ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
በድረ ገጻችን ላይ ለሚገኘው የቁርአን ግጭቶች ዝርዝር መልስ ለመስጠት በሞከረ አንድ ሙስሊም ጸሐፊ የተዘጋጁትን ምላሾች መፈተሻችንን ቀጥለናል፡፡ ለጥያቄ ቁጥር 36 እና 37 የሰጠውን ምላሽ እንዲህ ተመልክተናል፡፡
የዒሳ “አፈጣጠር” እንደ አዳም ከአፈር ወይስ በልደት?
http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-36/
ዒሳ ፈጣሪ ነው ወይስ አይደለም?
http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-contra-37/
1
2ጴጥሮስ 1:1

ይህ የመፅሓፍ ቅዱሳችን ክፍል በግራንቪል ቫርፕ የግሪክ definite article አጠቃቀም ሕግ መሰረት የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክነት ከሚያረጋግጡ ክፍሎች ውስጥ አንደኛው ነው። ስለዚህ ሕግ ከዚህ በፊት አይተን ስለነበረ እሱን መለስ ብላቹ ማንበብ ይቻላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሙስሊም ሰባኪያን ይሄን ክፍል ለማጣጣል ሙከራ ማድረጋቸውን ተገንዝበናል። ምንም ያህል ሙግታቸው ውሃ የማያነሳ፣ እውቀት የጎደለውና ቅጥፈት የሞላበት ቢሆንም መልስ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ከሙስሊም ሰባኪያን ሁሌ በማያውቀው ነገር ገብቶ ለሚበጠብጠው አንዱ ሰባኪ የሰጠነው መልስ እንደሚከተለው ነው።

የልጁ ሙግት እንዲህ ብሎ ይጀምራል

“...በ 330 ድኅረ-ልደት በተዘጋጀው በኮዴክስ ሳይናቲከስ እና በ 350 ድኅረ-ልደት በተዘጋጀው በኮዴክስ ቫቲካነስ መካከል የቃላት ሆነ የአሳብ ልዩነት አላቸው፥ ፊተኛው ኮዴክስ ሳይናቲከስ ያዘጋጁት ኢየሱስን "ጌታችን" ሲሉት ኃለኛው ኮዴክስ ቫቲካነስ ያዘጋጁት ደግሞ "አምላካችን" ብለውታል፦”

መልስ

በመጀመሪያ ደረጃ፣ ይሄ ልጁ የሰጠው የእድሜ ቁጥር(dating) ከየት እንዳመጣው አይታወቅም። ኮዴክስ ሳይናይቲከስ ከየት አምጥቶ ነው ኮዴክስ ቫቲካነስ በላይ እረጅም እድሜ የኖረው? ይሄ ልጅ ለራሱ ሙግት እንዲጠቅመው አውቆ እየዋሸ ነው ወይም ደግሞ አያውቅም ማለት ነው። ደረጃቸውን የጠበቁ የቴክስቿል ክሪትሲዝም መፅሓፍት እንደሚገልፁት፣ እነኚህ ሁለቱ እደ ኪታባት በእድሜ ቢቀራረቡ እንኳን ኮዴክስ ቫቲካነስ እንደሚቀድም(the oldest) መሆኑን ይገልፃሉ። ለምሳሌ J.K.Elliot, New Testament Textual Criticism: The Application of Thoroughgoing Principles, page 65 ላይ እንዲህ ብሎ ፅፏል “Cavallo suggested dates of 350(A.D)for codex Vaticanus and 360 for codex Sinaiticus..” ስለዚህ በግልፅ ኮዴክስ ቫቲካነስ ቀድሞ የተፃፈ መሆኑን እንረዳለን። ክርስትናን የማይቀበለው ታወቂው ምሁር ባርት ሔርማን(Bart Ehrman) እንኳን በመፅሃፉ ውስጥ ስለ ማርቆስ 1:41 ሲያወራ (ይህ ክፍል በሁለቱም ኮዴክሶች ውስጥ ቢኖርም) ኮዴክስ ቫቲካነስ የበለጠ ረጅም እድሜ እንዳለው ይናገራል። (Bart D.Ehrman, studies in the textual criticism of the new testament, 2006: page 123)። ስለዚህ፣ ሳይናይቲከስ ቀድሞ የተፃፈ ነው የሚለው ሙግት ውሸት መሆኑን ካሁኑ ደምድመን አለፍን ማለት ነው።

ይሚቀጥለው የልጁ ሙግት እንዲህ ይላል:-

2ኛ ጴጥሮስ 1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ *በጌታችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ* ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ። ϲυμεων πετροϲ δουλοϲ και αποϲτο λοϲ ιυ χυ τοιϲ ϊϲο τιμον ημιν λαχου ϲιν πιϲτιν ειϲ δι καιοϲυνην του κυ ημων και ϲωτη ροϲ ιυ χυ

እዚህ አንቀጽ ላይ በኮዴክስ ሳይናቲከስ "ኮዩ" κυ ብሎታል፥ "ኮዩ" የሚለው ቃል "ኩስ" κος ለሚለው አገናዛቢ ዘርፍ ሲሆን "ጌታችን" ማለት ነው። "ኩስ" κος የሚለው "ኩርዮስ" κύριος ማለትም "ጌታ" ለሚለው ምጻረ ቃል ነው። ቀጣዩን ልዩነት ደግሞ እንመልከት፦
2ኛ ጴጥሮስ 1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ *በአምላካችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ* ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ። ϲυμεων πετροϲ δουλοϲ και αποϲτο λοϲ ιυ χυ τοιϲ ϊϲο τιμον ημιν λαχου ϲιν πιϲτιν ειϲ δι καιοϲυνην του θυ ημων και ϲωτη ροϲ ιυ χυ

እዚህ አንቀጽ ላይ በኮዴክስ ቫቲካነስ "ቶዩ" θυ ብሎታል፥ "ቶዩ" የሚለው ቃል "ቴስ” Θς ለሚለው አገናዛቢ ዘርፍ ሲሆን "አምላካችን" ማለት ነው። "ቴስ” Θς የሚለው “ቴኦስ” θεός ማለትም "አምላክ" ለሚለው ምጻረ ቃል ነው።
ታዲያ የቱ ነው ትክክል? ስንል ኮዴክስ ሳይናቲከስ በእድሜ ኮዴክስ ቫቲካነስን በ 20 ዓመት ስለሚበልጥ የቀደመው በአንጻራዊ ተአማኒት አለው።


መልስ

1. ቅድም እንዳረጋገጥነው፣ ኮዴክስ ቫቲካነስ በእድሜ ከሳይናይቲከስ ይበልጣል እንጂ አያንስም። ይሄ ኡስታዝ ተብዬ ግን እንዴት ለራሱ ሙግት ብሎ እንደሚዋሽ እዩት። በሱ ሙግት እንሂድ ካልን፣ ቫቲካነስ በእድሜ ስለሚበልጥ የበለጠ ተቀባይነት ስለሚኖረው “#በአምላካችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ” የሚለው ትርጉም ትክክል ነው ማለት ነው።

