
👉ከንፈርዎን ቫዝሊን ወይንም የከንፈር ቅባት በመቀባት ያለስለሱ።

እንደተለመደዉ መረጃዉ ከተመቾት ላይክ 👍 ማረጎን አይርሱ

#መልካም #ጤና