መኀደረ ጤና
2.59K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#እርግዝናን #የመከላከያ #መንገዶችና #እውነታቸው

ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከልና ራስዎን ከአባላዘር በሽታዎች ለመጠበቅ ሲባል የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀሙ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የእነዚህን መከላከያዎች እውነታዎች አውቆና ተረድቶ ጥቅም ላይ ማዋል እጅግ ጠቀሜታ ይኖረዋል
#በወር #አበባ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ቢደረግ #እርግዝና (ይከሰት #ይሆን ?
👉የወር አበባን በምታይ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት የማርገዝ ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አይከሰትም ለማለት አይቻልም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የወር አበባ ከማለቁ በፊት እንቁላል ሊፈጠር ስለሚችልና ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር በማኅፀን ውስጥ እስከ 3 ቀን ወይንም ከዚያ በላይ የሚቆይበት አጋጣሚ ስለሚኖር ነው፡፡
#ጡት #ማጥባት #እርግዝናን #ይከላከላል ?
👉ጡት ማጥባት የእንቁላል መፈጠርን የሚከላከል ቢሆንም የሚቆይበት ጊዜ ግን ለጥቂት ወራት ብቻ ስለሆነ ሰውነት ወደቀድሞ ሁኔታው በሚመለስ ጊዜ የማርገዝ ዕድልም አብሮ ስለሚመለስ ጡት ማጥባት እርግዝናን የሚከላከልብት ጊዜ ውስን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
#የመጀመሪያ #ጊዜ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ማድረግ #ላልተፈለገ #እርግዝና #ያጋልጣል ?
👉አዎን! ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላልተፈለገ እርግዝና ላያጋላጥ ይችላል ብለው የሚያስቡ አንዳንዶች ያሉ ቢሆንም ይህ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ሕመምና ደም መፍሰስ ሊያጋጥም የሚችል ቢሆንም እርግዝናን ከመከላከል ጋር ግን ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቀቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ምን #ያህል #እርግዝናን #ይከላከላሉ ?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በትክክለኛው መንገድ ከተተገበሩ ከ90% በላይ የሚሆን የመከላከያ አቅም ያላቸው ሲሆን ተአቅቦ ግን ጥርጥር የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጣሪያ ለመጠቀም በሚታሰብ ጊዜ የትኛውን ዓይነት እንደምንመርጥና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሐኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
#በግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ጊዜ #ሁለት #ኮንዶሞች #ደርቦ #መጠቀም #በእርግጥ #እርግዝናን #የበለጠ #ይከላከላል ?
👉አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሁለት ኮንዶምን ደርቦ በመጠቀም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ሲሆን ይባስ ብሎ በሚፈጠረው ፍጭት (Friction) ምክንያት የኮንዶም መቀደድ በማስከተል ላልተፈለገ እርግዝና ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥን ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሁለት ኮንዶሞችን ደርቦ መጠቅም አይመከርም፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎችን #መውሰድ #ወዲያውኑ #እርግዝናን #ይከላከላል?
👉የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች አጠቃቀም እና የሚወሰዱበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ እርግዝናን ለመከላከል ጠቃሚ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወር አበባ በመጣ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን ውስጥ መጀመር ወዲውኑ ከአልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ሲሆን፣ ከዚያ ጊዜ ውጭ ከመጀመሩ ግን ወዲያውኑ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው ኮንዶምን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
#ሁሉም #የወሊድ #መቆጣጠሪያዎች #ከአባለዘር #በሽታዎች #ይከላከሉ #ይሆን ?
👉ከወሊድ መቆጣጠሪያዎች ውስጥ ኮንዶምን መጠቀም ብቻ ከአባላዘር በሽታ ራስን መከላከል የሚቻልበት ዋነኛው መንገድ ነው፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያ #እንክብሎች #የሰውነት #ክብደት #ይጨምራሉ ?
👉አንዳንድ ሴቶች የሰውነት ክብደት መጨመርን እንዳስከተለባቸው የሚናገሩ ሲሆን ምክንያቱም የምግብ ፍላጎትን መጨመርን ማስከተሉና ፈሳሽ በሰውነታችን እንዲቀመጥ ማድረጉ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠነኛ የሚባል የሰውነት ክብደት መጨመርን ያስከትላሉ፡፡
#የወሊድ #መቆጣጠሪያን #መጠቀም #መሃንነትን #ያስከትላል?
👉አያስከትልም! ሆርሞኖችን በውስጣቸው የያዙ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ መሃንነትን ያስከትላሉ ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም እነዚህን የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መካንነትን እንደማያስከትሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡
#ኮንዶምን #በሌሎች #ቁሳቁሶች #መተካት #ይቻላል?
👉በፍፁም አይቻልም! በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በሌሎች እንደ ላስቲክ፣ ፈኛ፣እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ተክቶ መጠቀም በፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ከአልተፈለገ እርግዝናም ሆነ ከአባላዘር በሽታም በጭራሽ እንደማይከላከል ሊያውቁት ይገባል