2. ሲጀምር፣ የእደ ክታባቱን ትክክለኛነት ወይም ተቀባይነት ለመረዳት እድሜ ብቻ በቂ አደለም። የፀሓፍቱ (scribes, copyist) ጥንቃቄና ትክክለኛነት(accuracy) በጣም አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ኮዴክስ 1739 የሚባለው ማኑስክሪፕት የ10th century እደ ኪታብ ቢሆንም እጅግ በጥንቃቄ የተፃፈ በመሆኑ እንደ 3ኛ፣ 4ኛ ወይም 5ኛ ም.አመት ማኑስክሪፕት ነው የሚታየው።

3. ኮዴክስ ቫቲካነስ ደግሞ ከሳይኒቲከስ ሲወዳደር እጅግ በጣም ፅዱ፣ ስርዝ ድልዝ ያልበዛበትና ንፁህ ተብሎ ነው የሚታወቀው። በሱ ላይ ደግሞ p75 ከሚባለው በጣም ጥንታዊ ማኑስክሪፕት(ሳይናቲከስ እና ቫቲካነስን በ~150 አመት የሚቀድም) ጋር ተቀራራቢ ከመሆኑ የተነሳ ተመሳሳይ ምንጭ (common ancestors) እንዳላቸው ይነገራል። ይህ ደግሞ ቫቲካነስ ከሳይናይቲከስ ይበልጥ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርገዋል። ላስነብባቹ:-
4. Eldon Jay Epp, Perspectives on New Testament Textual Criticism Collected Essays, 1962-2004; 2005 page 154 ላይ እንዲህ ይላል “...Codex Vaticanus holds a unique position since its text is not only pre-Syrian but substantially free from Western and Alexandrian adulteration......moreover, vaticanus very far exceeds all other documents in neutrality of text....codex Sinaiticus is next in purity among all other manuscripts..” ይህ ክፍል የሚነግረን፣ ኮዴክስ ቫቲካነስ ከሁሉም ማኑስክሪፕቶች የበለጠ ተዓማኒና ንፁህ መሆኑን ነው። ሳይናይቲከስ ደግሞ ከእሱ የሚቀጥል እንደሆነ ነው። በዚህው መፅሓፍ ገፅ 339 ላይ እንዲህ ይላል “...Original text is to be found in the best manuscripts, and the best manuscripts are, FIRST, CODEX VATICUNUS & SECONDARILY;CODEX SINAITICUS...” “..ኦሪጅናል ፅሁፎች የሚገኙት ምርጥ የሚባሉ እደ-ኪታባት ውስጥ ሲሆኑ፣ ምርጥ የሚባሉ ደግሞ #በመጀመሪያ_ደረጃ ቫቲካነስ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ሲናይቲከስ ነው..”
page 338 ላይ እንዲህ ይላል “..texts of p75 and codex vaticanus are almost identical, a fact that demonstrates that there is virtually a straight line from...
the text of a papyrus dated around 200A.D to that of a major, elegant manuscript of 150 years later...”

5. ታላቁ የዘመናችን የግሪክ ግራመር እና ቴክስቿል ክሪትሲዝም ምሁር ፕሮፌሰር ዳንኤል ዋላስ Jesus as Theos የተሰኘ አርቲክላቸው ውስጥ እንዲህ ብለው ፅፏል:-

"Second Peter 1.1 is another NT verse potentially calling Jesus θεός. Some MSS (a Ψ 398 442 621 l596 syrph vgmss copsa)136 read κυρίου instead of θεοῦ in v. 1:

ἐν δικαιοσύνῃ τοῦ θεοῦ
ἡμῶν καὶ σωτῆρος Ἰησοῦ Χριστοῦ


ἐν δικαιοσύνῃ τοῦ κυρίου ἡμῶν καὶ σωτῆρος Ἰησοῦ Χριστοῦ


The external support, however, overwhelmingly favors of θεοῦ. In fact, the NA27 and Editio Critica Maior together only list nine witnesses for κυρίου (mentioned above, with only the NA27 listing vgmss). This means virtually all other witnesses support θεοῦ."

ስለዚህ የዘመናችን ምሁራን ሁሉ እነ Bruce Metzger ጨምሮ፣ ለ 2ጴጥሮስ 1:1 ትክክለኛው አነባበብ #አምላካችን የሚለው እንደሆነ ደምድመው አልፏል።

በሚቀጥለው ክፍል ደግሞ ይህ እውቀት አልባ ኡስታዝ ተብዬው በ2ጴጥሮስ ፀሀፊ ላይ ያነሳቸውን ትችት የምንፈትሽበትና ምን ያህል ውሃ የማያነሱ ሙግት እንደሆኑ የምናሳይበት ይሆናል።

ይቀጥላል...

ወንድም ናኦል

@Jesuscrucified
ቅጥፈትና ስህተት የማይሰለቸው ኡስታዝ ወሒድ ቅሌቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ይህንን ጽሑፍ ያነበበ ማንኛውም ሙስሊም ከዚህ በኋላ የእርሱን ዝብዘባ ከቁምነገር ቆጥሮ አያነብም፡፡

የግራንቪል ሻርፕ ሕግና የሙስሊም ኡስታዞች ቅጥፈት
የክርስቶስን አምላክነት ለማስተባበል የተደረገ ከንቱ ጥረት
ሙሉ
ጽሑፉን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ፡፡
http://www.ewnetlehulu.org/am/sharp2/
ሳምራዊ ወይንስ ዘንበሪ?
ቁርአንን ከታሪካዊ ቅጥፈቱ ለመታደግ የተደረገ ከንቱ ጥረት

---------------
መሳሳት የማይሰለቸው አብዱል ለጻፈው "መልስ" የተሰጠ መልስ።

http://www.ewnetlehulu.org/am/samaritan/
ክፍል ሁለት፡-

ነጃሽ አልሰለመም አንድ፡- የሙስሊም ታሪክ ጸሐፍቱ ተዐማኒነት ሚዛን ላይ

በእስልምና ታሪክ ጸሐፊነት ከመጀመሪያው የእስልምና ዘመን ጀምሮ እስከዚህኛው ዘመን ድረስ በርካታ ሰዎች ስማቸው ይጠራል፡፡ አርዋን፣ ኢብን ኢስሀቅ፣ አል-ሻቢ፣ አል-ሱዲ፣ ዋሃብ ቢን ሙናቢህ ቀደም ካሉት ተርታ ይጠቀሳሉ፡፡ ከእነዚህ እልፍ ሲባል ደግሞ ስማቸው በሰፊው የናኘ ኢብን ሒሻምንና አት-ጦበሪን እናገኛለን፡፡ አንዳንዶች መተኪያ እንደሌላቸውም የታሪክ ሊቅ እንደሚቆጥሯቸው እሙን ነው፡፡ ሆኖም ስማቸው የገነነው የኢብን ኢስሃቅን የታሪክ ድርሳን አርትኦቱን በመሥራታቸው ነው፡፡ በሁለቱ ሰዎች ስም የሚታወቁት የእስልምና የታሪክ መጻሕፍት ከትንሽ ለውጦች በስተቀር እጅግ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በዚህ ሁሉ ከኢብን ኢስሃቅ ጋር ቀጥታ ግንኑነት የነበራቸው ሰዎች እንዳልነበሩ ከሕይወት ታሪካቸው ይታያል፡፡

እንግዲህ ነጃሽ እስልምናን ስለመቀበሉ በታሪክ ድርሳኑ ያተተ ኢብን ኢስሃቅ ሲሆን ሕይወት ዘርተውበት ዜናውን ያባዙት ኢብን ሒሻምና አት-ጦበሪ ናቸው፡፡ እውነት ነጃሽ እስልምናን ተቀብሎ ነበር? ይህን ለማረጋገጥ አንዱ ሚዛናችን የጸሐፍቱ ተአማኒነት ነው፡፡ ታዲያ የኢብን ኢስሃቅ፣ የኢብን ሒሻምና የአት-ጦበሪ ተአማኒነት ምን ያኽል ነው? በነቢዩ ሙሐመድና በሙስሊም ሊቃውንት ስለ እነዚህ ሰዎች የነበራቸው እይታ እስከ ምን ድረስ ነበር? ስለ ታሪክ ዐዋቂነታቸው የተሠጠው ምስክርነትስ ምን ይመስላል? የሚሉት ጥያዎች ምላሽ የሚያሻቸው ናቸው፡፡

እንደ እስልምና የመረጃ ምንጮች እነዚህ "ምትክ የሌላቸው" የተባለላቸው ሰዎችና ኢብን ኢስሃቅ የሠሩት ታሪክ ሊታመን የሚችል እንዳልሆነ ማስረጃዎችን ይሰጣሉ፡፡ ኢብን ሒሻምና አት-ጦበሪ የኢብን ኢስሃቅ ታሪክ (ሲራህ) አርታኢዎች እንደመሆናቸው ተዐማኒነታቸው በኢብን ኢስሀቅ እና በታሪኩ ተአማኒነት ላይ ተመሠረተ ነው፡፡ ኢብን ኢስሃቅ ደግሞ በእርሱ ዘመን በነበሩ ዕውቅ ሙስሊም ሊቃውንት ዘንድ የማይታመንንና በብዙ ጉድለቶች ይከሰስ የነበረ ሰው እንደነበር የእስልምና ታማኝ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ከተወለደበትና ካደገበት ቀዬ ለመሰደድ በቅቷል፡፡ ስለዚህ ኢብን ሒሻምና አት-ጦበሪም ከተዐማኒ የታሪክ ሊቃውንት ዝርዝር ውስጥ ይሰረዛሉ፡፡ የኢስላማዊ ማኅበረሰብ (ኡማ) መሐንዲሶች ዝርዝር ውስጥም የተካተቱ ሰዎች አይደሉም፤ አት-ጦበሪ በቁርአን ሐተታው ዝርዝሩ ውስጥ ተካቶ እናገኘዋለን፡፡ ስለ ኢ-ተዐማኒነታቸው ለዚህ ጽሑፍ ይመጥናሉ ያልኳቸውን አስረጅዎቼን ጀባ ልበላችሁ፡-

1. ነቢዩ ሙሐመድ፡-

ነቢዩ ሙሐመድ እነዚህ ሰዎች በኖሩበት ዘመን በሕይወት ባይኖሩ ባይተዋወቁም አንድ ያስተላለፉት መልእክት ግን እነዚህን ሰዎች ለመመዘን ሁነኛ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ እንዲህ ነበር ያሉት፡-

ሲራ ኢብን ሳድ ቅጽ 1, ክፍል 1.11.3
ነቢዩ የዘር ሐረጋቸውን ሲናገሩ ከመአድ ኢብን አድነን ኢብን ኡደድ በኋላ ያለውን ጠቅሰው አያውቁም፡፡ ከዚህ በኋላ ዝም አሉና እንዲህ አሉ፡- የዘር ሐረግ ቆጣሪዎች ውሸታሞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏል፡- … የእነዚያም ከእነሱ በኋለ የነበሩት ከአላህ በስተቀር ሌላ የማያውቃቸው (ሕዝቦች)… (ሱራ 14 ፡ 9) አሉ፡፡ ኢብን አባስ እንዲህ አለ፡- ነቢዩ ከአድናን በፊት ያለውን የዘር ሐረጋቸውን ከአላህ መስማት ቢፈልጉ ይችሉ ነበር፡፡

የእስልምና ዐውደ ጥበብ ላይ እንዲህ የሚል ሐሳብ እናነባለን፡-

"አል-አስረም፣ ሱለይማን አል-ጠይሚ እና ውሀይብ ቢን ኻሊድ እንደ ውሸታም (ኢብን ኢስሃቅን) ይመለከቱታል፡፡" (Encyclopidia of Islam vol 3, page 810-811)

በእስልምና ታሪክ ውስጥ የነቢዩ ሙሐመድን የዘር ሐረግ እስከ አዳም ድረስ መዘርዘር የቻለ የመጀመሪያው ሰው ኢብን ኢስሃቅ ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ ይህንን ሰው ሐሳዊ ብለውታል፡፡ ኢብን ሒሻምና አት-ጦበሪም የነቢዩን ቃል እና የእነዚህን ሙስሊም ሊቃውንት ትችት እያወቁ ምንም ዐይነት ማስተካከያ ሳያደርጉ ከኢብን ኢስሃቅ እንደተላለፈላቸው እንደዛው አስቀምጠው እናገኛለን፡፡ እናም ነቢዩ ሙሐመድ እና ሙስሊም ሊቃውንቱ በአንዳንዶች እንደ አይተኬ የሚቆጠሩትን ሐሳውያን ለማለታቸው ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡

2. የእስልምና ዐውደ ጥበብ የተለያዩ ሙስሊም ሊቃውንት ስለ ኢብን ኢስሃቅ የነበራቸውን አመለካከት ከስሙ ሥር ባሰፈረው ዘገባ አትቷል፡-