#መልካም #ጤና
#ለእርግዝና #የሚረዱ #ጥሩ #የግብረ #ሥጋ #ግንኙነት #ልምዶች

እርግዝና እንዲፈጠር #ወሲብ ከማዝናናት በላይ መሆን አለበት የማርገዝን አጋጣሚ ከፍ ለማድረግ በአልጋ ላይ ሁሉንም ነገር ማድረግ ያስፈልጋል።

እርግዝናን ለመፍጠር ምንም ዓይነት ዘዴ አልተገኘም. ሆኖም ግን በተወሰነ የግኑኝነት ተደጋጋሚነት በመጨመርና ግኑኝነት ላይ ጥቂት ለውጦችን በማድረግ እርግዝና የመከሰት እድልን ሊያሳድጉ ይችላሉ

👉 #ስፐርም (የወንድ የዘር ፍሬ)
እርግዝናን በሚያስቡበት ወቅት ሰው ሰራሽ ማለስለሻዎችን መጠቀም በፍጹም አይመከርም የዚህም ምክንያት ለወንድ የዘር ፈሳሽ ጎጂ ስለሆነ ነው፡፡ አንዳንድ ሴቶች የጥሬ ዕንቁላል ነጭ ክፍሉን እንደ ማለስለሻ ይጠቀሙበታል በዚህ አጋጣሚ እንቁላሉ የተበላሸ ከሆነ ኢንፌክሽን ሊከሰት ይችላል፡፡ የምህጸን በር ፈሳሽ ንፍጥን ለመጨመር ውሃ በብዛት መጠጣት
👉 #አቅጣጫ (ፖዚሽን)!
በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ወንድ ከላይ ሆኖ በሚያደርግበት ወቅት ለማህፀን በር ቅርብ ከመሆኑ አንፃር በጣም ተመራጭ አቅጣጫ ነው፡፡ በመሬት ስበት አማካይነት ሴቶች ከላይ የሚሆኑበት የግብረ ስጋ ግንኙነት አቅጣጫ በጣም ጎጂና ተመራጭ ያልሆነ ነው፡፡
👉 #በጀርባ #መንጋለል (መተኛት)!
አንዳንድ ሴቶች እንደሚሰጡት አስተያየት ከግኑኝነት በኋላ በዳሌያቸው ስር ትራስ አስገብቶ አልጋ ላይ በጀርባ ተኝቶ እግርን ልክ ብስክሌት እንደሚነዱ ከፍ በማድረግ ቢይንስ ለ 20 ደቂቃ መቆየት ጠቃሚ ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ሴቶች ደግሞ ቢያደርጉም ባያደርጉም ለውጥ እንደሌለው ይናገራሉ ምርጫው የእርስዎ ነው ዋናው ቁምነገር ግን ለ 20 ደቂቃ በጀርባዎ ተጋድመው የሚቆዩ ከሆነ ሊወጣ ወይም ሊወገድ የሚችለው ጤናማ ያልሆነ ስፐርምና የሴመን ፈሳሽ ነው፡፡ ጤናማ የስፐርም (የወንድ የዘር ፈሳሽ) ወደ ሴት ሃፍረተ ስጋ ውስጥ ከተረጨ በኋላ ወዲያው ወደ ማህጸን ይጓዛል ስለዚህ ከሴት ሃፍረተ ስጋ መርዛማ አካባቢ ይርቃል፡፡
👉 #የጡንቻዎች #ጥንካሬ
የሴት ሃፍረተ ስጋ ጡንቻዎችን ከመጨመር ባሻገር ኬግልስ የሚባለው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በሴት ሃፍረተ ስጋ ውስጥ የቀረውን የወንድ የዘር ፍሬ ወደ ውስጥ ለማስገባት መሥራት ጠቃሚ ነው፡፡
(ኬግልስ) ማለት የሴትዋ ብልት አካባቢ ያሉትን ጡንቻዎች ስፖርት ማሰራት ነዉ ማለትም ሴቷ በራሷ ከግኑኝነት በኋላ ያዝ ለቀቅ እያደረገች ለ 5 ደቂቃ መስራት ነዉ ታዲያ በዚህ ጊዜ ሽንትዎን መሽናት የለቦትም፡፡

#መልካም #ጤና

ከተመቾ👍