የነቢዩ ሙሐመድን ትክክለኛ ሐዲሶች ያሰባሰበውና "የእስልምና ማኅበረሰብ መሐንዲሶች" ከተባሉ ስመ ጥር ሙስሊም ሊቃውንት አንዱ የሆነው ኢማም ቡኻሪ ስለ ኢብን ኢስሃቅ የነበረውን ስሜት እንዲህ ይገልጸዋል፡-
"ኢማም ቡኻሪ እና ሙሐመድ ቢን አብደላህ ቢን ኑመይር በኢብን ኢስሃቅ ሪዋያ ደስተኞች አይደሉም፡፡" (Encyclopidia of Islam vol 3, page 810-811)

"ሐዲስን በተመለከተ አል-ኒሰኢና ያህያ ቢን ረተን ኢብን ኢስሃቅን አይቀበሉትም፡፡"

የእስልምናው ዐውደ ጥበብ "ፊህሪስት" የተሰኘውን የታሪክ መጽሐፍ የጻፉ ዕውቁ የእስልምና ሊቅ ኢብን አል-ነዲም እና የቁት እንዲህ ሲሉ ይከሱታል ብሏል፡-

"ኢብን ኢስሃቅ ሐሰተኛ እንደሆኑ የሚያውቋቸውን ግጥሞች በራሱ ሲራ ውስጥ አካቶ ይዟል"

3. የማሊክ ቢን አነስ ምስክርነት

ማሊክም የነቢዩን የዘር ሐረግ እስከ አዳም ስለሚዘረዝር ሰው (ኢብን ኢስሃቅ) ተጠይቆ ስለሰጠው መልስ እንዲህ ተብሎለታል፡-

ሲራ አል-ናባውያህ ቅጽ 1፣ ገጽ 51
መሊክ እስከ አዳም ድረስ የዘር ሐረግ ስለሚቆጥር ሰው ተጠይቆ ተቃውሞውን በገለጸበት ወቅት እንዲህ በማለት ነበር ትችቱን ያቀረበው፡- ይህንን የመሰለ እውቀት ከየት አገኘ? እስከ እስማኤል ድረስ ስላለው በተጠየቀ ጊዜም በተመሳሳይ ተቃውሞውን ሲገልጽ፡- ይህንን መረጃ ማን ማቅረብ ይችላል? ብሎ ጠይቋል፡፡ ማሊክ የነቢያትን የዘር ሐረግ አብርሐም የእንትና ልጅ፣ እንትና የእንትና ልጅ… እያሉ መቁጠርን ፈጽሞ ይጠላል፡፡

ስለዚህ ይላል መሊክ፡-

ኢብን ኢስሃቅ እጅግ ከማይታመኑ አጨበርባሪዎች አንዱ ነው፤ ስለዚህ ከራሱ ከተማ ከመዲና አባረነዋል፡፡ (Halabieh, I, page 93)

4. የኢብን ሒሻም ሐታቾች (commentators)

በኢብን ሒሻም ሲራ ላይ ሃተታ የሚሰጡ ዘመናዊ አታቾች እንዲህ ማለታቸውን ዶ/ር ረፋት አማሪ "Islam In the Light History" በተሰኘው መጽሓፋቸው ላይ እንዲህ የሚለውን አስፍረዋል ፡-

እንደነ መሊክ ቢን አነስ እና ሂሻም ቢን አሩአ ቢን አል-ዙበይር የመሳሰሉ ታማኝ ሐዲስ አስተላላፊዎችን አገኝን፤ ሁሉም ኢብን ኢስሃቅን ከታማኝ ሐዲስ አስተላላፊዎች ዝርዝር ውስጥ ደምስሰውታል፡፡ እነርሱ እርሱን በውሸት፣ በማጭበርበር፣ በማይገባ ባሕሪ፣ በማይታመኑ አስተላላፊዎች ላይ በመደገፍ፣ ግጥሞችን እየፈጠረ በራሱ መጽሐፍ ውስጥ በማስገባት እና ሐሰተኛ የዘር ሐረግ በመፍጠሩ ሲከሱት ፍጹም አያመነቱም፡፡ (Introduction to Ibn Hisham, page mim)

ኢብን ሒሻምና አት-ጦበሪም በዚሁ ወንጀል ውስጥ እየተንከባለሉ እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ሕይወት የዘሩበት የኢብን ኢስሃቅን ሲራ ነው፡፡ የተወሰነ ማስተካከያ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ አት-ጦበሪ ስለሠራው ታሪክ ሲናገር በመግቢያው እንዲህ ብሏል፡-
"… Hence, if I mention in this book a report about some men of the past, which the reader or listener finds objectionable or worthy of censure because he can see no aspect of truth nor any factual substance therein, let him know that this is not to be attributed to us but to those who transmitted it to us and we have merely passed this on as it has been passed on to us ''

ማጠቃለያ፡-

ኢብን ኢስሃቅ የጻፈውና የተናገረው እምነት ሊጣልበት የማይገባ መሆኑን ከነቢዩ ሙሐመድና በራሱ ዘመን ከኖሩና ከዛም በኋላ ከተነሡ የእስልምና ሊቃውንት ምስክርነት ተረድተናል፡፡ የእርሱ ታሪክ ድርሳን አርታኢዎችም ቢሆኑ ውድቅ ሊያደርጉት የተገባ ታሪክ ሆኖ ሳለ ጥቂት ማሻሻያ ብቻ አድርገው ያንኑ ጉድፍ በማስቀጠላቸው የሐሳዊነቱ ተጋሪዎች ሆነዋል፡፡ እነዲህ ከሆነ ታዲያ፡-
 ነቢዩ ሙሐመድ ውሸታም ያሉትን ማነህ መተኪያ የሌለው ልትል የምትችል? የውሸታምን የታሪክ ድርሳንስ እንደ ታማኝ ምንጭ ማን ሊጠቅስ ይችላል?
 እነዚህ መተኪያ እንደሌላቸው የቆጠሩ የታሪክ ሊቃውንት በምርምራቸው ድምዳሜ ላይ ከመድረሳቸው በፊት የነቢዩ ሙሐመድንና የሙስሊም ሊቃውንቱን አመለካከት ለማየት ሞክረው ነበርን? አዎን ከሆነ መልሱ ለታሪኩ እጅግ ቅርበት ያላቸው ሊቃውንት ሐሳውያን ያሏቸውን በምን ሚዛናቸው አይተኬ ሊሏቸው ቻሉ?
 ነቢዩ ሙሐመድ ውሸታም ያሉትን የዚህን ሰው የፈጠራ ታሪክ እየቆረጡና እየቀጠሉ አሽሞንሙነው ያበጁና እነሆኝ ታሪክ ያሉ ኢብን ሂሻምና አት-ጦበሪ በምን ሒሳብ በእኛው ጉዳይ ላይ "ከኢትዮጵያ ምንጮች" ይልቅ ተሽለው ተቀባይነት ሊኖራቸው ይችላል?
 እነዚህና ከእነዚህ የወጣውን ትርክት የተቀባበሉ ጸሐፍት ነጃሽ እስልምናን እንደተቀበለ ሲናገሩ አይ ይህኛው እንኳን እውነት ነው እንዴት ሊባል ይችላል?
ለዚህ ነው ታሪኩ የፈጠራ ነው፣ የሐሳውያን ነቢዩ ሙሐመድን ለማግነን የወለዱት ትርክት ነው፣ ነጃሽ እስልምናን አልተቀበለም፣ አልሰለመም የምንለው፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ክፍሎች የነጃሽን መስለም ትርክቶች ስንመረምር ጉዳዩ ግልጥልጥ ይልልናል፡፡ ለአሁን እዚህ ላይ ላብቃ…
ይቀጥላል

ሳሂህ ኢማን ነኝ!
ቸር ይግጠመን፤ ሰላሙን ሁሉ ተመኘሁላችሁ፡፡
የውርስ ኃጢአትና የሙስሊም ኡስታዞች ስህተት
ለአቡ ሐይደር የተሰጠ መልስ


ሙስሊም ወገኖቻችን አጥብቀው ከሚቃወሟቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች መካከል “የውርስ ኃጢአት” አንዱ ነው፡፡ ይህ አስተምህሮ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በተፈጥሮ በሚታዩት እውነታዎች ድጋፍ ያለው ቢሆንም ለብዙ ሙስሊሞች የሚዋጥ አልሆነም፡፡ የዚህም ምክንያቱ “የውርስ ኃጢአት” ምን ማለት እንደሆነ በትክክል አለመገንዘባቸው ነው፡፡ የአስተምህሮውን ምንነት በትክክል ቢገነዘቡና የገዛ መጻሕፍታቸውን ቢያገናዘቡ ኖሮ ትክክለኛውን መረዳት አግኝተው ከክርስትና ጋር በተስማሙ ነበር፡፡ ነገር ግን በርዕሱ ላይ የሚጽፉትና የሚያስተምሩት ብዙዎቹ ኡስታዞች አስተምህሮውን የተረዱና የገዛ መጻሕፍታቸውን ያጠኑ ባለመሆናቸው ምክንያት ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በተዛቡ መረጃዎች ላይ በተመሠረቱ ሙግቶች ለስህተት ተዳርጓል፡፡ ያለ በቂ መረዳት በጉዳዩ ላይ ለመጻፍ ብዕራቸውን ካነሱት ኡስታዞች መካከል አቡ ሐይደር (ኡስታዝ ሳዲቅ ሙሐመድ) አንዱ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ እርሱ ያቀረበውን ሙግት የምንፈትሽ ይሆናል፡፡ ሙሉ ጽሑፉን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ... http://www.ewnetlehulu.org/am/original-sin/
Abrogation
Several articles written by brother Daniel are up on English section of our website. ወንድማችን ዳንኤል በእንግሊዝኛ ያዘጋጃቸው በርካታ ጠቃሚ ጽሑፎች በድረገጻችን ላይ ታትመዋል።
-----
ISLAM AT GLANCE http://www.ewnetlehulu.org/en/islam-at-glance/

ISLAM IN AFRICA http://www.ewnetlehulu.org/en/islam-in-africa/

THE DROWSY ETHIOPIAN CHURCH AND THE LOOMING TSUNAMI OF RADICAL ISLAM http://www.ewnetlehulu.org/en/lousing-tsunami-of-radical-islam/

THE ADVENT OF ISLAM IN ETHIOPIA http://www.ewnetlehulu.org/en/the-advent-of-islam-in-ethiopia/

RADICAL ISLAMIC GROUPS AND THE AGONY OF THE CHURCH IN ETHIOPIA http://www.ewnetlehulu.org/en/radical-islamic-groups-in-ethiopia

Thanks for reading and sharing!
ክፍል ሦስት

ነጃሽ አልሰለመም ሁለት፡- የነጃሽ ሰለመ የታሪክ ድርሳናቱ ትርክት በቁርአንና በዛው ታሪክ መነጽር ሲመዘን

ደግመን ተገናኝተናል፡፡ የጀመርነውን ነጃሽ አልሰለመም አሁን እነቀጥላለን፡፡ በነጃሽ አልሰለመም አንድ የጸሐፍቱን ተአማኒነት ሚዛን ላይ መዝነን እንደ ነበር ታስታውሳላችሁ፡፡ ውጤቱም ምንም ሊታመኑ የማይችሉ ሆነው አግኝተናቸዋል፡፡ አሁን ደግሞ የነጃሽን አለመስለም በበቁርአን ታሪክና በዛው በታሪክ ድርሳናቱ መነጽር የምንመዝንበት ወቅት ነው፡፡

ነጃሽ እንደሰለመ የሚናገሩ የእነዚህ የእስልምና የታሪክ ድርሳናት ዘገባ በኋላ የተፈጠሩ ተረቶች እንደሆኑ በቁርአን ታሪክ ውስጥ ማየት በጣም ቀላል ነው፡፡ ትርክቶቹን ቀጥታ ከኢብን ኢስሀቅ ወይም ከኢብን ሒሻም ወይም ከአት-ጦበሪ መውሰድ ቢቻልም ከነዛ ከቀዱና በነጃሽ፣ በኢትዮጵያና በኢስላም ግንኙነት ዙሪያ በአማርኛ ከተጻፉ መጽሐፍት በመውሰድ ተረትነቱን ለዚህ ጽሑፍ በሚመጥን መልኩ ላስቃኛችሁ ቆርጫለሁ፡፡ እነሆ ተከተሉኝ፡-

ፈጠራ አንድ፡- በጃዕፈርና በነጃሽ የተደረገ ቃለ ምልልስ

የእስልምና ታሪክ ድርሳናት እንደዘገቡት የነቢዩ ሙሐመድ ተከታዮች ለሁለተኛ ጊዜ በስደት 616 ዓ.ም አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው መጥተዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ ይልቅ ቁጥራቸው በርከት ብሎ ነበር፡፡ እነርሱ እንደገቡ እግር በእግር ተከታትለው እነርሱን መልሶ የሚወስድ የቁሬይሾች ሁለት ልኡካንም ገቡ፡፡ ልኡካኑ የመጡበትን ጉዳይ ለነጃሽ ካስረዱ በኋላ ንጉሡ ሁለቱንም ወገን ፊት ለፊት በማገናኘት ጉዳያቸውን አድምጧል፡፡ በሁለት ዙር በተካሄደው ክርክር የስደተኞቹ ተወካይ ጃዕፈር ከተናገረው ውስጥ የወሰድኩትን እነሆ፡-

"ንጉሥ ሆይ! እኛ መሃይማን ሕዝቦች ነበርን፤ ጣኦታትን እናመልክ፣ በክት እንበላ፣ እናመነዝር፣ ዝምድና እንቆርጥና የጉርብትናን መብት እናጓድል ነበር፡፡ ከእኛ ኃያሉ ደካማውን(ይበዘብዛል) ይበላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን አላህ መልእክተኛ ላከልን፡፡… ወደ አላህ ጠራን፣ እርሱን በብቸኝነት እንድናመልከው፣ አባቶቻችን ያመልኳቸው የነበሩ ከእንጨትና ከድንጋይ የተጠረቡ (ጣኦታት) አማልክትን እንድንተው፣ እውነት እንድንናገር፣ እምነትን እንድንወጣ፣ ዝምድናን እንድንቀጥል፣ ጥሩ ጎረቤቶች እንድንሆን፣ ከእርም ነገሮች እንድንታቀብና የሰዎችን ደም እንዳናፈስ አዘዘን፡፡ …

ሙሐመድ አላህን በብቸኝነት እንድናመልከው፣ በርሱ ላይ ምንንም እንዳናጋራ አዘዘን፣ ሶላት እንድንሰግድ፣ ዘካ (ምፅዋት) እንድንሰጥና ጾም እንድንጾም አዘዘን…

ንጉሥ ነጃሽም በጥሞና ካዳመጡ በኋላ ይህን ጥያቄ ጠየቁ፤ ነቢያችሁ ይዞት ከመጣው መልእክት ውስጥ የምታቀርብልን ይኖርሃል? አለ፡፡ አዎን ንጉሥ ሆይ! አለ ጀዕፈር፡፡ አንብብልኛ! አለ ነጃሺ፡፡ ጃዕፈርም ከሱረቱል መርየም የመጀመሪያዎቹን አንቀፅ አነበበለት፡፡ ወላሂ ንጉሡ አለቀሰ፡፡ እምባው ጺሙን አራሰው፡፡ ቀሳውስቱም ተላቀሱ፡፡ እምባቸው መጽሐፍታቸውን አራሰው፡፡…"

"ከዚያም ወደ ንጉሡ ስንገባ ስለዒሳ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ምን ትላላችሁ!? ብሎ ጠየቀን ንጉሥ ነጃሺ፡፡ ጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጣሊብ እንዲህ አለ፡- ነቢያችን ያስተማረንን እንላለን፡፡ ዒሳ (ኢየሱስ) የአላህ ባሪያ፣ መልእክተኛና (እርሱ ከፈጠራቸው መንፈሶች መካከል አንዱ) መንፈሱ (ሩሁ) ነው፡፡ ወደ ድንግል መርየም የጣለው የሁን ቃሉም ነው፡፡ ንጉሥ ነጃሺ እጁን ወደ መሬት ሰደደና አንዲት ዘንግ አነሳ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ /ዒሳ አንተ ካልከው የዚህን ዘንግ ያህል እንኳን አያልፍም አለ፡፡ ይህን ሲናገር ቀሳውስቱ አጉረመረሙ፡፡" (ነጃሽና የሀበሻ ምድር በእስልምና መነጽር፣ ገጽ 60-61፤ ኢትዮጵያ እና ኢስላም፣ ገጽ 15-17)

ይህ ከላይ ያነበባችሁት በንጉሡ ፊት ሁለቱ የቁሬይሻውያን መልእክተኞችና በነቢዩ ሙሐመድ መልእክተኞች መካከል የተካሔደ ክርክር እንደሆነ አድርገው ታሪክ ጸሐፍቱ ዘግበዋል፡፡ ሆኖም በክርክሩ ውስጥ የሚታዩት አንኳር ሐሳቦች ታሪኩ ሆን ተብሎ በኋለኛው ዘመን የተፈጠረ ተረት ተረት መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ፡፡ ለዛም ነው ነጃሽ አልሰለመም ብዬ በድፍረት የምሞግተው፡፡ ለዚህ አስረጅዎቼን አነድ በአንድ ከቁርአን ታሪክ ጋር በማመሳከር እነሆኝ እላለሁ፡-

1. ስለ መንፈሳዊ ሕይወት በቅድመ እስልምናና በእስልምና ውስጥ የተባለው

ጀዕፈር እንዲህ እንዳለ ታሪኩ ያትታል፡-

"…እኛ መሃይማን ሕዝቦች ነበርን፤ ጣኦታትን እናመልክ፣ በክት እንበላ፣ እናመነዝር፣ ዝምድና እንቆርጥና የጉርብትናን መብት እናጓድል ነበር፡፡ …ከእርም ነገሮች እንድንታቀብና የሰዎችን ደም እንዳናፈስ አዘዘን፡፡ …"

ውሸት! ጀዕፈርና መላው ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት ጊዜ ላይ (615-616 ዓ.ም) ቆመን ይህንን አባባል በቁርአን መነጽር ስንመዝን ጀዕፈር ይህንን ሊናገር የሚችልበት እውቀት ላይ እንዳልነበር እናስተውላለን፡፡ ይህ የሐሳውያኑ የታሪክ ጸሐፍት የልባቸው ውሉድ ሐሰተኛ ታሪክ ነው፡፡ ቁርአን ውስጥ በክት መብላትን የሚከለክሉት አንቀጾች ቁጥር 5 ብቻ ናቸው፡፡ ይህንን "ሐላልና ሐራም በእስልምና" ከተሰኘው በዩሱፍ አል-ቀርዷዊ ተጽፎ በኡመር ሰኢድ ወደ አማርኛ ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ ማረጋገጥ ትችላላችሁ፡፡ አንቀጾቸም፡-

 55ኛ ደረጃ በወረደው በሱረቱል አል-አንአም
 70ኛ ደረጃ በወረደው በሱረቱል አን-ነህል
 87ኛ ደረጃ በመዲና በወረደው ሱረቱል አል-በቀራ
 55ኛ ደረጃ በወረደው በሱረቱል አል-አንአም
 114ኛ ደረጃ በወረደው በሱረቱል አል-ማኢዳ

በቁርአን ሱራዎች የአወራረድ ቅደም ተከተል መሠረት ከእነዚህ አራት ምዕራፎች የሚቀድመው 55ኛ ደረጃ የወረደው ሱረቱል አል-አንአም ነው፡፡ ሁሉም የኢስላም ሊቃውንት ይህ ሱራ የወረደበት ጊዜ ደግሞ 619 ዓ.ም አካባቢ እንደሆነ ይስማማሉ፡፡ ይህንን ማረጋገጥ የሚፈልግ ካለ ግብጻዊው የአዝሃር ዩኒቨርስቲ ምሩቅና ዳኛ Muhammad Habib Shakir, (1866–1939) የተባሉ ሰው የጻፉትን "Chronological Koran" የተሰኘውን መጽሐፍ ገለጥ ገለጥ ቢያደርግ በመጀመሪያዎቹ ገጾች ላይ ያገኘዋል፡፡ ታዲያ እነዚህ የቁርአን ምዕራፎች በወረዱበት ወቅት ጀዕፈርና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሙስሊሞች የት የነበሩ? ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ መካ አልነበሩም፡፡ እነርሱ ኢትዮጵያ ሲገቡና ቁሬይሻውያኑ ንጉሡ ፊት ሲያቀርቧቸው አንቀጾቹ ለነቢዩ ሙሐመድ ለመውረድ ሁለት ዓመታት ይቀራቸው ነበር፡፡ ታዲያ ባልነበረበት፣ ደግሞ ገና ከሁለት ዓመት በኋላ ሊወርድ ያለውን ጉዳይ እንደተማረው አድርጎ እንዴት ሊናገር ይችላል? ማን ነው ነቢዩ? ጀዕፈር ወይስ ነቢዩ ሙሐመድ? ምነው ጅብሪል ከነቢዩ በፊት ቀደም አድርጎ ለጀዕፈር የመጽሐፍቶችን እናት አስቃኝቶት ነበር እንዴ? ይህንን ማን አደረገ? ሐሳውያኑ የታሪክ ጸሐፍት ወይስ ሌላ? ለዚህ ነው ነጃሽ አልሰለመም የምለው፡፡

2. ነቢዩ ለተከታዮቻቸው ካስተላለፉት ትእዛዛት መካከል

"ሙሐመድ አላህን በብቸኝነት እንድናመልከው፣ በርሱ ላይ ምንንም እንዳናጋራ አዘዘን፣ ሶላት እንድንሰግድ፣ ዘካ (ምፅዋት) እንድንሰጥና ጾም እንድንጾም አዘዘን…"
👍2
ሐሳውያኑ የታሪክ ጸሐፍት ከልባቸው ወልደው የጻፉት ሌላው ታሪክ ይሄኛው ነው፡፡ በመሠረቱ ሶላትን፣ ዘካንና ጾምን የሚያዙ አንቀጾች የወረዱት መዲና ውስጥ እንጂ መካ ላይ አልነበረም፡፡ ታዲያ ከየት አምጥቶ ይህንን ሊል ይችላል? ታሪኩ ቅጥፈት ያለበት መሆኑን የተረዳው ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል "ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 39-40 ላይ በግርጌ ማስታወሻው እንዲህ የሚል ማስተባበያ ጽፎ እንመለከታለን፡-

"ኢብኑል ሐጀር፣ በፈትሁል ባሪ ጥራዝ 4፣ ገጽ 486 ላይ እንዳብራሩት ጃዕፈር 'በሶላት፣ በዘካትና ጾም ያዘናል' ያለው የኢስላም መሠረት የሆኑትን ሶላት (ስግደት)፣ ዘካ (ሰደቃ) እና ጾምን ሳይሆን እነኝህ ግዳጅ ሳይሆኑ በፈቃደኝነት ይደረጉ የነበሩትን ተግባራት ለመግለጽ ነው፡፡ እርሱ ይህንን በተናገረበት ሰዓት በበጎ ፈቃድ የሚፈጸሙ የአምልኮ ተግባራት ሱናን ነበሩ እንጂ ገና ግዳጅ አልተደረጉም ነበር፡፡ …"

ይህ ደግሞ ነገሩን እጅግ ያወሳስበዋል እንጂ ቅጥፈቱን አያስተባብለውም፡፡ እንደተባለው እነዚህ የኢስላም መሠረቶች ግዳጅ ከመሆናቸው በፊት በቁሬይሾች ዘንድ ይፈጸሙ የነበሩ የአምልኮ ተግባራት እንደ ነበሩ ከኢስላም የመረጃ ምንጮች ውጭም ያሉ ምንጮች ያረጋገጡት ጉዳይ ነው፡፡ ቁርአን በሱራ 2 ፡ 62 እና በሱራ 5 ፡ 69 ያወሳቸው ሳቢያኖችና መጁሶች (ሱራ 22፡ 17) እንዲሁም የነቢዩ ሙሐመድ ቤተሰቦች ከቅድመ እስልምናው ዘመን ጀምሮ ይተገብሯቸው የነበሩ የአምልኮ ተግባራት ስለሆኑ እንግዳ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ታዲያ ሱናን ነበሩ ሲባል የማን ሱናን? የሚል ጠንከር ያለ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ቀጠልም አድርጎ ኢስላም የእነዚህን የጣኦታውያን የአምልኮ ተግባራት የሃይማኖቱ መሠረት ካደረጋቸው ኢስላም እንዴት መለኮታዊ ሃይማኖት ሊባል ይችላል? ነቢዩ ሙሐመድስ የማን መልእክተኛ ናቸው? ቁሬይሻውያኑ ነቢዩ ሙሐመድን "ሳቢ" (የሳቢያን እምነት ተከታይ) እያሉ ይጠሯቸው የነበረው ለምን ነበር? የጣኦት አምልኮውን በተለየ ተጋድሎ አስቀጣይ ነቢይ ስለሆኑ? የሚሉና ሌሎች ወፈር ወፈር ያሉ ሞጋች ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ ለጊዜው ይህ ይቆየን፡፡ ለዚህ ሰፋ ባለ ሁኔታ ማብራሪያ የሚፈልግ ካለ ደግሞ አብዱልሐቅ ጀሚል የተባለ ጸሐፊ "ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን? መቸስ ተጀመረ?" በሚል ርዕስ ለንባብ ያበቃውን መጽሐፍ መመልከት ይችላል፡፡ ጥብስቅ ያለ ዕውቀትም ያገኙበታል፡፡ እናም ይኽኛውም የታሪክ ጸሐፍቱ ከሐሳዊው ልባቸው የወለዱት ሐሰተኛ ታሪክ ነው እያልከን ነውን? ካላችሁኝ አዎን ነው መልሴ፡፡ ለዚህ ነው ነጃሽ አልሰለመም የምለው፡፡

3. ስለ ኢሳ ማንነት የተሰጠ ማብራሪያ

"ከዚያም ወደ ንጉሡ ስንገባ ስለዒሳ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ምን ትላላችሁ!? ብሎ ጠየቀን ንጉሥ ነጃሺ፡፡ ጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጣሊብ እንዲህ አለ፡- ነቢያችን ያስተማረንን እንላለን፡፡ ዒሳ (ኢየሱስ) የአላህ ባሪያ፣ መልእክተኛና (እርሱ ከፈጠራቸው መንፈሶች መካከል አንዱ) መንፈሱ (ሩሁ) ነው፡፡ ወደ ድንግል መርየም የጣለው የሁን ቃሉም ነው፡፡ ንጉሥ ነጃሺ እጁን ወደ መሬት ሰደደና አንዲት ዘንግ አነሳ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ /ዒሳ አንተ ካልከው የዚህን ዘንግ ያህል እንኳን አያልፍም አለ፡፡

ሁሉም የእስልምና የታሪክ ጸሐፍት በታሪክ ድርሳናቸው ይህንን ታሪክ አስፍረዋል፡፡ አሁንም ጃዕፈር ስለ ኢሳ ማንነት ተጠይቆ "ዒሳ (ኢየሱስ) የአላህ ባሪያ፣ መልእክተኛና (እርሱ ከፈጠራቸው መንፈሶች መካከል አንዱ) መንፈሱ (ሩሁ) ነው፡፡ ወደ ድንግል መርየም የጣለው የሁን ቃሉም ነው፡፡" ብሎ እንደመለሰ መዘገቡ በቁርአን ታሪክ መነጽር ሲፈተሸ ፍጹም ውሸትና ታሪኩ ሆን ተብሎ ለማስመሰል የተፈጠረ መሆኑን እናስተውላለን፡፡ ጃዕፈር ስለ ኢሳ የተናገረው ሐሳብ ቁርአን ውስጥ ይገኛል፤ ሱረቱል አል-ኒሳዕ 4 ፡ 171፡፡ ከዚህ ክፍል ውጭ በየትኛውም የቁርአን ሱራ ውስጥ ይህንን አታገኙም፡፡ ታዲያ ይህ ሱራ ሲወርድ ጃዕፈር የት ነበር? ሱራው የወረደውስ የት ነበር? ውድ ወገኖቼ ይህ የቁርአን ሱራ በሱራዎች የአወራረድ ደረጃ 92ኛ ደረጃ የወረደ ሱራ ነው፡፡ መደቡም በመዲና ከወረዱት ተርታ ነው መደንይ ነው፡፡ ሊቃውንቱ የወረደበትን ጊዜም 626 ዓ.ም አካባቢ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የጥያቄና መልሱ ወቅት ደግሞ 615-616 ዓ.ም ነበር፤ ጃዕፈርም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የነበረው፡፡ ሱራው ለመውረድ 10 ዓመታት ይቀረው ነበር፡፡ ነገር ግን ጃዕፈር አንቀጹን አነበነበው አሉ፡፡ ይህ እንዴት ሊታመን ይችላል? አሁንም ደግሜ ልጠይቅ፤ ነቢዩ ማን ነበር? ጅብሪል ቀድሞ ጃዕፈር ጋር ሄዶ ነበር ማለት ነው? ነቢዩማ ሙሐመድ ናቸው ከተባለ ጃዕፈር ይህንን ገና ያልወረደን ዕውቀት ከየት ሊያገኘው ይችላል? ይህ የታሪክ ጸሐፍቱ ሐሳዊ ብዕር ከሐሳዊ ልብ ሰምታ የከተበችው ነው፡፡ ታሪኩ ኩሸት ነው፡፡ ነጃሽም "ወደ መሬት ሰደደና አንዲት ዘንግ አነሳ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ /ዒሳ አንተ ካልከው የዚህን ዘንግ ያህል እንኳን አያልፍም አለ፡፡ " የተባለውም እብለት ነው አላለም፡፡ አሁን ለምን ነጃሽ አልሰለመም እንደምል ግልጽ እየሆነለችሁ የመጣ ይመስለኛል፡፡

ይቀጥላል!

ሳሂህ ኢማን ነኝ!

ሰላሙን ሁሉ ተመኘሁላችሁ ቸር ይግጠመን!
2
ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ እንዳልሆነ ከሚያሳዩ ማስረጃዎች መካከል አንዱ በዙርያው ከነበሩ ባሕሎችና ሃይማኖታት የተለያዩ ሐሳቦችን በመቅዳት ከሰማይ የመጣለት መገለጥ አስመስሎ ማቅረቡ ነው፡፡ የእስልምና ጀማሪ የሆነው ሙሐመድ ምንም ዓይነት ኦሪጅናል መልእክት ያላመጣ ሲሆን ከተለያዩ ምንጮች የቃረማቸውን ነባር አስተምህሮዎች፣ ታኮችና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች መለኮታዊ መገለጥ በማስመሰል ሲያስተምር ነበር፡፡ በዘመኑ የነበሩት አረቦች እንኳ ይህንን እውነታ በመገንዘብ የሙሐመድን ትምህርት “…የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው” ይሉ እንደነበር በቁርአን ውስጥ በተደጋጋሚ ተጽፏል (ሱራ 83፡13፣ 68፡15፣ 46፡17)፡፡ ይህንን የሙሐመድ የመቅዳት ተግባር እስላማዊ ምንጮች እንዲህ ሲሉ ይናዘዛሉ፡-
www.ewnetlehulu.org/am/muhammad-plagiarism
ሙስሊም ሰባኪያን እንዴት ሕዝባቸውን እንደሚያጭበረብሩ ተመልከቱ፡፡ በጽሑፉ መጨረሻ ላይ የሚገኘውን የመጽሐፍ ቅዱስን አስደናቂ ትንቢት ማንበብን አትርሱ፡፡ http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-prophecy-2/
አስገራሚዎቹ የአላህ መሐላዎች
http://www.ewnetlehulu.org/am/allahs-oaths/
የቁርአን ትንቢት?

ቁርአን ስለ አተም ክፍልፋዮች ይናገራልን?


ሙስሊም ዳዋጋንዲስቶች በቁርአን ውስጥ ተተንብየዋል በማለት ከሚያቀርቧቸው ሳይንሳዊ እውነታዎች መካከል አንዱ አተሞችን የተመለከተ ነው፡፡ ቁርአን ስለ አተም ብቻ ሳይሆን በአተም ውስጥ ስለሚገኙት እንደ ኤሌክትሮን፣ ኒውትሮንና ፕሩቶንን ስለመሳሰሉት ጥቃቅን ክፍልፋዮች ተናግሯል ይላሉ፡፡ ከሙሐመድ ዘመን በብዙ ክፍለ ዘመናት ቀድመው የኖሩት ግሪኮች ስለ አተም አስቀድመው ስላስተማሩ አተምን የተመለከተ ጥቅስ በቁርአን ውስጥ አለ ቢባል እንኳ አስቀድሞ የተነገረን ዕውቀት ከመድገም የዘለለ ባለመሆኑ ከትንቢት የሚቆጠር አይሆንም፡፡ በማስከተል እንደምንመለከተው ሙስሊም ሰባኪያን ከሚነዙት የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በተጻራሪ ቁርአን ስለ አተምም ሆነ በውስጡ ስለሚገኙት ክፍልፋዮች ምንም የሚናገረው ነገር የለም፡፡ ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ... http://www.ewnetlehulu.org/am/quran-prophecy-3/
የሴት ውርስ በእስልምና ፍትሃዊ ነውን?
ለሙስሊም ኡስታዝ ቅጥፈት የተሰጠ መልስ

የሙስሊም ኡስታዞች ቅጥፈት ማለቂያ የለውም፡፡ http://www.ewnetlehulu.org/am/women-inheritance/